Friday, January 6, 2017

እስኪ ሰከን እንበል – #የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን። ቆንጅት ስጦታው



እስኪ ሰከን እንበል ———–#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን። ————- ግን እንደኛ አገርና ህዝብ አስፈሪ የህልውና አደጋ ላይ ያለ ይኖራል? እንደኛስ መላቅጡ የጠፋበት ህዝብ ይኖራል። 100 ሚሊዮን ህዝብ፣ 100 ቁዋንቁዋ፣100 የፖለቲካ ድርጅት ፣ 100 ብሄረሰብ ፤ በኢትዮጵያ የአየር ፀባይ፣ በኢትዮጵያ መልክአ ምድር፣ በኛ ጎረቤቶች፣ በኛ መንግስት፣ በኛ ድርቅና እና ራስ ወዳድነት! እስኪ አስቡት ጎበዝ ሳት ብሎን ጦርነት ውስጥ ብንገባ ምን ሊፈጠር እንደሚችል።
ተመድ፣ አአድ ገሌ መሌ ጭው ባለ ሜዳ አንድ ቁዋንዋ አንድ ሀይማኖት ላለው አገር እንኳ ምንም እንዳልፈየደ እያየን! አንድስ የሚያክል ጠላት አስቀምጠን የጠላት ያለህ፣ ጠላት አውርድ የምንል ምን ክነቶን ይሆን። ባለፉት አስርታት የወረደብን መአት እንኳን ለኛ ለአለም ትምህርት አይሆንምን? የ25 እና 40 አመት ሰቆቃና ስቃይ ያላስተማረን ምን ሊያስተምረን ነው? ምን ስንሆን ይሆን ባንክሮ ናማሰብ ማስተዋል የምንጀምረው? ወያኔን እንላለን እንጂ እኛው እራሳችን ነን ሀገራችንን በልተን እየጨረስናት ያለው። ወያኔስ ኢትዮጲያን ማጥፋት ስራው ነው። የኛስ ምን ይሉታል።
ወያኔን በርግጥ እንጠላለን። ግን ወያኔን የምንጠላበትን ድርጊት ላለማድረጋችን ምን ማረጋገጫ አለን? በየርከኑ ስንነሰነስና ስንበጣጠስ ስንት ትንንሽ ልንሆን እንደሆነ አስተውለነዋል? ተበጣጥሰን ተሰነጣጥቀንስ አማን ውለን አማን እንደማናድርስ ነጋሪ ያስፈልገናል? እኛ እኮ እስከየሩሳሌም ግዛታችን ነው ብለው የሚያልሙ አባቶች ልጆች ነን። እኛ እኮ ለአለም ጥቁሮች ሁሉ የነፃነትን ቀንዲል የለኮሱ አርበኞች ልጆች ነን። ሌሎች ከኛ ሊማሩ እንጂ ይሳለቁ ዘንድ እንዴት እንፍቀድ! አረ ተዉ ጎበዝ! አረ በባንዲራው! እኛ ስንጎማመድ እኮ የምትጎመደው ይች ምስኪን አገር ነች። ይረከቡት የሚያጡት እኮ ልጆቻችን ናቸው።
አረ በልጆቻችን! የኛ መጠላለፍ የጠላታችንን ክንድ እያፈረጠመው ነውና ወደ ልቦናችን እንመለስ። ሰከን፣ በሰል እንበል። ቅንነት ካለ ሁሉም ይቻላል። ወደ ጎን የሰበቅነውን ሰይፍ ወደ ጠላት እንቀስረው። ለህዝባችን ስንል ትንሽ ዝቅ እንበል። ዝቅ ያለን ሁሉ አንድየ ከፍ ያደርገዋል። ይሄንን የማህበራዊ መገናኛ አሳፋሪ ጦርነት ዛሬውኑ አቁመን ትግላችን ላይ እናተኩር። አገራችን አታልቅስብን። ወገናችን አይዘንብን፣ ልጆቻችን አይፈሩብን። ጠላታችንም አይሳለቅብን። የኢትዮጵያ መፃኢ እጣ ፈንታ በእጃችን ነው። ቅን ከሆንን እግዚአብሄርም ያግዘናል።
#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።
#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።

No comments:

Post a Comment