Wednesday, August 2, 2017

የአማራው ነገድ ኢትዮጵያዊ ብኩርናው ላይ መቼም ቢሆን አይደራደርም! [በወንድወሰን ተክሉ] source abbay media

ለዶ/ር አቤል ዮሴፍ መልስ የተጻፈ
[በወንድወሰን ተክሉ]
ውድ የአማራው ነገድ ሆይ ከአይሁዶቹ ታሪክ የምንማረውን እና የማንማረውን ለይተን እንወቅ
**አንድ- የዶ/ሩ የወቅቱ የነገደ አማራ አደረጃጀት ንጽጽር ከጀርመኖቹ አይሁዶች ጋር ያቀሩቡት ተወራራሽነት እና ተያያዥነት በሌላቸው ጉዳዮች የመሆኑ ፋላሲ።
በቅድመ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ያሉ አይሁዳውያን በ1880ዎቹ መገባደጃ ላይ በአሜሪካዊው አይሁድ ሄርዝል የተቃቃመውን ዓለም አቀፍ የአይሁዳውያንን ማህበር በሁለተናዊ መልኩ ከመቀላቀልና እና ተደራጅተው ከመታገል ይልቅ ከአምስት እስከ አስር ትውልዳቸው በተወለደበት “ሀገራቸው” ሆላንድ፣ሩሲያ፣ፈረንሳይ..ወዘተ ይበልጥ ይሰማቸው ነበርና ድጋፋቸው እጅግ ውስን ወይም ከእነ አካቴውም ገለልተኛ ሆኖ ይታይ እንደነበረ ግልጽ ነው።
የናዚው ሂትለር ሰይፍ ይህንን ቸልተኝነት፣ዳተኝነትና ገለልተኝነትን ጠራርጎ ሊያጠፋባቸው ያስቻለን ሁሉን አቀፍ ጥቃት/ፍጅት/በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ በመፈጸሙ ሁሉም አስበውትና አምነውበት የማያውቁትን የጽዮናዊነትን መንፈስና እምነት እንዲላበሱ በማድረግ በ1948 ለተቃቃመችው አይሁዳዊታ የእስራኤል ሀገር መመስረት የማእዘን ድንጋይ ሚናን በመጫወት ታላቅ ተጋድሎና መስዋትነትን ሊከፍሉ ችለዋል።
ይህ የእነሱ ታሪክ ነው።የአማራው ወቅታዊም ሆነ የወደፊት ህልውናዊ እጣፈንታው ከአውሮፓውያኑ አይሁዶች ቅድመ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር አንዳችም አይነት ተዛማችነትን የምንይበት ክስተት ስለመኖሩ ያየነውና የኖርነው ነገር እንደሌለ የገሃድ እውነታ ነው። አይሁዶቹ ከሁሉም በላይ ጭፍጨፋውና ጥቃቱ [In Human Discrimination ]የተፈጸመባቸው የራሳቸው በሆነው ምድር/ሀገር ሳይሆን እንደ መጤ በሚቆጥራቸው የሰው ሀገር ሲሆን በቅድመ ጭፍጨፋው ከአይሁድነታቸው ይልቅ ጀርመናዊነታቸውን፣ሆላንዳዊነታቸውን፣ፈረንሳዊነታቸውን..ወዘተ ይበልጥ የመረጡበት ሁኔታ ከአምስትና ከዚያ በላይ ትውልድ በተወለደበት ሀገር የዜግነት እና የሀገራዊ ብሔርተኝነት ስሜታቸው ማየሉ ሳይሆን ጥፋት የሚሆነው ያንን ስሜትና እምነት ባይኖራቸው ነበር እንደጥፋት የሚቆጠረው።
አይሁዶቹ በየሀገራቱ እንደዜጋ ሳይሆን እንደመጤ በዝባዥና ዘራፊ ተደርገው ታዩና ለጥቃት ተጋለጡ።በማን ሀገር? በ”ሰው” ሀገርና ምድር ማለት ነው።መገለሉ መጠቃቱና እንደመጤ መታየቱ በጀርመን ብቻ የተፈጸመ ሳይሆን እንደየ ደረጃው በተበተኑበት ምድር ሁሉ የተፈጸመ ነበር።
የነገደ አማራው ታሪክ ከአይሁዳውያን ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ክስተት ተፈጽሞበታልን?
በፍጹም።ምንም የሚያመሳስለን ክስተት በታሪካችንም ሆነ በአሁኑ ሰዓትም አልተፈጸመብንም-ሊፈጸምብንም አይችልም።
በእርግጥ ነገደ አማራ ህልውና ላለፉት 40ዓመታት በጥቃት ስር ያለ ነገድ ሲሆን የጥቃቱ መጠን እና ይዘት በዘመነ ህዋታውያን አድጎና ተለውጦ ለህልውናው መጥፋት ስጋት ደረጃ መድረሱ እውነት ነው።
ማንም ሊያስተባብለው የማይቻለው እውነታ የነገደ አማራ ህልውና በከፍተኛ አደጋ ላይ የመገኘቱ እውነታ ሲሆን ይህ ጥቃት እየተፈጸመ ያለው ግን እንደ አይሁዶቹ በሰው ሀገር እንደ መጤና ዘራፊ በሚያያቸው ህዝብና ስርዓት ሳይሆን አማራው ከ3400ዓመት በላይ እትብቱ በተቀበረበት የግል እርስቱና ሀገሩ ላይ በአቻ የሀገሩ ተወላጅ የመሆኑ እውነታን የተለያዩ ክስተቶች እንደሆኑ እናያለን።
አማራው በምድሩ ነው የተጠቃው-እየተጠቃም ያለው። አይሁዶቹ በመጤነታቸው በሰው ሀገር የተጠቁ ሲሆን አማራው ግን በራሱ ምድር በታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያን በመመሰረት፣በመጠበቅ ሂደት ውስጥ ነገዱ በሀገሪቱ ውስጥ በመሰረተው ፓለቲካዊ የስልጣን የበላይነት፣የባህል፣የቃንቃ፣የኢኮኖሚ የበላይነቱን ሚናን በእጅጉ በጠሉና በቀኑበት አቻ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሃይሎች የተከፈተበት ጥቃት እንደሆነ እናያለን።
በኢትዮጵያዊው የአማራ ነገድ ላይ የጠላትነትን መንፈስና እምነት ምንጩ የደደቢት በረሃ ተወላጁ ህወሃት እና ህወሃት ብቻ እንደሆነ ከሁሉም በፊት በጥልቅ ልንረዳውና ልናውቀው ይገባል።
የአማራው ነገድ ከህወሃት በስተቀር በሌሎች ሃይሎች ተጠቅቶ አያውቅም እያልኩ እንዳልሆነ ከግንዛቤ ሊያዝልኝ ይገባል።ምንም እንካን የኦ.ነ.ግ ኦ.ብ.ነ.ግ እና ሻእቢያ ሃይሎች ለአማራው ነገድ ፍቅር ያላቸው ሃይሎች ናቸው የሚያስብል የጥላቻ ስሜትና ቅስቀሳን የሚያደርጉ መሆናቸውን ብናውቅም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በድርጅቱ መተዳደሪያ ፕሮግራም ላይ “ጨቃኛ የአማራ ብሔር የመደብ ጠላታችን ናት”ብሎ አርቅቆና አጽድቆ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሃይል የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻውም ህወሃትና ህወሃት ብቻ እንደሆነ እናውቃለን።
