Wednesday, March 8, 2017

ወያኔ የዩንቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞችን ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ስብሰባ ጠምዶ ይዟል፤ muluken tesfaw

ወያኔ የዩንቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞችን ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ስብሰባ ጠምዶ ይዟል፤
muluken tesfaw . የትግሬ ወያኔ መንግሥት በሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ያሉ መምህራንና ሠራተኞችን ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ስብሰባ ጠምዶ እንደያዛቸው ከየዩንቨርሲቲዎቹ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከወሎና ከዓለማያ ዩንቨርሲቲዎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ የመልካም አስተዳደርና የተገልጋዩ ሕብረተሰብ ውጣ ውረድ መማረር ነው በሚል ለሚዲያ ሽፋን ለመስጠት ደፋ ቀና እያለ ነው ብለዋል፡፡
ምሁራኑ እንደሚሉት ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ለመገምገሚያ በቀረበው ሰነድ መሠረት በሕዝብ የተጠየቁ ጥያቄዎች ቦታ አልተሰጣቸውም ተብሏል፤ ‹‹ይልቁንም በመልካም አስተዳደር እጦት በሚል እየጠሸፈኑ ነው›› ሲሉ ተችተዋል፡፡
በወሎ ዩንቨርሲቲ በሁለቱም ግቢዎች ያሉ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በስብሰባው ‹‹ከሕዝብ ጋር የመታረቅ ፍላጎት የሌለው መንግሥት›› ሲሉ ተችተዋል፡፡ በዓለማያ ዩንቨርሲቲ አፍረንቀሎ አዳራሽ መምህራን፣ በኦዲተሪየም ወይም አሮጌው አዳራሽ የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም በሴቶች ላይብራሪ ደግሞ የጽዳትና የጥበቃ ሠራተኞች ከትላንት ጀምሮ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የዐማራ ተወላጅ መምህራን በዘራቸው ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን በደል አንስተዋል ተብሏል፡፡
ምሁራኑ በውጭ በነጻነት የሚኖሩ ምሁራን አስተያየታቸውን ይሰጡበት ዘንድ የተሃድሶ ሰነድ የተባለውን ዶክመት አብረው የላኩ ሲሆን ከፊሉ ከዚህ ዜና ጋር አብሮ ተያይዟል፡፡

No comments:

Post a Comment