Friday, October 28, 2016

የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን ማፈን ጀመረ። ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሏል።



የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን ማፈን ጀመረ። ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
Minilik Salsawi
በኢትዮጵያ ውስጥ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ኣውጥቶ በኣፈናና በዘረፋ ላይ የተሰማራው የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የሚባለው መስሪያ ቤት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላቶችን በማፈ እና ሕዝብን በማስፈራራት በፍተሻ ስም ዘረፋ ላይ መሆኑን ሕዝቡ በምሬት ገለጸ።
በዚህም መሰረት ከሰማያዊ ፓርቲ የታፈኑት ወደ ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉ ሾን ከኣዋጁ በፊት መታፈናቸው ቢገለጽም ሰሚ ኣካል ባለመገኘቱ በእስር እየተንገላቱ እንደሆነ ታውቋል። ከትላንትና ጀምሮ በተጀመረው ኣፈና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አቶ ሰሎሞን ስዩም ትናንት ምሽት በደህንነቶች ከመኖሪያ ታፍኖ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።እንዲሁም የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሃላፊ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የነበረው ወጣት ዳግማዊ ተሰማ በዛሬው እለት በድህንነት ሃይሎች ተይዞ ፮ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ኣፈናውን ኣጠናክሮ የቀጠለው ኮማንድ ፖስቱ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን በክትትል ቀለበት ውስጥ ኣስገብቶ ለመያዝ መዘጋጀቱ ታውቋል። ከተመሰረተ ገና ኣንድ ሳምንት ሳይሞላ ከኣስራ ኣምስት ሺህ ዜጎች በላይ እስር ቤት እንደከተተ የሚነገርለት ኮማንድ ፖስቱ ስራው ማፈን\ማሰር ብቻ ሳይሆን ዘረፋም እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በሕዝቡ ላይ የገንዘብና የሞባይል የጌጣጌጥና የኤለክትሮኒክስ እቃዎችን በመዝረፍ ላይ እንደሚገኙ ሲታወቅ እነዚሁ የኮማንድ ፖስት ኣባላት በተሰጣቸው ስድ ስልጣን ነገ ሴቶችን ከመድፈር እንደማይመለሱ በመናገር ሕዝቡ ሮሮውን በማሰማት ላይ ይገኛል። #ምንሊክሳልሳዊ

በኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጠ



በኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጠ
ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ላሰቡ አሜሪካውያን ዜጎቿ ባለፈው ሳምንት ላወጣችው የጉዞ ማስጠንቀቂያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰጠውን ምላሽ ባለፈው ሰኞ ማቅረባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ማስጠንቀቂያው የወጣው የኢትዮጵያ ሁኔታ በተረጋጋበት ጊዜ መሆኑን ሲያመለክት በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለም ጠቅሷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ማክሰኞ በተለያዩ የዓለማችን ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ፣ የኢትዮጵያም ጉዳይ ተነስቶ ነበር። ማብራሪያውን የሰጡት፣ ቃል-አቀባዩ ጆን ከርቢ ናቸው። ዘገባውን አዲሱ አበበ ተከታትሎታል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡ http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/10/27/428bb9ee-11ba-4052-9b33-284ec8abad21.mp3
Vm
P

ጆን ከርቢ /የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ/

ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም! (ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም)



ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም! (ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም)
ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ” ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!
የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ ግለሰቦችም መንግሥቶችም ሞልተዋል፤ ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የሚመኙ ጭንጋፍ ልጆችም አሏት፤ ማኅጸንዋ እየደማ እየረገማቸው ሰላምና እንቅልፍ አጥተው አብጠው ይፈነዳሉ፤ የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ መንግሥቶች ሁሉ ከዚህ በፊት ቀድመው ፈራርሰዋል፤ ወደፊትም ይፈራርሳሉ።
የአገራቸው ፍቅር፣ የእርስበርሳቸው ዝምድና፣ የተራራውና የሸለቆው፣ የሜዳውና የገደሉ፣ የበረሀውና የለምለሙ፣ የዝናቡና የወንዙ፣ የዓየሩና የነፋሱ፣ የበዓላቱና የድግሱ፣ ያለውን አብሮ መቋደሱ፣ ተዝካሩ፣ ሙታዓመቱ ለሞቱ፣ መላእክቱ፣ ቅዱሳቱ፣ ሰማዕታቱ፣ እየተሸከሙ ያደረሱት ጸሎቱ፣ ለምዕተ-ዓመታት የተከማቸው እምነቱ፣ ሃይማኖቱ፣ በዚህ ሁሉ የተገነባው ኅብረቱ እንዴት ይፈርሳል! ማን ችሎ ያፈርሰዋል! አፍራሾች ቀድመው ይፈርሳሉ!
አንዳንዶች ቢጨነግፉም፣ አንዳንዶች ቢክዱም፣ አንዳንዶች ሆዳም ቢሆኑም፣ አንዳንዶች ቢወላውሉም፣ ኢትዮጵያ ልጆች አሏት፣ አሁንም የሚሞቱላት፣ ያልበሏት፣ የሚሳሱላት፤ ያልሸሿት፤ አፈሯን የሙጢኝ ብለው አፈርሽ እንሁን የሚሏት፣ ደሀነትም ሆነ ጭቆና ካንቺ አይለዩንም የሚሏት፤ ኢትዮጵያ ዛሬም ልጆች አሏት ስትፈርስ ቆመው የማያዩ፣ ሲያማት ነፍሳቸውን ዘልቆ የሚያማቸው፣ ሳልፈርስ አትፈርስም ነው ቃል ኪዳናቸው!
ቱርክና ግብጽ መጥተው ሄደዋል፤ ፖርቱጋል መጥቶ ሄዷል፤ እንግሊዝ መጥቶ ሄዷል፤ ኢጣልያ መጥቶ ሄዷል፤ ጠላቶች እየመጡ በመጡበት ተሸኝተዋል፤ ወዳጆች በጨዋነት ተስተናግደው ተዋኅደዋል፤ ቤተ ሙሴ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ እስልምና ኢትዮጵያዊ ሆነዋል፤ ዛሬ እንግዳ አይደሉም፤ ዛሬ ባዕድ አይደሉም፤ ኢትዮጵያ በፍቅር ለመጣ ፍቅር ነች፤ ምቹ ነች፤ በጠብ ለመጣ እሾህ ነች፤ ትዋጋለች።
ኢትዮጵያ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለአንቺ የተናገረው ይመስለኛል፤ ‹‹ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፤ አብሪ፤ እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ አሕዛብም ወደብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደመውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ። ዓይኖችሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደአንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል፤ በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደአንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደአንቺ ስለሚመጣ አይተሽ ደስ ይልሻል፤ ልብሽም ይደነቃል፤ ይሰፋማል፤ የግመሎች ብዛት የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ፤ የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደአንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፤ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።›› (60፡1-7)
ኢትዮጵያ ትወድቅ ይሆናል፤ ግን ያለጥርጥር ትነሣለች፤ በፊትም ወድቃ ተነሥታለችና፤ ኢትዮጵያ ትሰነጠቅ ይሆናል፤ ግን ያለጥርጥር ትገጥማለች፤ በፊትም ተሰንጥቃ ገጥማለችና፤ ለኢትዮጵያ በጎ የማይመኙላት የአየሉ ቢመስሉም የንስሐ ጊዜ ስትሰጣቸው ነው፤ ኢትዮጵያ ዕብሪተኞችንም ትሕትና ታስተምራቸዋለች፤ ዕብሪተኞች ከነዕብሪታቸው በራሳቸው እሳት ቀልጠው እስቲያልቁ ኢትዮጵያ ትእግስትዋ አያልቅም፤ ኢትዮጵያ ትእግስት ነችና።
በበጎ መንፈስ እስከተመራን ድረስ፣ ፍርሃትንና አለመተማመንን፣ ጥላቻን፣ ጠብንና ድብድብን፣ ሊዘሩብን ከሚፈልጉ ርኩሳን መናፍስት ከራቅን ኢትዮጵያችን አትፈርስም፣ የደፈረሰውም ቶሎ ይጠራል።
ምንጭ፡ Mesfin Woldemariam Blog

ሕዝቦችን ያማከለ አንድነት ለትግሉ ስኬት – ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ)



Image may contain: text
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና የውርስ አደራ የታላቅነት ተምሳሌት ነው ኢትዮጵያዊነት!!! በዚህ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ በጸረ – ኢትዮጵያ አቋም የሚዳክር በታታኝ ዘረኛ ቡድንና የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው። በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ ሕዝቦችን ያማከለ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በእርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።
ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን። አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::
እውነትን እና ስልጡን ፖለቲካን ቢተናነቀንም እንደምንም ልንውጠው ግድ ይላል::ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::በፈረንጅ አገር ወያኔ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የላካቸው ባለስኮላርሺፖች አዛኝ ቂቤ አንጓች የአንድነት ሃይል መስለው ሰርገው በመግባት እየሰሩ ያለው ስራ እጅግ ያሳዝናል::
ከመወራጨት ውጪ ከነአጨብጫቢዎቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡና የለውጥ እንቅፋት እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ

Thursday, October 27, 2016

ስድስት የኬንያ ፖሊሶች በኢትዮጵያ ፖሊሶች ታስረዋል። ቆንጅት ስጦታው 



የኬንያ ጋዜጣ ዴይሊ ኔሽንን እንደዘገበው ስድስት የኬንያ ፖሊሶች በኢትዮጵያ ፖሊሶች ታስረዋል። ኬኒያ ሞያሌ ላይ በሚገኘው ሊያዞን ኦፊሰር አማካኝነት ፖሊሶቹን ለማስፈታት ጥረት እያደረገች ነው ተብሏል።
Ethiopian police arrest six Kenyan police officers :
ESAT — Ethiopian police arrested six Kenyan police officers over the weekend including a police chief at the border with Kenya, according to a report by the Kenyan Daily Nation.
The team of Kenyan police had crossed the border to secure the release of a reservist, Salim Kala, who had been arrested on October 21 for allegedly fishing along the shores of Lake Turkana on the Ethiopian side, the report said.
They were all armed but were placed in custody after their firearms were confiscated.
The Kenyan authorities said that efforts to release them were under way through a liaison officer in Moyale, a border town, and that they were in contact with the local administrator at Jinga Omarate district, where the officers are being held.
Marsabit County police commander Ben Kogo has confirmed the officers were arrested.
But he said officials were yet to be told why the officers were arrested.
Several incidents have been reported this year involving security agencies from both countries.
The report said on October 16, Kenya Defence Forces soldiers from the Oda Camp were deployed to Sololo after the Ethiopian army raided a village in Marsabit.
About 100 Ethiopian soldiers entered Kenya and surrounded Golole Village, about 9km west of the Sololo Police Station.
The soldiers claimed they were pursuing Oromo Liberation Front militants suspected to have killed police officers in Ethiopia.
In the process, a herder was killed by the Ethiopian soldiers, the newspaper reported.
Source ESAT

Wednesday, October 26, 2016

አሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የወጣውን ክልከላ መንግሥት ተቃወመ  EthiopianReporter



አሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲሰርዙ የሚከለክል መግለጫ መውጣቱን መንግሥት ተቃወመ፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዝ እንዲታቀቡ ማሳሰቡን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተቃውመውታል፡፡
አቶ ጌታቸው ሰኞ

Monday, October 24, 2016

የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራዊ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::ምንሊክሳልሳዊ



የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራዊ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::
 
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል።የሕዝቡ ብሶት ገንፍሎ ኣደባባይ በመውጣት የወያኔን ዘረኛ ኣገዛዝ እየተፋለመ ያለውም ለዚሁ ለለውጥ ያለው ፍላጎት ነው። ለውጥ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::
 
የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ። #ምንሊክሳልሳዊ

‹‹ጦርነት›› ከፊታችን የተደቀነ ልንጋፈጣው የሚገባ ዕውነት! Muluken Tesfaw



‹‹ጦርነት›› ከፊታችን የተደቀነ ልንጋፈጣው የሚገባ ዕውነት! Muluken Tesfaw
ኧረ ጥራኝ ጫካው ኧረ ጥራኝ ዱሩ!
ላንተም ይሻልሃል ብቻን ከማደሩ፡፡
በሕዝባዊ እምቢተኛነትና ተቃውሞች አገዛዙ የሕዝብ ጥያቄዎችን ሊመልስ ይችላል የሚል ተስፋ የነበራቸው ወጣቶች አሁን ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ ሽህዎችን ገድሎ ሽዎችን አካለ አጉድሎ አሁን ምንም የማይመስለው ሥርዓት መሆኑን እያየን ነው፡፡ ሥርዓቱ ፋሽስታዊነቱን የበለጠ አጠናክሯል፡፡ በየቀኑ የምንሰማው ስለሚገደሉ፣ ስለሚታሰሩና ስለሚሰደዱ ዜጎች ነው፡፡ ግን እስከ መቼ?
‹‹እኛ ርሀባችን ችለን ዝም አልናቸው፤ እነርሱ ግን ጥጋባቸውን መቻል አቃታቸው›› ያለው ማን ነበር ባያሌው? ከተራበ ለጠገበ እዘኑ እንዳሉት አበው ቀጣይ ጊዜያት ከተገዥዎች ይልቅ የገዥዎች ፀሐይ እንደምትጨለም ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
የጠገቡት ጥጋባቸውን መያዝ አልቻሉም፤ የሚገድሉ ሰዎች አገዳደላቸውንም መመጠን አልሆነላቸውም፡፡ የሚገዙ ፋሽስቶች በተገዥዎች ላይ የጫኑት ቀንበር ቀሊል አይደለም፡፡ የሰላም በሮች በሙሉ ተዘግተዋል፡፡ በገዥዎችና በተገዥዎች መካከል ያለው ልዩነት መጥበብ የሚችል አልሆነም፡፡ ገዥዎች በሚያዩት ምልክት ማመን አልቻሉም፡፡ ሥልጣን ያሳብዳል፤ ኅሊናን ያሳውራል፡፡ በምልክት ብዛት ሕዝብ የሚለቅ ቢሆን ወያኔ ባለፈው ክረምት ብቻ የግብጹ ፈርዖን ካየው ምልክት የበለጠ አይቶ ነበር፡፡ ግን የወያኔ ግብዝነት ከፈርዖን እልፍ ጊዜ ይበልጣል፡፡
የዐማራ ወጣቶች ሆይ አስከፊ የሆነ ነገር ከፊታችን ተጋፍጧል፤ ልንሸሸው የማንችለው- ጦርነት፡፡ ጦርነቱን እኛ ስለፈለግነው የሚመጣ ወይም የሚቀር አይደለም፡፡ አገዛዙ አፈሙዙን ስቦብናል፡፡ በዚህም ከሁለት አስቀያሚ ምርጫዎች ጋር ልንጋፈጥ ግድ አለን፡፡ ሁለቱም መጥፎ አማራጮች ናቸው፡፡ ወይ ዝም ብሎ መገደል አሊያም እየገደሉ መሞት፡፡ የትኛው ይሻላል?
ሁለቱም መጥፎች ናቸው፡፡ ግን የተሻለ መጥፎ አለ፡፡ ሊገድል የሚመጣን ጠላት እየገደሉ መሞት የአባቶቻችን ስለሆነ ምርጫው ይህ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የተሻለው መጥፎ ይህ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ ግን የምንገብረውን የሰው ሕይወት መቀነስ ይኖርብናል፡፡
የምገብረውን የሰው ሕይወት ለመቀነስ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? ደግመን ደጋግመን እንደተናገርነው ጊዜ ሳናባክን ደም እንለግስ፡፡ የሕክምና ባለሙያዎች ድንገተኛ ሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት ዝግጁ እንሁን፡፡ ይህም ልናደርገው ከሚገባን ጥንቃቄ በጣም ትንሹ ነው፡፡
በመጨረሻም የዐማራ ወንድሞች ሆይ የዘንድሮ ቀጠሯችን ገና ለመጫወት፣ በጥምቀት ሎሚ ለመወርወር እንዳልሆነ እናውቃለን፤ የገናው ሜዳ ወደ ጦር ሜዳ ተለውጧል፡፡ በቀጠሯችን ለመገናኘት የአባቶቻችን አምላክ ያብቃን፡፡


Saturday, October 22, 2016

የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወያዬ:: በጉዳዩ ላይ ሠኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ቆንጅት ስጦታው

Join the discussion. Post your articles or comments here. REGISTER or LOGIN


የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ዛሬ ረፋድ ሲወያዬ አርፍደዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የኢህአዴግ አባል ስለጉዳዩ እንደገለፁልኝ ከሆነ በአሜሪካዋ አምባሳደር ፓትሪሽያ ኃስላች ሰብሳቢነት በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከኢህአዴግ በኩል አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ደብረፅዮን፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎችም የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የተወሰኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የተለያዩ የሲቪል ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
Image may contain: sky and outdoor
ስብሰባው በዋነኝነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ በተከሰቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ሲሆን ስለጉዳዩ የመንግስት ባለስልጣናት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ችግራቸውንም ለመቅረፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ውይይቱን ይመሩት የነበሩት አምባሳደር ፓትሪሽያ ኃስላች እንደተናገሩት ከሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ያለአግባብ ያሰራቸውን እስረኞች መፍታት እንዳለበት ብሎም በሀገር ቤት ከሚገኙት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይም በርካታ ደጋፊ ካላቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ መስራት ብሎም ሁሉንም ያሳተፈ ፖለቲካዊ ስርዓት መገንባት እንዳለበት የገለፁ ሲሆን ፍርድ ቤቶች፣ ምርጫ ቦርድና ሲቪል ተቋማት ከመንግስት ጫና ውጭ ሆነው ገለልተኛ በሆነ መልኩ እንደአዲስ እንዲዋቀሩ ተናግረው የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የተረጋጋ መንግስት እንዲፈጠር እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት ግለሰብ ጨምረው እንደገለፁት ውይይቱ የአንድ ወገን የበላይነት የታየበት ከመሆኑም በላይ ስብሰባው ከውይይት በላይ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ እንዲሆን የሚፈልገውን ብቻ የገለፀበት የነበረ ሲሆን በመጪው ሐሙስ በዚሁ የአሜሪካ ኤምባሲ ኬነዲ ሆል የኢህአዴግ፣ የኦፌኮ፣ የሰማያዊና የመኢአድ አመራሮች በተገኙበት ተጨማሪ ውይይት እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ሠኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
#ኤርሚያስ_ቶኩማ

ባህርዳር ላይ የአሰቸኳይ ግዜ አዋጁን በመተላለፍ የስራ ማቆም አድማ አድርጋቹሃል የተባሉ 68 ነጋዴዎች በእስር ላይ ይገኛሉ ቆንጅት ስጦታው 



ባህርዳር ላይ የአሰቸኳይ ግዜ አዋጁን በመተላለፍ የስራ ማቆም አድማ አድርጋቹሃል የተባሉ 68 ነጋዴዎች በእስር ላይ ይገኛሉ በጎንደርም በተመሳሳይ መልኩ ከመቶ በላይ ነጋዴዎች መታሰራቸውም ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት ታሳሬዎቹን ከነገ ዛሬ ይፈታል እያልን ብንጠባበቅም ይባስ ብሎ በአሰቸኳይ አዋጁ ደንብ መሰረት የአምስት አመት እስር ይጠበቃቸዋል እሚል ከአንድ ፖሊስ አዛዥ ተነግሮናል ፡፡
ሰለዚህ የባህርዳር ህዝብ እና ነጋዴዎች የወገኖቻችን እስር በዋዛ ፈዛዛ የምናልፈው ጉዳይ አይደለም በሚል በከተማው በቅደመ ሁኔታ የተንጠለጠለ የስራ ማቆም አድማ እና ሰልፍ ለማድረግ ህብረተሰቡ እየተመካከረ ይገኛል፡፡
1ኛ መንግስት 68 ታሳሬዎችን እስከ ጥቅምት 20 ካልፈታ ጥቅምት 30 /2009 ዓም ለ3ቀን እሚቆይ የስራ ማቆም አድማ መደረግ እንዳለበት የታሳሪ ቤተሰቦች ጥሬ አድርገዋል፡፡
2ኛ ከስራ ማቆም አድማው በኅላ መንግስት ታሳሪዎችን ለመልቀቅ ይሁንታውን ካላሳየ ጥቅምት 26 ቅዳሜ ቀን ላይ የአደባባይ ሰልፍ ከቅዳሜ ገበያ ጀምሮ ወደ ጊዎርጊስ ቤተክርስቴያን ከዛም ወደ ርዕሰ መስተዳዳር በመጓዝ ሰልፍ እንደሚደረግ ጥሬ እንዲተላለፍ እና ህብረተሰቡም ዝግጂት እንዲያደርግ መልዕክት እየተላለፈ ይገኛል ፡፡እና እናተም በገፃቹህ ይህን ጥሪ ታስተላልፋልን ዘንድ በማክበር እንጠይቃለን፡፡
የታሳሬ ቤተሰቦች

Friday, October 21, 2016

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረጓ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር (180 ሚሊዮን ብር) አካባቢ ማጣቷ ተገለጸ ቆንጅት ስጦታው  




በኢትዮጵያ የተከሰተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ሃገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረጓ ምክንያት ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር (180 ሚሊዮን ብር) አካባቢ ማጣቷን አንድ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አደረገ።
ሃገሪቱ ለስድስት ወር የሚይቆየውን አዋጅ ተግባራዊ ካደረገች በኋላ የሞባይል ኔትወርክና ኢንተርኔት መዘጋት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳ እንደሚገኝ ካርትዝ አፍሪካ (Quartz Africa) የተሰኘ መጽሄት ዘግቧል።
ገዢው የኢህአዴግ መንግስት ተግባራዊ በተደረገው በዚሁ አዋጅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ገቢን ከሚያጡ የአፍሪካ ሃገራት መካከል ግንባር ቀደም ሆና ተፈረጃለች።
መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎትን ዝግ በማድረጉ ምክንያት ስራቸው እየተስተጓጎለ መሆኑን ባለፈው ሳምንት ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ እጅግ ዝቅተኛ የተባለ የኢንተርኔት እና የሞባይል ስልክ ግንኙነት ተጠቃሚ ሃገር ናት።
በህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት በኦሮሚያ ክልል በዚህ አመት ብቻ 4 ጊዜ የማህበራዊ ሚዲያ ማቋረጡን ዘገባው አመልክቷል።
በቅርቡ ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሞባይል ኔትዎርክ በመቋረጡ ሃገሪቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች እያጣች ነው።
አክሰስ ናው (Acces Now) በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሰብ-ሰሃራ አፍሪካ ፖሊሲ ተንታኝ የሆኑት ኤፕሬም ፔርሲ ኬንያቶ መንግስት በኢንተርኔት የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦችን ዝግ ቢያደርግም ህዝባዊ ተቃውሞው ግን ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን ዕርምጃ እንዲያጤነው በመጠየቅ ላይ ናቸው።

የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኮማንድ ፖስት ሳያሳውቁ ከሃገር እንዳይወጡ ዕገዳ ተጣለ Command Post ban govt officials from leaving Ethiopia using the SoE : ESAT ቆንጅት ስጦታው  



በቅርቡ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኮማንድ ፖስት ሳያሳውቁ ከሃገር እንዳይወጡ ዕገዳ መጣሉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ለህዝብ ይፋ በሆነው የአፈጻጸም መመሪያ ላይ በግልፅ ባይጠቀስም ኮማንድ ፖስቱ ሳያሳውቅ ከሃገር መውጣት አይችሉም።
ዕሁድ መስከረም 29, 2009 ይፋ የሆነውና ከመስከረም 28 ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑ የተገለፀው፣ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በመላዋ ኢትዮጵያ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል። ይህንን የሚያስጽም መመሪያ ቅዳሜ ጥቅምት 5 ፥ 2009 ይፋ ቢደረግም፣ የመንግስት ባለስልጣናትን የተመለከተው የማስፈጸሚያ ክፍል ተቆርጦ በውስጣዊ መመሪያነት ተገድቧል።
ኢትዮጵያውያን በምልክት ቋንቋ መነጋገርን ወይንም ምልክት ማሳየትን ጨምሮ በሚናገሩት ብቻ ሳይሆን በሚያዩትና በሚሰሙት ነገር ላይ ጭምር ገደብ የጣለው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ ከ40 ኪ/ሜትር የበለጠ መንገድ ለመጓዝ ከፈለጉ ለኮማንድ ፖስቱ ማሳወቅ ግዴታቸው መሆኑንም አስቀምጧል። በትምህርት ተቋማት ሌላው ቀርቶ በመንፈሳዊ ስፍራዎች ጭምር በሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስብከቶች ላይ ጭምር ገደብ የሚጥለው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአፈጻጸም መመሪያ ከህዝቡ ግልጽ ተቃውሞ እንደገጠመው በኦሮሚያ ክልል በሜታ ሮቢ በአንድ አጋዚ ወታደር በተገደለ የ9 አመት ተማሪ ስነስርዓት እንዲሁም በጎንደር ከተማ ቢያንስ ለሁለት ቀናት በቀጠለው አድማ ታውቋል።
High ranking government officials are not allowed to leave the country without the authorization of the command post that was set up to enforce the state of emergency declared in Ethiopia a week ago, sources disclosed to ESAT.
The ban was not included in the details of the emergency law that was released last week but sources say an internal memo sent to higher officials by the command post prohibit government officials from leaving the country without the knowledge of the command post.
The so called command post is run by three veteran members of the TPLF, namely Abay Tsehaye, Debretsion Gebremichael and Samora Yunis, the sources said adding Siraj Fergessa of the OPDO was just the media face of the Tigrayan clique running the command post.
The Ethiopian regime declared a state of emergency on October 9, 2016 after a year long protest by the Oromos and the Amharas against Tigrayan domination of the economy and political power.
The people of Bahir Dar and Gondar in the Amhara region held a strike this week defying the state of emergency, although the martial law prohibits strikes and protest demonstrations, among others.
Source: Ethsat.com

Wednesday, October 19, 2016

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ወጣ፤ቆንጅት ስጦታው



በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ወጣ፤
የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንትና የሰሜን ምዕራብ ቀጠና ኃላፊ የነበረውና በቅርቡ ከወራት ስቅይት በኋላ ከእስር የተፈታውን አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ 78 በሚሆኑ የጎንደር ዙሪያ ወጣቶች ማደኛ መውጣቱን ዛሬ ሰምተናል፡፡ እነ ዘመነ ምሕረት ላይ የወጣው ማደኛ ግለሰቦቹን መያዝ ካልተቻለም በተገኙበት እንዲገደሉም ትዕዛዝ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአቶ ዘመነ ምሕረት ጋር በተፈላጊነት ስማቸው ከወጣው ዐማሮች መካከል 18ቱ የብአዴን አባላትና በአመራርነትም ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
አቶ ማሙሸት አማረን እና አቶ አብርሃም ጌጡን ጨምሮ የመኢአድ ሕጋዊ አመራሮች በተለያየ ጊዜ ታስረው የተሰቃዩ ሲሆን በቅርቡም ብዙ የፓርቲው አባላት በእስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከቀናት በፊት አቶ ጫኔ ዘየደ እና አቶ ኢዮብ ታስረው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ በወገራ፣ በበለሳና አርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ ገበሬዎችን ይቅርታ አድርገንላችኋል በሚል ትጥቃቸውን ለመቀማት አዲስ ስትራቴጂ መነደፉን ሰምተናል፡፡ መረጃውን ያቀበሉን ሰዎች እንደሚሉት ገበሬዎቹ ይቅርታውን ከተቀበሉ ለተሀድሶ በሚል ሰበብ ወደ ብር ሸለቆ ወስዶ ለማሰር እቅድ መኖሩን ጭምር ነግረውናል፡፡
Image may contain: 1 person

Tuesday, October 18, 2016

ወደ አማራ ክልል እንዲንቀሳቀስ የታዘዘው ጦር ማብራሪያ ጠየቀ። ቆንጅት ስጦታው   



ወደ አማራ ክልል እንዲንቀሳቀስ የታዘዘው ጦር ማብራሪያ ጠየቀ።
#Ethiopia #EthiopianArmy #TPLFArmy #StateofEmergency #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – mereja.com የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ደህንነት ምንጮች እንደገለጹት ከእዙ የተለያዩ ቡድኖች ተዋቅረው የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ለመተግበር ወደ ኣማራ ክልል እንዲንቀሳቀሱ የታዘዙ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቃቸውን ጠቁመዋል። የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁ ከሕዝቡና ከሕገመንግስቱ ኣንጻር ያለውን ሃገራዊ እደምታ በተመለከተ እንዲሁም የግጭት ኣፈታትን በተመለከተ ከሕዝብ ጋር መወያየትን ያጣመረ ስራ ስለመሰራቱ ማብራሪያ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸው ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ በተላከ መመሪያ መሰረት በጎንደር በመተማ በባህርዳር በደብረማርቆስና በመተከል ያሉትን የወያኔ ኣግዓዚ ወታደሮች እንዲረዱ የታዘዙት የምስራቅ እዝ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቃቸውን ተከትሎ በዚህ ሳምንት ከመከላከያ ሚኒስቴር ኣንድ ቡድን ወደ ምስራቅ እዝ ይዘልቃል ተብሎ ይጠባቃል ሲሉ ወታደራዊ ደህንነቶች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።
በምስራቅ እዝ ያሉ ወታደሮችን ወደ ኣማራ ክልል ወስዶ በምትካቸው በምስራቅ በኩል ከሶማሊያ የሚመለሰውን ጦር ለማስፈር ያቀደው ወያኔ በወታደሮች እምቢተኝነት ጉዳዩ የዘገየበት ሲሆን ከሶማሊያ የተመለሱ ወታደሮችን በኣማራና ኦሮሚያ ክልል ለማስፈር ያሰበው እቅድን ያጠፈው የሰላም ኣስከባሪ ሃይሎች የሚላቸውን እና ስለ ወቅታዊ የትዮጵያ ጉዳይ በቂ መረጃ ያላቸውን ወታደሮች ሌላ ጥያቄ ስለሚያነሱ በሂደት ኣስፈላጊውን ለማከናውን ትልም የነደፈ ሲሆን ኣብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ከሶማሊያ እየተመለሱ በኣማራ ክልል ያለውን የኣግዓዚን ገዳይ ጦር መቀላቅላቸውም ምንጮቹ ገልጸዋል። #ምንሊክሳልሳዊ
Image may contain: one or more people

በአዲስ አበባ በግዳጅ ዲሽ እየተፋታ ነው።



በአዲስ አበባ በግዳጅ ዲሽ እየተፋታ ነው። (መረጃ ምንሊክ ሳልሳዊ በስልክ ከኣዲስ ኣበባ)
የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ተከትሎ በኣዲስ ኣበባ ዲሽ እየተፈታ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል፤ ኢሳትና ኦኤምኤን መመልከት ኣይቻልም የተባለው ኣዋጅ ኣስታኮ ፖሊሶችና የቀበሌ ካድሬዎች የኣዲስ ኣበባ ነዋሪዎችን ዲሻቸውን እንዲፈቱ በማስገደድ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
Image result for ዲሽ እየተፋታ ነው
 

Monday, October 17, 2016

የወያኔ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ተከትሎ በጎንደር ጸረ ወያኔ ቤት የመቀመጥ ኣድማ ተጀመረ። ቆንጅት ስጦታው 



የወያኔ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ተከትሎ በጎንደር ጸረ ወያኔ ቤት የመቀመጥ ኣድማ ተጀመረ።
በኢትዮጵያ የሕወሓት ኣገዛዝ የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ብሎ ግድያውና ኣፈናውን ሕጋዊ ያደረገበት ኣዋጅ ከወጣ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕጉን በመቃውም ጸረ ወያኔ ቤት የመቀመጥ ኣድማ በጎንደር መጀመሩ ታውቋል። ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ የተባለው ማንኛአንም ተቃውሞ የሚከለክል ቢሆንም የጎንደር ሕዝብ ግን እምቢ ለነጻነቴ እምቢ ለመብቴ ሲል ጸረ ወያኔ ቤት የመቀመጥ ኣድማ በማድረግ የጎንደር ከተማ ጭር ኣድርጓታል።
ሕዝቡ ድርጅቶቹን በመዝጋት ቤቱ በመቀመጥ የጀመረው ኣድማ ኣሁን ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል። የኣሁኑ ኣድማ የንግድ ድርጅቶችን እና ኣጠቃላይ የኣገልግሎት ሜስጫዎችን ጨምሮ ትራንስፖርት በሙሉ በኣድማው ይሳተፋሉ። በዚህ ኣድማም የመንግስት ሰራተኞች ምንም ኣይነት ኣማራጭ ስለማያገኙ ቤታቸው በመቀመጥ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል። የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማው ለሳምንት የታቀደ ሲሆን በባህር ዳርም ባለፈው ሳምንት ኣድማው ተግባራዊ እንደነበር ይታወሳል።
ዝርዝሩን ፡ http://mereja.com/network/post/200/a-week-after-ethiopia-s-state-of-emergency-gonder-starts-a-gene
Gonder

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ቆንጅት ስጦታው  



Image may contain: 1 person
የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ከመግለጫው የተወሰደ
” ከዚህ በኋላ የፍትህና የነፃነት ኃይሎች ዋና ተግባር ያላቸውን አቅም ሁሉ አስተባብረውና ነፃነት የራበውንና የጠማውን ሕዝባቸውን ከጎናቸው አሰልፈው፤ ጊዜውና ሁኔታው የሚፈቅደውን ተለዋዋጭና ተለማጭ የትግል ስልት እየተጠቀሙ ይህ አዋጅ በፍጹም ተግባራዊ እንዳይሆንና እንዳይሳካ ማድረግ ነው።
ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም በመሪነትና በዋና አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች፤ ይህ የባርነት አዋጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተገበርና እንዲሳካ ለማድረግ የሚሞክሩ ወይንም ከዚህ ዘራፊ ሥርዓት ጋር በጥቅም ተሳስረው ከዚህ የባርነት አዋጅ ጋር የሚተባበሩ ማናቸውም ኃይሎች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ የሕዝባዊ ትግሉ ቀንደኛ ዒላማዎች መሆናቸውን ግልጽ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል።
በዚህ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚሳተፉ የሕዝብ ወገኖችም ሆነ ይህንን ዘራፊ ሥርዓት የሚያግዙ ኃይሎች በደንብ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ይህን አዋጅ አከሸፍነው ማለት የወያኔ ሥርዓት አከተመለት ማለት እንደሆነ ነው። ይህ አዋጅ ተሳካ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተወሰነ ጊዜ በባርነት መቀመቅ ውስጥ ሊኖር ተፈረደበት ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን የገባንበት ትግል የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ነው የምንለው።”
“በዚህ የመጨረሻ የፍልሚያ ወቅት ጥቂቶቻችን ልናልፍ እንችላለን። ለነፃነታችን ስንል ሕይወታችንን ብንሰጥ ፈጣሪያችን በአምሳሉ ሲፈጥረን የሰጠንን የሰውነት ማንነት እውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል ነውና የምናልፈው፤ የፈጣሪያችንን ፈቃድ ለማስፈጸም የገበርነው ሕይወታችን ነውና በደስታ የምንጠጣው ጽዋችን ነው። ይልቅስ ፈጣሪያችን ለምንግዜውም ይቅር የማይለን ከሌላው እንሰሳ ለይቶ የሰጠንን ይህን በነፃነት የታጀበ የሰው ልጅነት፤ እንደ እንሰሳ ለሚበላና ለሚጠጣ ቁሳዊ ጥቅም ሸጠን፤ ሰው መሆንን በእንሰሳዊ የባርነት ሕይወት ቀይረን እኛ ባርነትን ተቀብለን ከራሳችን አልፎ ባርነትን ለልጆቻችን ያስተላለፍን እንደሆነ ነው። የዛሬ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የባርነትን ኑሮ ከኛ እንዳያልፍና ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ ማስቆም ታሪክ የጣለብንና በእርግጠኛነት የምንፈጽመው ተግባራችን እንደሆነ ከቶውንም አልጠራጠርም።”

