Friday, July 7, 2017

አማራውንና ኦሮሞውን ለመከፋፈል ወያኔ ያወጣው አዋጅን የኦሮሞ ድርጅቶች እየተቃወሙት ይገኛሉ source zehabesha

የፍኖተ ዴሞክራሲ ዜናና ኃተታ – 
#ርዕሰ ዜና

#ተመድ ከ800 ሺ ዜጎች በላይ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል አለ
#አነስተኛ ነጋዴዎች ከመጠን በላይ የተቆለባቸው ታክስ እያስመረራቸው ነው
#በአፍሪካ ቀንድና በየመን የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወደ አውዳሚ ደረጃ እየተዛወረ ነው
#እስራዔል የአፍርካ ስደተኞችን ሁኔታ አባባሰች ተባለ
#አማራውንና ኦሮሞውን ለመካፋፈል ወያኔ ያወጣው አዋጅ የኦሮሞ ድርጅቶች እየተቃወሙት ይገኛሉ
#የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ለቀ.ኃ.ሥ ሃውልት ለመስራት ሲወስን ወያኔ ለመለሰ ካልተሰራ በማለት እያስቸገረ ነው

##ዝርዝር ዜናዎች##
#የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ባሰባሰባው መረጃ መሰረት በድርቁ ምክንያት በኢትዮጵያ 843ሺ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ መሆናቸውን ገልጿል። 36,750 የሚሆኑ ዜጎች በኮሌራ በሽታ መያዛች ገልጾ ከዚሁ ውስጥ 780 መሞታቸውን መረጃ የደረሰው መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፤ 110 680 የሚሆኑ ህጻናትም በተመጣጣኝ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውና እስካሁን ድረስ የነበረው የበልግ መኸር በበርካታ አካባቢዎች በጣም አነስተኛ መሆኑን ገልጾ በዘንድሮ ክረምት በአንዳንድ አካባቢዎች ከአማካዩ ከፍ ያለ ዝናም መዝነሙ የተመዘገበ ቢሆንም በደቡብና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች የጣለው ዝናም አነስተኛ በመሆኑ የረሃቡ ችግር ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል ብሏል።
#የቀን ገቢ ግምት በሚል ፈሊጥ የወያኔ አገዛዝ በማንአለብኝነት በአነስተኛ ነጋዴዎች ላይ የቆለለው ታክስ ብዙዎችን ያስቆጣና ያስመረረ መሆኑ ከዚህ በፊት የተዘገበ ሲሆን ታክሱ በዝቷል በሚል አቤቱታ በሚያቀርቡ ነጋዴዎች ላይ የአገዛዙ ባለስልጣኖች ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ እየሰጡ መሆናቸው ተገልጸ። በነሲብና በማን አለብኛነት ይህን ያህል ገቢ አለህ፤ ይህን ያህል ታተርፋለህ በማለት በእያንዳንዱ ነጋዴ ላይ በዘፈቀደ የተቆለለው ታክስ አግባብ አይደለም በማለት ነጋዴዎቹ ቅሬታቸውን እያሰሙ ሲሆን በቡድን በመሆን ቅሬታ ማሰማት አይቻልም፤ ታክስ ሰብሳቢዎችን አመናጭቃችኋል ፤ አስፈራርታችኋል በማለት በነጋዴዎች ላይ ክስ መስርተውውባቸዋል። ነጋዴዎቹ በግለሰብ ደረጃ ቅሬታ እንዲያቀርቡ ቢነገራቸውም ታክሱን ከመክፈል እንደማይድኑም ታውቋል።
