Thursday, January 5, 2017

የወያኔ ተልዕኮ አማራን የማጥፋት ዘመቻ = መምህር አሸናፊ ሸዋርካብን በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ውስጥ እረሽነውታል፡፡ቆንጅት ስጦታው



የባህር ዳር ማረሚያ ቤት እና የወያኔ ተልዕኮ አማራን የማጥፋት ዘመቻ
በአማራዋ ፈርጥ ከተማ ባህር ዳር ሀዘን ፣ጩኸት ፣ለቅሶ ፣ሽብር ፣ሁከት በፀረ አማራው ቡድን ወያኔ የዕለት ከዕለት ጉዳይ ከሆነ አመታትን አስቆጥራልች፡፡የአማራን ህዝብ ለማጥፋት እና ለማዳከም ጠላቴ ነው ብሎ በፕሮግራም ነድፎ በ1968 ዓ.ም የተነሳው ወያኔ አማራ የሆኑና በአማራነታቸው ፅኑ አቋም ያላቸውን የአማራ ልጆች ቤት ለቤትና በአደባባይ ካለምንም ምክንያት መረሸኑ ሳያንሰው ካለው ፍርሃትና ጭንቀት የተነሳ በቁጥጥር ስር አድርጎ በማረሚያ ቤት የፍርድ እስረኛ ያደረጋቸውን የአማራ ልጆችንም ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ እየረሸነ ጭራቃዊ ተልዕኮኑን እየፈፀመ ይገኛል፡፡
በታህሳስ 24፦2009 ዓ.ም መምህር አሸናፊ ሸዋርካብን በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ውስጥ እረሽነውታል፡፡
መምህር አሸናፊ ሸዋርካብ በታሪክ ትምህርት የሁለተኛ ድግሪ የነበረው ሲሆን ሟች ወንድማችን በጎጃም ክፍለ ሃገር በአገው ምድር አውራጃ በአዲስ ቅዳም ከተማ መሰናዶ ት/ቤት የታሪክ መምህር ሲሆን ትግሁ እና ሀገር ወዳጅ የሆነ በተማሪዎቹና የስራ ባልደረባዎቹ ዘንድ ተወዳጅ አስተማሪ ነበር፡፡አሸናፊ ሀገሩን ወዳድና በተለይ ወያኔ በአማራው ላይ የሚያደርሰውን ግድያ ፣ማፈናቀል፣ዘረፋ እና ሰብዓዊ ጥሰትን አጠንክሮ ይቃወምና በአማራነቱን በፅኑ የነበረ ጀግና ነው፡፡አሸናፊ ሀገር ውስጥ የነበረው ትግል ያስቸግረው ስለነበር ሀገር ውስጥ የነበረው አደረጃጀት ከጨረሰ በኋላ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመቀላቀል ወሰነ፤ከእዚያም በሀምሌ ወር 2007 ዓ.ም ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ(አዴሃን) ለመቀላቀል መንገዱን ወደ በረሃ አደረገ፡፡ነገር ግን ሁሉም ነገር እንደጠበቀው ሳይሆን ቀረና አብሮኝ ይሞታል የትግል አጋሬ ነው ብሎ ያስከተለው አቶ ፍቃዱ አጥናፍ ብርሃኑ የተባለ የወያኔ ሰላይ አብሮት በመከተል ሁመራ ላይ ለወያኔ ደህንነቶች ሊያሲዘው ችሏል፡፡ፍቃዱ አጥናፍም ተልዕኮውን በወገኑ አሸናፊ ላይ ከፈፀመ በኋላ በወያኔ ትልቅ ምስጋና ተችሮት በአገው ምድር አውራጃ በአንከሻ ወረዳ ግምጃ ቤት ከተማ ገንዘብና ፕላን ፅህፈት ቤት ውስጥ ሹመት ተቀብሏል፡፡
አሸናፊ ሸዋርካብ አማራነቱ ሚያንገበግበው እና ሚሳሳለት ማንነቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ያረጋግጥ ነበር፤ይህም በጠላት ምርመራ ወቅት የሰሜን ምዕራብ ቀጠና የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ወንጀል መርማሪ በሆነው ባንዳ በትውልዱ አማራ በኢንስፔክተር አብረሃም ታምራት ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊና አካላዊ ጉዳት ቢደርስበትም ጀግናው እና ኩሩው መምህር አሸናፊ ሸዋርካብ በአማራነቱ ምንም ሳያፈገፍግ እስከ ዕለተ ሞቱ ተጋፍጧል፡፡ወያኔ በአሸናፊ ላይ የአምስት(5) አመት የእስራት ቅጣት በይኖበት የነበረ ቢሆንም አማራን በማሰር ብቻ የማይረካው ወያኔ በቀን 24 ፡04፦2009 ዓ.ም አሸናፊን ከማረሚያ ቤት ውስጥ ገድሎታል፡፡
የቀብር ስነ ስርዓቱም በደቡብ ጎንደር አዲስ ዘመን በቀን 25፡04፥2009 ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡
ለሟች በቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን እየተመኘን አዴሃንም ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል፡፡ድርጅታችን አሸናፊ የሰዋለትን አላማ አማራን ከጥፋት በማዳን ዳር እናደርሳለን፡፡

የአማራ ህዝብ በቆራጥ ልጆቹ ማንነቱን ያስከብራል!!

No comments:

Post a Comment