Friday, July 29, 2016

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ ከጎጃም ሕዝብ የተላከ



የወያኔ መንግስት በአንተ በውዱ ወገናችን ላይ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ እየፈፀመ ያለውን የማን አለብኝነትና የእብሪት ተግባር በቁጭትና በእልህ እየተከታተልንና ከአንተ ወገናችን ጎን በመቆም ያለንን አጋርነት እየገለፅን ቢሆንም፣ ይህንን የእናት ጡት ነካሽ የሆነውን የዘረኛና የፋሽስት መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጠራርጎ ለማስወገድ ተግባራዊ ስራዎችን ተባብረን መስራት ስለሚጠበቅብንና የመይሳው ካሳና ልጆች ሲጠቁ የበላይ ዘለቀ ልጆች አርፈው አይተኙምና የሚከተሉትን ነጥቦች በማንሳት የትግል አጋርነት መልዕክታችን ይድረሳችሁ እንላለን።
1. የብአዴን አመራር አባላት (እንደ አለምነው መኮንንና ብናልፍ አንዷለም) ሌሎችም ከአማራው ይልቅ ለሆዳቸው አድረው ከወያኔ ጋር በተሰለፉ የአማራው ካድሬዎች ላይ ሁሉ የማያዳግም ርምጃ መውሰድ፤
2. የስርዓቱ ተጠቃሚ በሆኑ በወያኔ/ብሕአዲን የንግድ ተቋማትና ጥቅማ ጥቅሞች ላይ እንዲሁም ከአንዱ አካባቢ ወደሌላው አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የስርዓቱ የንግድና የግል ተሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ መውሰድ፤
3. ታፍነው የተወሰዱ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ካልተለቀቁ፣ በምትኩ የወያኔ ገዥ አባላትንና ቤተሰባቸውን አፍኖ በመውሰድ መደራደሪያ ማድረግ፤
4. ከአሁን በኋላ ለሚሰነዘርብን ማንኛውም ጥቃት ሁሉ አፀፋዊ ምላሻችን እጥፍ ድርብ መሆን ይኖርበታል፤ እነሱም የያዙት እንደኛው ነፍስ ነውና ለሚሰነዝሩት ጥቃት ማንኛውም ዜጋ በተጠንቀቅ በመቆም አይቀጡ ቅጣት ልንቀጣችው ይገባል። ጀግንነትን ተወልዶ ያደገው ከእኛው ዘንድ መሆኑን ቢያውቁትም የበለጠ ማንነታችንን ልናስተምራቸው ይገባል።
5. እነሱ ያላከበሩትን ሕግ ሌላው ዜጋ እንዲያከብረው ደጋግመው የሚጠይቁትን፣ ድርድርና ሽምግልና እያሉ ጊዜ ለመውሰድና ትግሉን ለማኮላሸት የሚጠቀሙበት ስልት ስለሆነ ካለፈው ተምረን በዚህ ሳንታለል ጊዜያችንን በስር-ነቀል ለውጥ እንጂ በጥገናዊ ለውጦች እንዳንታለል።
6. የወያኔ መንግስት መሳሪያችንን ለማስፈታት እያሴረ በመሆኑ፣ ይህን ለማስፈፀም የሚንቀሳቀስ ሰራዊት ከመጣ ውረድ እንደውረድ ተባብለን በምናውቀው ተራራ ዋሻና ቀዳዳ መፋለም ይኖርብናል። በቁማችን ከሞትን ቆይተናል፤ የወልቃይት ጠገዴና የጠለምት ሕዝብ 36 ዓመት ተገድሏል፣ ታስሯል፣ ተሰዷል በአካል ያለውም መሬቱን ተነጥቋል፤ የተቀረው ሕዝብም መንገድ ከፍቶ ላሳለፋቸው ውለታ 25 ዓመታት በሙሉ የሰቆቃ በትራቸውን አሳርፈውበታል። ጣሊያንም ከዚህ የበለጠ በወገናችን ላይ አልፈፀመም።
7. ማንነቱን እንዲረሳ ወደ ትግራይ በግዳጅ የተካለሉ አካባቢዎችን ሆን ተብሎ ወደ ትግርኛ ስያሜ እየተቀሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ በነዚህ ስሞች በምንም ዓይነት እንዳይጠቀም ተገቢው ቅስቀሳ መካሄድ አለበት።
8. ለወሎ ወገናችን፣ ግዛትህ ተቆርሶ እንደ ጎንደር ተወስዶ፣ ክብርህ ተዋርዶ፣ ማንነትህ ተንቆ እንደ ስልቻ እየታሰርህና እየተፈታህ ባለህበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ከጎንህ አለንና ተነስተህ ከጎንደር ወገናችን ተሰልፈህ የተነጠቅኸውን መሬት ለማስመለስ ተነስ። ሁሌም የማታሳፍረን የሸዋ ወገናችን ለጥሪያችን በተንቀቅ ተዘጋጅተህ ጠብቀን።
9. የአማራ የመከላከያ ሰራዊት ሆይ፣ መሳሪያህን በአማራ ሕዝብ ላይ በማንሳት ይቅርታ የማይደረግለት ስህተት እንዳትፈፅም፤ የመሳሪያህን አፈሙዝ በወያኔና በግብረ በላው ብሕአዲን ላይ እንድታዞር ጥሪ አቅርበንልሃል።
10. ዋናው ግባችን የወያኔ/ኢሕአዲግ ፋሺስታዊ መንግስትን መገርሰስ በመሆኑ፣ ለማይቀረው ድል አብረን እንሰለፍ። እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ ከጎንህ ነንና ትግላችን በድል ሳይጠናቀቅ አርፈን እንደማንተኛ ልናረጋግጥልህ እንወዳለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

No comments:

Post a Comment