Sunday, October 2, 2016

VIDEO – ቢሾፍቱ ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል



ቢሾፍቱ ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል
ወታደሮቹ በፒካፕና በኦራል መኪና ከተማዋን እየናጧት ይገኛሉ ይህንን ሁሉ ህዝብ ይፈራ መስሏቸው ይሁንና ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች ሲቶችና እና ወንዶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል::ለወትሮም ቢሆን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የማይታጣት ቢሾፍቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባላ በአጋዚ ጦር ውስጥ ወድቃለች በኢሬቻ በአል ምክንያት በቢሾፍቱ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሰው እየከተመባት ይገኛል ሰላም ለማስከበር ዱላም ሲበዛ ነው የዚህን ያህል መሳሪያ ይዞ መገኘት አሳዛኝም አስነዋሪም ጭምር ነው በየ 10 ሜትት እርቀት ውስጥ በርከት በርከት ብለው የቆሙ አጋዚዎች የያዙት መሳሪያ ሰላማዊ ሰውን ለመጠበቅ አይመስልም
ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከሸዋና ከወሎ የተውጣጡ ከ200 በላይ የሚሆኑ አማሮች እጅግ የበረታውን የወያኔ ፍተሻ በማለፍ በአምስት ከፍተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተሳፍረው ደብረ ዘይት በመግባት ለኦሮሞ ወንድሞቻቸው ያላቸውን አጋርነት በኢሬቻ በዓል ላይ በእንግድነት በመገኝት እየገለጡ ይገኛሉ። አማሮቹ ደብረ ዘይት ሲደርሱ በአባ ገዳዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አማሮቹም ለአባ ገዳዎች የአማራን ህዝብ ከልብ የመነጨ ወንድማዊ ሰላምታ አቅርበዋል። ይህ የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትብብር የአማራ ተጋድሎና የኦሮሞ ተቃውሞ የጋራ ትግል ምዕራፍ የሚከፈትበት የመሰረት ድንጋይ ነው።
አጋዚዎች በቀጥታ ለጦርነት ተልከው የመጡ ነው የሚመስሉት ህዝቡን ከጠዋት ጀምሮ ማሸበር ተያይዘውታል በፅሁፍ ልገልጠው በማልችለው መልኩ ወታደሮች የመጡት ሀገራቸው ውስጥ አይመስልም ወታደሩን ሳየው የኔ ወገን አልመስልህ አለኝ በቅኝ ግዛት ውስጥ ያለው ሀገሬን የተቀማው ይኽል ከበደኝ በእርግጥ ሀገሬን ከቀሙኝ ቆይቷል ማንነቴን ቀምተው ማንነት አልባ ሊያደርጉኝ ቢጣጣሩ ነው ማንነቴን መልሱ እያልኩ መጮህ የጀመርኩት ብቻ ወደ ቢሾፍቱ ቅኝቴ ልመልሳችሁ እና ወታደሮቹ በፒካፕና በኦራል መኪና ከተማዋን እየናጧት ይገኛሉ ይህንን ሁሉ ህዝብ ይፈራ መስሏቸው ይሁንና ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች ሲቶችና እና ወንዶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል እስካሁኗ ባለው ሰአት ከላይ ወደታች ከታች ወደላይ እያሉ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ሲሆን ይህ ተቃውሞ በነገው እለትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምናለው እኔም እስከዛሬ በፀሁፍ ብቻ ኢህአዲግን ከምቃወም በነገው እለት ከኢትዮጵያውያ ወንድምና እህቶቼ ጋር በድምፅ እቃወመዋለሁ አዎ ህዝብ እንቢ ካለ እንቢ ነው ማንም ከህዝብ ማዕበል ሊያመልጥ አይችልም ይሄ አላስፈላጊ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱ አይቀርም Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
https://www.youtube.com/watch?v=0Q6cy0BS4pQ   video link

No comments:

Post a Comment