Monday, June 26, 2017

በኦሮሚያ ክልል ሁለት አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች ደረሱ * በሁለት የመኪና አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ source zhabesha

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እንደዘገበው በኦሮሚያ ክልል ዛሬ በደረሱ ሁለት የትራፊክ አደጋዎች የ28 ህይወት አለፈ።
ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ 60 መንገደኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በምዕራብ ሀረርጌ ሂርና ከተማ ሲደርስ ፍሬን አልታዘዝ በማለቱ ነው በአከባቢው ለነበሩ 14 ወንድ እና ስምንት ሴት እግረኞች ሞት ምክንያት የሆነው።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የሰሌዳ ቁ.ኮድ 3-50262 ኢት የሆነው ተሽከርካሪ ቆመው በነበሩ ሶስት ሚኒባስ፣ አራት ባጃጆችና አራት አይሱዙ መኪኖች ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ንጉሴ ግርማ እንደገለጹት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም። አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ከደምቢዶሎ ወደ አዲስ አበባ አስክሬን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ሃይሩፍ ሚኒባስ በምዕራብ ወለጋ ጉቴ ወረዳ ገባ ሰንበታ ሲደርስ ገደል ውስጥ ገብቶ 6 ተሳፋሪዎች ላይ የሞት አደጋ አድርሷል ያለው ኢቢሲ በአደጋው አንድ አባት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ሂወታቸው አልፏ ል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ሹፌሩ ካለ እረፍት ለ3 ቀናት ሲያሽከረከር እንደነበረ ገልጸው ፖሊስም በስፋት በማጣራት ላይ ነው ሲል ኢቢሲ ዘገባውን ቋጭቷል::

No comments:

Post a Comment