Sunday, July 2, 2017

ሁከት አንስተዋል የተባሉ እስረኞች ከቅሊንጦ እስር ቤት ወደ ሌሎች እስር ቤቶች ተዛወሩ source zhabesha

file photo
የፍኖተ ዴሞክራሲ ዜናና ኃተታ –
ርዕሰ ዜና

#ሁከት አንስተዋል የተባሉ እስረኞች ከቅሊንጦ እስር ቤት ወደ ሌሎች እስር ቤቶች ተዛወሩ
#አመጽ ቀስቃሽ ግጥሞችን በዩቲዩብ አሰራጭተዋል የተባሉ ጋዜጠኞች ክስ ተመሰረተባቸው
#በጎንደር አንድ የሞርታር ጥይት ፈንድቶ በህይወትና በአካል ላይ ጉዳት አደረሰ
#ሳኡዲ አረቢያ የጣለችውን የቀን ገደብ ለ30 ቀን አራዘመች
#በአገራችን የገባው የተምች መንጋ በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋቱ አሳሳቢ ነው ተባለ
##ዝርዝር ዜናዎች##

#በቅሊንጦ ከሚገኘው የወያኔ እስር ቤት ውስጥ ከ20 የሚበልጡ እስረኞች ወደ ዘዋይ እስር ቤት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሌሎች ደግሞ ወደ ሸዋ ሮቢት የተዛወሩ መሆኑ ታውቋል። እስረኞቹ ወደ ሌሎች እስር ቤቶች የተዛወሩበት ምክንያት በመካከላቸው በዘር ላይ የተሰመረተ ግጭት ፈጥረው ሁከት በማስነሳታችው ነው የሚል ምክንያት እየተሰጠ ሲሆን ከተዛወሩት መካከልም ከዚህ በፊት #እስር ቤቱን በማቃጠል የተከሰሱ እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል። ላለፉት ጥቂት ቀናት በቅሊንጦ እስር ቤት ዞን 4 እና 5 ውስጥ የታሰሩ እስረኞች ዘመዶቻቸው እንዳያዩዋቸው የተከለከሉ መሆናቸውም ታውቋል። እስር ቤት ውስጥ የታጨቀው እስረኛ በጣም በርካታ ከመሆኑ የተነሳ እስረኞች በጥበቱ የተማረሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መግለጻችው ይታወቃል። በ 900 ሚሊዮን ብር እየተሰራ ነው የሚባለውም እስር ቤት ምን ያህል ችግሩን ሊያቃልል እንደሚችል አልታወቀም ተብሏል።
#በጋዘጠኛነት ሙያ ተሰማርተው የነበሩና አመጽ ቀስቃሽ ግጥሞችን በዩቱዩብ አሰራጭታችኋል የተባሉ ሰባት ሰዎች ክስ የተመሰረተባችው መሆኑ ታወቀ። ሰባቱ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው የተሰነሰዘረባቸው ክስ የተሰማ ሲሆን ከተከሳሾች በኩል የሚቀርበውን የመጀመሪያ የመቃወሚያ ሀሳቦችን ለመሰማት ለሐምሌ 7 ቀን ቀጠሮ የተያዘ መሆኑ ታውቋል።
#በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ አሮጌ ብረት ተራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሞርታር ጥይት በመፈንዳቱ ምክንያት ሁለት ስዎች ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸውና ሌሎች ሶስት ሰዎች የቆሰሉ መሆናችው ተነገረ። የሞርታር ጥይቱን ለብረት ሙቀጫ ለማዋል በብረት መጋዝ በመቁረጥ ላይ እንዳሉ ጥይቱ በመፈንዳቱ ሰዎቹ ወዲያውኑ ሊሞቱ የቻሉ መሆናቸው ተነግሯል።
#የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ህገ ወጥ ናቸው የሚላቸው ስደተኞች ከአገሩ እንዲወጡ አውጆት የነበረውን የቀን ገደብ ለ 30 ቀናት ያራዘመው መሆኑን ገለጸ። ለቀን ገደቡ መራዘም በሳኡዲ መንግስት በኩል የተሰጠ ማብራሪያ ባይኖርም የወያኔ አገዛዝ እና አንዳንድ ወገኖች ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጠ መልስ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለ። በሳኡዲ አረቢያ ከ400000 እስከ 450000 ሺ የሚገመቱ ኢትዮጵያን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ይኖራሉ ተብሎ ሲገመት እስካሁን የተመለሱት ቁጥር ከ45000 እንደማይበልጥና የመጓጓዣ ሰነድ ተሰጥቷቸዋል የተባሉት 111 ሺ ብቻ መሆናቸው ተነግሯል።
#በአገራችን የገባው የተምች መንጋ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ በመሄዱ ሁኔታው በጣም አሳሳቢ መሆኑ ተነገረ። እስካሁን ድረስ በ35 ዞኖች በ136 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የተዘሩ ሰብሎችን ያበላሸው ይኽው የተምች መንጋ በቅርቡ እስከሁለት ሚሊዮን ሄክታር በሚድርስ ቦታዎች ላይ የተዘሩትን አዝርዕት ሊያበላሽ እንደሚችል ተገምቷል። ይኽም በአገሪቱ ውስጥ ለእርሻ ተስማሚ ከሆኑ መሬቶች መካከል አንድ ስድሰተኛ የሚሆን ሲሆን ተምቹ የሚያደርሰው ጥፋት የረሃቡንና የድርቁን ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ሊያስፋፋው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ተምቹ በሰዓት ከ 100 ኪሎ ሜትር በላይ የመብረርና በአንድ ጊዜ 1500 እስከ 2000 እንቁላል የመፈልፈል አቅም እንዳለው ባለሙያዎች ይናገራሉ። በወያኔ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስተር ተምቹን ለማጥፋት የተደረገው ጥረት የተወሰነ ውጤት ቢኖረውም ተምቹን ለመቆጣጠር ያልተቻለ በመሆኑ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment