Monday, January 30, 2017

ዶ/ር መረራ ጉዲና ለሦስተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው – ታምሩ ጽጌ

ዶ/ር መረራ ጉዲና
በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ፣ ፖሊስ ለሦስተኛ ጊዜ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡
የመድረክ የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ላይ፣ ብዙ ምርመራዎችን ማድረጉን ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ፖሊስ አስረድቷል፡፡ ነገር ግን ቀሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን ገልጾ፣ ተጨማሪ 28 ቀናት እንዲቀፈድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
የዶ/ር መረራ ጠበቆች ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመቃወም፣ ደንበኛቸው ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ የተጠየቀውን የዋስትና መብት በማለፍ ፖሊስ የጠየቀውን የ28 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ ለየካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 መሠረት ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አንድ ዕድል ይቀረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment