Thursday, June 29, 2017

የወገራ ገበሬዎች ላይ የታወጀው ፍጅት እና የእኛ ዝምታ source zehabesha

የወገራ ገበሬዎች
ከሙሉቀን ተስፋው
አገዛዙ በዐማራ ገበሬዎች ላይ ይፋ ጦርነት ካወጀ አንድ ዓመት ሆነው፡፡ በተለይ ደግሞ የወገራ ገበሬዎች ላይ ከባድ መሣሪያ ሳይተኮስ፣ የገበሬዎች ቤት ሳይቃጠል፣ ሰው ሳይሞት ሳምንት አይደፍንም፡፡ የትግሬው አገዛዝ በከባድ መሣሪያ ቤቶችን ሲያነድ፣ ሕጻናትንና አቅመ ደካሞችን ሲገደል እያየንና እየተመለከትን ምንም እያደረግን አይደለም፡፡ ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ትኩረት እንኳ እንዲያገኝ እያደረግን አይደለም፡፡ በወገራ መንግሥትን ይጥላ፣ ይውደድ አገዛዙ ጉዳዩ አይደለም- በአካባቢው የተገኘ ዐማራ የሆነ ሁሉ እስካፍንጫው በታጠቀ የትግሬ ጦር ዒላማ ይደረጋል፡፡
በርካቶች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል፤ ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው ተለይተዋል፡፡ የአባውራ ሴቶች ይደበደባሉ፡፡ ይህ የአለፉት ስምንት ወራት የወገራ ገበሬዎች ሁኔታ ነው፡፡ ይህችን ትንሽ ማስታዎሻ ስጽፍ እንኳ ሁለት ወንድማማቾች በከባድ መሣሪያ ወድቀዋል- የአባ ጋሻው ልጆች (መልካሙና አደራጀው)፡፡ የወገራ ገበሬዎችን አንድም ሳይለይ ነው አገዛዙ ጦርነት የከፈተባቸው፡፡
ከሁለት ቀናት በፊት በግብርናውም ሆነ በጉብዝናው የታወቀ አቶ ጓዴ ጌጡ የሚባል ወጣት ነበር፡፡ ሦስት የትግሬ ወታደሮች ከበቡት፡፡ ሦስቱንም አጋደማቸው፤ በመጨረሻ በትግሬ እጅ አልወድቅም ብሎ ራሱን ሰዋ፡፡ ገበሬው ያለበት ሁኔታ ይህ ነው፡፡ በየቀኑ ወደ አካባቢው የሚጨመረው ጦር ከሕዝብ ጋር ሳይሆን ከውጭ ወራሪ ኃይል ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው የሚመስለው፡፡
ስለ ወገራ ገበሬዎች ዝም ማለት የለብንም!! የሕዝባችን ዕልቂት ሊገደን ይገባል!!

No comments:

Post a Comment