#በአፍሪካ ቀንድና በየመን ያለው የረሃብን የበሽታ የኮሌራ ወረርሽኝ ሁኔታ ከአስደንጋጭ ወደ አጥፊና አውዳሚ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ሲሉ ታዛቢዎች አስጠነቀቁ ። በደቡብ ሱዳን ባለው ቀውስ በመንግስት ግድ የለሽነት ሚሊዮኖች ለሞት አደጋ ተጋልጠዋል ያሉ ክፍሎች ኮሌራ በደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያና በየመን በመስፋፋት ላይ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ። ወያኔን በመደገፍ የሀገር ኤኮኖሚ እያደገ ነው የሚሉ ክፍሎች በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ አቅልለው እያቀረቡ ቢሆንም በአፋር፤ኦጋዴን፤ሰሜን ሸዋ ፤ደቡብ ኢትዮጵያ ወዘተ ረሃቡ መግደል ከጀመረ ውሎ አድሯል እየተባለም ነው ። የግልገል ግቤ 3 ግድብ አርሶ አደሮችን የሚያርሱት መሬት ማሳጣቱም ለችግሩ አስተዋጾ አድርጓል የተባለ ሲሆን ብዙ ሳይነገርለትም የተጀመረው የግልገል ግቤ 4 ግድብ ስራ በአካባቢውና አልፎም በኬንያ ችግር ፈጣሪ መሆኑ አይቀሬ መሆኑ ተዘግቧል ። እየተደበቀ ያለውን የአስከፊ ረሃብ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጋለጥ የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው በሚልም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
#በጨካኝና ዘረኛ ጸረ ስደተኛ አቅዋሟ ውግዘት የደረሰባት እስራኤል ከዓለም አቀፍ ትኩረት በተሸፈነ መንገድ የአፍሪካ ስደተኞችን መከራ አባብሳ ትገኛለች በሚል ተወገዘች ። ይህ ውግዘት የተመሰረተው እስራኤል የሱዳንና ኤርትራ ስደተኖችን በመደለልም ሆነ በማስገደድ ወደ ሩዋንዳ ኪጋሊ ወስዳ መጣል ላይ ስለተሰማራች ነው ተብሏል ። በምትሄዱበት ጥገኝነትን ታገኛላችሁ የሚባሉት ስደተኞች በኪጋሊ እንግልት እየደረሰባቸውና ከዚያም ወደ ዩጋንዳ በገንዘብ ክፍያ ተወስደው እንደሚጣሉ ሊታወቅ ተሏል ። እስካሁን እስራኤል ወደ 2 ሺ የሚጠጉ ስደተኞችን ማባረሯ ታውቋል ። የእስራኤል ባለስልጣኖች በአሳፋሪ ዘረኝነት የአፍሪካ ስደተኞችን ካንሰር በሽታ ብለው መሰየማቸውና ዘግናኝ ዘረኝነትንም ማንጸባረቃቸው የተሰማና የታየ ነው ያሉ ታዛቢዎች በዩጋንዳና ሩዋንዳ ስደተኞቹ መነገጃ ሆነው ለአስከፊ ስቃይ የተዳረጉ መሆናቸው ታውቋል ብለዋል ። እስራኤል ለርዋንዳና ዩጋንዳ የተወሰነ ገንዘብ ከፍላ ተጨማሪ ስደተኞችን ልታጓጉዝ ተዘጋጅታለችም ተብሏል ።
#ወያኔ ኦሮሞና አማራን መከፋፈል በሚለው መርሁ መሰረት በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ ያወጣው መሰሪ አዋጅ በአብዛኛው የኦሮሞ ድርጅቶችና ቡድኖች በሰፊው የተወገዘ መሆኑ ተዘግቧል ። ኦሮሞዎችን በዚህ መንገድ ደልዬ እጠቀምባቸዋለሁ ብሎ በንቀት የተነሳው ወያኔ ከወዲሁ ዕቅዱ ስለከሸፈበት ልዩ ስብሰባ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ማድረጉም ተጋልጧል ። ታዛቢዎች በማስተር ፕላን ሽፋን የሕዝብን መሬት ሊቀማ ተነስቶ የከሸፈበት ወያኔ በዚህ አዋጅም የሕዝብን መሬት በራሱ እጅ ሊያስገባ እንጂ ለማንኛውም ሕዝብ ሊጠቅም ተነስቶ አይደለም ሲሉ አጋልጠውታል ። የወያኔ ተንኮል ከወዲሁ ከሽፏል ሊባል ይቻላልም ተብሏል ። በመጪው የሕዝብ ቆጠራ ወያኔ አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ትግሬ ነው ብሎ እንደ ወልቃይት ጠገዴ ከተማይቷን የትግራይ ከማለት የሚመለስ አይደለም ሲሉ አንዳንድ ክፍሎች ተችተዋል ።
