Tuesday, December 6, 2016

በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተቃጥሏልMuluken Tesfaw



በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተቃጥሏል፤
o በዐማራ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቸልታ እያየው ነው፤
Muluken Tesfaw – የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በዐማራው ሕዝብ ላይ እያደረሰው ያለው በደል ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ሒዷል፤ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ የእልቂት አዋጅ ታውጇል፡፡ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል እየተጋደሉ ያሉ ዐማሮች በሕይወታቸውና በንብረታቸው ላይ ይህ ነው የማይባል ጉዳት ደርሷል፡፡ በተለይ በሰሜን ጎንደር በአርማጭሆና በወገራ ወረዳዎች የዐማራ ገበሬዎች ቤት እየተቃጠለ፣ ንብረታቸው እየተወረሰና እወደመ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችና አዛውንቶች በሜዳ ላይ ተበትነዋል፡፡
ሰሞኑን ከኅዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በወገራ ወረዳ በእንቃሽና ጃኖራ ቀበሌዎች ይኖሩ የነበሩ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ተበትነዋል፡፡ በጎተራና በአውድማ ያለ ሰብል ከከባድ መሣሪያ በሚወጣ እሳት ዶጋ አመድ ሆኗል፡፡ በ2007/8 ዓ.ም. በነበረው ድርቅ ያላገገሙ ቤተሰቦች ዘንድሮ ያመረቱት ምርት በወያኔ መንግሥት ያለምንም ምሕረት ወድሟል፡፡ ይህ የለየለት አረመኔያዊ ተግባር ሲሆን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጉዳይ ቢሆንም በቸልታ እየታየ ነው፡፡
ዛሬ ከተጎጅ ቤተሰቦች ጋር ባደረግነው ውይይት በእንቃሽ ቀበሌ ከ50 በላይ ቤቶች ወድመው ወደ 200 የሚሆኑ ቤተሰቦች ተበትነዋል፤ በጃኖራ ቀበሌም ተመሳሳይ ውድመት ደርሷል፡፡ ትናንት እና ዛሬ ተበትነው የሚገኙ ቤተሰቦች ወደ 500 እንደሚደርስ ተጎጅዎች ተናግረዋል፡፡ የሚከተሉት አባውራ ቤቶችና ቤተሰቦች ስም ዝርዝራቸውን ያገኘናቸው ነው፤
ስም የቤተሰብ ብዛት ቀበሌ
1) ምስጋነው አጠኔ 12 እንቃሽ
2) መለሠ ተሾመ 7 እንቃሽ
3) ተሾመ ደሴ 5 እንቃሽ
4) ታደለ መልሰው 4 እንቃሽ
5) ደመወዝ ነጋሽ 10 እንቃሽ
6) ለከው ይለፉ 10 እንቃሽ
7) ካሣው ታየ 5 እንቃሽ
8) ዘሪሁን ተዘራ 4 እንቃሽ
9) ንጉሥ ዘሬ 3 እንቃሽ
10) ታከለ ማረው 4 እንቃሽ
11) ቀኑ ገሠሠ 2 እንቃሽ
12) ያለው አበበ 9 እንቃሽ
13) ደጉ በዜ 5 እንቃሽ
14) መሳፍንት ተስፋ ጃኖራ
የችግሩ አሳሳቢነት ከዚህ ላይ የተገለጸውን ያክል ብቻ አይደለም፡፡ በጎዳና የተበተኑ ሕጻናትንና አቅመ ደካማ ሰዎችን ልቅሶ መስማትም የበለጠ የሚያም ነው፡፡ ማንኛውም በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እልቂት የሚያሳስበው ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ይህን አረመኒያዊ ድርጊት እያወገዘ በሚቻለው ሁሉ እንዲያግዝም ጥሪ ቀርቧል፡፡

No comments:

Post a Comment