Wednesday, October 5, 2016

የኢትዮጵያ ዉሎ – መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም #ግርማ_ካሳ

  



#AmharaResistance #OromoProtests #KonsoProptests #EthiopianProtests
መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም በቢሾፍቱ የተፈጸመው ኢሰብአዊ ጭፍጨፋን ተከትሎ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ተቃዉሞዎች ተቀስቅሰዋል። ገዢው ፓርቲ “አዘነናል” ከማለት ዉጭ ምንም ሃላፊነት ያልወሰደ ሲሆን “የጥፋትና የአመጽ ሃይል በፌጠሩት ሁከት ዜጎች በመረጋገጥና ገደል ዉስጥ በመግባት ሞተዋል። የተተኮሰ ጥይት የለም” የሚል መግለጫ ነው የሰጠው። ተቃዉሞ ከተቀሰቀሰባቸው ቦታዎች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡
አዲስ አበባ
———
በአየር ጤና ፣ በጎጃም በረንዳ ፣ ወደ ቦሌ መስመር ተቃዉሞ፣ ካራ ቆሬ ተነስቶ ነበር። ተቃዉሞ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ወደ አዲስ አበባ እየገባ ነው። እንደ መርካቶ ያሉ ቦታዎች ሱቆች በጊዜ ነበር የተዘጉት። የአገዛዙ ሜዲያ “በአዲስ አበባ ምንም ነገር አልተፈጠረም ፣ በአዲስ አበባ ተቃዉሞ ተነስቷል እያሉ በሶሻል ሜዲያ የሚያራግቢት የጥፋት ሃይሎች ናቸው” ይላል። የኦዲዮ፣ የቪዲዮ ፣ የመስል መረጃዎች በስፋት እየወጡ፣ በዚህ መልኩ አይን ያፈጠጠ ዉሸት መዋሽት ትልቅ ዝቅጠት ነው።
ጂማ
—-
የጂማ ዞን እስከአሁን በተደረጉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ብዙ ተቃዉሞ ያልተሰማባት ከተማ ነበረች። በኦሮሚያ አዳማ ቀጥሎ ትልቋ ከተማ ስትሆን ብዙ ብሄር ብሄረሰቦች በሰላም የሚኖሩባት ከተማ ናት። ወደ 45% የሚሆነው ነዋሪ አንደኛ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ሲሆን 55% አንደኛ ቋንቋዉ ከአፋን ኦሮሞ ሌላ ነው።
በጂማ በሚገኘው ትልቁ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በሕወሃት ዘመን ያልታየ ትልቅ ክስተት ነበር የተፈጸመው። ህወሃት በኦሮሚያ ያሉ ወገኖች አማርኛ እንዳይማሩ አድርጎ፣ በኦሮሞዉና በሌላው ማህበረሰብ መካከል መግባባት እንዳይኖር፣ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችን በጋራ እንዳይጠይቁ ለማድረግ ችሎ ነበር። በዩኒቨርሲቲዎች የኦሮሞ ተማሪዎች ለብቻቸው ሌላው ለብቻው ነበር ህብረት የሚያደርገው። አይተማመኑም ነበር። ያም በዋናነት ሲጠቅም የነበረው አገዛዙን ነበር። በዚህ መልክ ተማሪዎችን በዘር ከፋፍሎ እርስ በርስ እያጋጨ በተለምዶ የሕዝብ ጥያቄ የሚንጸብረቅባቸው የትምህርት ተቋማትን ከጨዋታ ዉጭ ለማድረግ ችሎ ነበር።
ዛሬ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ ሳይባባሉ በነቂስ በመዉጣት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምጻቸውን እስከ ማታ ድረስ ኢስያሰሙ ነበር”” መፈክሮችን እያቀባበልይ አንዴ በኦሮምኛ አንዴ በአማርኛ እያሰሙ ነበር በኦሮሞ፣ በአማራው በኮንሶ ወገኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍን በደል ሲያወግዙና ሲቃወሙ የነበሩት።
በአዲስ አበባ ዙሪያ
—————-
– ከጀሞ ኮንድምኒየም አጠገብ የምትገኝ የኦሮምያ ሰፈር በተደጋጋሚ የመሳርያ ጩኸት ሲሰማ የነበረ ሲሆን ፖሊሶች ግርግሩን በመጠቀም ስማርት ሞባይሎች ከሕዝብ እየቀሙ ነው !! ምናልባትም ሰዎች መረጃ ፎቶ እንዳያነሱና እንዳይቀባበሉ ታስቦ ይሆናል !!! በፊሪ በተነሳው ታቃውሞ ምንም አይነት የወያኔ መኪና አያልፍም በማለታቸው የመሳርያ ድምፅ አልቆም ስላለ በጄሞ አካባብ ያሉት የግል ትምህርት ቤቶች ሰዓት ሳይደርስ ልጆቻችውን አውጡ ስላሉ፣ በጄሞ አካባብም ልጆቹን ለመውሰድ ቤተሰብ ሲሯሯጥ ነበር !! ከፍተኛ ወታደር የያዙ ተሸከርካሪዎች ወደ ጀሞ አቅጣጫ ሄደዋል።
– በሰበታ እና አለምገና የሚገኙ የስርዓቱ አካል ናቸው የተባሉ ኢንዱስትሪዎች ተቃጥለዋል። ፖሊሶች የህዝቡ ተጋድሎ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ፈርተው የሸሹበት ሁኔታ ነው የነበረው።
– በአቃቂ አካባቢም የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር።
– በቡራዩ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ተካሂዷል። አሸዋ ሜዳ ሁሉም ሱቆች ዝግ ነበሩ። ቦታውም በፌድራል ተወሮ ነበር። የታጠቅ ፋብሪካዎች ሰራተኞቻውን በጊዜ ነው የተበተኑት። ጉጄ አካባቢም እንደ አሸዋ ሜዳ ውጥረት ነግሶ ነበር። በርካታ የአገዛዙ ደጋፊዎች ንብረት ነው በተባሉ ላይ ዉድመት እንደነበረም ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ባንኮፕች ተዘግተዋል። መኪና በከተማዋ አያልፍም።
ጎጃም
—–
– በጎጃም ኮሶበር – ዳሸን ቢራ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ንብረትነቱ የኤፈርት የሆነ የጭነት መኪና በኮሱበር ጥቃት ደርሶበት ከጥቅም ዉጭ ሆኗል። በጭነት መኪናው የንመበሩት ቢራዎች መንገድ ላይ ሙሉ ለሙሉ ተደፍተዋል።
– ጎጃም መተከል (አሁን ወያኔዎች በቤኔሻንጉል ክልል ዉስጥ አደርገዉታል) በሚገኘው 23/45ኛው ወታደራዊ ካምፕ ይኖሩ የነበሩ ከ30 በላይ ወታደሮች የታጠቁትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዘው ህዝባዊ ተጋድሎውን ለመቀላቀል ጫካ ገብተዋል። የመተከሉ 23/45ኛው ወታደራዊ ካምፕ ማለት በአማራ ተጋድሎ ወቅት ወጣቶች የተገደሉበት፤ አካለ ጎደሎ የሆኑበትና በስቃይ ርሃብና ጥም ውስጥ ደንጋይ እንዲፈልጡ ሲደረግብት የነበረ አካባቢ ነው። ወታደሮች ጫካ የገቡት ሌሊት ላይ የመሳሪያ መጋዘን በመስበር ከውስጥ የነበረውን በትንሹ 10 መትረጌየስና መሰል ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመያዝ ነው። በዚህ የተነሳም መተከል ከፍተኛ የሆነ ፍለጋ ተጀምሯል።ፓትሮል በየጫካው ተጀምሯል። የወያኔ ደህንነቶችና ጀሌዎች እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ በግልገል በለስ ዞን አስተዳደር አዳራሽ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ከወታደሮቹ በተጨማሪ በአማራ እና ኦሮሞ ላይ ወያኔ እየወሰደው ባለው ግድያ ሲበሳጩ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ጥቂቶቹ ዛሬ ህዝባዊ ተጋድሎውን ተቀላቅለዋል።
– ጎጃም ሸርቆሌ አካባቢ ህዝብ ሊገድሉ የሄዱ 16 የወያኔ ወታደሮች ላይ ህዝቡ ራስን የመከላከል እርምጃ ወስዶባቸዋል። ሸርቆሌ አካባቢ የ12ኛ ክፍለ ጦር መገኛ ነው።
ምእራብ አርሲ፡
————
– በሻሸመኔ ላይ የኦሮሞና የትግሬ ወታደሮች ጎራ ለይተው እርስ በእርስ እየተታኮሱ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው።
– በሻላ ወረዳ ተቃዉሞ ነበር። ህዝቡ የገዳንና የኦነግን ባንዲራ (ብዙዎች እንደ ኦነግ ባንዲራነት ሳይሆን እንደ ትግል አርማነት የሚያዩት) ሰቅለዋል።
ሰሜን ሸዋ፡ በአቦቴ ወረዳ ሰሜን ሸዋ ተቃዉሞ ነበር።
ምስራቅ ሸዋ
———-
– በዛሬው ዕለት በአዳማ የተነሳው ተቃውሞ ተከትሎ ብዙ የካድሬዎች የእርሻ ማሳ በእሳት ወድሞዋል አመፁ 40 ኪሎሜትር ድረስ እስከ አዋሽ መልካሳ ተስፋፍቶዋል። ከአዳማ አሰላ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶዋል።
– ማምሻዉን በአዳማ እየተደረገ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ የአጋዚ ወታደር ተኩስ የከፈተ ሲሆን የኦሮምያ ክልል ፖሊስ ከተቃዋሚዎች ጎን ሆኖ ሕዝቡ ሲከላከል ነበር።፡እየተከላከለ ነው።
– በኑራ ሄራ ንብረትነቱ የአላሙዲን የሆነው የጥጥ ፋብሪካ በእሳት ተቃጥሏል። ወደ 20 የሚሆኑ የጭነት መኪናዎቹና ትራክተሮቹም እንደዚሁ።
– በመቂ በዝዋይ ተቃዉሞ ነበር።
ባሌ

ባሌ ሮቢ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም። ሁሉም ነገር ተዘግቷል። አጋዚ ወአትደር ብቻ ነው በከተማዋ የሚራወጠው። የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለም ኡሉ ተዘግቷል።
ቦረና ዞን
——
በቡሌ ሆራ ወረዳ ሕዝቡ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስነስቷል። ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ህዝቡ የወረዳዉን ፖሊስ ጣቢያ ፣ የአገዛዙ ጽ/ቤትን አዉድሟል። አድማ በታኞች መቆጣጠር ስላልቻሉ ሸሽተው ሄደዋል።

No comments:

Post a Comment