Friday, August 11, 2017

የሜቴክ ውንብድና….በአዲስ አበባ ትራንሰፖር አውቶቢስ ግዢ ላይ (ጥብቅ መረጃ) source zehabesha

በበዛብህ ሲሳይ (2009) ሀይድራባድ ህንድ
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ሰሞኑ በቀድሞ የስርዓቱ ልሳን በነበረው በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሜቴክ ከንግድ መርከብ ስለገዛቸው ሁለት መርከቦችና ሊያቋቁመው ስላሰበው የውሃ ትራንስፖርት ንግድ ስራ እንዲሁም በአገሪቷ ላይ ያደረሰውን ኪሳራ ካይሁ በኃላ ነው፡፡ እውነት ነው ተቋሙ ሲቋቋም ጀምሮ ለገዢው ጉጅሌ ኢኮኖሚያዊ ትርፍ እንዲያመጣ ተብሎ ብቻ አይደለም የትግራይ ተወላጆችን ከሰሜን ኤርትራዋኖች ላይ እንዲሁም ከደቡብ ደግሞ ሰፊው የኢትዮጰያ ህዝብ ላይ የፖለቲካዊ ልእልና እንዲያመጣ ጭምር እንጂ፡፡ ስለዚህ አቶ ኤርምያስ እንደ አስቀመጠው የሜቴክ መሪዎቹ ሲጋራን በቄንጥ ሚያጨሱ ብቻ ሳይሆኑ በዚህ እኩይ አላማቸው ላይ የሚሳተፉትን ሆድ አደር “ሙሁራን” ወይም ባለሰርተፊኬቶችን ወይም እንዴት ማስተዳደርና መጠቀም እንዳለባቸው ስለሚያውቁ ይሄው ይሄ ሁሉ ጉዳት በአገሪቱ ላይ ሊያደርሱ ቻሉ፡፡ አንዳንዴ የፈረንጅንም ጫማ ላሾችንም (Bootlikers) ይጠቀማሉ፡፡ በዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ ሜቴክ ተልዕኮውን እንዴት እንደሚያሳካ ለማሳይት የታሰበ ሲሆን ፅህፉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታን ብቻ የሚያሳይ ነው..ፍርዱን ደግሞ እናነተ ስጡ… መልካም ንባብ !!

በመጀመሪያ ግን አንባቢያን ሊገነዘቡት የምፈልገው ሜቴክ መቆጣጠር ሚፈልገው የኢኮኖሚ አውታር በዋነኝነት ከአገር ውስጥ ወይም ከዉጭ ሃገር ልዪ የፋይናንስ ድጋፍ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ሲሆን ትራንስፖርት ደግሞ ዋነኛ ነው ምክንያቱም ከአለም ባንክ ወይም ከቻይና ኤግዚም ባንክ አብዛኛው ብድር የሚሰጠው ለመሰረተ ልማት ግንባታ በመሆኑ ነው፡፡ ሜቴክ ገና ጥርሱን ሳይነቅል ዘሎ ዝርፊያውን የጀመረው የቀድሞ ኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ሃዲድ ላይ ጉብ በማለት ነው፡፡ ለተበተነው የባቡር ሰራተኞች ደሞዝ እከፍላለሁ በሚል ተልካሻ ሰበብ በ1907 የተመረተውን ንፁህ የባቡር ሃዲድ ብረት ወረሰው፡፡ ካለምንም ማስረጃ፡፡ ለዚያውም በ ፈረንጆች 2006 ከአውሮጳ ህብረት በተገኘ የ50 ሚሊዮን ዩሮ ብድር የመልሶ ማቋቋም እድሳት ስራ ጀምሮ የነበረውን እንዲቋረጥ በማድረግ ነው (ግርጌ ፎቶውን ይመልከቱ)፡፡ በመስኩ የተሰማሩት ባለሞያዎች እንሚሉት የቀድሞ የባቡር መስመር በትክክል ቢሰራ ኢትዮጵያ የምታስገባውንም ሆነ የምታስወጣውን ጭነት በአስተማማኝ ከማስተናገዱ አልፎ ሃገሪቱ በሚቀጥሉት ሃያ አመታት ልታመጣው የምትችለውን የኢኮኖሚ እድገትም መሸከም የሚችል ነበር፡፡ ይሄ ለነክንፈ እና አርከበ አይገባቸውም፡፡ የአዲስ አበባ ባቡርም በሰዓት ሃያ ሺህ ህዝብ ያመላልሳል በለው ጉፋያአቸወን ነፍተው አመት እንኳን ሳያገለግሉ ግማሽ ያህሉ ወላለቀው መሃል ሜዳ ላይ ቆሙ!! ሌላው ቢቀር ኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ታሪካዊነቱ ታይቶ ልክ በሰለጠኑት አገራት እንደሚገኙት የድሮ የባቡር መስመሮች ለቱሪዚም አገልግሎት መዋል ይችል ነበር፡፡ በተለይ ከአዲሱ መስመር በበለጠ በብዙ ከተሞች ላይ ማረፊያ ተሪሚናሉች ስላሉት ከተሞችን በንግድ በማስተሳሰር ከፍተኛ አስተዎጽኦ ማምጣት ይችል ነበር፡፡ይሄም ባቡር ወደ 32 ሚሆን ቦታ ላይ ሲያርፍ የቀድሞ ግን ከ100 በላይ ቦታዎች ላይ በማረፍ የከተሞች የኢኮኖሚ እና የማህበረሰብ ትስስርን ያጠናክር ነበር፡፡ ሆኖም ለታሪክ ደንታ የማየሰጣቸው የትግራይ ጉድሌዎችን ያቀፈው ሜቴክ ታሪካዊዉን የበቡር ሃዲድ ብረት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ስልቅጥ አድርጎ በላው፡፡

ከዚህ የረቀቀ አገርን የማውደም ሴራ በሰተጀርባ ያለውን ለመረዳት ግን ከጀነራሎቹ ጋር በመሆን ለሜቴክ ጭንቅላት የሆኑትን ሆድ አደር ምሁራን ተብየዎችንም አብረን ማየት ያለብን፡፡ ምክንያቱም ጠቋሚዎቹና አስተባባሪዎቹ እነሱ ስለሆኑ!!!
ሙሁር ተብየዎችን በማፍራት ግንባር ቀደም የሆነው ገና ከተቋቋመ 20 አመት በሞላው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የሜቴክን አላማ የሚተገብሩለትን በላተኞችን የሚኮተኩትበት ዋነኛ ወታደራው ተቋም ነው፡፡ አካዳሚያዊነቱን ግን ብላሽ ብቻ አይገልፀውም፡፡ አንዴ እዚያ የሚያስተምር ጓደኛየን C ሰጠኅን ብለው ደብድበውታል፡፡ ከዚህ ተቋም የሚመረቁ “ባለሞያዎች” የወታደር ስነ-አምሮ የተላበሱ በመሆናቸው በሲቨል ተቋም ዉስጥ ሲገቡ ይሄንን የመታዘዝና-የማዘዝ ህግጋትን ስለሚተገብሩ ወይም በውይይትና የአመክንዮ ልእልና ስለማያምኑ በሜቴክ አለቆች ዘንድ እጅጉን ጀርባ የሚጣልባቸውና የሚወደዱ ናቸው፡፡ በዩንቨርሲቲው ትምህርት ላይ እያሉም እርስ-በራስ የመገማገምን ትምህርትና የሰዎችን ጉልበት ማሟጠጥ የሚችሉበትን ክህሎት ይቀስማሉ፡፡ ስለዚህ ወደ ስራ ሲገቡ የራሳቸውን ኔትዎርክ በቶሎ ይዘረጉና ምዝበራውን ያሯሩጡታል፡፡ በለራዕዩ መለስ አገሪቱ የተማረ ወታደር አያሰፈልግጋትም ካለ ከዚህ ተቋም የሚወጡት ለሌላ አላማ ነው ማለት ነው፡፡
ከዚህ ቀጥሎማ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ተቋማቶችን በአይን በመማተር ለአለቆቻቸው ሹክ ይላሉ፡፡ ገሚሱን ቻይና በመላክ የውንብድና ሊቅ ሲያረጉዋቸው የተቀሩትን ደግሞ አይናቸውን ጨፍነው አገራዊ (local) ሮል ሞዴል እንዲያበጁ ያረጓቸዋል፡፡ እኔም ከአምስት ከማያንሱ የቀድሞ የስራ ባለደረቦቼ የተረዳሁት አብዛኛዎቹ መለስን እንዲሁም ጥቂቶቹ ስየን እንደ ትልቅ ሮልሞዴል እንደሚዩዋቸው ነው፡፡ ሁለት ዘራፊዎችን!!! ከዚህ ዝግጅት በኃላ ወደ ሲቭል ተቋማት በማስገባት ነባር ተቋማትን በማፍረስ በምትካቸው አዳዲስ ለሚቋቋሙጽ ስም በመስጠት በሮዎችን መክፈት !…ለምሳሌ ኤጀንሲ ፣ባለስልጣን፣ ፅ/ቤት ፣ ተቆጣጣሪ፣ …የረሳሁት ካለ አግዙኝ! ከዚህም አዳዲስ የሚቋቋሙበት ዋና አላማ ተቋሙን ለማደራጀት ተብሎ ከሚመደበው የማቋቋሚያ ገንዘብ ለቤት ክራይ፣ ለጠረቤዛ፣ ለመኪና፣ ..ወዘተ ብለው እንዲጨርሱትና አዳዲስ ተቋማት ውስጥ የራሳቸውን ሰዎች በመሰግሰግ ወደፊት ለሚዘርፉት መንገድ በማበጀት ተጠያቂነት ፈፅሞ እንዳይኖር ለማድረግ ነው፡፡
