Tuesday, August 8, 2017

የብአዴን ነገር ( ግዛው ለገሰ ) source zehabesha

የብአዴን መስራቾች አንድማን እንደሆኑ ለሚያውቅ ሰው ብአዴን የአማራ ብሄርተኛ ድርጅት አለመሆኑን ለማወቅ ቀላል ነው:: የዘር ስብጥሩን  ስሌት ትተን የትግል መስመራቸውን ስናይ ቢያንስ ቢያንስ ኢትዮጵያ የብሔሮች እስር ቤት ናት የሚለው የዋለልኝ መኮንን የሞቅ ሞቅ ደቀመዛሙርት  መሆናቸውን እናያለን።
ስለሆነም የስልጣን ማንነታቸው ምሶሶ ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት እንጂ የአማራ ብሄርተኝነት አይደለም:: የብሄርተኝነት መገለጫዎች የበላይነት ስነልቦና ፣ የታሪክ ማጋነን፣ የግዛት ማስፋፋት፣ የተጠቂነት  ትረካን ናቸው:: እነዚህ እሴቶች “እኛ” እና “እነሱ”፣ ወዳጅና ጠላት የሚለውን አጥር ይስራሉ:: ስለሆነም የ”አኛ” ቅርጫት ውስጥ ያለው በጭፍንነት የምታደርገውን ሁሉ ይደግፋል፣ ”እነሱ” ቅርጫት ውስጥ ያለውን በጠላትነት፣ በጥርጣሬ ይመለከታል። ይህ የህውሃት አርባ ዓመት አካሄድ ሲሆን አብዛኛው የግራይን ወጣት እና ምሁራን በከሏል::
ብአዴን በዚህ ሲለካ ባዶ ነው። መሪዎቹም፣ ተከታዮቹም፣ አብዛኛው ካድሬዎችም ብሄርተኞች አልነበሩም:: ግን ሰው በመሆናቸው ራሳቸውን መከላከል ተፈጥሯዊ ግዴታቸው ሊሆን ይገባ ነበር:: የዛሬ ዓመት በጎንደር እና በጎጃም የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የትግራይ ብሄርተኞች በብአዴን ላይ ከፍተኛ ቅስቀሳ በቀጣይነት እያኬያሄዱ ነው። አሁን አሁን የቅስቀሳው ስፋት እና ጥልቀት ህወሓት በማንፈስቶው ያስቀመጠው ታሪካዊ ተጠቂነት ትረካ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስላል። በመሆኑም ይወል ይደር እንጂ ህወሓት የገዛ ፍጡሩን ብአዴንን እንደገና ሊጠፈጥፈው መሆኑ ግልጽ ነው::
አመላካች ከሆኑት ክስተቶች አንዱ አሁን አሁን የአገሪቱ ችግሩ በሙሉ የብአዴን በ”ትምክህት” አስተሳሰብ መበከል ውጤት መሆኑ በህውሃት መዳፍ ስር በሚገኙት ሚድያዎች (EBC፣ ፋና፣ ዛሚ፣ ENN፣  Reporter፣ ሰንደቅ) እና በማህበራዊ ሚድያዎች እየተነገረ ነው።

ሙስና ብአዴን፣ መልካም አስተዳደር ብአዴን፣ የ”ጥልቅ ተሃድሶ” አዝጋሚነት ብአዴን፣ ሕዝባዊ አመጽ ብአዴን  ወዘተ  ሁሉም ነገር የብአዴን ችግር።
ሰሜን ጎንደር ውስጥ ስር እየሰደደ ያለው የመሳሪያ ታግል የብአዴን ቸልተኝነት፣ የወልቅይት ማንነት ጥያቄ የብአዴን ትምክህተኝነት፣ የኮሎኔል ደመቀ ጀግንነት የብአዴን አመራር ከጸረ ስርዓቱ ጋር ተባባሪነት ተደርገው እየተነገሩ ነው::
አሁን ደግሞ በጠራራ ጸሃይ በባህር ዳር በአልሞ ተኳሽ የተገደሉ ወጣቶች የብአዴን ሰለባዎች ተደርገው እየቀረቡ ነው። በህወሃት ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን በሚሉ የትግራይ ተወላጆች  ለምሳሌ አስራት አብርሃም፣ አብርሃ ደስታ ወዘተ።
ይህ ሁሉ እየሆነ ለምንድነው ብአዴን ዝምታን የመረጠው? ድርጅቱ/መሪዎቹ ብይናገር/ሩ  አገር ቤትም ውጭም ያሉ ደገፊዎቹ ለምን መልስ አይሰጡም? የብአዴን ምሁራንስ ለምና ዝም አሉ? እውንስ ብአዴን ብሔርተኛ ቢሆን ይህን ሁሉ ጥቃት በዝምታ ያልፈዋል? ብአዴን ነጻ ድርጅት ቢሆን ኖሮ የሚደርደርበትን ወንጀል አይከላከልም?
የነዚህ ጥያቄዎች መልስ በብአዴን ውስጥ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን እንደአሉ እውቅና ሰጥተን የሚቀጥለው ግንዛቤ መድረስ እንገደዳለን::
ብአዴን ብሔርተኛ አይደልም፣ ብአዴን የአማራ ድርጅት አይደለም፣ ብአዴን ነጻ አይደልም፣ ብአዴን ራዕይ የለውም። ብአዴን በህወሓት የተጸነሰ፣ በህወሓት የሚያስብ፣ በህወሓት የሚተኩስ፣ በህወሓት የሚወጣ፣ በህወሓት የሚወርድ የደካማ ግለሰቦች ይዞታ ነው:: ብአዴን አማራ ክልልን አይገዛም፣ ኦህዴድ ኦርምያን አይገዛም፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን አይገዛም።
የሁሉም ገዢ ህወሓት ነው:: ህውሃት ሲሸነፍ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ ወዘተ ይሸነፋሉ:: ስለዚህ ሁሉም አይኖች ወደ ህወሓት!!

No comments:

Post a Comment