Tuesday, July 4, 2017

“ነጭ ኑግ ጥቁር ወተት ውለዱ” – 25 አመታት የሌላውን ሁሉ ውጣ የማትጠረቃው ክልል! ! [ቬሮኒካ መላኩ] source zhebesha

ትናንት ነበር ሌላም ጊዜ እንደማደርገው ለአመታት የጆሮዬ ጓደኛ የሆነውን የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ሰአቱን ጠብቄ ከፍቸው ነበር። የእለቱ የራዲዮ ፕሮግራሙ አስተዋዋቂ ” አድማጮቻችን በዛሬው የፕሮግራማችን ሁለተኛ ክፍል ላይ ኢትዮጵያ በኤርትሪያ ላይ የምትከተለው ፖሊሲ በትግራይ ክልል እየፈጠረ ያለውን ችግር የሚያስረዱ ሁለት እንግዶች ስለሚቀርቡ ይሄን ዝግጅት እንድታዳምጡ እንጋብዛለን> > በማለት ፕሮግራሙን አስተዋወቀ። እኔም ሰአቱን ጠብቄ ፕሮግራሙን መከታተል ጀመርኩኝ ። … የፕሮግራሙ አዘጋጅ የሆነችው አንጋፋዋ ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሃዬ ስትሆን የጋበዘቻቸው ሰዎች ደሞ ከወደ ትግራይ እንደሆኑ በሚናገሩት አማርኛ በደንብ መረዳት ይቻል ነበር። ሲጀመር ይሄ ፕሮግራም መቅረብ የነበረበት በቪኦኤ የትግርኛ ፕሮግራም ነበር በአማርኛው ክፍለ ጊዜም ይቅረብ ከተባለ ቢያንስ አንድ አይነት አመለካከት ፣አንድ አይነት አስተሳሰብ ያላቸውን እንግዶች ከማቅረብ በጉዳዩ ላይ የተለየ አመለካከት ያላቸው እንግዶች ቢቀርቡ ፕሮግራሙን ሚዛናዊ ማድረግ ይቻል ነበር። … በነገራችን ላይ አንጋፋውና ተወዳጁ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በአንድ ክልል እና ብሄር የእጅ አዙር ቁጥጥር ስር የገባ ይመስላል። ቪኦኤ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በተለየ ከትግራይ ክልል የሚዘግብ ዘጋቢ አለው ፣ በትግሪኛ ቋንቋ የሚያሰራጨው በክልሉ ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና እና ሌሎች ጉዳዮች ብቻ አትኩሮ የሚሰራ የ30 ደቂቃ ፕሮግራም አለው ። ይሄ ሁሉ አልበቃ ብሎ የአማረኛውም ፕሮግራም ብዙ ጊዜውን የሚያጠፋው ስለትግራይ በመዘገብ ነው። … ወደ ዋናው የትናንቱ የቪኦኤ ፕሮግራም ይዘት ስገባ ፕሮግራሙ በሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር: ። በፕሮግራሙ የቀረቡት እንግዶች ