የአውሮፓ ኅብረት የማይታጠፍ ጫና ኢትዮጵያ ላይ እንዲያሳድር ተጠየቀ

በኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት የታሠሩት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና የተገኙበትን የአውሮፓ ፓርላማ የእማኝነት መስሚያ መርኃ ግብር ያዘጋጁትና ግብዣውንም ያደረጉት የፓርላማው አባል አና ጎምሽ የአውሮፓ ፓርላማ የዶ/ር መረራን እሥራት በብርቱ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ — ዶ/ር መረራ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያለማወላወል ጫና እንዳያሳድሩና መታሠራቸው በራሱ ኢትዮጵያ ግዴታ የገባችባቸውን የኮቶኑ ስምምነት የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች የጣሰ መሆኑን የኅብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሞጌሪኒ አጢነው በብርቱ እንዲያወግዙት አና ጎምሽ አሳስበዋል፡፡

Audio Player
ለተጨማሪ ዘገባውንና ከአና ጎምሽ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል የያዘውን ፋይሎች ያዳምጡ

ዶ/ር መረራ ጉዲና /ፎቶ ፋይል/
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የሪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን የብር ሜዳልያ አሸናፊው ፈይሣ ሌሊሣ የአውሮፓ ፓርለማ መቀመጫ ወደሆነችው የቤልጅግ ዋና ከተማ ብራስልስ ሄደው በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ እማኝነታቸውን እንዲሰጡ የጋበዙ፣ መድረኩንም ያዘጋጁት አና ጎምሽ የዶ/ር መረራ መታሠር “ቢያስደነግጠኝም አልገረመኝም” ብለዋል፡፡Audio Player
Vm
P
No comments:
Post a Comment