#በርካታ የአፍሪካ መሪዎችና የፖለቲካ ሀይሎች ከአፍሪካ ህብረት መስራቾች አንዱ ለሆኑት ለአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ይቁማላቸው ማለታቸው ታወቀ; ወያኔ በዚህ አስታኮ ለከሀዲውና የባዕዳን ቅጥረኛ ለሆነው ለመለስ ዜናዊም በተጽዕኖ ሀውልት ሊያቆም መወሰኑ ተወግዟል ። አጼው ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራቾች አንዱ ሲሆኑ መለስ ዜናዊ ግን ለአፍሪካ የቆመ ሳይሆን ኢትዮጵያና አፍሪካን ለምዕራባውያን የሸጠና የኢምፔሪያሊዝም ቅጥረኛ የነበረ በመሆኑ ሀውልት ሊሰራለት ቀርቶ በጸረ አፍሪካነት መወገዝ ያለበት ከሀዲ ነው ሲሉ ብዙዎች በጥብቅ ተቃውመዋል።
#የአፍሪካውያን ቁጥር ጨምሯልና መቀነስ አለበት ባዩ የአሜሪካው የጠገበ ሀብታም ቢል ጌትስ ውድቅ የወያኔ የጤና ተቋሞችን ቢያዳንቅም ሆነ ድህነት በስተፋፋበት ሀገር ኤኮኖሚ ተመነደገ ተብሎ ቢዋሽም በተደረጉ ጥናቶች በወያኔ አገዛዝ ስር ትምህርት ሳይሆን ድንቁርና መስፋፋቱ ተጋልጧል ። አንደኛ ደረጃ ትምህርት ጨርሰው ማንበበና መጻፍ በሚገባው ደረጃ የማይችሉ ብዙዎች ናቸው ያሉ ክፍሎች በየእርከኑ የተመደቡ አስተማሪዎችም ቢሆን ብቃታቸው አጠያያቂ ነው ብለዋል ። ወያኔ ብቃይ ያላቸውን አስተማሪዎች መንጥሮ ማባረሩ አይረሳም ያሉ ክፍሎች የአስተማሪዎችንም ታሪካዊ ማህበር አፍርሶ ለዘረኛ ፖለቲካው በሚያመች ደረጃ ትምህርትን አዳክሟል ሲሉ ከሰዋል ። ይህ ሕዝብ ሁሉየሚያውቀው ሀቅ በባዕዳንም ጥናት ዛሬ እየተረጋገጠ በመሆን ውግዘት መቀበል የተገደደው ወያኔ በውሸቱ በመቀጠል ከ97 በመቶአ ያላነሱ ሕጻናት ትምህርት ቤት መግባታቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ባልታየ ደረጃ የማንበብ መጻፍ ችሎታ ያለው ሕዝብ ቁጥር እጥፍ ድርብ ጨምሯል በሚል ቅጥረኞቹን እያስዋሸ ነው በሚልም ተጋልጧል ።
የፍኖተ ዴሞክራሲ ዜናና ኃተታ – ሰኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. #ርዕሰ ዜና #ተመድ ከ800 ሺ ዜጎች በላይ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል አለ #አነስተኛ ነጋዴዎች ከመጠን በላይ የተቆለባቸው ታክስ እያስመረራቸው ነው #በአፍሪካ ቀንድና በየመን የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወደ አውዳሚ ደረጃ እየተዛወረ ነው #እስራዔል የአፍርካ ስደተኞችን ሁኔታ አባባሰች ተባለ #አማራውንና ኦሮሞውን ለመካፋፈል ወያኔ ያወጣው አዋጅ የኦሮሞ ድርጅቶች እየተቃወሙት ይገኛሉ #የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ለቀ.ኃ.ሥ ሃውልት ለመስራት ሲወስን ወያኔ ለመለሰ ካልተሰራ በማለት እያስቸገረ ነው ##ዝርዝር ዜናዎች## #የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ባሰባሰባው መረጃ መሰረት በድርቁ ምክንያት በኢትዮጵያ 843ሺ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ መሆናቸውን ገልጿል። 