Tuesday, December 13, 2016

ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አንድ ጥናት አመለከተ።ጌቱ በቀለ በዳዳ



ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አንድ ጥናት አመለከተ።
በኢትዮጵያውያን ዙሪያ በፈረንጆቹ 2017 መባቻ ላይ ቁጥራቸው መቶሰባ በሚደርሱ ኬኒያውያን የማህበራዊ ሳይንስ ፕሮፌሰሮች የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ፣ ዜጎችዋ የርስበርስ ትምምናቸው ከመጡበት የዘመናት የመተጋገዝ ያኗኗር እሴታቸው ክፉኛ እየተንሸራተቱ እንደመጡ ከሀያ ሺህ ባላነሱ ከአራቱም ማዕዘን ከተውጣጡ ዜጎችዋ በርካታ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የተገኘው የጥናት ናሙና አመላክቷል።
·
የጥናቱ ዋነኛ ማጠንጠኛ፣ እጅግ ቀላል የሆኑ ጥያቄዎችን በሰንጠረዥ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ቅፅ በመበተን የተገኘ ሲሆን ፣ ከጥያቄዎቹ ውስጥ እንዲህ የሚሉ እንደሚገኙበት በቅርበት ጥናቱ ላይ በማስተርጎም ስራ ሲያግዛቸው የነበረ ስሙ እንዳይገለፅ የፈለገ ኢትዮጵያዊ ጥናቱ ስፖንሰር በተደረገው፣ ጊዚያዊ መቀመጫውን ጅቡቲ ባደረገው አለም አቀፍ የማህበረሰብ ጥናት መድረክ ለአለም ይፋ ከመሆኑ በፊት አፈትልኮ እንዲወጣ አድርጎታል።
·
√ የጉርብትና መስተጋብራችሁን ግለፁ፣
√ የበዓል ጊዜ ቅርርባችሁን አስፍሩ፣
√ ጋብቻን መፈፀም የምትፈልጉት ዘርን መሰረት አድርጋችሁ ወይስ ፍቅርን?
√ የስራ አቀጣጠራችሁ በሀገር ልጅነት ወይስ በሞያ ብቃት?
√ ዘር ምንድነው ላንተ(ቺ)
√ ትምክታችሁ በዘር በሚማሰላችሁ የፖለቲካ መሪያችሁ ላይ ምን ያህል ርቀት ይሄዳል?
√ በየእምነት ተቋምህ ተገኝተህ ትፀልያለህ?
√ ለመንግስትህ ያለህ ፍቅርና አክብሮት ምን ያህል ነው?
√ ተቃዋሚዎች ላንተ ምንድን ናቸው?
√ በመንግስትህ ላይ እምነትህ ምን ያህል ነው?
√ ዘርን መሰረት አድርገው ከሚመሰረቱ ቡድኖች በስንቱ ውስጥ ያለማቋረጥ ትሳተፋለህ?
√ በታሪክ ከሚጠቀሱልህ በመሪዎች የተሰሩ ስህተቶች፣ የአሁኑ ትውልድ የመጠየቅ ግዴታ አለበት ትላለህ?
ወዘተ… እና መሰል መጠይቆችን በትነው ያገኙት ምላሾች እጅግ የበረከቱት ፍፁም አስደንጋጭና ተስፋን የሚያሳሱ ሆነው አግተዋቸዋል።
·
የጥናቱ ዙረት እና መልሶች የተሰበሰቡት ከ80% ያላነሱት ያተኮረው ዕድሜያቸው ከ20—30 በሚደርሱ ወጣቶች ላይ ሲሆን አብዛኞቹ ወንዶች ናቸው፣
15% ደግሞ በ40 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ጎልማሶች ላይ ነበር 5%ቱን የሚይዙት በተማሩና ዕድሜያቸው ወደ 50 ገፋ ባደረገ አዋቂ ወንዶች ዙሪያ የተጠየቀ ነው።
·
60% ቱ የመጠይቆቹ መልሶች አሉታዊና የአብሮ መኖር እሴትን የናቁ በራስ ወዳድነት ስሜት የተሸበቡ፣ ለመጡበት ዘር ፍፁም ያደሉ፣ እጅግ አስደንጋጭና በርካታ የቤት ስራን ለትውልዱ የተወ መልስን ከሶስቱም ዕድሜ ጣሪያ ከተውጣጡት የተገኘው የአብዛኛው መልስ አመላክቷል።
·
5% ቱ ብቻ አዎንታዊ መልሶችን የሰጡና፣ የቀድሞውን እሴት በጠበቀ መልኩ መኖርን የሚመርጡና በዚያው መንገድ ላይ እየኖሩ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የቀሪው 35% መልሶች በኤክስ ምልክት የተሞሉ፣ ስርዝ ድልዝ የበዛባቸው፣ መልስ መስጫ ወረቀቶቹ የተበሳሱ፣ 95%ቱ ደግሞ አላውቅም እና እኔጃ በሚሉ ቃላቶች ተሞልቶ የተመለሱ ናቸው።
·
ፕሮፌሰሮቹ እንዳጠኑት ከሆነ ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አመላካች ፍንጭ ከጥናቱ አግኝተናል ብለዋል።
·
ይሁንና አሁንም በህዝቡ ህዝነ ህሊና ውስጥ ለዘመናት የነበረው ይሉኝታ በአሁኑም ትውልድ ውስጥ መኖሩ በብዙ መልኩ እንደጠቀማት በዳሰሳ ጥናታቸው ደርሰውበታል።
·
ይህ ሳይታወቅ አብሮአቸው የሚኖረው ጨክኖ ያለመጨካከን የይሉኝታ መንፈስ ከአሁን በኋላም አብሮ የመኖር እሴታቸውን እንዲቀጥል በርካታ የቤት ስራን ፣ በአዋቂ ሽማግሌዎች፣ በአዋቂ የሃይማኖት አባቶች፣ በአዋቂ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ በአዋቂ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚሰሩ ክፍተቶችን ከሞሏቸው አስፈሪው ደመና መግፈፉ አይቀርም ብለዋል።
·
ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ጥራዝ ነጠቅ ምሁራን ደግሞ ለአመታት ብሄራዊ እርቅ እየተባባሉ ከገዢው ፖርቲ ጋር ያልተግባቡበትንና የሚላዘነውን ቀረርቶም ተወት አድርገው፣ መንደር ተወርዶ ከቤተሰብ ጀምሮ ጉርብትና ላይ እርቅና ቅርርብን እንደቀድሞው እንዲጀምር በየአካባቢው ባሉ የየእምነት ተቋማት የቤት ስራው እንዲጀምር ማበረታታት ከቻሉ ፣ ድምር ውጤቱ ወደ ብሄራዊ እርቅ ማደጉ አይቀርም ብለዋል በመፍትሄው የጥናት ክፍላቸው ላይ።
·
ከዚያ ባሻገር ትውልዱ በተመሳሳይ የታሪክ ሁነት ላይ የተለያየ ድምዳሜ መያዛቸውም እጅግ አሳሳቢ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ጠቀስ አድርገው አልፈዋል። እንደውም ፈጣን ዕልባት ካልተበጀለት በዘር ጉዳ በሚነሱ የጥላቻ ልዩነት አንቦርቃቂና ብጥብጥ ፣እንደ ቁርቁስ መነሻ አንኳር መንስኤ ሆኖም ሊያገለግ ይችላልን ስጋታችን ነው ብለዋል።
·
ጥፋቶችን አጥፍተዋል በሚባሉ የቀድሞ እና በስልጣን ላይ ያለን መሪዎችን ዘር የያዘ ጎሬቤታቸው ላይ ጥርስ መናከሱ የበዛ መሆኑን ፍንጮችን ከምላሾቹ አግኝተናል እያሉ ነው።
·
ዘርን መሰረት ባደረገው መቧደን ዙሪያ ለተጠየቀው ጥያቄ ባብዛኞቹ የተሰጠው መልስ ፣ የጊዜው ብቸኛ ምርጫችን ነው የሚል ተስፋን የሚያዳፍን ድምዳሜያቸው ፣ ትውልዱ ምን ያህል ወደተገፋው እንደሚገፋና ቻሌንጅ በማድረግ ሌላ መንገድን ለመሞከር ስንፍና እንዳለበት ከምላሾቹ አውቀውበታል።
·
እየተበላሸ የመጣውን የአኗኗር ነባር እሴት ወደቀደመው የክብብርና አብሮ የመተባበር ኑሮ መመለስ ሀላፊነት አለባቸው ከተባሉት ወገኖች ባሻገር የእኛ ድርሻ ምን ድረስ ነው የሚል መልስን ከያንዳንዳችን ጥናቱ ይፈልጋል።
·
የጥናቱ ከፊል መረጃ በሚመጣው እሁድ ሳምንት ከታተመው የኬኒያ ሰንደይ ታይምስ ጋዜጣ የተገኘ ነው።
ጌቱ በቀለ በዳዳ

No comments:

Post a Comment