Tuesday, July 26, 2016

እርምጃ ይወሰድባቸዋል (ትረሸናላችሁ) ከተባሉ መካከል የሰባ እስረኞች የስም ዝርዝር ቃሊቲ እስረኞች ቦርድ ላይ ተለጥፏል፡፡

እርምጃ ይወሰድባቸዋል (ትረሸናላችሁ) ከተባሉ መካከል የሰባ እስረኞች የስም ዝርዝር ቃሊቲ እስረኞች ቦርድ ላይ ተለጥፏል፡፡ ==================================================================
የቃሊት መረሚያ ቤት ሊረሽናቸው የፈለገውን ታራሚዎች የስም ዝርዝር በገሃድ ለጥፎታል።
የቃሊት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት አድማ አስነስተዋል ወይም ለማምለጥ ሞክረዋል የሚል ሰበብ በመፍጠር እንደ ልማዱ ለመረሸን ያዘጋጃቸውን የሰባ የህግ ታራሚዎች የስም ዝርዝር በቀድሞ አጠራር ዞን አንድ የታራሚዎች ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ፣የ84 ታራሚዎች የስም ዝርዝር በዞን ሁለት የታራሚዎች ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ለጥፏል፡፡ ከነዚህም መካከል የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነው የአህመዲን ጀበል ስም ይገኝበታል፡፡
ይህንን ለማረጋገጥ የሚፈልግ የስራ ሃላፊ ወይም ባለ ስልጣን የቀድሞ ዞን አንድ እና ዞን ሁለት ውስጥ ገብቶ በማስታወቂያ ቦርዱ ላይ ማየት እንደሚችል ከማረሚያ ቤት የደረሰን መረጃ ያሳያል።
በማስታወቂያ ቦርዱ ላይ የስም ዝርዝራቸው የወጣው በግፍ የታሰሩ 1 /የአማራ ክልል ተወላጆች 2 /የኦሮሞ ክልል ተወላጆች 3 / የደቡብ ክልል ተወላጆች ናቸው፡፡
በዚህ ዝርዝር ውስጥ ትግርኛ ተናጋሪ ታራሚዎች አልተካተቱም ። በዚሁ ቃሊቲ ማረሚያ በ1998 የተነሳውን ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ተከትሎ በዚህ አይነት የዘር ጥላቻ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ታራሚዎች ረብሻቹሃል በሚል ሰበብ መረሸናቸው የሚታወቅ ነው።
አሁኑም በህዝበ ሙስሊሙ የገቡ ታራሚዎች፣ በኦነግ ስም የታሰሩ፣በግንቦት 7 እና በአርበኞች የታሰሩ ታራሚዎች እና ከነሱ ጋ ይበላሉ ይጠጣሉ ወይም ይጫወታሉ የሚሉዋቸውን ታራሚዎች በመቀላቀል የበቀል ስሜት የወለደውን የጥፋት እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል።
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ ዋናው አስተዳዳሪው ፣ የጥበቃ እና ደህንነት ሃላፊው የደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ ሃላፊዎች ፣ የዞን ተጠሪ ፣ የሽፍት መሪ ፣ የህክምና ክፍል ነርሶች ተብለው የተመደቡት ባጠቃላይ ትግሬዎች ናቸው። በቃሊቲ ውስጥ ኦሮሞ አልያም አማራ ኮሎኔል ሻለቃ ወይም መቶ አለቃ በትግሪኛ ተናጋሪ ተራ ወታደር የሚታዘዝ ነው።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተደራጀ ፣ህውሃት ከየ ክልሉ የሚፈልጋቸውን ሰዎች የሚያጉሩበት እስር ቤት ነው ። የህወሀት መንግስት አሁን እስረኞችን ለመረሸን የተነሳው በተለይ በአሁኑ ሠዐት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳበትን ተቃውሞ ማስተንፈሻና መበቀያ ነው።
ድምፃችን ይሰማ ‪#‎EthioMuslims‬ ‪#‎EthioMuslimCommitteeMembers‬ ‪#‎EthioMuslimsPeacefulStruggle‬ ‪#‎GovtBrutalityAgainstMuslims‬ ሰበር ዜና!!! መንግስት በእስር የሚገኙ የሰላም አምባሳደሮቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና እና ጥቃት ቀጥሎበታል!
‹‹እርምጃ ይወሰድባቸዋል›› ከተባሉ እስረኞች መካከል የ4ቱ ወኪሎቻችን ስም እንደሚገኝ የውስጥ መረጃዎች ጠቁመዋል! ማክሰኞ ሐምሌ 19/2008 የህዝበ ሙስሊሙ ድምጽ በመሆናቸው ብቻ ያለአንዳች ወንጀል በሐሰት ክስ ተፈርዶባቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙት ጀግኖቻችን መካከል 4ቱ በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጫና እና አካላዊ አደጋ ስር መሆናቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል፡፡ ገና ከጅማሮው ከቶርቸር አንስቶ ጠያቂ እስከመከልከል፣ ጨለማ ክፍል እስከመታሰር እና ቤተሰቦቻቸውን እስከማንገላታት የሚደርሱ የተለያዩ ህገወጥ ጫናዎች ሲደርስባቸው የቆዩት ህጋዊ ወኪሎቻችን በእስር ቤት ሆነውም ሰላም እንዳያገኙ ለማድረግ የመንግስት ደህንነቶች ሲያደርጉ የቆዩትን ጥረት አሁንም አጠናክረው የቀጠሉበት መሆናቸው ታውቋል፡፡ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ‹‹ረብሻ ለመፍጠር አሲራችኋል›› በሚል በርካታ እስረኞችን በሃሰት የወነጀለ ሲሆን ከጀግኖቻችን መካከል 4ቱም እርምጃ ለመውሰድ ከተዛተባቸው እስረኞች ስም ዝርዝር መሐል ስማቸው መካተቱን እና መለጠፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ዓይነቱ አሰራር መንግስት ቂም በያዘባቸው ታሳሪዎች ላይ በ‹‹ብጥብጥ አስነስተዋል›› ሰበብ እስከ ግድያ የሚደርስ እርምጃ ሲወስድ የቆየበት አሰራር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዓመታት በፊት በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ‹‹ለማምለጥ በሚል ብጥብጥ አስነስተዋል›› በሚል ውንጀላ በማረሚያ ቤት ጥበቃዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን አሁንም መንግስት ተመሳሳይ እርምጃ በሰላም አምባሳደሮቻችን እና በሌሎች ታሳሪዎች ላይ ለመውሰድ እቅድ የያዘ ስለመሆኑ የውስጥ አዋቂ ምንጮች እየጠቆሙ ነው፡፡ ህገ መንግስታችን የእስረኞችን ከህገወጥ ጥቃት እና ጫና የመጠበቅ መብት በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን አገሪቱ ተቀብላ የፈረመቻቸው በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ውሎችም በእስረኞች ላይ የሚደርስን አላግባብ ጥቃት አጥብቀው ይኮንናሉ፡፡ በመሆኑም በሰላም አምባሳደሮቻችን ላይ ዘርፈ ብዙ ጥቃት ሲያደርስ የቆየው መንግስት አሁን ላይ ለማድረስ አቅዷል እየተባለ ካለው ህገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆጠብ እያሳሰብን በእስር በሚገኙ ብርቅዬ መሪዎቻችን ላይ በሐሰት ‹‹የብጥብጥ ድራማ›› ሰበብነት አንዳች ጉዳት ቢደርስ መላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም መንግስትን ተጠያቂ ከማድረግ ወደኋላ የማይል እና በደለኞችንም እስከመጨረሻው የሚፋረድ መሆኑን በአጽንኦት እናስታውቃለን! እስረኞችን ማዋከብ እና ማጥቃት ህገ መንግስቱን የሚጻረር ወንጀል ነው! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል! አላሁ አክበር!
 

No comments:

Post a Comment