36,750 የሚሆኑ ዜጎች በኮሌራ በሽታ መያዛች ገልጾ ከዚሁ ውስጥ 780 መሞታቸውን መረጃ የደረሰው መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፤ 110 680 የሚሆኑ ህጻናትም በተመጣጣኝ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውና እስካሁን ድረስ የነበረው የበልግ መኸር በበርካታ አካባቢዎች በጣም አነስተኛ መሆኑን ገልጾ በዘንድሮ ክረምት በአንዳንድ አካባቢዎች ከአማካዩ ከፍ ያለ ዝናም መዝነሙ የተመዘገበ ቢሆንም በደቡብና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች የጣለው ዝናም አነስተኛ በመሆኑ የረሃቡ ችግር ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል ብሏል። #የቀን ገቢ ግምት በሚል ፈሊጥ የወያኔ አገዛዝ በማንአለብኝነት በአነስተኛ ነጋዴዎች ላይ የቆለለው ታክስ ብዙዎችን ያስቆጣና ያስመረረ መሆኑ ከዚህ በፊት የተዘገበ ሲሆን ታክሱ በዝቷል በሚል አቤቱታ በሚያቀርቡ ነጋዴዎች ላይ የአገዛዙ ባለስልጣኖች ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ እየሰጡ መሆናቸው ተገልጸ። በነሲብና በማን አለብኛነት ይህን ያህል ገቢ አለህ፤ ይህን ያህል ታተርፋለህ በማለት በእያንዳንዱ ነጋዴ ላይ በዘፈቀደ የተቆለለው ታክስ አግባብ አይደለም በማለት ነጋዴዎቹ ቅሬታቸውን እያሰሙ ሲሆን በቡድን በመሆን ቅሬታ ማሰማት አይቻልም፤ ታክስ ሰብሳቢዎችን አመናጭቃችኋል ፤ አስፈራርታችኋል በማለት በነጋዴዎች ላይ ክስ መስርተውውባቸዋል። ነጋዴዎቹ በግለሰብ ደረጃ ቅሬታ እንዲያቀርቡ ቢነገራቸውም ታክሱን ከመክፈል እንደማይድኑም ታውቋል። #በአፍሪካ ቀንድና በየመን ያለው የረሃብን የበሽታ የኮሌራ ወረርሽኝ ሁኔታ ከአስደንጋጭ ወደ አጥፊና አውዳሚ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ሲሉ ታዛቢዎች አስጠነቀቁ ። በደቡብ ሱዳን ባለው ቀውስ በመንግስት ግድ የለሽነት ሚሊዮኖች ለሞት አደጋ ተጋልጠዋል ያሉ ክፍሎች ኮሌራ በደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያና በየመን በመስፋፋት ላይ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ። ወያኔን በመደገፍ የሀገር ኤኮኖሚ እያደገ ነው የሚሉ ክፍሎች በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ አቅልለው እያቀረቡ ቢሆንም በአፋር፤ኦጋዴን፤ሰሜን ሸዋ ፤ደቡብ ኢትዮጵያ ወዘተ ረሃቡ መግደል ከጀመረ ውሎ አድሯል እየተባለም ነው ። የግልገል ግቤ 3 ግድብ አርሶ አደሮችን የሚያርሱት መሬት ማሳጣቱም ለችግሩ አስተዋጾ አድርጓል የተባለ ሲሆን ብዙ ሳይነገርለትም የተጀመረው የግልገል ግቤ 4 ግድብ ስራ በአካባቢውና አልፎም በኬንያ ችግር ፈጣሪ መሆኑ አይቀሬ መሆኑ ተዘግቧል ። እየተደበቀ ያለውን የአስከፊ ረሃብ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጋለጥ የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው በሚልም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። #በጨካኝና ዘረኛ ጸረ ስደተኛ አቅዋሟ ውግዘት የደረሰባት እስራኤል ከዓለም አቀፍ ትኩረት በተሸፈነ መንገድ የአፍሪካ ስደተኞችን መከራ አባብሳ ትገኛለች በሚል ተወገዘች ። ይህ ውግዘት የተመሰረተው እስራኤል የሱዳንና ኤርትራ ስደተኖችን በመደለልም ሆነ በማስገደድ ወደ ሩዋንዳ ኪጋሊ ወስዳ መጣል ላይ ስለተሰማራች ነው ተብሏል ። በምትሄዱበት ጥገኝነትን ታገኛላችሁ የሚባሉት ስደተኞች በኪጋሊ እንግልት እየደረሰባቸውና ከዚያም ወደ ዩጋንዳ በገንዘብ ክፍያ ተወስደው እንደሚጣሉ ሊታወቅ ተሏል ። እስካሁን እስራኤል ወደ 2 ሺ የሚጠጉ ስደተኞችን ማባረሯ ታውቋል ። የእስራኤል ባለስልጣኖች በአሳፋሪ ዘረኝነት የአፍሪካ ስደተኞችን ካንሰር በሽታ ብለው መሰየማቸውና ዘግናኝ ዘረኝነትንም ማንጸባረቃቸው የተሰማና የታየ ነው ያሉ ታዛቢዎች በዩጋንዳና ሩዋንዳ ስደተኞቹ መነገጃ ሆነው ለአስከፊ ስቃይ የተዳረጉ መሆናቸው ታውቋል ብለዋል ። እስራኤል ለርዋንዳና ዩጋንዳ የተወሰነ ገንዘብ ከፍላ ተጨማሪ ስደተኞችን ልታጓጉዝ ተዘጋጅታለችም ተብሏል ። #ወያኔ ኦሮሞና አማራን መከፋፈል በሚለው መርሁ መሰረት በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ ያወጣው መሰሪ አዋጅ በአብዛኛው የኦሮሞ ድርጅቶችና ቡድኖች በሰፊው የተወገዘ መሆኑ ተዘግቧል ። ኦሮሞዎችን በዚህ መንገድ ደልዬ እጠቀምባቸዋለሁ ብሎ በንቀት የተነሳው ወያኔ ከወዲሁ ዕቅዱ ስለከሸፈበት ልዩ ስብሰባ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ማድረጉም ተጋልጧል ። ታዛቢዎች በማስተር ፕላን ሽፋን የሕዝብን መሬት ሊቀማ ተነስቶ የከሸፈበት ወያኔ በዚህ አዋጅም የሕዝብን መሬት በራሱ እጅ ሊያስገባ እንጂ ለማንኛውም ሕዝብ ሊጠቅም ተነስቶ አይደለም ሲሉ አጋልጠውታል ። የወያኔ ተንኮል ከወዲሁ ከሽፏል ሊባል ይቻላልም ተብሏል ። በመጪው የሕዝብ ቆጠራ ወያኔ አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ትግሬ ነው ብሎ እንደ ወልቃይት ጠገዴ ከተማይቷን የትግራይ ከማለት የሚመለስ አይደለም ሲሉ አንዳንድ ክፍሎች ተችተዋል ። #በርካታ የአፍሪካ መሪዎችና የፖለቲካ ሀይሎች ከአፍሪካ ህብረት መስራቾች አንዱ ለሆኑት ለአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ይቁማላቸው ማለታቸው ታወቀ; ወያኔ በዚህ አስታኮ ለከሀዲውና የባዕዳን ቅጥረኛ ለሆነው ለመለስ ዜናዊም በተጽዕኖ ሀውልት ሊያቆም መወሰኑ ተወግዟል ። አጼው ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራቾች አንዱ ሲሆኑ መለስ ዜናዊ ግን ለአፍሪካ የቆመ ሳይሆን ኢትዮጵያና አፍሪካን ለምዕራባውያን የሸጠና የኢምፔሪያሊዝም ቅጥረኛ የነበረ በመሆኑ ሀውልት ሊሰራለት ቀርቶ በጸረ አፍሪካነት መወገዝ ያለበት ከሀዲ ነው ሲሉ ብዙዎች በጥብቅ ተቃውመዋል። #የአፍሪካውያን ቁጥር ጨምሯልና መቀነስ አለበት ባዩ የአሜሪካው የጠገበ ሀብታም ቢል ጌትስ ውድቅ የወያኔ የጤና ተቋሞችን ቢያዳንቅም ሆነ ድህነት በስተፋፋበት ሀገር ኤኮኖሚ ተመነደገ ተብሎ ቢዋሽም በተደረጉ ጥናቶች በወያኔ አገዛዝ ስር ትምህርት ሳይሆን ድንቁርና መስፋፋቱ ተጋልጧል ። አንደኛ ደረጃ ትምህርት ጨርሰው ማንበበና መጻፍ በሚገባው ደረጃ የማይችሉ ብዙዎች ናቸው ያሉ ክፍሎች በየእርከኑ የተመደቡ አስተማሪዎችም ቢሆን ብቃታቸው አጠያያቂ ነው ብለዋል ። ወያኔ ብቃይ ያላቸውን አስተማሪዎች መንጥሮ ማባረሩ አይረሳም ያሉ ክፍሎች የአስተማሪዎችንም ታሪካዊ ማህበር አፍርሶ ለዘረኛ ፖለቲካው በሚያመች ደረጃ ትምህርትን አዳክሟል ሲሉ ከሰዋል ። ይህ ሕዝብ ሁሉየሚያውቀው ሀቅ በባዕዳንም ጥናት ዛሬ እየተረጋገጠ በመሆን ውግዘት መቀበል የተገደደው ወያኔ በውሸቱ በመቀጠል ከ97 በመቶአ ያላነሱ ሕጻናት ትምህርት ቤት መግባታቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ባልታየ ደረጃ የማንበብ መጻፍ ችሎታ ያለው ሕዝብ ቁጥር እጥፍ ድርብ ጨምሯል በሚል ቅጥረኞቹን እያስዋሸ ነው በሚልም ተጋልጧል ።

No comments:

Post a Comment