Thursday, December 8, 2016

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ!Muluneh Yohannes



የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ!
በዛሬ ቀን ወያኔ የብሄረሰቦች ባሕል ብሎ ያመጣውን ማወናበጃ በጎንደር ዬኒብርሲቲ አልተከበረም። ምክኒያቱም ወልዲያ ላይ የታሰሩ ተማሪዎች አሉ። ከጥቂት ቀናት በፊት በግፍ የታሰሩ ከ120 በላይ የጎንደር የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብር ሸለቆ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ ስለሆነ ተማሪው አድማ ላይ ነው።
በተጨማሪም በሃገራችን ገበሬ ላይ የተከፈተው የግፍ ጦርነት በህዝባችን ላይ ወያኔ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ነው የሚል እልህና ቁጭት በተማሪው ሁሉ ላይ ፈጥሯል። ተማሪዎች እንደገለፁት ብዙወችም ወገን እያለቀ ቁጭ ብለን አናይም በማለት እየሸፈቱ በርሃ እየገቡ ነው። ሁኔታው እጅግ እየተካረረ የመጣበት የጎንደር ሁኔታ ወያኔን ጭንቅ ውስጥ ከቶታል። ሰፋ ያለ ከተማዎችን ያቀፈ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ተማሪዎች እንደገለፁት እነሱም ትምህርት አቁመው ህዝባቸውን ወደመታደግ እንደሚገቡ በቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ በጎንደሬው ገበሬ ላይ ያወጀው ጦርነት እራሱን መልሶ እየለበለበው ነው። ጦርነቱም በርትቶ ቀጥሏል። በየቀኑ ብዛት ያለው የወያኔ ሙትና ቁስለኛ ወደ ጎንደርና ሌሎች የወረዳ ከተማ ጤና ማእከላት እየተከማቸ ስለመሆኑ ዛሬም የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ሙሉነህ ዮሃንስ
Muluneh Yohannes

No comments:

Post a Comment