የሜቴክ መሰሪ አላማ ለመመልከት እስቲ የአዲስ አበባ የመንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮን እንይ፡፡ በ2005 ከንቲባ ደሪባ ኩማ ሲሾሙ የከተማይቱን የትራንሰፖርት ችግር ይቀርፋሉ ተብሎ በሰፊው ተዘግቦ ነበር፡፡ በተለይ ፎርቹንና ሪፖርተር ከተቋሙ ጋር ልዩ ጥቅም ስላላቸው የማይመስል ወሬ በማራገብ አንደኛ ናቸው-ለምሳሌ አዲስ አበባ የብስኪሌት ታክሲ ልታገኝ ነው (1 ቀን ሳየሰራ 16 ሚሊዮን ብር አፈር ድሜ ያበላና የከተማዋ ነዋሪዎችም ሽንታቸው እስኪለቁ የሳቁበት)…..15 ፎቅ ያለው ዘመናዊ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ፓሪኪንግ ተመረቀ (አጠገቡ ያሉ ኢንተርኔት ቤቶች በኤሌክትሪክ መጥፋት ስራቸውን እንደተዉ ከንቲባው ሳይሰማ ለአድቬንቸር ብሉ የ85ሚሊዮን የብረት ሼልፍ ይመርቃል)… ሌላም ብዙ ብዙ፡፡
ወደ ትራንስፖርት ቢሮው ልመለስና የከተማው ነዋሪ ያለበትን የትራንሰፖርት ችግር ለመቅረፍ አዲስ ተቋም ያስፈልጋል በሚል የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በሚል እንዲቋቋም ይደረጋል፡፡ ይታያቹህ ለዝርፊያው ያመች ዘንድ መጀመሪያ የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ተብሎ የነበረው ፅ/ ቤት ባንዴ እንጣጥ ብሎ የፕሮግራም ማሰተባበሪያ ሆነ! እውነቱ ግን በየትኛውም አለም የተለያዩ ፕሮግራሞችን ማሰተባበር አይቻልም … የእውር መንገድ ለመሆኑና ለመዝረፍ ተብሎ በሜቴክና በከንቲባው የተቀናበረ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እንደ ፀጉራም ዉሻ አግዝፈው ትልቅ በጀት ለመመደብ እንደሆነ ለሁሉም ባለሞያ ግልፅ ነበር፡፡ የሆነውም ይህንን ተቋም እንዲመራ በብ/ጀ ክንፈ ዳኜው የተመደበው የመከላከያ ዩንቨርሲቲ ምሩቁና የቀድሞ የመረጃ ደህንነት ሰራተኛ የነበረው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ሲሆን ከመጀመሪያውኑ የሜቴክን አላማ ለማሳካት የተተከለ ወታደር ነው፡፡

