Saturday, July 30, 2016

ጎንደር በፌደራልና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ተጨናንቃለች :: ዋናው የሰልፉ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› እንዳይዳፈን ስጋት አለ

መፈክሮች ታትመው ተዘጋጅተው ኣልቀዋል። ጎንደር ነገ በነጻነት ጠያቂ ሕዝቦች ትጥለቀለቃለች።Minilik Salsawi – mereja.com – በጎንደር ተሰማርቶ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የልዩ ሐይልና የአካባቢ ሚሊሻ ባጠቃላይ ነገ የሚካሄደዉን የጎንደርን ሰልፍ ተነተርሶ የተሰጣቸዉን ሰላማዊ ሰልፍ የማክሸፍ ሴራ ያለማቀበላቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ደርሰዉናል። ነገ በጎንደር የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀላቀል ዛሬ ከባህር ዳር ብዙ ወንድምና እህቶቻችን ወደ ጎንደር እየገቡ ነው ። ምንም እንኳ ስንዝር ለሆነች መንገድ ሶስት ጊዜ መፈተሽ ግድ ቢሆንባቸውም እንኳን ይህን ሌላም ፈተና ቢመጣ እንጋፈጠዋለን በማለት ወደ ጎንደር እየተጓዙ ነው
ዋናው የሰልፉ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› እንዳይዳፈን ስጋት አለ
ጎንደር በፌደራልና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ተጨናንቃለች
ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ ዐማሮች ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ፡፡ ይህን ተከትሎ ከባሕር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ደባርቅ፣ ቆላ ድባ፣ ሳንጃና ጭልጋ መተማ የሚመጡ መኪኖች ላይ ታላቅ ፍተሸ እየተካሔደ ነው፡፡ ከጭልጋ ሰራባ አካባቢ እንዲሁም ከባሕር ዳር ብዛት ያላቸው የመከላከያ ኃይል አባላት ወደ ጎንደር መጥተዋል፡፡ በጎንደር የሚታየው ፖሊስ ዛሬ በጽጥታ አካላት ብቻ ሰልፍ የተካሔደ አስመስሎታል፡፡
ዐማሮች ከሁሉም ቦታ ወደ ጎንደር እየጎረፉ ነው፡፡ የሰልፉ ዓላማም አንድ እና አንድ ነው፤ ይኸውም የወልቃይት ዐማሮች የማንነት ጥያቄን ለማዳፈን የሚደረገውን ጥረት መቃወም ነው፡፡ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መጠየቅ፤ ወልቃይት ዐማራነትን መመስከር ነው፡፡
ይህ ሰልፍ ከዚህ የዘለለ ሌላ ዓላማ የለውም፡፡ ሆኖም ይህን ሰልፍ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› ለመሸፍ የሚደረግ ጥረት አለ፡፡ የኦሮሞ ወንድሞቻችን ግድያና አፈና፣ የሀብታሙ ሕመም ሁላችንም የምናወግዘው ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያን መበታተን ማንም አይሻም፡፡
እነዚህ ‹‹ቅዱስ ዓላማ›› ያላቸው መፈክሮች ጎልተው የሰፊውን ዐማራ ሕዝብ ጥያቄ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለማዳፈን የሚደረገው ጥረት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ስለዚህ የዐማራውን ሕዝብ ትግል እንቅስቃሴ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በማጋለጥ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፡፡ ሁሉም የሰልፉ ተሳታፊ የዐማራ ሕዝብ ከወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ጥያቄን በደንብ አጉልቶ ማውጣት አለበት፡፡

No comments:

Post a Comment