ህወሃት እንደ ነገደ አማራ ኢትዮጵያዊ ነው ሃይል ነው።ግን ጸረ-አማራ ሆኖ እራሱን በአማራ ጠላትነት ያደራጀና ለመንግስትነት የበቃ ሃይል ነው። ባለው የጸረ አማራ እምነቱ እና ባለው የአናሳ ነገድ ተወላጅነቱ የተነሳ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት 81 ነገዶች ውስጥ በሕዝብ ብዛቱ በሁለተኛ ደረጃ ያለውን የአማራ ነገድ ተጽእኖ ብቻውን መመከት አይቻለውምና ሌሎችም ነገዶች ጸረ-አማራ እምነትና አመለካከት እንዲኖራቸው ለማድረግ ላለፉት ሁለት ዓስርተ ዓመታት ውስጥ በመንግስታዊ አቅሙ ከፍተኛ የሆነ ፕሮፖጋንዳን ዘራ። አማራውን እንደ ጨቃኝና በዝባዥ በማድረግ ከፍተኛ ቅስቀሳን አደረገ።ሌሎችንም በጸረ አማራነት አደራጅቶ አስታጠቀ ብሎም አማራውን እራሱም መትቶ በሌሎችም አስመታ። የህወሃት ጸረ-አማራ ፕሮፖጋንዳ ሰለባ በመሆን ጸረ አማራ አቃም ያሳዩና ብሎም ያራመዱም ይኖሩ ይሆናል ግን ጸረ አማራነታቸው የራስ ወለድ የሆነ ሳይሆን ህወሃት ወለድ በመሆኑ ለጠላትነታቸው መሰረት ያላቸው ሆነው አናያቸውም።
ይህ ክስተት የነገደ አማራውን ክስተት ከአውሮፓውያኑ አይሁዶች ክስተት ጋር ፈጽሞ የማይገናኝበትን ሂደት ያየንበት ነው።
**ሁለት-የአማራው ነገድ አደረጃጀት ከዚህ በፊት የተደራጁትን እንደነ የጎንደር ህብረት፣የጎጃም ህብረት፣የወሎ ህብረት፣የሸዋ ህብረት እና በኢትዮጵያዊነት ስር የተደራጁትን ሃይሎች እንደ የአማራው ጠላትና ጸረ-አማራዊ ሃይል አድርጎ የሚያይ ከሆነ መሰረት በሌለው ዓየር ላይ እራሱን ለአማራ ተቆርቃሪ ድርጅት አድርጎ የሚያይ መፍትሄ ያለው ተደራጅ ሃይል ሳይሆን በቅዥት አለም የሚቃዥ አሊያም የአማራውን እውነተኛ የመደራጀት ግብን ለማጨናገፍ የተነሳ ቅቡል ሃሳብ ነው ብዪ ለመናገር እችላለሁ።
እስቲ ከምን እሳቤና ፍልስፍና ነው ለአማራው ነገድ ተቆርቁሬያለሁ ብሎ እራሱን እያስተዋወቀ ያለ ግለሰብም በሉት ቡድን ወይም ድርጅት በጎንደር፣በወሎ፣በጎጃም፣በሸዋ ያሉትን አማሮች ከደረሰባቸው ጥቃት ለመታደግ ተደራጅተው የበኩላቸውን ታላቅ ተጋድሎን እና ድጋፍን እያበረከቱ ላሉት የጎንደር ህብረት፣የጎጃም ህብረት፣የሸዋ ህብረት እና የወሎ ህብረትን የአማራው ነገድ ጠላቶች ናቸው ለማለት የተቻለው?