በመጀመሪያ አዲስ የሚቋቋሙትን ተቋማት ከመደበኛ የሲቪል ሰርቪስና የፋይናንስ ቢሮክራሲ በማስወጣት በቦርድ እንዲተዳደር ማድረግ ሲሆን የቦርድ አባላቱም ባብዛኛወቹ አብሮ በላተኞችና በዶ/ሩ የተመረጡና የቀድሞ የመከላከያ ምሩቃንን የሚያጠቃልል ነበር፡፡ ከንቲባውም ቦርዱን አንድ ቀን ሳይሰበስበው ዶ/ሩ ሁሉን የሚያዝ ሆነ፡፡ ከዚህ በኃላማ ማን ይመልሰው……ልጁ ቀማኛ …አባቱ ዳኛ ሆነው እርፍ! የከተማይቱ ነዋሪ የሚፈልገው ግማሽ ኪሎሜትር ከሚደርሰውን የታክሲ ወረፋ የሚገላግለው ሆኞ ሳለ ባለ 15 ፎቅ ፓርኪንግ፣ ደብል ዴክ የአቶቢስ ማቆሚያ፣ ተርሚናሎች፣ የማይሰሩ የትራፊክ መብራቶች በየአደባባይ መትከል….ብቻ በአጠቃላይ ሜቴክ እንደሚያረገው ጉፋያውን መንፋት ብቻ ሆነ፡፡ ለዚህም ከከንቲባውና ምክትሉ አቶ አባተ ስጦታው ጋር ልዩ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ነባሩን አንበሳ አውቶቢስን (ከአፄው ጊዜ ጀምሮ የነበረ) እንደማጠናከር ፋንታ ሌላ በዚሁ ትራንስፖርት ቢሮ ስር የሚተዳደር አዲስ ሸገር አውቶቢስ የሚባል በመፍጠርና ሜቴክን በአውቶቢስ ግዢ ማክበር ሆነ ዋነኛው አላማ፡፡ በአምባሳደር ሱለማን ደደፎ ደብዳቤ ላይ እንደተገለፀው አዲስ የመርከብ ንግድ ሊጀምሩ እንዳሰቡት ማለት ነው!
ለዚህም ከመስተዳድሩ የሚበጀትና ከአለም ባንክ ሊገኝ ከታሰበው ከ300 ሚሊዮን ዶላር አብዛኛው ለሜቴክ አውቶቢስ መግዢያና ለትራፊክ መብራት መትከያ የሚውል ሲሆን ሜቴክ እስከ አሁን ወደ 1000 አውቶቢስ አገር ዉስጥ ገጣጥሞ ለመስተዳድሩ ያስረከበ ሲሆን አሁን ደግሞ የ750 አውቶቢስ አዲስ ውል አስሯል፡፡ እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ሃተታ ሜቴክ አንዱን አውቶቢስ በ3.6 ሚሊየን ብር ሲሸጥ ሌላው በግል የሚተዳደረው አልያንስ ባስ ደግሞ ተመሳሳይ አውቶቢስ በ 1.6 ሚሊየን ከቻይና ያለቀለት ያስመጣል፡፡ ልዩነቱ የአልያንስ አውቶቢስ ካሜራ ስላልተገጠመለት ብቻ ነው!! በጣም አስቂኝና የሜቴክ- ከንቲባው ድብቅ አላማ ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ይሄም ሜቴክ አደናጋሪ ቃላት በሲቨል መስሪያቤቶች በወተፋቸው ወታደሮቹ እያስነገረ ህዝቡን ማደኸየትና መሰረታዊ ለውጥ በማሓከለኛው ሃገር እንዳይመጣ በማድረግ የፖለቲካዊ አላማውን ያስፈፅማል፡፡ ሌላው የሜቴክ ዘመዶች ደግሞ የተሳተፉበት የሰብ-ኮንትራት ቢዝነስ በትራፊክ መብራት በመትከል ሰበብ ዘመዶቻቸውን ዊስኪ ጨብጠው ለሊቱን እንዲያነጉ ያደረጓቸዋል፡፡ ለዚህም ወደ 170 ሚሊየን ዶላር አዲስ የተመደበ የወንበዴው ወርልድ ባንክ ብድር መንገድ ላይ ነው፡፡ ለዚሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንድም አቶ ገነቱ ደሳለኝን ስራ አስኪያጅ አድርጎ ዝርፊያውን መሸፋፈንና አጋላጭ እንዳይኖር ማድረግ ነው፡፡
ይህን ሁሉ ስናይ እነዚህ ሰዎች ሁዋላ ከማን ጋር ሊኖሩ ነው የሚለው የሚያስጨንቅ ጥያቄ በአምሮየ ይመላለሳል …..ውይይይ… ሰው ልቦና ከሌለው ለምንም አይሆንም…ለልጆቻቸው ግን ወየዎላቸው……..ግፉ ሲበዛ በሃይለኛው መልሶ ይገፋችኃል፡፡ በ 1960ዎቹ የተማሪ ንቅናቄ ጊዜ የምንለው ነበር……ነቅናቂው ተነቃናቂውን ሲነቀንቀው ተነቃናቂው ነቅናቂውን መልሶ ነቀነቀው!! …..ሰው እያወቀ ነው ዝም ያለው……. ልብ ግዙ ነው ምክሬ!!!! በሚቀጥለው ደግሞ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲን ላይ አስነብባቹሃለሁ፡፡
ሠላም ሁኑ!

No comments:

Post a Comment