Sunday, October 16, 2016

ከአማራ ክልል የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና አዲስ የትግል ጥሪ! ቆንጅት ስጦታው  



ከአማራ ክልል የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና አዲስ የትግል ጥሪ!
አዲስ የትግል ጥሪ !!
_ቀጣዩ እቅድ አንባገነኑ መንግስት በአማራና በኦሮሚያ እንዲሁም በጋንቤላና በኮንሶ በሰላም ባዶ እጁን ለተቃውሞ በወጣ ህዝብ ላይ በአልሞ ተኳሽ ህዝብን መጨፍጨፍ ሥራ ብሎ ይዞታል። ዛሬም ወጣትነት እስኪጠላ ድረስ በጅምላ ይጨፈጭፋል ፤በጅምላ ያፍናል፤ በጅምላ ያስራል፤ አስሮም አድራሻ አጥፍቶ ይገላል፤ ወላጆችም በሞቱት ልጆቻቸው አንጀታቸው ተቆርጧል። ልጆቻቸው የታሰሩባቸውም በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ለማወቅ ተቸግረው ሌት ተቀን እያለቀሱ ይገኛሉ።
በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ ሰሞኑን በቢሾፍቱ የተፈጠረው ሁኔታ ሁላችንንም የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ አስገብቶናል። ጠንከር ያለ እርምጃ እንድንወስድም አስገድዶናል። በመሆኑም ባለን ውክልና በአማራ ክልል የወሎ፣ የጎንደርና የጎጃም የህዝብ ትግል አስተባባዎች የሆንነው አካላት አዲስ የትግል ጥሪዎችን አውጥተናል።
የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ትግል አስተባባሪዎችም እንዲህ አይነት የትግል ስልቶችን በመጠቀም ከወገኖቻቸው ጋር በመተባበር በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ በማሰቃያ ቤቶች የሚገኙ ወንድሞቻቸውን እና 40 ሚሊዮን የሚገመተውን የኦሮሚያን ክልል ህዝብ ከሌላው ወንድሙ ጋር በማስተባበር ፤ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እንድንተባበር ይህን የትግል ጥሪ ስናቀርብ፤ሌሎችም በህወሀት አገዛዝ ታፍነው የሚገኙት የደቡብ ፣የጋምቤላ፣ የሶማሌ፣ የሀረሪ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር እና የትግራይ ክልል ሕዝብ ከሌላው ወገናቸው ጋር በትግሉ በመተባበር ሁላችንም ነፃ ልንወጣ ይገባል የሚል እምነት አለን።
እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነጋዴዎችና አጠቃላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች፤ የንፁሀን ወገኖቻቸውን ያልተቋረጠ ስቃይ ለማስቆም የሌሎች ወንድሞቻቸውን ጥሪ ሊተገብሩ ግድ ይላቸዋል።
በመሆኑም እኛ የአማራ ህዝብ ትግል አስተባባሪዎች፣ አፋኙን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ህዝብን በማይጎዳ መልኩ ከዚህ በፊት ካካሄድነው የስራ ማቆም አድማ በበለጠ ጠንካራና ገዥውን ቡድን የሚያሽመደምድ ትግል የቀረጽን ሲሆን ህዝብም ይህን አንድ ሀሙስ የቀረው ቡድን አሽቀንጥሮ ለመጣል ይህን የትግል ስልት ያለፍርሀትና ያለመለያየት በጋራ ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል።
የትግል አይነቶች፦
የትግል ስልት1ኛ
-ለግል ድርጅቶች የ2008 ዓ/ም ግብር እስከ ተህሳስ 30 ታክስ አለመክፈል።
ከላይ እንደተመለከተው የወርሃዊ ቫት አለመክፈል ጥሪ ያስተላለፍን ሲሆን፤ አንድ ነጋዴ አገዛዙን ፈርቶ ታክስ እከፍላለው ካለ እስከ ታህስስ 30 ድርጅቱን የመዝጋት አማራጭ ቀርቦለታል። ምክንያቱም ህዝብ አንድ ከሆነ፤ አሸባሪው ቡድን ምንም ማድረግ አይችልምና።ይህን ጥሪ ጥሶ ለገዳዩ መንግስት ታክስ እየከፈለ ሌላውን የሚያሳጣውንና ለወንድሞቹ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ድርጅትም ለመፋረድ ዝግጅት አድርገናል።
ምክንያቱም እኛ ወጣቶች ለነፃነት የህይወት መስዋትነት እየከፈልን ባለበት ሁኔታ አንዳንድ ነጋዴዎች ለንብረት ሣስተው ለገዳዩ መንግስት የጥይት መግዣ የሚሆን ግብር ከከፈሉ እኛም ለነሱ ዋጋቸውን እንከፍላለን። ከሌላው ወገኑ ጋር ያልተባበረ ነጋዴንና ከህዝብ ያልወገነ የታክስ መስሪያ ቤት ሰራተኛንም ከገዳዩ የህወሀት ቡድን በምንም አይነት ለይተን የማናያቸው መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።
በተጨማሪም ነጋዴው ታክስ እንዳይከፍል የሂሳብ ባለሙያዎች ነጋዴውን በነፃ እንዲያማክሩት እናሣስባለን። ከምክሮቹም ውስጥ 1ኛ የወርሃዊ ቫት ሪፓርትና አመታዊ ታክስ ክፍያን ለወራት በማቋርጥ በወር በ2000 ብር ቅጣት ሳይከፍል እንደሚቆይ ማስገንዘብ፣ 2ኛ የአመታዊ የትርፍ ግብር የኪሳራ ሪፓርት ማቅረብ እና 3ኛ ተመላሽ ክፍያወችን መጠየቅ የሚሉት ይገኙበታል። ይህን በተመለከተ ለበጠ መረጃ የሂሳብ ባለሙያወችን ያማክሩ ።
እኛ የአማራ ክልል የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ከሌሎች ወንድሞቻችን እና ከሕዝባችን ጋር በመሆን በነዚህ ወራት ይህን ዘረኛና ገዳይ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እየጣርን ባለበት ሁኔታ የገዳዩን ቡድን እድሜ ለማራዘም ይህን ግብር ያለመክፈል ጥሪ የሚጥሱ ነጋዴዎችን ስምና አድራሻ የታክስ መስሪያቤት ሰራተኞች እንዲተባበሩን ጠይቀናል፣ አሁንም እንጠይቃለን።
በተጓዳኝ ከህዝብ ያልወገኑ የታክስ መ/ቤትና የንግድና ትራንስፖርት መ/ቤት ሰራተኞችን ስም ፣ የሥራ ቦታና እድራሻቸውን ነጋዴው ሊያደርሰን ይገባል።
የትግል ስልት 2ኛ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ተባባሪ ድርጅቶች ፦
ሀ- የጥረት ድርጅቶች ፣ለ- የሸህ ማህመድ አል አሙዲ ድርጅቶች፣ ሐ- በክልላችን የሚተላለፉ የህወሀት ተሽከርካሪዎችና ንግድ ድርጅቶች ስራችውን እንዲያቆሙ ጥሪ እያስተላለፍን፤ ይህን ጥሪ ከተላለፉ እርምጃ እንደምንወስድባቸው እናሳውቃለን!!!
የህወሀት ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ወንድሞቻችንም በክላችን እንዳትንቀሳቀሱ በውንድሞቻችን ደም እንጠይቃለን!!!
የትግል ስልት 3ኛ
ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ አማራ ብድር እና ቁጠባ ባንክ ተጠቃሚ የሆናችሁ የአማራ ክልል ነዋሪዎች በ15 ቀን ውስጥ ገንዘባችሁን እንድታወጡ እንጠይቃለን። ከ15 ቀን በሗላ ማንም የአማራ ክልል ህዝብ ገንዘብም በነዚህ ባንኮች እንዳይገባና እንዳይወጣ፤ እንዲሁም ከነዚህ ባንኮች የወሰደውን ብድር እንዳይከፍል፤ በነዚህ ባንኮች በእዳ የተያዙና ለጨረታ የቀረቡ የግለሰብ ቤቶችን እና ተሽከርካሪዎችንም ማንም እንዳይገዛ እናሣስባለን። ይህን ጥሪ ጥሶ በእዳ የተያዙ ንብረቶችን የሚገዛ፤ ነገ ጧት ሀብቱ የህዝብ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
በትጓዳኝ ሌሎች ባንኮችም ቅርንጫፎቻቸውን እንዲያሰፉ ባልተቋቋሙባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን እንዲከፍቱ እንጠይቃለን!
የንግድ ባንክ፣ የአንበሳ ባንክ፣ የዳሽን ባንክ፣ የአባይ ባንክ፣ የአበቁተ ባንክ ስራ አስኪያጆች፤ ገንዘቡን ወጭ የሚያደርገውን ህዝብ ያለምንም ችግር እንዲያስተናግዱ በሞቱት ወንድሞቻችን ስም እንጠይቃለን!ከዚህ በሗላ በነዚህ ባንኮች እየተጠቀመ ለወንድሙ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ግን እንፉረደዋለን!!!
ህዝብ ከከፈለው ግብር በአመታዊ በጀት ተመልሶ ለልማት ሊደርሰው ይገባ ነበር። የእኛ የአማራ ህዝብ ግን፦ “ሰነፍ ነው፤ አይሰራም” ተብሎ ግብር ከፍሎ ከተመደበለት 4.5 ቢሊዮን ብር (ልብ በሉ ሚሊዮን እይደለም)የአማራ ክልል ልማት ባንክ በጀት ገንዘብ፤ ወደ ትግራይ ተወስዶ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ለህወሀት ወታደሮች ስልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት እኛ በህወሀት በሚሽከረከሩ ባንኮች ገንዘባችንን ማስቀመጥ ፈጽሞ የለብንም!!!
የትግል ስልት 4ኛ
በመድን ኢንሹራንስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ ፣አንበሳ ኢንሹራንስ፣ አባይ ኢንሹራንስ ፣አፍሪካ ኢንሹራንስ ፣ተጠቃሚ የአማራ ህዝብ ከነዚህ ድርጅቶች ገንዘቡን ተመላሽ በማድረግ ሌሎች ኢንሹራንሶች እንዲገባ ጥሪ እናስተላልፉለን!!ሌሎች ኢንሹራንሶችም ለህብረተሰቡ የተመጣጠነ ዋጋ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን።
የትግል ስልት 5ኛ
በውጭ የሚኖረው ማህበረሰብ በወገኑ ላይ እየደረሰ ያለውን አይን ያወጣ ስቃይ እያየ ወደ ሀገር ቤት በባንክ ገንዝብ መላክ፤ ሕዝብን በተጋድሎው በማገዝ ፋንታ ወገንን ለማስገደል መንግስትን እንደማገዝ ይቆጠራልና ቢችሉ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ገንዘብ እንዳይልኩ እንጠይቃለን!!
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ግዴታ መላክ ካለበዎት በጥቁር ገበያ እንዲልኩ አለዚያም ዘመድዎ ሀገር ውስጥ ካለ ዘመድ ወይም ወዳጅ ተበዳድረው እንዲቆዩ ያደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን። ይህ ውጪ ላለው ወገናችን ለራሱ ህሊና የሚተው ጥሪ ሲሆን፤ ይህን ጥሪ ጥሶ በባንክ ገንዘብ የላከን ከአጋዚ ለይተን አናየውም።
የትግል ስልት 6ኛ
ማንኛውም ህዝብ ከዛሬ ጀምሮ የመሬት ሊዝ ማንኛውንም አይነት ክፍያ ለአማራ ክልል ለከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች እንዳይከፍል!!
የትግል ስልት 7ኛ
ትራፊኮች፣ አደጋዎችን ከመቆጣጠር ውጭ ተሽከርካሪዎችን በገንዘብ እንዳትቀጡ!
የትግል ጥሪ 8ኛ
የመንግስት ተላላኪዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ከህዝብ ጎን የማትቆሙ ከሆነ በናንተና በንብረቶቻችሁ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን!!
የትግል ስልት 9ኛ
የመንግስት ባለስልጣን እና ካድሬ ንብረቶችን ባልተጣሩበት ሁኔታ ከዛሬ ጀምሮ በእዳ መያዣም ይሁን በግዥ ማንም እንዳይገዛ ጥሪ እናቀርባለን! እነዚህን ንብረቶች ገዝቶ የተገኘ ፤ነገ ጧት ወደ ህዝብ ንብረትነት መመለሳቸው እንደማይቀር ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
ከላይ የተዘረዘሩት ከዛሬ ጀምሮ የሚተገቡሩ የትግል ስልቶች ሲሆኑ ፤አሸባሪው ቡድን የህዝብን ጥያቄ የማይቀበል ከሆነ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው በየደረጃው ከዚህ የተሻሉ ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ መኾኑን እናሳውቃለን።
የአማራ ክልል ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ!

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” VS ሕዝባዊ አሻጥርና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ቆንጅት ስጦታው  



“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” VS ሕዝባዊ አሻጥርና ሕዝባዊ እምቢተኝነት
Tadesse Biru Kersmo
“በይፋ አለመታወጁ ነው እንጂ ድሮም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ነው የነበረነው” በሚል እሳቤ ስለዚህ ጉዳይ ምንም የመፃፍ ፍላጎት አልነበረኝም። ማታ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” ስሰማ ግን መሳሳቴን አወቅሁ። በዚህ ላይ ካልተፃፈ በምን ይፃፋል???
ስለዚህ መመሪያ ያለህን አስተያየት በአንድ ዓረፍተ ነገር ግለጽ ብባል እንዲህ እላለሁ።
“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” ስለሕዝባዊ አሻጥር እና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ውጤታማነት የተሰጠ የምስክርነት ቃል ነው።
ወደፊት የምመለስበት ሆኖ አሁን ትንሽ ዘና እንበልበት።
1. የኢትዮጵያ ከተሞች ከገጠር የሚለያቸው ዋና ባህሪ የቤቶቻቸው ጣራዎች ቆርቆሮ መሆኑ ነው። “ከዋና ዋና መንገዶች በግራና በቀኝ 25 ኪሜ ርቀት” እያሉ ለመለካት የሚያስቸግር ነገር ከሚያስቀምጡ “የቆርቆሮ ቤቶች ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ“ ቢባል ይሻል ነበር።
2. መመሪያውን እንደወረደ ለሚተረጉመው ሰው የሚገባው ነገር የሚከተለው ነው – “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚፀናበት ቦታ መኖር ክልክል ነው”። በህገመንግሥታቸው “ኢትዮጵያዊያን የመኖር መብት አላቸው” የሚል አንቀጽ እንዳለ አስታውሳለሁ። ይህ መመሪያ የከለከተለው እሱን ነው፤ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ የመኖር መብት የላቸውም እያለን ነው።
3. መመሪያውን እንደወረደ ሳይሆን በጥንቃቄ ለሚያጠና ሰው ግን በርካታ ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛል፤ ትኩረቴ ሁለት ነጥቦች ላይ ነው።
3.1. መመሪያው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ምን ላይ ማትኮር እንዳለበት ፍንጭ ሰጥቷል። ለምላሴ፣ ሁከት ማስነሳት፤ ዘረፋ መፈፀም፤ ንብረት ማውደም ከልክሏል (እነዚህ የተፈቀዱበት አገር ስለመኖሩ እኔ አላውቅም)። የሕዝባዊ እምቢተኝነት ትርጉም አድርጉ የተባሉትን አለማድረግ፤ አታድርጉ የተባሉትን ማድረግ በመሆኑ ምን ምን ላይ ማትኮር እንዳለብን ጥቆማ ሰጥቶናል። መንገዶች፣ የአገዛዙ ተቋማት ንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎች የሕዝባዊ እምቢተኝነት ዒላማዎች የነበሩ መሆናቸው ትክክል መሆኑ መመሪያው አረጋግጦልናል፤ ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል ነው።
3.2. መመሪያው ስለሕዝባዊ አሻጥር ውጤታማነት የተሰጠ መረጃ አድርገን ልንወስደው እንችላለን። “ሥራ መበደል ክልክል ነው” (በነገራችን ላይ ሥራ መበደል አለመበደሉን ማረጋገጥ ራሱ ትልቅ ሥራ ነው)፤ ሥራን ማስተጓጎል፤ አገልግሎት አለመስጠት፤ የስፓርት ሜዳዎችን ለተቃውሞ አለመጠቀም …. እያለ እኛ አገር ውጤታማ የሚሆኑ የሕዝባዊ አሻጥር ዓይነቶችን ይዘረዝራል። መመሪያው የሕዝባዊ አሻጥር ዋና ዋና ማዕከላትንም ይዘረዝራል፤ ለምሳሌ የትምህርት ተቋማት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት። ባጭሩ ይህ መመሪያ ስለሕዝባዊ አሻጥር የተፃፉ ጽሁፎችን እንድናነብ፤ እኛም ለሀገራችን በሚስማማ መንገድ እንድንጽፍ እና ተግባራዊ እንድናደርጋቸው ይማፀናል።

Saturday, October 15, 2016

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሟል፤አዲስ ሃኪምና መድሃኒት ይፈልጋል – ዶ/ር መረራ ጉዲና ቆንጅት ስጦታው  



* የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሟል፤አዲስ ሃኪምና መድሃኒት ይፈልጋል
* ኢህአዴግ ውስጥ ካለው ምሁር በተቃዋሚው ጎራ ያለው በእጅጉ ይልቃል
* ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ውለታ እንዲውል እጠይቀዋለሁ

ለ3 ወራት ገደማ አሜሪካ ቆይተው የተመለሱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በወቅታዊ አገራዊ ችግሮች ዙሪያ ቃለምልልስ አድርገዋል፡; በተጨማሪ በአሜሪካ በነበራቸው ቆይታ ምን እንዳከናወኑ፣ የዳያስፖራው ፖለቲካ ምን እንደሚመስልና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል – ዶ/ር መረራ ጉዲና፡፡
እስቲ የአሜሪካ ጉብኝትዎ አላማ ምን እንደነበር በዝርዝር ይንገሩኝ?
በሶስት ምክንያቶች ነበር ወደ አሜሪካ የተጓዝኩት። አንደኛው የዲፕሎማቲክ ስራ ነው። ይሄን ሃገር እንግዲህ ቅኝ እየገዙ ነው የሚባሉት አሜሪካኖች ናቸው፡፡ በማይሆን ግንኙነት እንዳይጎዱን፤ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ፖሊሲ እንዲመረምሩ፤ ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል እንዲያግዙ…ወዘተ መጠየቅ አንዱ አላማ ነበር፡፡ በሁለተኛነት፣በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር ለመወያየት ነው፡፡ በሶስተኝነት፣ ለድርጅታችን ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው።
ከአሜሪካ ባለስልጣናትም ጋር ተገናኝተዋል፡፡  ውይይታችሁ በምን ላይ ያተኮረ ነበር?
የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት የሴኔት አባላት፣ በተለይ የህግ ጉዳዮችን ከሚያዘጋጁት ጋር ተነጋግሬያለሁ፡፡ ከ‹‹ሠማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ይልቃል ጌትነት ጋር ‹‹አትላንቲክ ካውንስል›› ከሚባል የአሜሪካ የሃሣብ አመንጭዎች ቡድን ጋር ተወያይተናል፡፡ እዚያ ውስጥ ከነበሩትና አስቀድሞ ከማውቃቸው መካከል፣ በ1983 ለንደን ላይ ኢህአዴግ ሃገር እንዲረከብ፣ ምርቃት የሰጠው፣ ሄርማን ኮኽ የሚባለው ሰው ነበር፡፡ የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺል የሚባለውም ነበር፡፡ እንዲሁም ከሌሎች የአሜሪካ ባለ ራዕዮችና ሃሳብ አመንጪዎች ጋር 2 ሰዓት የፈጀ ውይይት አድርገናል፡፡ በአብዛኛውም አሁን በሃገሪቱ ባሉ የህዝብ ተቃውሞዎች ላይ አተኩረን ነው የተወያየነው፡፡
በሃገሪቱ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ምን አስተያየት አላቸው? የተሟላ መረጃስ ያገኛሉ?
እነሱ ሁሉንም ያወቃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታና የሚደረገውን ነገር በተመለከተ በቂ መረጃ አላቸው፡፡ የራሳቸው መንግስት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲም ችግር እንዳለው ያውቃሉ፡፡  በተደጋጋሚ፣‹‹ተቃዋሚው አንድ ሆኖ አልወጣም፤ አንድ ላይ ሆናችሁ ለማየት እንፈልጋለን›› የሚል ሀሳብ ነበር የሚሰነዝሩት፡፡
ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር ያደረጋችሁት ውይይትስ—-ምን ይመስላል?
ስለ ዳያስፖራው ፖለቲካ፣በመፅሐፌ ላይ ገልጬዋለሁ፡፡ ዳያስፖራው እንደ ማናችንም በሃገር ጉዳይ የሚጨነቅ ነው፡፡ ክፍፍሉ እዚህም እንዳለው፣ እዚያም ይንፀባረቃል፡፡ ምናልባት እዚህ ካለው ጎልቶ ይታይ ይሆናል፡፡ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የማክረር ዝንባሌ ይታያል፡፡ ጎንደር ላይ በተደረገው ሰልፍ፣ህዝቡ የኦሮሞን ህዝብ ደግፎ እንደሚቆም ከገለጸ በኋላ፣ በዳያስፖራው ዘንድ ቀድሞ የነበረውን አመለካከት የቀየረው ይመስላል፡፡ በአገር ውስጥ የተፈጠረው አንድነት፣ የዳያስፖራውን ክፍፍል ማስቀረት ብቻ ሳይሆን አዲስ አይነት ግንኙነት እንዲጀመርም አድርጓል፡፡ አንድ ላይ ሠላማዊ ሠልፍ የመውጣት፤ በጋራ የመሠብሠብ ነገር መፈጠሩን ለማየት ችያለሁ፡፡ አሁን በዳያስፖራው የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ለውጥ አለ ብዬ መናገር እችላለሁ፡፡
በሃገር ውስጥ ያለው ተቃውሞና ግጭት የተለያየ መልክና ቅርፅ እየያዘ ወደ አንድ አመት ገደማ ሊያስቆጥር ነው፡፡ ተቃውሞው ከቀጠለ ሁኔታዎች ወዴት የሚያመራ ይመስልዎታል?
እኔ ደጋግሜ እንደምለው፣ ሃገሪቱ አሁን መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት፡፡ የኢህአዴግ መሪዎች ልቦና ገዝተው፣ ሃገሪቷንና ህዝቦቿን ወደተሻለ የጋራ የፖለቲካ ስርአት… ማለትም መነጋገርና መደራደር ወደሚቻልበት መስመር ካልገቡ፣ ቻይኖች፤ ‹‹ቀውስ የተሻለ ሁኔታን ይዞ ይመጣል›› እንደሚሉት፣ያ እድል ሊመጣ ይችላል፡፡ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ የሚችልበት ዕድልም አለ፡፡
መንግስት ችግሮች ለመፍታት ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከዚህ በተረፈ የሚፈጠሩ ሁከቶች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ጠቁሞ፣በሃይል እርምጃ ህግና ስርዓት አስከብራለሁ ብሏል፡፡ ከእነዚህ የመፍትሄ መንገዶች ምን ውጤት ይጠብቃሉ?
ተሃድሶና የሃይል እርምጃ ከዚህ በፊትም ውጤት እንዳላመጡ ታይቷል፡፡ እኛ ከዚህ ቀደም መሬት ዘረፋን በሚመለከት፣በተለይ ማስተር ፕላን ብለው ባወጡት ጉዳይ ላይ መንግስትን ለመምከር ሞክረን ነበር፤አልሠሙንም፡፡ እንደፈራነውም ችግር ተፈጠረ፡፡ ከዚያ በኋላም በየደረጃው እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ችግሮችን በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ፤ መንግስት ያልተመጣጠነ ሃይል መጠቀሙ መፍትሄ እንደማይሆን ተናግረናል። ህዝብ ለውጥ እየፈለገ ነው፤መሠረታዊ ለውጥ ነው የሚያስፈልገው፤ እርምጃዎች ውሰዱ ብለን በተደጋጋሚ ወትውተናል፡፡ ነገር ግን ሃሳባችን ቸል በመባሉ የበለጠ ቀውስና ደም መፋሰስ ተከስቷል። አሁንም ቢሆን በፖሊሲዎቻቸው ላይ ደጋግመው ካላሰቡና ወሳኝ እርምጃዎችን ካልወሰዱ አሳሳቢ ነው፡፡ ተሃድሶ የሚባለው ጨዋታ ነው፡፡ ኢህአዴግ ችግር በገጠመው ቁጥር  ተሃድሶ ይላል፡፡ ውጤቱ ግን ጉልቻ መቀያየር ነው የሚሆነው፡፡ ፊት ያለውን ባለስልጣን ወደ ኋላ ወስደው፣ ኋላ የነበረውን ወደፊት ያመጣሉ፤በቃ የእነሡ ተሃድሶ ይሄው ነው። አዲስ ፖሊሲ፣ አዲስ አስተሳሰብ የላቸውም። በተለይ ዲሞክራሲያዊ አሰራር አልታየም፡፡ በኔ እምነት፣ ከዚህ በኋላ ምንም የቀራቸው የሚታደስ ነገር የለም፡፡ ህዝብም ተሃድሶ አይደለም እየጠየቀ ያለው፤ መሠረታዊ ለውጥን ነው፡፡
በብዙዎች ዘንድ ኢህአዴግ ስልጣን ቢለቅ፣ሃገርን ተረክቦ ማስተዳደር የሚችል ሃይል የለም የሚል ስጋት አለ፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው? ስጋቱስ ከምን የመነጨ ነው ይላሉ?
በዋናነት መሰረታዊ ችግሩን የሚፈጥረው ኢህአዴግ ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ተቃዋሚዎች እንዳይፈጠሩ ትንሽ ብቅ የሚሉትን እጅና እግራቸውን አስሮ፤ ቢሮ እንዳይከፍቱ እየከለከለና እንዳይንቀሳቀሱ እያደረገ ያለው ኢህአዴግ ነው፡፡ ለዚህ ተጠያቂ መሆን ያለበትም ተቃዋሚው ሳይሆን ኢህአዴግ ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን በተግባር ላይ አላዋለም፡፡ ህገ መንግስቱ፣ነፃ ሚዲያ ይላል፤ ይሄ በተግባር የለም፡፡ ነፃ የዲሞክራሲ ተቋማትን ህገመንግስቱ ይፈቅዳል፤ በተግባር ግን የሉም፡፡ ተቃዋሚም በሚፈለገው ደረጃ እንዳይወጣ አድርጎ የፖለቲካ ምህዳሩን ያበላሸው ኢህአዴግ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ሽብርተኛ ተብለው ይታሠራሉ፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ተቃዋሚ ጠንክሮ እንዳይወጣ ሆኗል። ከ97 በኋላ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዴት እንደተፈለጡና እንደተቆረጡ ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል ይሄን እያደረገ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹እኔ ከሌለው ሃገሪቱ አትኖርም›› እያለ ፕሮፓጋንዳ ያሠራጫል፡፡ አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ካለው ምሁር በተቃዋሚው ጎራ ያለው በእጅጉ ይልቃል፡፡ ይሄ በገሃድ የሚታይ ሃቅ ነው፡፡
በልምድም በእውቀትም ኢህአዴግ ውስጥ ካሉት ሰዎች በተቃዋሚ ደጋፊነት ያሉት ይልቃሉ። ስለዚህ አንዳንዶች እንደሚሉት፤እኔ በዚህ በኩል ስጋት የለኝም፤ በርካታ ይህቺን ሀገር ለማስተዳደር የሚመጥኑ ሰዎች አሉ፡፡ ተቃዋሚው ምሁራንን አስተባብሮ ለመምራት ሰፊ አቅምና ተቀባይነት አለው፡፡ ስለዚህ ጭንቀቱ በዋናነት የኢህአዴግ ነው፡፡ “እኔ ከሌለው ሀገር ይፈርሳል፣ መአት ይወርዳል›› እያለ የሚያስወራው ኢህአዴግ ነው፤ ስጋቱም የኢህአዴግ ነው፡፡ በእውቀትም በልምድም ብዙ ምሁራን የመስራት እድል አላገኙም፡፡ ስንት ኢኮኖሚስቶች ናቸው ያሉት? ተቃዋሚው ጋ ስንመጣ፣ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር የሚያስተምሩ፣ አለም ያከበራቸውና እውቅና የሰጣቸው ሰዎች አሉ፡፡ ስንት ፖለቲካል ሳይንቲስቶች ናቸው ከኢህአዴግ ጋር የሚሰሩት? በአጠቃላይ ሀገሪቷን መምራት የሚችል በእውቀትና በልምድ የዳበረ የሰው ኃይል ያለው በተቃዋሚው ወገን ነው፡፡ ተቃዋሚው እድሉን ቢያገኝ፣እነዚህን የእውቀት ሀብቶች በአግባቡ ተጠቅሞ ሀገሪቱን ይታደጋት ነበር፡፡
አሁን በአገሪቱ ለተከሰቱት ቀውሶች መፍትሄው ምንድን ነው ይላሉ?
እኔ ኢህአዴግ አንድ ውለታ እንዲውል የምጠይቀው፣ ብሄራዊ የአንድነት መንግስት እንዲቋቋም እድል እንዲፈጥር ነው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን ከፍቶ፣ ጉዳዩ ያገባናል ከሚሉ እውነተኛ የህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት መጀመር አለበት። ‹‹ታድሻለሁ›› ብሎ ተቀባብቶ መቅረብ የትም አያደርስም፡፡ መሰረታዊ የሆነ የፖሊሲ፣ የአሰራርና የአመራር ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ አንድ መድኀኒት አልሰራም ካለ፣ ሀኪም ያንኑ መድኃኒት መልሶ አያዝም፤ መድኃኒቱን ይቀይራል፡፡ የኢህአዴግም ተሃድሶ ተደጋግሞ ታይቶ፣ ተፈትኗል፤ የመጣ ለውጥ የለም፡፡ ተፈትኖ የወደቀ መድኃኒትን በህዝብ ላይ ደጋግሞ መሞከር ለውጥ አያመጣም፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሟል፡፡ ለህመሙ አዲስ ሃኪምና መድኃኒት ያስፈልገዋል፡፡ የሚለዋወጡት ሹመኞች እኮ ከካድሬ ትምህርት ያለፈ እውቀት የሌላቸው፣ ተቀባብተው የሚቀርቡ ሰዎች ናቸው፡፡
‹‹የብሄራዊ አንድነት መንግስት›› ይቋቋም ሲሉ፣ ይሄን ማን ነው ኃላፊነት ወስዶ ማስተባበር የሚችለው?
ሁሉም አካል አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ፣ ከስልጣን እስካልወረደና የደህንነትና ሌሎች ኃይሎችን እስከተቆጣጠረ ድረስ ለዚህ ሃሳብ መንገድ መክፈት ያለበት እሱ ነው፡፡  ይሄ ካልሆነ አስቸጋሪ ነው። ለዚህ ነው ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ መልኩ ውለታ ይዋል ያልኩት፡፡ አፈና ከሌለ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች ወደፊት ለመውጣትና የሂደቱ አካል ለመሆን አይቸገሩም፡፡
በኦሮሞ የኢሬቻ በአል ላይ በደረሰው አስከፊ እልቂት፣ መንግስትና ተቃዋሚዎች በመንስኤውና  በሞቱ ሰዎች ቁጥር ዙሪያ እየተወዛገቡ ነው፡፡ ህዝቡ ሃቁን እንዲያውቅ ምን መደረግ አለበት?
ይሄ ግልፅ ነው፡፡ ገለልተኛ አካል ጉዳዩን መመርመር አለበት፡፡ የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ያሉበት አካል፣ጉዳዩን እንዲያጣራ እንፈልጋለን፡፡ የሟቾችን ቁጥር መደበቅ ምንም የፖለቲካ ትርፍ አያመጣም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በተሰበሰበበት አስለቃሽ ጭስ ከተለቀቀና ሰዎቹ ታፍነው ጉዳት እንዲደርስ ከተደረገ በኋላ፣ ‹‹የለም እኔ ጥይት አልተኮስኩም›› ማለት አያዋጣም፡፡ ወጣቶቹ በወቅቱ ከተቃውሞ ጩኸት በላይ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ በጥፊ እንኳ የተመታ የመንግስት ባለስልጣን የለም፡፡ ገና ለገና የሆነ ነገር ይፈጠራል በሚል ነው እርምጃው የተወሰደው፡፡ ለመቃወም ፈቃድ አያስፈልገውም። ሰዎች ለምን ተቃወሙ አይባልም፡፡ እስከ 3፡30 ሁሉም ነገር በሰላም ይከናወን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ከመንግስት ጋር የተለየ ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚታሰቡ የቀድሞ አባ ገዳን አምጥተው ንግግር እንዲያደርግ ማድረጋቸው አግባብ አልነበረም፡፡ ሌላው ህዝብ መተላለፊያ እንደሌለው እየታወቀ፣ ከባድ ድምፅ የሚያወጣ ጭስ መተኮስ ምን ማለት ነው? ባለስልጣን ባልተነካበት፣ የመንግስትና የህዝብ ንብረት ባልወደመበት… ለምን ጭስም ሆነ የፕላስቲክ ጥይት ይተኮሳል? ይሄ አሳዛኝ ነው፡፡
መንግስት በደረሰው አደጋ ማዘኑን ገልፆ፤የ3 ቀን ብሄራዊ የሃዘን ቀን አውጇል ….
እኔ ይሄን እንደ ፌዝ ነው የቆጠርኩት፡፡ ከዚያ በኋላም ሰላማዊ ሰልፈኞች ተገድለዋል፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ፍጥጫዎች ነበሩ። ከልብ ቢታዘን ኖሮ፣ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆ፣ ‹‹ከዚህ በኋላ አይደገምም፤የፀጥታ ኃይሉ የወሰደው እርምጃ ትክክል አይደለም›› ተብሎ ይነገራል። ከዚያ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ለፀጥታ ኃይሉ ምስጋና ነው ያቀረቡት፡፡ ሃዘኔታው ከልብ መሆኑ የሚያጠራጥረው እዚያ ላይ ነው፡፡

አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወዱ እርምጃዎች ቆንጅት ስጦታው  



አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወዱ እርምጃዎች
እርምጃ ለመውሰድ ስልጣን ስላለው ሰው በተደነገገበት የመመሪያው ክፍል፤ የህግ አስከባሪዎች የመመሪያውን ድንጋጌ ተላልፈው በተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እርምጃዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተመላክቷል።
ክልከላዎች ሲጣሱ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ፤ በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራት ተፈፅመው ሲገኙ፤
1. ህግ አስከባሪዎች ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላሉ፤
2 አዋጁ ተፈፃሚነቱ እስከሚያበቃበት ድረስ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስነው ቦታ እንዲቆዩ የማድረግ፤
3 ተገቢውን የተሃድሶ ትምህርት በመስጠት የሚለቀቀውን እንዲለቀቅ፣ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርበውን ደግሞ እንዲቀርብ ማደረግ
4 ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በማንኛውም ስአት ብርበራ የማድርግ፤ የአካባቢውን ህዘብ እና ፖሊስ በማሳተፍ ማንኛውንም ወንጀል የተፈፀመበት ወይም ሊፈፀምበት የሚችል ንብረት መያዝ፤ወይም ንበረቱ እንዲጠበቅ ማደረግ
5 በማንኛውም ሬድዮ ቴሌቭዠን ድምፅ፣ ምስል ፎቶ ግራፍ፣ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልእክቶችን መቆጣጠር እና መገደብ ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል
6 የተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ
7 በትምህርት ተቋማት ሁከት እና ረብሻ ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምት መውሰድ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለተቋማቱ ትእዛዝ መስጠት
8 ማንኛውም የህዝብን ሰላም እና ፀጥታ ሊያደፈርሱ ይችላሉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩ እና የሚታሰቡ ሰዎችን እንዲሁም ቡድኖችን ወደ ተወሰነ አካባቢ እንደይገቡ፣ እንዳይገኙ ወይም በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ ማድረግን ጨምሮ አግባብነት ያለቸውን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።
ራስን ለመከላከል በፀጥታ ሀይልች ስለሚወሰድ እርምጃም መመሪያው ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።
ህግ አስከባሪዎች እና በድርጅት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጦር መሳሪያ ወይም በስለት ህይወታቸውን እና ንብረተቻውን አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት በተሰነዘረ ጊዜ ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።
በትምህርት ተቋማት የመግባት ስልጣንም በመመሪያው ስንጋጌ ወጥቶለታል። መመሪያው እንደሚለው በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ችግሩን ለማስቆም የህግ አስከባሪ አካላት በተቋማቱ ውስውጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይችላሉ።
በሌሎች የመንግስት እና የግል ተቋማት አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አካላት እና ባልደረቦች በተቋማቱ ውስጥ ለመግባት እና አስፈላጊ ከሆነ ለማቆየት ይችላሉ።
ተሃድሶ እና ፍርድ ቤት ማቅረብን በተመለከተም መመሪያው ይህንን ይላል፤ 
በህግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረግ የተሃድሶ እርምጃዎች እንደሚኖሩ በተጠቀሰበት የአዋጁ ድንጋጌ፤ ኮማንድ ፖስቱ ለፍርድ መቅረብ ያለበትን እንዲቀርብ ያደርጋል፤
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በተፈፀሙ የሁከት እና የነውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ
የጦር መሳሪያ ሳይዝ የመንግስትም ሆነ የግለሰን ንብረት የዘረፈ እና በአቅራቢያው ለሚገኝ ፀጥታ አስከባሪ ሃይል የዘረፈውን መሳሪያ እና ንብረት፤ ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን የሰጠ ፤
ከዚህ በፊት ለህገ ወጥ ተግባራት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ፣ወረቀት በመበተን፣ አድማ በማድርግ የተሳተፈ እና ያነሰሳ፣ ሰው የገደለ፣ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ፣ማንኛውንም ወንጀል የፈፀመ ስው፤
ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን ከሰጠ እንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላል እና ከባድነት ዋና ፈፃሚ እና አባሪ ተባባሪ መሆኑ ታይቶ፣ በኮማንድ ፖስቱ የተሃድሶ ትምህርት ተሰጥቶት እንዲለቀቅ ይደረጋል።

Source  Fana Broadcast

Friday, October 14, 2016

በዘረኝነት መጠቃቀሙ ቀጥሏል፤ለምርምርና ድህረ ምረቃ በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡት የትግራይ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው ተረጋግጧል። ቆንጅት ስጦታው



በዘረኝነት መጠቃቀሙ ቀጥሏል፤ለምርምርና ድህረ ምረቃ በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡት የትግራይ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው ተረጋግጧል።
በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የምርምርና ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ማመልከቻ ያስገቡ ተማሪዎች ውድቅ ሆኖባቸው ትምህርት ቤቱ ከትግራይ ክልል ለመጡ ብቻ በመፍቀድ የሕወሓት የበላይነትን ማረጋገጡ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የሚገኙ የኣስተዳደርና የትምህርት ክፍል የሚመለከታቸው ምሁራንና ሰራተኞች በምሬት ይናገራሉ።
በተለይ ከባህራ ዳር ዩንቨርስቲ የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው ዩንቨርስቲው ለዚህ ኣመት ሊያስተናግዳቸው የፈለገውን የኦሮሚያና የኣማራ የምርምርና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በመመለስ የትግራይ ተማሪዎችን እንዲቀበል ትእዛዝ መተላለፉ ታውቋል። በዘረኝነት መጠቃቀሙ የቀጠለ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀውና ኣሁንም እንደሚሰራበት በገሃድ እንደሚታየው ኣለማቀፍ ስኮላርሺፕ ከሚሰጣቸው ተማሪዎች ውስጥ ዘጠና ስምንት ከመቶው የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በግልጽ ይታወቃል።
ጋዜጠኛና ኣክቲቪስት ሙሉቀን ተስፋው በሰጠው ኣስተያየት ፤ እነዚህ ሰዎች እኮ ምንም እፍረት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም። በውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚንስትር ለሁለተኛ ዲግሪ ወደ ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ የተላኩ ተማሪዎችን ዝርዝር ተመልከቱት፦የትግራይ የበላይነት የሌለባት ኢትዮጵያ ይህች ናት። ለማንኛውም የባሕር ዳር ወጣቶች ሰዎቹ ለመማር ይሁን ለሌላ ሥራ አመጣጣቸው ስለማይታወቅ በዝርዝር ማወቃችሁ አይከፋም። ብሏል።

የወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመውደቂያው ሰበር ዜና ነው – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት ቆንጅት ስጦታው  



የወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመውደቂያው ሰበር ዜና ነው – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት
የወያኔ መንግስት ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያደረበት ፍርሃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና እንደሰደድ የተያያዘው የህዝባዊ እምቢተኝነት ድል የነሳውና ያንበረከከው የመሆኑ ምልክት ነው። ላለፉት 25 ዓመታት በወታደር ጠመንጃና በደህንነት ታፍኖና ተወጥሮ የኖረ ህዝብ በጊዜያዊ አዋጅ ሥር ነውና ለምን ይህን አዋጅ ማወጅ እንዳስፈለገ ግልጽ አይደለም። የበለጠ ያለ ገደብ የመግደያና የማሰር፣ ሰላማዊውን ሕዝብ የማንገላታት አድማሱን አስፍቶ ለማንም ስብዕናና ሕሊና ላለው የማይዋጥ የመጨፍጨፊያ ፈቃድ አለን ለማለት ካልሆነ በስተቀር።
ከትቂት ዓመታት በፊት የወጣው የፀረ ሽብሩ አዋጅ የሃገሪቱን ሕገመንግስት ገርስሶ፣ የህዝብ መብት ነጥቆ፣ አስተዳደሩን በወታደር፣ በሰላዮችና በካድሬዎች ሥር የጣለው መሆኑን ወያኔ ዘንግቶት አይመስለንም። የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብና የእምነት ነጻነት ህዝቡ ከተነፈገ ዓመታት አስቆጥሯል። የወያኔ ገዳዮች፣ አሳሪዎችና ዘራፊዎች አይከሰሱም አይገሰሱም። ስለሆነም የፀረ ሽብር አዋጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነበር ለማለት ነው።
በአገሪቱ ሕግ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ያለበት አገር በውጭ ጠላት ሲወረር፤ የተፈጥሮ አደጋ ሲፈጠርና ደህንነትን የሚያናጋ የወረርሽኝ ደዌ ሲደርስ ነው። አዋጅ የሚሆነውም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተደንግጎና አልፎ በ2/3 ድምፅ የተወካዮች ምክር ቤት ሲያፀድቀው ነው። ወያኔዎች ሕግ አውጭም አስፈፃሚም ናቸውና በፓርላማ ሣይፀድቅ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያወጁት። ማን ቢጠይቃቸው?
በአሁኑ ሰዓት አገርን ባስመረረው የአግአዚ ጦሩና እንደ ተፈጥሮ አደጋ የደሀውን ቤት በሚያወድመው አፍራሽ ግብረ ሃይሉ አማካይነት ሰላማዊውን ሕዝብ በማሸበርና በማስጨነቅ ሕዝቡን በሽታ ላይ የጣለው ራሱ የወያኔ ሥራዓት ነው። ስለዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማወጅ የነበረበት በሕዝቡ ላይ ሳይሆን በራሱ ላይ ነበር።
ይህ የህዝብ ማጥቂያ አዋጅ የህዝቡ ቁጣና ቁርጠኝነት እንዲያይልና እንዲገነፍል ከማድረጉም በላይ እንደ ባህር ሞገድ የወያኔን የተንኮል ጀልባና ባለስልጣናቱን አረፋ እያስደፈቀ የሚያሰጥም እንደሚሆን ጥርጥር የለንም።
መታወቅ ያለበት ወያኔ የመጨረሻውን ሲቃ እስከሚተነፍስ ድረስ ከመቸውም የከፋ አደጋ ማድረሱ አይቀርምና ወገኖቻችን በአንድነት፣ በብልህነትና በጀግንነት በጋራ ለመመከት መዘጋጀት አለባቸው። ወያኔዎች ስልጣን ያሰከራቸውና በተዘረፈ ገንዘብ ያበዱና ራስ ወዳዶች ናቸውና አጥፍቶ መጥፋት የሚሳናቸው አይደሉም።
ህዝብም እርስ በእርሱ እንዲጠፋፋ ባላቸው ፕላን መሰረት የወያኔ ካድሬዎችና የደህንነት ሰዎች ባቀነባበሩት ሴራ በደቡብ ክልል በጌድዮ ዞን በዲላ ወረዳ በወያኔ በተወናበዱ ጥቂት የጌድዮ ተወላጆች በአማራና በጉራጌዎች ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ በመክፈታቸው አብያተ ክርስቲያናት፣ መስጊዶችና መኖሪያ ቤቶች የንግድ ተቋሞች እንዲቃጠሉ ተደርጓል። ይህ ዓይነቱ ወንጀል በሌላም አካባቢዎች እንዳይደገም ሕዝቡ ነቅቶ መጠበቅ አለበት።
በቂሊንጦ እስር ቤት ወገኖቻችንን በእሳት የፈጁበት ሀዘን ከሰው ልብ ሣይጠፋ በዝዋይ እስር ቤት የሚፈልጓቸውን እስረኞች ለመግደል በማሴር የወያኔ ካድሬዎች ባስነሱት እሳት 11 እስረኞች እንደተገደሉ ይፋ ሆኗል።
ምዕራባውያን አገሮች የህዝቡ ደም ለዓመታት በግፍ ሲፈስ ጉዳዩ አሳስቦናል ከማለት ባለፈ እልቂቱን የሚያስቆም እርምጃ ካለመውሰዳቸውም በላይ ይህን የወንበዴ ሥራዓት መደጎማቸውን እንደቀጠሉ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀም በኋላ አሁንም ዓይኔን ግንባር ያድርገው ምንም አላየሁም የሚሉ ይመስላሉ። ያለፈው ልምዳችን እንደሚያሳየን ከሆነ ግን ከነሱ ብዙም መጠበቅ እንደለለብን ነው።
እነሱ በሚለግሱት ገንዘብ በተሸመተ ጥይት ሕዝባችን እንደ ቅጠል ሲረግፍ በእሳት ሲፈጁትና ገደል ሲያስገቡት ምዕራባውያን አድም እርምጃ አልወሰዱም። በዚህም ድርጊት ከእኛ ህይወት የራሳቸው ጥቅም እንደሚያመዝን እየነገሩን ነው። ስለሆነም መገንዘብና ማመን ያለብን የወያኔ ሥራዓት እየፈፀመ ካለው ድብደባ፣ ግድያ፣ እሥራትና ሽብር የፈጣሪ እርዳታ ተጨምሮበት ሕዝባችንን መታደግ የምንችለው እኛና እኛ ብቻ መሆናችንን ነው።
የወያኔን ሰው በላ ሥራዓት ከሥሩ ነቅንቆ ያንገዳገደውና ፍርሃትን በ25 ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰበረው የሙስሊሙ አይበገሬ ፊልሚያ፣ የኦሮሞው ጀግንነትና የአማራው ቆራጥነት በድምሩ የወያኔ ሥራዓት ተንኮታኩቶ ግብዓተ መሬቱ በቅርቡ የሚፈፀም መሆኑን አመላካቾች ናቸው።
መሣሪያ ታጠቃችሁ ይህን ሥርዓት በማገልገል ላይ የምትገኙ ወገኖቻችን በተለይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ ከራሳችሁ ጋር መክራችሁ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን መግደል አቁማችሁ ከወያኔ ካምፕ ውጡና ወደ ሕዝብ ጎራ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
በአገርና በውጭ ያለችሁ የትግራይ ወገኖቻችንም እናንተን የማይወክሉና ሊወክሏችሁም የማይችሉ ጥቂት ወንጀለኞች በእናንተ ስም በኦሮሞ፣ በአማራውና በኮንሶ ሕዝቦች ላይ የሚያደርሱትን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በማውገዝ እየደማ፣ እየቆሰለና እየሞተ ካለው ወገናችሁ ጎን ተሰልፋችሁ የወያኔን ስራዓት በቁርጠኝነት ታገሉ።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት የወያኔ ሥራዓት የአገሪቱን ሕገ መንግስት በመጣስና የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም በአስቸኳይ አዋጅ ከለላ ሥር ለራሱ የሰጠውን ሕዝብን የመፍጀት የምስክር ወረቀት ወይም ፈቃድ በጽኑ ያወግዛል።
የወያኔ ሥራዓት ያስተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመውደቂያው ሰበር ዜና ነውና አገዛዙ ሙሉ ለሙሉ እስኪያከትም ድረስ መራራውን ትግል በጋራ እንድንቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋላን።
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፍ ይቀጥላል!
ምንጊዜም ድል የሕዝብ ነው!
አላሁ አክበር!!!
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት
No automatic alt text available.

የኢትዮጵያ ጀግና የብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ተፈራ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ ቆንጅት ስጦታው  




ሶማሊያ ኢትዮጵያን በምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ ግንባሮች በወረረችበት ወቅት (1969-1970) በተዋጊ ጄት አብራሪነት ወደር የሌለው ጀግንነት በመፈጸማቸው ከቀድሞው መንግሥት ‹‹የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ›› እና የ‹‹የካቲት 1966 1ኛ ደረጃ ኒሻን›› ተሸላሚ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ተፈራ ሥርዓተ ቀብር መስከረም 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
Teddy Habesha's photo.
በሥርዓተ ቀብራቸው በተነበበው የሕይወት ታሪክ እንደተገለጸው፣ ከሶማሊያ ጋር በ1969 ዓ.ም. በነበረው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር ኃይል በምዕራፍ አንድ ዘመቻው ጄኔራል ለገሠና ጓዶቻቸውን አሰማርቶ ከሐምሌ 17 ቀን እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1969 ዓ.ም. ድረስ በተናጠልና በቡድን ሆነው ከሶማሊያ አየር ኃይል ጋር ባካሄዱት የአየር ለአየር ውጊያ የጠላትን 12 ሚግ 21 እና 13 ሚግ 17 በድምሩ 25 ተዋጊ አውሮፕላኖች ከአየር ላይ በማራገፍ አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ ጄኔራል ለገሠ በደቡብ ግንባር መስከረም 11 ቀን 1970 ዓ.ም. በነበረው ውጊያ አውሮፕላናቸው በመመታቱ በፓራሹት በመውረድ ቢተርፉም በሶማሊያ ሠራዊት እጅ በመውደቃቸው ለ11 ዓመት በጦር እስረኝነት ሶማሊያ ውስጥ ቆይተዋል፡፡ ከአባታቸው ከአቶ ተፈራ ወልደ ሥላሴና ከእናታቸው ከወይዘሮ ተናኜ ተክለ ወልድ፣ ነሐሴ 13 ቀን 1934 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ሾላ ላም በረት አካባቢ የተወለዱት ብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ፣ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በደጃዝማች ወንድይራድና በኮከበ ጽባሕ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል፡፡
Teddy Habesha's photo.
አገራቸውን በውትድርና ሙያ ለማገልገል በነበራቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ፣ ጥቅምት 1 ቀን 1956 ዓ.ም. በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሐረር ጦር አካዴሚ የ7ኛ ጊዜ ተወዳዳሪ ዕጩ መኮንን በመሆን፣ አንጋፋውን የምድር ጦር ሠራዊት ሲቀላቀሉ፣ በሐረር አካዴሚ የአዛዥነትን ትምህርት ሲያጠናቅቁም ወደ አየር ኃይል ተዛውረዋል፡፡ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበሩትና በ75 ዓመታቸው ያረፉት ጄኔራል ለገሠ ሥርዓተ ቀብር በኢትዮጵያ አየር ኃይል እግረኛ ወታደር ታላቅ አጀብና የማርሽ ባንድ የሐዘን ዜማ ታጅቦ ሲፈጸም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፣ የቀድሞዎቹ የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍሥሐ ደስታና ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስን ጨምሮ የቀድሞ መንግሥት ከፍተኛ መንግሥታዊና ወታደራዊ ባለሥልጣናት እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ተገኝተዋል፡፡

Thursday, October 13, 2016

ሰማያዊና መኢአድ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ቤት ናቸው – #ግርማ_ካሳ  



13259998_1026870737397860_7809576735746440482_n
የሰማያዊ ፓርቲ ካለፈው ምርጫ ጀመሮ ለአንድ አመት ከአራት ወራት ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ አለማድረጉ ይታወቃል። ይሄም የሆነበት ዋና ምክንያት በሊቀመንበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እና በሌሎች አመራሮች መካከል አለመስማማቶች በመፈጠራቸው ነበር።
በፓርቲው ድርጅታዊ ደንብ መሰረት የድርጅቱ የበላይ አካል ጠቅላላ ጉብዬው ነው። የድርጅቱን ሊቀመንበር ፣ የድርጅቱን ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እና የደርጅቱን ኦዲት ኮሚሽን አባላት የሚመርጠው ይሄው ጉብዬ ነው። ሊቀመንበሩ አብረዉት የሚሰሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መርጦ በብሄራዊ ምክር ቤቱ ያጸድቃል። እንግዲህ እነዚህ ሶስቱ አካላት አንዱ ሌላውን እንዳያዝ ተደርገው ነው የተዋቀሩት። ይሄ ተጠያቂነት እንዲኖር ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ፈረንጆች check and balance የሚሉት አይነት ነው።
በፓርቲው ዉስጥ አለመስማማቱ ነገሮችን ሁሉ አስሮ ባለበት ወቅት፣ ለሁለት አመት በወህኒ ሽብርተኛ ተብሎ ከነሃብታሙ አያሌው ጋር ሲሰቃይ የነበረውና የድርጅቱ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢው የሺዋስ አሰፋ ከወህኒ ይወጣል። ሁሉም አመራሮች በማሰባሰብ የፓርቲው ችግር በዉይይት እንዲፈታ ለማድረግ ይጥራል። በዚህ ወቅት ነው ከአምስት ወራት በፊት፣ ከዚህ በታች የምታይዋት ፎቶ ለሕዝብ የተለቀቀችው። የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢውና የሕግ ባለሞያው አቶ ይድነቃቸው ከበደ፣ የምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀመነበሩ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ የኦዲት ኮሚሽን መሪ አቶ አበራ ገብሩ እና የህግ ባለሞያ የሆኑት አቶ ሳምሶን ገረመውን ነው በፎቶ የምናያቸው።እነዚህ ስድስት ወገኖች በሰማያዊ ፓርቲ ዉስጥ ያሉ ሶስት ተቋማት መሪዎች ነበሩ። ከኢንጂነር ይልቃ በስተቀር ሁሉም አሁንም መሪዎች ናቸው።
የሰማያዊ ፓርቲ መስከረም 28 ቀን ጠቅላላ ጉብዬ አድርጓል። በዚህ ፎቶ ላይ ካሉት ዉስጥ አምስቱ በጠቅላላ ጉብዬው ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በአባላት ፊት ቀርበው በድጋሚ ለመመረጥም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያላቸዉን አቋም ለመግለጽ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ጠቃላላ ጉባዬው የተጠራው ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ነው ይላሉ። ሆኖም ግን የድርጅቱ ኦዲት ኮሚሽን ጉባዬ መጠራት እንደሚችል በደንቡ ላይ በማያሻማ መልኩ በገልጽ ተቀምቷል። እርግጥ ነው እርሳቸውም ባሉበት ጉብዬው ተደርጎ ቢጠናቀቅ ኖሮ በጣም ጥሩ ይሆን ነበር። ግን በተለያዩ ምክንያቶች ለመገኘት ፍቃደኛ ካልሆኑ ፣ መቼም የሰማያዊ ፓርቲ የአንድ ሰው ፓርቲ ስላልሆነ፣ “እርሳቸው በተመቻቸው ጊዜ ሲመጡ ይመጡ” ብሎ ትግሉን ከመቀጠል ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖርም። (በዚህ አጋጣሚ ለወንድም ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በትግል ዉስጥ አለመስማማትና ግጭት እንዳለ ተረድተው፣ ከአዲሱ የሰማያዊ አመራር ጋር አብሮ በመስራት የድርሻቸዉን እንዲወጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ብዙ ሊሰሩና ሊያገለግሉ እንደሚችሉ አወቃለሁ። የሚያስፈልገው ፍቅርና ቅንነት ነው። ለመታግል፤ የግድ ሊቀመንበር መሆን የለብንም)
በመጨረሻ አንድ በጣም ትንሽ የሚመስል ግን በጣም ጠቃሚ የሆነ ነጥብ ማስቀመጥ እፈልጋለሁ። የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉብዬዉን ያደረገው በመኢአድ ጽ/ቤት ነው። ባለኝ መረጃ በዶር በዛብህ ደምሴ የሚመራው የመኢአድ አመራር “እኛና እናንተ እኮ አንድ ነን። ጽ/ቤታችን የናንተም ጽ/ቤት ነው። በፈለጋችሁበት ጊዜ ጽ/ቤቱን መጠቀም ትችላላችሁ። እኛ በፊትም መለያየት አልነበረብንም፤ አንድ ነን” በሚል ሰማያዊዎች ምን ነገር ሳይከፍሉ ጉባዬያቸውን በመኢአድ ጽ/ቤት እንዲያደረጉ በመፍቀዳቸው ነው ጉብዬው ሊደረግ የቻለው። ይህ የአንድነትና የሶሊዳሪቲ መንፈስ በአንድነት የለዉጥ ሃይሉ መካከል ፣ ያልነበረ በጣም መበረታታት ያለበት መንፈስ ነው። በዚህ አጋጣሚ ለመኢአድ አመራር አድናቆቴን እና ምስጋናዬን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።
አሁን በአገራችን ባለው ሁኔታ የአገዛዙ የግፍ ቀንበር ከመብዛቱ የተነሳ ዜጎች ወደ አመጽ እየሄዱ ነው። ፖለቲካው እጅግ በጣም ሲበዛ ከሯል። ሆኖም ግን መቼም ቢሆን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተባበረ መንገድ፣ በእውቀት ከተመራ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ጥርጥሬ የለኝም።
ሌላው ደግሞ አሁን እያየን ያለነው እንቅስቃሴ ዘር ተኮር የሆነ ብዙ ወገኖች ያላቀፈ እንቅስቃሴ ነው። ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ ያቀፈ፣ ለዘርና ለጎሳ ቦታ የማይሰጥ ድርጅት ያስፈልጋል። እንግዲህ እንደ መኢአድ ሰማያዊ ያሉ ደርጅቶች አሉ። መኢአድም ሰማያዊ አዲስ አመራር ነው ያላቸው። አብሮ የመስራት ፍላጎታቸው በጣም ጠንካራ ነው። እነዚህን ድርጅቶች በማጠናከርና በማገዝ በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ሥር እንታገል። ብሶት የምናሰማ ሳይሆን የምንታገል እንሁን። ትግል ደግሞ ከአልጋ ወደ አላጋ መዝለል አይደለም። የተሰበረዉን ጠግኖ፣ የደከመዉን አጠናክሮ መዉጣት

Wednesday, October 12, 2016

ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገድን አድርጎ አማራውን በሶስት ዙር ትጥቁን ለማስፈታት ወስኗል። ቆንጅት ስጦታው  



ፋሽስት ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገድን አድርጎ አማራውን በሶስት ዙር ትጥቁን ለማስፈታት ወስኗል። ከውስጥ አርበኞቻችንና የጎበዝ አለቆቻችን ባገኘነው መረጃ መሰረት ፋሽስት ወያኔ በመጀመሪያ ዙር ትጥቅ የሚያስፈታው የአማራን ልዩ ኃይል ነው። የአማራን ልዩ ኃይል ትጥቁን ካስፈታች በኋላ የቀጣዩ ዙር ኢላማ ደግሞ የአማራ ገበሬ ነው። በእቅዱ መሰረት በሶስተኛ ደረጃ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ የሚደረጉት የአማራ ሚሊሻዎች ወይንም በተለምዶ «ጉጅሌ» የሚባሉት ናቸው።
በዚህ መሰረት ዛሬ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ከዛሬ ጀምሮ ትጥቅ እንዲፈቱ እየተደረገ ነው። ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት ሁሉም የልዩ ኃይል አባላት አይደሉም። በቅድሚያ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት የልዩ ኃይል አባላት የአማራ ተጋድሎ ሲካሄድ «ግደሉ» የሚል ተልኮ ተሰጥቷቸው «ወገናችንን አንገድልም!» በማለት የህዝብ ወገን መሆናቸውን ያስመሰከሩት ህዝብ አክባሪዎች ናቸው። እነዚህ የህዝብ ልጆች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ከተደረጉ በኋላ ለግዳጅ በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል፡፡
ተስፋ የቆረጠ ህዝብ ትጥቁን ስለፈታ፣ ስለተገደለ፣ ወይንም ስለታሰረ ተጋድሎውን ሊያቆም አይችልም። ይህ ያልገባው ወያኔ የማይበስል ነገር ጥዶ በከንቱ ማገዶ ይጨርሳል

Tuesday, October 11, 2016

በሳሞራ የኑስ የሚመራ ጨፍጫፊ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ። ቆንጅት ስጦታው  



በሳሞራ የኑስ የሚመራ ጨፍጫፊ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ።
ሳሞራ የኑስ —  አሰፋ አብዩ —- ሲራጅ ፉርጌሳ ——–
እነርሱ ጭፍጨፋው ከ Civilian Dictatorship ወደ Military Dictatorship ጭፍጨፋ ማደጉን ነው ይፋ ያደረጉልን ፣ ሌላ አዲስ ነገር የለም ፣ መጨፍጨፍ በቃን ማለት የኛ የተጨፍጫፊዎች ድርሻ ነው ።
Zelelie Tsegaselassie's photo.
Zelelie Tsegaselassie's photo.
Zelelie Tsegaselassie's photo.

የኦሮሚያ ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏ ቆንጅት ስጦታው



የኦሮሚያ ከተሞች ህዝባዊ እምቢተኝነት በእጅጉ አይሏል፡፡ ትላንትም ሆነ ዛሬ የሚደረጉ ተቃውሞዎች የበረቱ ሲሆን፣ ህወሓትም ተቃውሞዎችን በአጋዚ ወታደሮቹ በኩል ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ከአጋዚ ወታደሮች ቁጥጥር እየወጡ መምጣታቸው እጅግ ያሳሰበው ገዥው የህወሓት መንግስት ጀምበር ያዘቀዘቀችበት እንደሚመስል ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ብርቱ ተቃውሞ መካሔዱን የሚገልጹ የዓይን ምስክሮች፣ በተቃውሞ ወቅት በተደረገ ራስን የመከላከል ድርጊት ከአጋዚ ወገን ከ30 በላይ ወታደሮች ሲያልቁ ከታጠቁ አርሶ አደሮች ወገንም የተጎዱ መኖራቸውን ምስክሮቹ ገልጸዋል፡፡ አጋዚዎቹ ተቃውሞ በሌለበት ሁኔታ አስቀድመው ተኩስ የከፈቱ ሲሆን፣ ከተገደሉት ወታደሮች በተጨማሪም የቆሰሉ መኖራቸውንም እነዚሁ የዓይን ምስክሮች አስረድተዋል፡፡
በምስራቅ ሐረርጌ ህዝባዊ ተቃውሞ መኖሩን መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን፣ በስፍራው ያለው የንግድ እንቅስቀሴ እጀግ ተዳክሞ ሱቆች ተዘግተው መዋላቸውን ከስፍራው የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡በምስራቅ አርሲ ዞንም ህዝባዊ ተቃውሞ መኖሩን እማኞች ገልጸዋል፡፡ እንደዚሁም በድሬዳዋ የተቃውሞ መንፈስ ከተማዋን የተቆጣጠራት ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም የአጋዚ ጦር በተለይ ለገሀሬ በሚባለው የከተማዋ ስፍራ መስፈሩን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
በአወዳይ ከተማ ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩን የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በርካታ ወታደሮችም በኦራል መኪኖች ተጭነው ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡ እንደዚሁ በወለጋ ያለው ሁኔታ ካለመረጋጋቱ በተጨማሪ፣ ጋምቤላን ከቄለም ወለጋ ጋር የሚያገናኘው የመኪና መንገድ በህዝቡ መዘጋቱን ተከትሎ አጋዚዎች ማለፊያ ማጣታቸውን የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአዳማ ቱሉ ህዝባዊ ቁጣ መነሳቱን ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመለከተ ሲሆን፣ በባቱ እና አካባቢው በተነሳው ተቃውሞም ቃድሮ አቦ የተባለ ወጣት በአጋዚዎች መገደሉን ተከትሎ ከተማዋ በከፍተኛ የህዝብ ቁጣ መናጋቷን እማኞች ገልጸዋል፡፡
Image may contain: text and one or more people

Monday, October 10, 2016

የአማራ ተጋድሎ መሪ አለው፣ የአማራ የጎበዝ አለቆች (አቻምየለህ ታምሩ)



የአማራ ተጋድሎ መሪዎች በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የሚገኙ የጎበዝ አለቆች ናቸው። የፊታችን ጥቅምት ሶስት ወር የሚሆነው ይፋዊ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆቻችን በብቃት እየመሩት ነው።
የወያኔ ልሳኖቹ ኢቢሲ፣ ሰንደቅና ሪፖርተር ሊያንቃቸው ጋት የቀረውን ተጋድሏችንን «መሪ የሌለው ትግል» አድርገው ሊያቀርቡት ይቃጣቸዋል። እነሱ የሚያውቁት የመሪ ሞዴል ከኮምኒስት ማኒፌስቶ የሚሳብ፤ በአብዮታዊ ዲሚክራሲ የተጠመቀ፤ እንደ ሊቀ መንበር መለስ ዜናዊ አይነት ፈላጭ ቆራጭ ግለሰብ ስለሆነ ከዚያ የተለየ አገርኛ የትግል አመራር ዘዴ ውጤት እንኳ ቢያመጣ «መሪ» ያለው መስሎ ሊታያቸው አይችልም።
የኛ ተጋድሎ የመሪ ሞዴል እንደነሱ ከአውሮፓ ያመጣነው የአንድ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት የሚሰፍንበትና ሙታን እድምተኞች ጀሌ ሆነው የሚሰለፉበት ድንግዝግዝ ሳይሆን ከአባቶቻችን የወረስነው፤ ወራሪዎቻችንንም በተደጋጋሚ ያሳፈርበት አገርኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ነው።
የጎበዝ አለቃ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ጎበዞች ከመሃከላቸው አንዱን ጎበዝ አለቃ አድርገው ስራቸውን የሚሰሩበት አገርኛ የአርበኞች አደረጃጀት ነው። የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት እንደ መለስ ዜናዊ አንድ «ጎበዝ» ሺ ነፈዞችን በዙሪያው አሰልፎ የሚነግራቸውን ብቻ የሚደግሙ ደናቁርት የተሰበሰቡበት ስምሪት አይደለም። በጎበዝ አለቃ አደረጃጀች ሁሉም ጎበዞች ስለሆኑ በመካከላቸው የበላይና የበታች የለም። የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት እንደ ወያኔ አንዱ ሲሞት ያለመሪ የሚቀር ስብስብ ሳይሆን ሁሉም በማንኛውም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አለቃ የመሆን ችሎታውም ሆነ ፈቃደኝነቱ ያላቸው ጎበዞች አደረጃጀት ነው።
መለስ ዜናዊ የፈጠረው «የአብዮታዊ ዲሞክራሲ» አደረጃጀት በበሉበት የሚጮሁ፣ በሆዳቸው የሚገዙ ካድሬዎች ጥርቅም ነው። ስለሆነም ኮንትራክታቸው ሆዳቸው እስከሞላ ድረስ ስለሆነ አለመተማመን፣ አለመከባበር፣ ጥላቻ፣ አንዱ ባንዱ ላይ መረማመድ የስብስቡ መገለጫ ነው። የኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ግን የመዋቅሩ መሰረት የቆመው በእኩልነት ላይ በመሆኑ መተማመን፣ መከባበር፣ መፋቀር፣ አንዱ ላንዱ ከኔ ይብስ መባባል ጎልቶ የሚታይ የስብስቡ መገለጫ ነው። መለስ ዜናዊ የገነባው «አብዮታዊ ዲሞክራሲ» ግን የበላይና የበታች ያለበት፤ መጠራጠር፣ ፍራቻ፣ ጥላቻ፣ ቅናትንና ጊዜን ጠብቆ መጠቃቃት መርሁ የሆነ የእፉኝት ልጆች ስብስብ ነው።
መለስ ዜናዊ የፈጠረው አደረጃጀት የአንድ ግለሰብ አስተሳሰብ ያለ ገደብ የሚፈጸምበት ስርዓት ነው። ስለሆነም የሚያኮርፈው፣ የሚከፋው፣ የሚያዝነውና ቂም የሚቋጥረው ሎሌ፣ አሽከርና ጀሌ ቁጥር የትየለሌ ነው። የኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ግን የሁሉም ሃሳብ በእኩልነት የሚስተናገድበት፤ የተሻለው በውይይት ተቀባይነት የሚያገኝበት፤ ከሃሳቦች ሁሉ ምርጥ የሆነው በሁሉም የጎበዝ አለቆች ይሁንታ አግኝቶ በሙሉ ስሜት ተግባራዊ የሚሆንበትና ውጤቱም ሁሉንም የሚያረካ ስርዓት ያነበረ የአባቶቻችን አስተዳደራዊ መዋቅር በሆኑ የሚያኮርፍ፣ የሚከፋ፣ የሚያዝንና ቂም የሚቋጥር አንድም ሰው የለም።
እኩልነት ብሎ ነገር ደብዛው የሌለበት የሊቀ መንገበር መለስ ዜናዊ «የአብዮታዊ ዲሞክራሲ» አደረጃጀት ስብስቡ የሚዘወረው በአንድ ሰው ሃሳብ፣ በአንድ ሰው ፍላጎት ስለሆነ የተሻሉ ሃሳቦች ወደፊት የመምጣት እድል የላቸውም። ሊቀ መንበሩም ከራሱ የስልጣን ጥቅም አንጻር ብቻ ስለሚያስብ ውጤቱ አብዛኛውን የስብስቡን አካላት የማያረካ ይሆናል።ይህ የበለጠ ጥርጣሬ፤ የበለጠ በቀለኝነት ያሰፍናል። ሊቀ መንበሩም ይህንን ስለሚያውቅ ጥርጣሬና በቀልተኝነትን ለመቆጣጠር ሲል ነጻነትን እያፈነ ይሄዳል። «ውስጣዊ ዲሞክራሲ» የሚለው የመለስ ዜናዊ «አብዮታዊ ዲሞክራሲ» አስተሳሰብ በግለሰብ አምባገነንበት የተደመደመው ጥርጣሬና በቀልተኝነትን ለመቆጣጠር ሲል ነጻነትን በማፈኑ ነው።
የአማራን ተጋድሎ መሪ የሌለው አድርጋችሁ የምታስቡ የአማራ ተጋድሎ መሪ እንዳለው ማወቅ ይኖርባችኋል። መሪዎቹ ደግሞ በአባቶቻችን ትውፊት የተደራጁትና በዘመናዊ መልክ የተቀናጁ መሬት ላይ ያሉት የአማራ የጎበዝ አለቆች ናቸው። የአማራ የጎበዝ አለቆች የአማራን ተጋድሎ እየመሩ ያሉት እንደ ወያኔ በሞቀ ቤታቸው ቤተ ሽፍታ [ቤተ መንግስት ላለማለት ነው] ሳይሆን ህዝባችን መሃል እየዋሉ፣ እያደሩና የህዝቡ አካል ሆነው ነው። የጎበዝ አለቆቻችን ትግሉን እየመሩ ያሉት የተሰዋውን አርበኛ በክብር መዝገብ አስፍረው እንደየ ቤተ እምነቱ በክብር እንዲያርፍ በማድረግ እንጂ እንደ መለስ ዜናዊ መለስ ዜናዊ «የሟች ወታደሮችን አሃዝ ይፋ የማድረግ ግዴታ የለብኝም» በማለት የአርበኞችን ሞራል በመግደልና የጠላትን ሞራል ደግሞ ከፍ በማድረግ አይደለም።
ጀግኖች አባቶቻችን ፋሽስትን አምስት አመታት ሙሉ በዱር በገደል የተፋለሙት በመሰረቱት የጎበዝ አለቃ ስርዓት ነው። ጥሊያን የዚህን አገርኛ አደረጃጀት መሪ ቢገድልም ሁሉም የጎበዝ አለቆች መሪ ሊሆኑ የሚችሉ ጎበዞች ስለሆኑ አንድ መሪ የጎበዝ አለቃ ቢሰዋ ትግሉ ነጻነታችንን መልሰን እስክናገኝ ድረስ ሊቆም ያልቻለው ለዚያ ነበር። ይህም በመሆኑ ነጻነታችንን ልናስመልስ ችለናል። አሁንም እየሆነ ያለው ያ ነው።
ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው የሚያውቁት ግን አንድ መሪ ብቻ ስለሆነ አንዱ ሲሞት ሌላውን ደምስሶ የሚገዛ እንደ መለስ ዜናዊ አይነት አንድ ግለሰብ ያለ ስለማይመስላቸው ተጋድሏችን መሪ የሌለው ይመስላቸዋል። ወያኔዎቹ በሙሉ የባንዳ ልጆች ናቸው። ጥሊያን በወረረን ጊዜ የጥሊያን አገልጋይ የነበሩትን ባንዶቹን አባቶቻቸውን ጀግኖቹና አርበኞቹ አባቶቻችን አቧራ አስገስተው ያሸነፏቸው በዚህ አገርኛ የጎበዝ አለቆች ስርዓተ ማህበር ተደራጅተው ነበር። ዛሬም ታሪክ መደገሙ አይቀሬ ነው። የአባቶቻችን ልጆች የሆንን የዛሬ ወጣቶች አባቶቻችን በመሰረቱት የጎበዝ አለቃ ስርዓት ተደራጅተን የባንዶች አባቶቻቸው ልጆች ከሆኑት ከወያኔዎች ነጻ እንወጣለን። እኛም ከአርበኞች አያቶቻችን አናንስም፤ ወያኔዎችም ከባንዶች አባቶቻቸው አይበልጡም። በአንድ ልብ ሆነን ህልውናችንን ሊያጠፋ በመጣ ጠላት ላይ የምናደርገውን ትግል የወያኔ ኢንተርኔት ቢቋረጥ፤ የትግራይ ነፍሰ በላ ጦር ሰራዊት ቢሰማራ ወይንም ሌላ ፋሽስት ወያኔያዊ ምድራዊ ኃይል ቢመጣ የአማራን ተጋድሎ ሊያስቆመው አይችልም።
#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!



የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወደከፋ ጦርነት የሚወስደን ነው – #ግርማ_ካሳ



የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው በሶስት ምክንያቶች ብቻ ነው። አንደኛው የዉጭ ወራሪ ሃይል ሲመጣ ነው። አሁን ኢትዮጵያ በማንም አልተወረረችም። ሁለተኛ የተፈጥሮ አደጋ ወይንም ጅምላ ጨራሽ ተላላፊ በሽታ ሲመጣ። እግዚአብሄር የተመሰገ ይሁን ይሄም ብዙ በሌሎች አንዳንድ አገሮች እንደሆነ በኛ አገር ብዙም ታየ ማለት አይቻልም።
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የአስቸኳይ አዋጅ ትላንት አውጇል። (ሕወሃት አውጆ ሃይለማሪያም እንዲያነብ ተደርጓል) ከላይ በተጠቀሱት ሁለት ምክንያቶች ሊሆን አይችልም። በሶስተኛው ምክንያት እንጅ።
በሕገ መንግስቱ የተጠቀሰው ሶስተኛው ምክንያት ህግና ስርዓት ፈርሶ የሕገ መንግስታዊ ስርዓቱና አደጋ ላይ ከሆነ እና በመደበኛ የሰላም አስጠባቂ ሃይላት ነገሮች መቆጣጠር ካቃጣቸው የሚል ነው። እዚህ ላይ ልብ እንበል፣ የሕግ መንግስቱ ስርዓት አደጋ ላይ መዉደቁ ብቻ በቂ ምክንያት አይደለም። ግን የሕግ አስጠባቂ ሃይላት ሁኔታውን መቆጣጠር ካልቻሉ የሚል አለበት።
ብዙ የአገዛዙ ደጋፊዎች ነገሮች አታካብዱ ፣ ይሄን ያህል ብዙ ችግር የለም ሲሉን ነበር። ሆኖም ይኸው ድርጅታቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዉጇል። ነገሮች መቆጣጠር እንዳልችሉ፣ አገር አደጋ ላይ እንዳለች አምነዋል።
አዋጁን ተከትሎ ጠቅላይ አቅቤ ህጉ የሚከተሉትን ብለአል፡
መንግስት የተጠረጠረ “ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ ይችላል። ቤቱንም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መበርበር ይችላል”
“ሁከት እና ብጥብጥ የሚያነሳሱ ድብቅ ቅስቀሳዎች ማድረግ ክልክል ነው”
“በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ኮማንድ ፖስት “ማንኛውንም ዓይነት የመገናኛ ዘዴ የመዝጋት ስልጣን አለው” ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌታቸው አምባዬ።
ሰዎቹ አንድ የዘነጉት ነገር ቢኖር ግን ይሄ አዋጅ መታወጁ የሚለዉጠው ነገር አለመኖሩ ነው። የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው የሕዝቡን ጥያቄ በማክበርና በመስማት ነው። በዉይይት፣ በብሄራዊ መግባባት ነው። አዋጅ እያወጡ ህዝቡን ማስፈራራትና መለፈፍ፣ በሕዝቡ ላይ መዛት የሚለዉጠው ነገር አይኖርም። የበለጠ ቀዉሱን ያባብሰዋል እንጅ።
ሌላው አላሉትም እንጅ አሁን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እናደርገዋለን ያሉት ላለፉት በርካታ አመታት ሲያደረጉት ነበር። እስከ አሁን ማረጋጋት ሳይችሉ አሁን ምን ተዓምር ተገኝቶ ማነጋገር የሚችሉት ? ከሰራዊቱ መሃከል ብዙዎች ጥለው እየሄዱ ነው። ሰራዊቱ እየተከፋፈለ ነው። የትኛው ሃይል ነው ድፍን ጎጃማ፣ ድፍን ጎንደርና አብዛኛውን ኦሮሚያስ ሊያረጋጋ የሚችለው ?
ለምን ይህ አዋጅ ነገሮችን በክፉ አቅጣጫ እንደሚያባብሰው አንድ ተጨማሪ ምክንያት አልቅርብ። ከዚህ በኋላ ሰው ሰለፎችና ተቃዉሞዎች በአደባባይ አያደርግም። ሕዝቡ በአደባባይ ብሶት ቢገልጽ ይሻል ነበር። አሁን ግን ነገሮችን በአደባባይ ሳይሆን በሕቡእ ወደ ማድረግ ነው የሚኬደው። አሁን ካየነው በባሰ ሁኔታ ነው ከፍተኛ ጥፋትና ዉድመት የሚደርሰው። ህዝብን በአዋጅ አፍኖ መግዛት በችራሽ አይቻልም።
የሃይማኖት አባቶች፣ አበው፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን….ሁሉም በፊናው አገዛዙ ችግሮችን በዉይይት እንዲፈታ፣ ለብሄራዊ መግባባት እንዲዘጋጅ ሲጠይቁና ሲማጸኑ ነበር። ከነርሱ መካከል አንዱ የሆኑኢት አቶ ገዱ አንዳራግቸው ራሳቸው ህዝብን አክብሮ፣ ከሕዝብ ጋር በመወያየት እንጅ በፖሊስ፣ በደህንነት፣ በመከላከያ ሰላም ማምጣት አይቻልም ነው ያሉት። ሆኖም ግን ህወሃቶች ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። በሕዝቡ ላይ በድጋሚ ጦርነት አውጀዋል።
በሕገ መንግስቱ ላይ ያለው ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚደነግገው ሕግ ከዚህ በታች ቀርቧል፡
Article 93 Declaration of State of Emergency
(1) (a) The Council of Ministers of the Federal Government shall have the power to decree a state of emergency, should an external invasion, a break down of law and order which endangers the Constitutional order and which cannot be controlled by the regular law enforcement agencies and personnel, a natural disaster, or an epidemic occur.
(b) Sate executives can decree a State-Wide state of emergency should a natural disaster or an epidemic occur. Particulars shall be determined in State Constitutions to be promulgated in conformity with this Constitution.
(2) A state of emergency declared in accordance with sub-article 1 (a) of this article:
(a) If declared when the House of Peoples’ Representatives is in session, the decree shall be submitted to the House within forty-eight hours of its declaration. The decree, if not approved by a two-thirds majority vote of members of the House of Peoples’ Representatives, shall be repealed forthwith.
(b) Subject to the required vote of approval set out in (a) of this sub-article, the decree declaring a state of emergency when the House of Peoples’ Representatives is not in session shall be submitted to it within fifteen days of its adoption.
(3) A state of emergency decreed by the Council of Ministers, if approved by the House of Peoples’ Representatives, can remain in effect up to six months. The House of Peoples’ Representatives may, by a two-thirds majority vote, allow the state of emergency proclamation to be renewed every four months successively.
(4) (a) When a state of emergency is declared, the Council of Ministers shall, in accordance with regulations it issues, have all necessary power to protect the country’s peace and sovereignty, and to maintain public security, law and order.
(b) The Council of Ministers shall have the power to suspend such political and democratic rights contained in this Constitution to the extent necessary to avert the conditions that required the declaration of a state of emergency.
(c) In the exercise of its emergency powers the Council of Ministers can not, however, suspend or limit the rights provided for in Articles 1, 18, 25, and sub-articles 1 and 2 of Article 39 of this Constitution.
(5) The House of Peoples’ Representatives, while declaring a state of emergency, shall simultaneously establish a State of Emergency Inquiry Board, comprising of seven persons to be chosen and assigned by the House from among its members and from legal experts.
(6) The State of Emergency Inquiry Board shall have the following powers and responsibilities:
(a) To make public within one month the names of all individuals arrested on account of the state of emergency together with the reasons for their arrest.
(b) To inspect and follow up that no measure taken during the state of emergency is inhumane.
(c) To recommend to the Prime Minister or to the Council of Ministers corrective measures if it finds and case of inhumane treatment.
(d) To ensure the prosecution of perpetrators of inhumane acts.
(e) To submit its views to the House of Peoples’ Representatives on a request to extend the duration of the state of emergency

Sunday, October 9, 2016

ሰበር ዜና፣ሕወሃት አጣብቂኙ ስለበረታበትና ህዝባዊ ተቃውሞው እየለበለበው ስለመጣ የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ



stateofemeየመጨረሻው ሰዓት ነው። ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ አውጇል። በኦሮሞና በአማራ ክልሎች ያለው የሕዝብ ተቃውሞ በመበርታቱ አላላውስ ያለውና አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ወያኔ ትላንትና ከሰዓት በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ለተላላኪው ለኃይለማርያም ደሳለኝ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነገር አድርጓል። ይህም ወያኔ

ሰበር መረጃ !…… የሐገር መከላከያዉ ከፍተኛ አቅም ወደ ትግራይ ተዘዋዉሮ አለቀ! [ልኡል አለም]




samora-yenusበሐገር መከላከያ ሚኒስቴር ዉስጥ የብቃትና ጥራት መመዘኛ ይዘትን ተንተርሶ ኢትዮጵያን እንደ ሐገር በማቆየት ለማስቀጠል የሚያስችለዉ የማጥቃትና የመከላከል ብቃትን ባጠቃላይ ትግራይ ክልል ተረክባለች!
በተለይም የአየር ሐይል መረጃዎችን ተንተርሶ ከብርጋዴል ጄኔራል ሞላ ሐይለማሪያም ትእዛዝ ዉጪ ( Commander of the Air Force: Brigadier General Mola Hailemariam ) የበረራ ቴክኒካል እና መካኒካል ዘመናዊ መገልገያዎች ጉድለት የሌለባቸዉ ማለትም የተመረጡ የጦር ጀቶች የጦር ሄሊኮፍተሮች ዘማናዊ ሬዲዮ ቴለስኮፖች እጅግ ዉድና ዘመናዊ የራዳር ቃኚዎች አየር መቃወሚያዎች ባጠቃላይ እንከን አልባ የተባሉ ታንኮችና በተሽከርካሪ ላይ የሚጫኑ የተራቀቁ ሚሳየሎች ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘዉ መጠናቀቃቸዉን ከሐገር መከላከያ የደህንነት ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።
በመሆኑም ሐገሪቷ ካላት 180 000 ጠቅላይ ሐይል Total force strength 3/4ኛዉ 108 000 የሰሜናዊዉ ትግራይ እና አካባቢዉ ዋልታ እንዲሆን ሲደረግ ከ 3 500 የተመረጡ የአየር ሐይሎች 1 300 በላይ የሰመኑ እዝ ትግራዊያን ክልልል ዉስጥ እንዲተላለፉ ተደርገዋል።

ከዚህ በታች በሊስት ዉስጥ ከተቀመጠዉ የሐገር መከላከያ ንብረት ዉስጥ 75 በመቶዉ ወደ ትግራይ የተወሰደ ሲሆን በሊስቱ ላይ የማይሰሩና የተዳከሙት ባጠቃላይ በኣለበት የተተወ ነዉ 
reportint20130214103009703Total force strength Army: 180 000
Air Force: 3 500
Army 
Armour 75: T-62
240: T-54/55
60: T-72 (200 on order to replace T-54/55)
Reconnaissance 70: BRDM-1/2
AIFV 20: BMP-1
APC 90: BTR-40/60/152
110: M-113
Self-propelled artillery 10: 2S1 Carnation 122 mm
10: 2S5 152 mm
10: 2S19 Farm 152 mm
Towed artillery ?: M-1942 76 mm
?: M-1938 122 mm
100: D-30 122 mm
6: M-46 130 mm
18: WA-021/Type 88 155 mm
Multiple Rocket Launcher 50: BM-21 122 mm
25: Type 63 107 mm
Mortar ?: 82 mm
?: 120 mm
Anti-armour ?: AT-3/4 Sagger/Spigot
TOW
Recoilless rifle ?: D-44 85 mm
Rocket launcher RPG-7 Knout 73 mm
Air defence gun ?: ZSU-23-4 23 mm
?: ZU-23 23 mm
?: ZU-57
?: S-60 57 mm
?: M-1939 37 mm
Air defence missile ?: SA-2 Guideline
?: SA-3 Goa
?: SA-7 Strela
Air Force 
Combat aircraft 15: MiG-21 Fishbed
10: MiG-23 Flogger
12: Su-27 Flanker
8: Su-25 Frogfoot
Trainer aircraft 7: L-39 Albratros
4: SF-260
Transport aircraft 9: An-12 Cub
2: C-130 Hercules
2: DHC-6 Twin Otter
2: Y-12 
8: C-47
1: An-26
1: An-32
1: Yak-40
Combat helicopter 18: Mi-24/35 Hind
12: UH-1H (Ethiopian Army Aviation)
Transport helicopter 8: SA-316 Alouette 3
10: Mi-6 Hook
20: Mi-8/17 Hip
1: SA 330 Puma
2: Mi-14 Haze
ልኡል አለም

የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ



የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ
– ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ይወያያሉ
በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት (ቻንስለር) አንገላ መርከል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት ቻንስለሯን በፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ቢጠይቅም፣ መርከል ግን ‹‹በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ውስጥ ንግግር ማድረግ ምንም ለውጥ አያመጣም፤›› በማለት ግብዣውን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቻንስለሯ ከእሑድ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገሮች የሚጐበኙ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወደ ማሊና ኒጀር ተጉዘው ኢትዮጵያ ሲመጡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ይገናኛሉ፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረትን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡ ቻንስለሯ አዲስ አበባ ሰኞ አመሻሽ ላይ እንደሚደርሱ፣ አብሯቸውም የጀርመን ፌዴራል ጽሕፈት ቤት ባልረደቦች ብቻ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡ ከቻንስለሯ ጋር ምንም ዓይነት የቢዝነስ ልዑካን የማይመጣ ሲሆን፣ ይህም በሎጂስቲክስ ችግር መሆኑ ታውቋል፡፡ ቻንስለሯ ሰኞ አመሻሽ ላይ ከገቡ በኋላ ማክሰኞ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አቀባበል የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ረቡዕ ይገናኛሉ፡፡
ምንጮች ለሪፖርተር፣ ‹‹ቻንስለር መርከል በአገሪቱ በተፈጠረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ዜጐች ላይ እየወሰዱት ስላለው አላስፈላጊና ከመጠን ያለፈ ኃይል ከመንግሥት ጋር ይወያያሉ፤›› ከዚህም ባለፈ፣ ‹‹በቁጥጥር ሥር በተከፈተ›› የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ይወያያሉ ብለዋል፡፡ ቻንስለሯ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ስደተኞችን በተመለከተና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል፡፡
ቻንስለሯ መርከል በአዲስ አበባ ቆይታቸው ወቅት፣ ከተመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ቻንስለሯ ስድስት ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በጀርመን ኤምባሲ ይወያያሉ፡፡ ሆኖም የውይይቱ አጀንዳንና ተሳታፊዎቹ ማን እንደሆኑ ምንጮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
በቅርብ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ የአገር መሪዎች በተለየ ቻንስለሯ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችን ያነጋግራሉ ተብሏል፡፡ በቅርብ ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ፣ የደቡብ ኮሪያዋ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጉዊን ሃይና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትኒያሁ ከተቃዋሚዎች ጋር አለመገናኘታቸው ይታወሳል፡፡
ቻንስለሯ በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን አዲሱን የጁሊየስ ኔሬሬ የሰላምና ደኅንነት ሕንፃ ማክሰኞ የሚመርቁ ሲሆን፣ በኅብረቱ አዳራሽም ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ ከኅብረቱ ሊቀመንበርንና ከሌሎች የኅብረቱ አመራሮች ጋር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ አዲሱ የሰላምና ደኅንነት ሕንፃ እንዲገነባ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የጀርመን ፌዴራል የውጭ ጉዳይ ሲሆን፣ ሕንፃው የተገነባውም በጂአይዜድ ነው፡፡
ይህ የቻንስለር መርከል ጉብኝት ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እ.ኤ.አ. በ2007 ነው፡፡

በሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ኩባንያዎች ወደሙ ቆንጅት ስጦታው


በሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ኩባንያዎች ወደሙ
ካለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እንደገና ባገረሸው ተቃውሞ፣ እስካሁን ከ130 በላይ ግዙፍና መለስተኛ ኢንቨስትመንቶችን ማውደሙ ተገለጸ፡፡
በተለይ ከአዲስ አበባ ከተማ በ100 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች፣ የኤሌክትሪክና የኮሙዩኒኬሽን ኬብሎች ፋብሪካ፣ የፕላስቲክ ታንከር ፋብሪካ፣ የጠጠር ማምረቻ ፋብሪካ፣ የአበባና የተለያዩ እርሻዎች፣ ሎጆች፣ ወዘተ. ሙሉ ለሙሉና በከፊል ወድመዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የሕዝብ ማመላለሻ፣ ከባድ የጭነትና የግልና የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ወድመዋል፡፡
እንዲሁም የቀበሌ አስተዳደር ሕንፃዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ የአርሶ አደሮች ማሠልጠኛ፣ የጤና ኬላዎች ተቃጥለዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይል የሌለ እስኪመስል ድረስ በጉትጎታ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ኩባንያዎች፣ አገር በቀል ኩባንያዎች፣ የግለሰብ ቤቶችና ንብረቶች ተዘርፈዋል፤ በእሳት ጋይተዋል፡፡
ከሰኞ መስከረም 23 ጀምሮ እስከ ዓርብ መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ባሉት አምስት ቀናት ብቻ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታና ቱሉ ቦሎ አካባቢ 11 ፋብሪካዎችና አራት የአበባ እርሻዎች ወድመዋል፡፡ 62 ከባድ የሕዝብና የጭነት ተሽከርካሪዎች ወድመዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግዙፉ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሳይገን ዲማ፣ ሱፐር ፋይቨር ሮቶ ታንከር ፋብሪካ፣ ቱቱ እና ቤተሰቧ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ ቢኤምኢቲ ኬብል ፋብሪካ፣ ዳስ ትሬዲንግና ሰላም ባልትና ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ለ40 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
በምዕራብ አርሲ ጎልጀታ አካባቢ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢኮ ሎጅ የሆነው ቢሻንጋሪ ሙሉ ለሙሉ ሲወድም፣ በዚሁ አካባቢ የሚገኝ የእህል መጋዘንና የፖሊስ ጣቢያም ጋይተዋል፡፡
በምዕራብና በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ወለጋ ደምቢዶሎ፣ ቀደም ሲል አገረ ማርያም አሁን ቡሌ ሆራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ በምዕራብ አርሲ (ነገሌ፣ አሳሳ፣ ዶዶላ) ውድመቱና ደም አፋሳሽ ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግጭቱ ያስከተለውን ውድመት በትክክለኛው መረጃ ለማወቅ ከተለያዩ ቦታዎች ሪፖርቶች ቀርበዋል፡፡ ነገር ግን የክልሉ መንግሥት ሪፖርቶቹን ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ከገመገመ በኋላ በይፋ እንደሚገልጽ ጠቁመው፣ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ድርጅቶች አንዱ ቢሻንጋሪ ሎጅ ነው፡፡ የባገርሽ ቢዝነስ ግሩፕ እህት ኩባንያ ኢኮ ሎጅ እ.ኤ.አ. በ1998 የተመሠረተ ነው፡፡ ኩባንያው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ጎልጀታ አካባቢ 100 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ ግንባታ ካካሄደ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በ2002 ዓ.ም. ታዋቂውን ቢሻንጋሪ ኢኮ ሎጅ ለኢትዮጵያ በማስተዋወቅ ደንበኞችን መቀበል ጀመረ፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢኮ ሎጅ ሆኖ የተመሠረተው ቢሻንጋሪ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን፣ 60 ሠራተኞች አሉት፡፡ ኩባንያው ሙሉ ለሙሉ የሥራ ዕድል የፈጠረው ለአካባቢው ነዋሪዎች ሲሆን፣ ለአካባቢውም ነዋሪዎች 17 የቢዝነስ ሐሳቦችን በማመንጨት በዶሮ እርባታ፣ በዕደ ጥበብና በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ እገዛ በማድረግ ምርታቸውን ከመረከቡም በላይ፣ በሎጁ ውስጥም መደብር ተከፍቶ ለተጠቃሚዎች እንደሚሸጥ አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለአካባቢው ትምህርት ቤት ውኃ አውጥቶ ከመስጠት ጀምሮ፣ የተለያዩ እገዛዎች ያደርግ እንደነበር የኩባንያው መሥራችና ባለቤት አቶ ኡመር ባገርሽ ባለፈው ዓርብ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
የቢሻንጋሪ ሎጅ ኦፕሬሽን ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ ዘለዓለም ቤኩማ፣ ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት 3፡00 ሰዓት ላይ በሎጁ ጀርባ የተወሰኑ ሰዎች መግባታቸውን፣ የሎጁ የጥበቃ ሠራተኛ ሰብረው ከገቡት መሀል አንዱን በመያዝ ለአካባቢው ሽማግሌዎች በደንቡ መሠረት አሳልፈው መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ሽምግልናው ሳይሠራ የተያዘው ሰው ተለቀቀ ይላሉ፡፡ ማክሰኞ ደግሞ የተደራጁ 60 የሚሆኑ ወጣቶች እየዘፈኑ ዋናውን በር ሰብረው ገቡ፡፡ ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ወጣቶችን በመለመን እንደመለሷቸው አቶ ዘለዓለም ተናግረዋል፡፡ በተደጋጋሚ የተደረገው የማግባባት ሥራ በመጨረሻ ውጤት ማስገኘት ግን አልቻለም፡፡
ረቡዕ ምሽት 5፡00 ሰዓት ላይ ወጣቶቹ በተደራጀ መንገድ የሰው ኃይል ጨምረው ገቡ፡፡ ‹‹አሁን ከሽማግሌዎችም ሆነ ከሎጁ ሠራተኞች አቅም በላይ ስለነበር ወጣቶቹ ዘረፋ ጀመሩ፤›› ሲሉ አቶ ዘለዓለም ሁኔታውን ያስረዳሉ፡፡ ወጣቶቹ የቻሉትን ያህል ከዘረፉ በኋላ ሎጁ ላይ እሳት ለኩሰው እንደሄዱ አስረድተዋል፡፡
‹‹ለአርሲ ነገሌ ፖሊስ ሁኔታውን ብናስረዳም ፖሊስ ጣቢያው ድልድዮች በመሰበራቸው መምጣት እንደማይችሉ፣ ይልቁኑም እኛ ራሳችን ተደራድረን ችግሩን እንድንፈታ ገልጸውልናል፤›› ሲሉ አቶ ዘለዓለም ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ላለፉት 14 ዓመታት በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ቱሪስቶችን ሲያስተናግድ የቆየው ቢሻንጋሪ ሎጅ ሙሉ ለሙሉ መውደሙን፣ በአሁኑ ወቅትም ከቃጠሎ የተረፈው ንብረትም መዘረፉን ገልጸዋል፡፡
‹‹ልጄ የሞተብኝ ያህል ነው ያዘንኩት፤›› ሲሉ የቢሻንጋሪ ሎጅ መሥራችና ባለቤት አቶ ኡመር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ቱሪስት እና ሰላም አይነጣጠሉም፡፡ ቢሻንጋሪን ዳግም የመገንባት ዕቅድ የለኝም፤›› ሲሉ አቶ ኡመር ተስፋ በቆረጠ አንደበት ገልጸዋል፡፡ ከቢሻንጋሪ ሎጅ ባሻገር የሚገኘው የቀድሞ በቀለ ሞላ ሆቴሎች ሥር ይተዳደር የነበረው የአሁኑ ሲምቦ ቢች ሪዞርት ባለፈው ዓርብ በከፊል ቃጠሎ ደርሶበታል፡፡
የሲምቦ ቢች ሪዞርት ሎጅ ኩባንያ መሥራች አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ሎጃቸው በከፊል የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል፡፡ ነገር ግን የውድመቱን መጠን ለማወቅ መረጃ ተጠናቅሮ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል፡፡
ሱፐር ፋይቨር ኩባንያም ከባድ ውድመት አጋጥሞታል፡፡ ይህ ኩባንያ በሰበታ ከተማ በ13 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የፕላስቲክ ታንከር ፋብሪካ ከፍቶ ላለፉት አሥር ዓመታት ምርቱን ለገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
የሱፐር ፋይቨር ኩባንያ ባለድርሻ ወ/ሮ ትዕግሥት ጌትነት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ረቡዕ መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡30 ላይ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ በርካታ ወጣቶች መጡ፡፡ ወጣቶቹ በጀሪካን ነዳጅና ተቀጣጣይ ጎማ ይዘው በመግባት የጥሬ ዕቃ ማከማቻና ያለቀለት ምርት ማቆያ መጋዘን ላይ እሳት መልቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ትዕግሥት እንዳሉት እሳቱ ወደ ፋብሪካው ባይዘመትም፣ የተከማቸ ጥሬ ዕቃና ያለቀለት ምርት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡ ቢያንስ የወደመው ንብረት 35 ሚሊዮን ብር ግምት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹1,500 ሠራተኞች ነበሩን፡፡ አሁን ግን ሙሉ ለሙሉ ሥራ አቁመናል፡፡ ይህ ፋብሪካ የእኛ ብቻ ሳይሆን የሕዝብም ጭምር ነበር፤›› ሲሉ የገለጹት ወ/ሮ ትዕግሥት፣ ፋብሪካቸው ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከጉድጓድ ውኃ አውጥቶ ይሰጥ የነበረ ቢሆንም የውኃ ማጠራቀሚያውን ጭምር እንዳጠፉት አስረድተዋል፡፡
‹‹አጥፊዎቹ የሽምቅ ተዋጊ ዓይነት ባህሪ አላቸው፡፡ የፀጥታ ኃይሎች እንዳይገቡ መንገድ እየዘጉ ነው ይህንን እኩይ ተግባር የሚፈጽሙበት፤›› ሲሉ የተናገሩት ወ/ሮ ትዕግሥት፣ መንግሥት በተቻለው አቅም ለዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡
ሱፐር ፋይቨርን ጨምሮ በሰበታ ከተማ ከተቃጠሉት 11 ፋብሪካዎች መካከል ቢኤምኢቲ ኢነርጂ ቴሌኮም ኢንዱስትሪ ኤንድ ትሬድ የተባለው ኩባንያ ይገኝበታል፡፡ ይህ የቱርክ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ2012 በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ የሆነውን የኤሌክትሪክና የኮሙዩኒኬሽን ኬብሎች ማምረቻ ፋብሪካ ገምብቶ ወደ ምርት ገብቷል፡፡
ኩባንያው ሦስት ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ወደዚህ ሥራ ቢገባም፣ ምርት ከጀመረ ከአራት ዓመት በኋላ ያላሰበውና ያልገመተው ውድመት ገጥሞታል፡፡
የኩባንያው የሰው ኃይልና የፋይናንስ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ደረጀ ደሳለኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ብዛት ያላቸው ወጣቶች ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት ዋና መሥሪያ ቤቱን አቃጥለዋል፡፡ በቢሮው ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችና ኮምፒውተሮች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡
‹‹ከባዶ ነው የምንነሳው፤›› በማለት ፋብሪካው ያለ ሰነድ መቅረቱን አቶ ደረጀ ተናግረዋል፡፡ የኬብል ፋብሪካው ባይነካም ቢሮው ከነሰነዱና ከጂቡቲ ዕቃ ጭነው የገቡ አራት ከባድ ተሽከርካሪዎች ከያዙት ዕቃ ጋር ነደዋል፡፡
‹‹አጥፊዎቹ ብዛት ስላላቸው በወቅቱ የሚያስቆማቸው ኃይል አልነበረም፤›› በማለት የገለጹት አቶ ደረጀ፣ በአሁኑ ወቅት የፌዴራል ፖሊስ ግቢውን እንደተቆጣጠረ ገልጸዋል፡፡ የወደመው ንብረት መጠን እስካሁን አለመታወቁንም ጨምረው አስረድተዋል፡፡
ሌላኛው የጥቃቱ ሰለባ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ታዋቂ እየሆነ የመጣው አሰር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ይገኝበታል፡፡
አሰር ኮንስትራክሽን ከአዲስ አበባ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቢሾፍቱ – አዱላላ-መቂ ያለውን 55 ኪሎ ሜትር አቋራጭ መንገድ በ700 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተረክቧል፡፡
አሰር ኮንስትራክሽን ለመንገድ ግንባታ ያሰማራቸው ዘጠኝ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች በዚህ ሳምንት በተለያዩ ቀናት ውስጥ እንደወደሙበት ታውቋል፡፡
ከአሰር ኮንስትራክሽን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ በአካባቢው ንብረቶችን የሚያወድሙ አካላት ካምፑን ለማውደም በሚዘጋጁበት ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ደርሶ ከቃጠሎ አድኖታል፡፡ አሰር ኮንስትራክሽን የዚህን መንገድ ግንባታ 70 በመቶ ያህል አጠናቆ እንደነበር መረዳት ተችሏል፡፡
በኦሮሚያ ካለፈው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እንደገና ሥር እየሰደደ በነበረው ተቃውሞ ሰፊ ቦታ የሚሸፍን በመሆኑ፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና ፌዴራል ፖሊስ ሊቆጣጠሩት እንዳልቻሉ እየተነገረ ነው፡፡
ተቃውሞው እየተካሄደ ያለው የፀጥታ ኃይሎች እንዳይደርሱ መንገድ እየተዘጋ ጭምር በመሆኑ፣ አመጹም ሰፊ ቦታ የሚሸፍን ስለሆነ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ንብረት እየወደመ ነው፡፡
እየወደሙ ከሚገኙት ንብረቶች መካከል ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ፋብሪካዎች፣ የአበባ እርሻዎች፣ የቱሪስት ማረፊያ ሎጆችና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
የኦሮሚያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱና የፌዴራል ፖሊስ ምንጮች ፖሊስ አመፁን እየተቆጣጠረ መሆኑን ቢገልጹም፣ ከኦሮሚያ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን ክልሉን ቃጠሎ እየበላው መሆኑን የሚገልጹ ናቸው፡፡
አመጹ የትራንስፖርት እንቅስቃሴንም የገታ ሲሆን፣ ለአብነት በወዲያኛው ሳምንት ቅዳሜና እሑድ በምዕራብ አርሲ በሚገኙ የገበያ ሥፍራዎች ለንግድ የተጓጓዙ ነጋዴዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች እስካለፈው ዓርብ ወደ ቀዬአቸው አልተመለሱም፡፡ ከሐረር ወደ አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦና ነቀምት የሚደረጉ ጉዞዎች እንዲሁ ችግር እንደገጠማቸው መንገደኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተለይ በምዕራብ አርሲ የቀበሌ አስተዳደር አካላትን በማስወገድ በጎበዝ አለቃ ለመተዳደር እየተሞከረ መሆኑ ታውቋል፡፡
እየወደሙ ያሉ ንብረቶች የባንክ ብድር ያለባቸውና የኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸው ናቸው፡፡ ይህ ክስተት በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ተሠግቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት ዋስትና ሰጥቶ ያስገባቸው ኩባንያዎችም እንደመሆናቸው፣ ይህ ያልተጠበቀ ክስተት መንግሥትን በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ካሳ ሊያስከፍለው እንደሚችል ባለሙያዎች እየገለጹ ነው፡፡
በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መሠረት በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ ከ350 በላይ ወረዳዎች ዳግም ባገረሸው ተቃውሞ ጉዳት የደረሰው በ50 ወረዳዎች ነው፡፡ ባለፈው ዓርብ ግን በአብዛኞቹ ሥፍራዎች መረጋጋት መፈጠሩን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ በምዕራብና በምሥራቅ አርሲ ከሚገኙ ሁለት ወረዳዎችና ከነገሌ ቦረና በስተቀር ሰላማዊ ድባብ መፈጠሩን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባ አዲስ አበባ የመጡት የ31 ዓመቷ አሜሪካዊት የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ሻሮን ግሬይ ቡራዩ አካባቢ በተወረወረ ድንጋይ ተመተው ሞተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተገደሉት አሜሪካዊ አስከሬን ወደ አገራቸው ተሸኝቷል፡፡