Friday, December 16, 2016

ጎንደር – ወያኔ የተዳከመውን ሰራዊት በአዲስ ልትቀይር ነው!ሙሉነህ ዮሃንስ



የጎንደር ሕዝብ ትግል ከቋራ እስከ ጃናሞራ!
ወያኔ የተዳከመውን ሰራዊት በአዲስ ልትቀይር ነው!
ሃሙስ ታህሳስ 6 ቀን 2009

እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የመጣው የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል። በአርማጭሆ፣ በቆላማው ወገራ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ በመተማና ቋራ በገበሬወች ላይ ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ሰሞኑን ወደ ስሜን በኩል ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው አዳዲስ ሶስት ግንባሮች ላይ ጦርነት ተከፍቶ ፍልሚያ አለ። የተገፋው ገበሬ እራሱን ለመከላከል እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እያደረገ ነው።
ግራ የገባው ወያኔ የወረዳ መንገዶችን በኬላ በመዝጋት ፍተሻ እያደረገ ነው። ከጎንደር ሾልኮ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው ወያኔ ከፍተኛ የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰበትን ጦር አንስቶ በአዲስ ለመተካት እንቅስቃሴ እያደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።
ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ ህፃናትን፣ እናቶችንና አረጋዊያንን በመያዣነት አስሮ በግፍ እያንገላታ ነው። ለጊዜው ስማቸውን የማንጠቅሰው የገበሬ ሴት ቤተሰቦች ከ6 አመት ህፃን ጋር ጎንደር ውስጥ በ1ኛ ፖሊስ ጣብያ ታስረው ይገኛሉ። ይህ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት የህዝቡን እልህና ቁጣ እየጨመረው እንደሚገኝ ከቦታው ካናገርናቸው ተረድተናል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

2 comments:

  1. በሰይጣን የሚያምን የፈለገውን ለማድረግ ደም ለሰይጣን ሳይገብር አይፈጸምለትም፤ይህንን የሚያውቅ ጉጅሌ ጨካኝ ነው ብሎ አያውራ፣ጭካኔ ለስልጣኑ ያስፈልገዋልና።ስለዚህ ይህን የማያውቅ ካለ፣አልሰሜ ነውና ግባ በለው፤ወደመከራ።
    ስለዚህ ወደፈተናም አታግባን ብለው የማይጸልዩ ትርፋቸው መከራ ነው።




    **…አክታን አናድነውም...ጉጅሌንም አናድነውም****

    አፋችን ደርሶ ብናቆየውም፤
    አክታን ብንደብቀውም።
    በውርደት እያየነውም፤
    ጉጅሌን በፍፁም አናድነውም።
    አክታም ቢሆን ይሄው ነው፣
    ወደ ውስጥ እንኳ ብንምገውም፤
    ሆዳችን ታዛዥ ነው ለተፈጥሮ :-
    ያለ ሕሊና አናድነውም።
    ከእኛው ተፈጥሯል ብንልም ያውም፤
    እንደአክታ በምንም አባብለን አናድነውም።
    አናድነውም ፍጹም ሓቁን ስናየው በተጨባጭ፤
    ጉጅሌስ በሰላም ሥም ፣ አልሆነም እንዴ አሽቃባጭ?
    ለሃያ ዓመት ይቅርና በእጥፉ ስሌት ለአርባ፤
    "ቢደረፍለትም ጓንዴ በሰገባ፤
    ሕድሪ ሰውዓትና ሎሚ ዝጠለሙ፤
    ሐገርና ዝሸጡ ብደም ዝፈረሙ፤"
    ሁሉም ያገኛሉ እንደ በደላቸው፤
    አያ ጊዜ መጥቶ:-
    ይብላኝ ወዮላቸው!!!
    የሰው አክታም ሆነ ጉጅሌውም ያልፋል ፤
    አያ ጊዜ መጥቶ በሕዝብ አፍ ይተፋል።
    በግዴታ አክታ ቁልቁል መተፋቱ፤
    ጉጅሌም አይቀርም በቀን መደፋቱ።
    እናም በአፋችን ድብቅ አርገነውም፤
    ፍፁም ከመትፋት በቀር ማንም አያድነውም።
    ከላንቃ-ጥግ ቢኩረፈረፍ፣ትፋትን ሆዳችን አምጦ፤
    እየተገመደ ቢዝለገለግ፣ካሳምባ ጥግ ተሸምጥጦ፤
    ትንፋሽ በሽምቅ እየገፋው፤እብጥ ብሎ በጉንጫችን
    ምላስ ለፍላፊው ሊተፋው፤ቢከላከል ከንፈራችን፤
    እየገዘፈ በጭብጥ ባዕድነቱን ስንቀምሰው፤
    ስንጠላው ለራሳችን እያጣጣምን ስንልሰው፤
    ወደድነውም፣ጠላነውም፤
    በውርደት እያየነውም፤
    አክታን ብንወደውም
    ጉጅሌን አናድነውም።
    ከንፈራችን ሲያሞጠሙጥ ላንቃ በንዝረት ከጠረገ፤
    የቀረልን ይመስለናል ፤ በአፍንጫችን ከተማገ።
    አክታ ግን ከተማገ በትናጋ ታግዞ፤
    አንድም አይቀር ተጎልጉሎ፤ይወጣታል ጓዙን ይዞ።
    ባዕድ ሆኖ ሲኩረፈረፍ እስከትናጋችን ሞልቶ፤
    ከሕሊናችን ሲሟገት በራስ ዳኝነት ተጠልቶ፤
    ጥርስ ለማኘክ ቢሆንም-ቅሉ፣ሕሊና ያልወደደውን፤
    ያክታን መኖር ልባችን ለመቼም የማይፈቅደውን፤
    በምላስ እንደታዘለ በትንፋሽ እንኩርፍ ፈልቶ፤
    በጭ-ጮ አሊያም ባዝቶ ሲከፋ ከደም ተጣብቶ፤
    እብጥ እንዳለ ጉንጫችን፤ወደድነውም፣ጠላነውም፤
    ቢከላከልም ከንፈራችን፤
    አክታን አናድነውም።
    አፋችን ደብቆት ቢቆይ:-ጥርሳችን ቢሸፍነውም፤
    ጎልጉለን ከመትፋት በቀር በማጨቅ አናድነውም።
    በኢኮኖሚ ግንባታ በዶላር በብር ቢሸሸግም፤
    በግድብ ተስፋ ለመኖር የሕዝቡን ሥልጣን ቢፈልግም፤
    ዘረኝነትን የሚዋጋ ኢትዮጵያዊነትን የሚያነግስ፤
    ቆየ'ኮ ከተፈጠረ ግብረ-ጉጅሌን የሚያረክስ።
    ልባቸው ባልተቸነፈ ሕሊናቸውን ባልሸጡ፤
    ኢትዮጵያዊነትን አንግበው ነፃነትን በሚያምጡ፤
    እየደሙ እየሞቱ በትግል ውስጥ እየፋሙ፤
    ባልታሰበ አቅጣጫ ከጉጅሌው በሚቀድሙ፤
    እሳት ባሕርን ሊያሻግሩን፤
    በልብ አፍንጫቸው አሽትተው፤
    የገዳዮችን ኅጢያት፤
    በሞት ሸለቆ ሸኝተው፤
    የመቅሰፍት ፍትፍት የበሉትን በዘረኝነት ደም ሰክረው፤
    ያሳዩታል ለሕዝቡ በመቅሰፍት ድንጋይ ተወግረው።
    የጉድፍ የእድፍ መጨረሻው፤
    በቃ መቃብር በመሆኑ፤
    ጉጅሌም እንደአክታ፤
    በደም ታጅሏል አይኑ።
    እናም.....
    በውርደት እያየነውም፤
    ጉጅሌንም አናድነውም።
    አክታን ባንወደውም
    ጉጅሌን ብንጠላውም:-
    በፍፁም ከመትፋት በቀር፤
    ለያይተን አናድነውም።

    ReplyDelete
  2. OOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKK

    ReplyDelete