ዶ/ር አቤል ዮሴፍ በሚያስደንቅ ድፍረት እነዚህን ድርጅቶች የወያኔን አላማ አስፈጻሚዎች ናቸው እስከማለት የወረደ አመለካከት አራምዳል። በእርግጥ እሱ አማራ ከሆነ ከአንድ አማራ በሌላው አማራ ላይ ሊሰነዘር የማይገባን ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም መፍትሄ አቅራቢ ሳይሆን ልዩነትን እና ክፍፍልን ፈጣሪና አስፋፊ ሆኖብኝ ታይቶኛል።
በአስቸካይ መቆም አለበት። ራእይ አለኝ ባይ አማራ ሌላውን አማራ ካልተከተልከኝ ይሁዳ ነህ የሚል እንጭጭ ድምዳሜን ከመስጠት መቆጠብ ይጠበቅበታል።
እንደ ባለራእይነቱ ደግሞ ራእዩን በጥራትና በትጋት ማስተማር እንጂ መጫን ከቶም አይገባውም። ከሁሉ በፊት የአማራው መደራጀት በጸረ የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች፣በጸረ ኢትዮጵያዊነትና ብሎም ለአማራዊው ሀገር ምስረታ ላይ መሰረት ያደረገ ከሆነ የሚካበው ድርጅት ከእንባይ ካብም የባሰ መሰረት የለሽ እንደሆነ ወደደም ጠላም ማወቅ አለበት። ዶ/ር አቤል ዮሴፍ በጎንደር ህብረት፣በአግ7 እና በኢትዮጵያን አንድነት ላይ ያላቸው የጠላትነት አመለካከትና አቃም ሎጂካል ሆኖ አላየሁትም-ምክንያታዊነት ያለው ሳይሆን ስሜታዊነትና ብሎም ግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ እንጂ የአማራውን ነገድ ጥቅምና ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እንዳልሆነ ልረዳ ችያለሁ።
**ሶስተኛ-ኢትዮጵያዊው የአማራ ነገድ ከአይሁዶቹ የሚማረው እውነታ ምንድነው?
በወርሃ ግንቦት 1948 እስራኤል የተባለች የአይሁድ መራሽ መንግስት በቀድሞዋ ፍልስጥኤም በተመስረተች ማግስት የዓረብ ሀገራት በአጭሩ ለመቅጨት ከየአቅጣጫ ወረራ ፈጸሙ። አዲሲታ ሀገርም ምድራችን ብለው ያመኑበትን የከነዓንን ምድር አሳልፎ ላለመስጠት ተፋለሙ። ሁሉንም መስዋእትነትን ከፍለው ምድራችን ያሉትን የከነዓንን ምድር እስራኤል በሚል መጠሪያ የሰየሙትን ሀገር ተከላከሉ። አይሁዳውያኑ በጀርመን እና አውሮፓ እያሉ እጅግ ዘግናኝ የሆነ አሰቃቂ ጥቃት ቢደርስባቸውም እራሳቸውን ለመከላከል ያደረጉት ፍልሚያ አልነበረም። ያሉት በሰው ሀገር ነውና።
ኢትዮጵያዊው አማራ ከአቻው የኦሮሞ ነገድ እና ሌሎች ጋር የኢትዮጵያ የበኩር ነገድ የሆነ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በመገንባት ደረጃ ከ3ሺህ በላይ በፈጀው ተጋድሎና ግንባታው አማራ በታሪክ ተጽፎ ያለን ታላቅ መስዋእትነትን የከፈለበት ውድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ነች።
ይህ ታላቅ ሚናውም እንደ ህወሃት ያሉትን ጠባብ ሃይሎች በነገዱ ላይ የመረረ ጥላቻና የጠላትነት መንፈስ እንዲያውጁ አድርጎዋቸዋል። አማራው ነገድ ልክ እስራኤላውያኑ በእርስታቸው ከነዓን ምድር እየተጋደሉና እየተማማቱ እንዳለው እሱም በኢትዮጵያዊነቱ በኢትዮጵያ ደረጃ ያለውን ሚና እና ድርሻውን ለግዜውም ቢሆን መንጠቅ ለቻለው የህወሃት ሃይል አሳልፎ በመስጠት ኖሮበትና ዓይቶትም ሆነ አልሞት የማያውቀውን የአማራ አነስተኛ ግዛት ሀገር እፈጥራለሁ ብሎ ሊማማት አይችልም -አይገባውምም።
እኛ የበኩር ልጆች ነን-ብኩርናችንን ደግሞ ልክ እንደ ኤሳው በምስር ወጥ እንደሸጠው እኛም ኢትዮጵያዊ ብኩርናችንን በአባት አማራ መሰል ክልላዊ ሀገር ልንሸጥ አንችልም-አይገባንምም።
[ይቀጥላል]

No comments:

Post a Comment