Thursday, July 6, 2017

በባህርዳር መግቢያ መውጫወች በተለይ በጎንደር መስመር ከፍተኛ ወታደራዊ ፍተሻ እየተደረገ ነው !! source satenewa

ይህ የወያኔ ፍተሻ የሚያገኘው ነገር ኖሮ ሳይሆን በህዝቡ ላይ የፍርሃት ቆፈን በመጫን የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ያለመ ነው። ህወሓት /ወያኔ ውርደቱን ለመሸፋፈን ያዙኝ ልቀቁኝ አብዝቷል። የደረሰበት መተረማመስና መፈረካከስ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ አላደረገውም። የነፃነት ሃይሎች ያልተጠበቀና ምንም መረጃ ባልወጣበት የሚፈፀም ጥቃት ፋታ ነስቶታል። ወደ ጎጃም እየገሰገሰ የሚገኘው የነፃነት ትግል ፋና የውስጡን አለመረጋጋት እና ጎራ ለይቶ እርስ በርሱ በጥርጣሬ መተያየቱን በጉልህ ጥርሱን አግጥጦ እንዲታይ አድርጎታል። በባህርዳር አየር ማረፊያ የተያዘው ተቀጣጣይ ፈንጂ ደግሞ የነፃነት ትግሉ አድማሱን ማስፋቱና ከእጁ እየወጣ የሚገኘው የቀጠናው የነፃነት ታጋዩች እንቅስቃሴ በወታደር ብዛት መግታት እንዳልቻለ ያረጋገጠ ትልቅ ስጋት ሁኖበታል።በዚህም የራሴ የሚላቸውን ሰወች በመጠራጠር እስከ ማሰር እንደደረሰ መረጃወች ይጠቁማሉ። በቀጣይ ይደርስብኛል ብሎ ከሰጋቸው አንኳር ጥቃቶች በመነሳት በለሊት ማንኛውንም የስራ መኪና እንቅስቃሴ በሰሜኑ ቀጠና እስከማገድ እና በኬላወች ለፍተሻ በማስቆም እንዲያድር ያደርጋሉ። በዛሬ ዕለተ ረዕቡ ሰኔ 28/2009 ዓ.ም አነጋግ የጀመረው ፍተሻ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች (ባለማዕረግተኞች)በስምሪት የተሳተፉበት ነበር። በትናንትናው ምሽት በበግ ተራ አካባቢ ሰወች እየታደኑ ይያዙ እንደነበር የአይን እማኞች ይናገራሉ። በወታደሮች እየተያዙ የተወሰዱ ሰወች ትክክለኛ ማንነትና ቁጥር እስካሁን ለማረጋገጥ አልተቻለም። ይህ በህወሓት ወንበዴ ቡድን የሚፈፀም ድንገተኛ የተጋነነ ወታደራዊ ሰልፍና ፍተሻ በመውጫ መግቢያወች ምንም የሚያገኘው ኑሮ ሳይሆን በነዋሪው ህዝብ ላይ የፍርሃት ቆፈን በመደረብ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ያለመ ውርደቱን መሸፈኛ ካባ ነው ። ስነልቦናው እንደ አለት በጠነከረ ህዝብ ላይ ጫና ለመፍጠር መሯሯጥ ትርፉ መላላጥ ብቻ ነው። ድል ድል ይሸታል አየሩ ፣ ትርምስምስ ብሏል ጠላት መንደሩ ። ድል ምንጊዜም የህዝብ ነው !! @እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ     

No comments:

Post a Comment