Saturday, October 1, 2016

በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው።Tadesse Biru Kersmo


በብዙዎች የመምህራን “ስልጠናዎች” ላይ ዝምታ ከቃላት በላይ ተቃውሞን ለማስተላለፍ ጠቅሟል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን አላስችል ያላቸው መምህራን ካድሬዎቹን አሳፍረዋል። ”ለምን እንዲህ አደረጋችሁ”፤ “ምን አቅብጧችሁ ተናገራችሁ?” ማለት አይቻልም፤ የካድሬዎቹ ድፍረት ትዕግስት ያስጨርሳል። ክፋቱ በእነዚህ አዳራሾች ውስጥ የነበሩ ጆሮጠቢዎች ሪፓርት የሚያደርጉትን አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው።
ተናገሩ ተብለው ተወትውተው ስለተናገሩ ታሰሩ !!! ያሳዝናል !!! ለዚህ ኢፍትሀዊነት ውሳኔ የምሰጠው ምላሽ ምንድነው?
ዘንድሮ ት/ቤቶች እንደተከፈቱ ወዲያውኑ የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች መጀመር አለባቸው። በሥራ መለገም፤ የታዘዙትን ሳይሆን ያልታዘዙትን መፈፀም … ወዘተ ከቀን አንድ ጀምሮ ተግባራዊ ልናደርጋቸው ይገባሉ ብዬ አምናለሁ።
“የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች” እና “የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን” የሚሉ ሁለት አጫጭር መጣጥፎችን በፌስቡኬ ለጥፌዓለሁ። እነዚህ ለመነሻ ያህል የቀረቡ ናቸው። ዜጎች እኔ ከዘረዘርኳቸው የተሻሉ ተግባራት ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህም ሆኑ ሌሎች ትምህርት እንደተጀመረ በሥራ ላይ ቢውሉ መልካም ነው እላለሁ።
ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ መምህራን የሚሆኑ ሌሎች ዝርዝሮችን ማዘጋጅት የሚያስፈልግ ከሆነም እናስብበት።
2009 የትምህት ዘመን የሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ የሕዝባዊ አሻጥር እና የአዝባዊ አመጽ – ማለትም የሁለገብ ትግል – ዘመን ይሆናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!! Tadesse Biru Kersmo

No comments:

Post a Comment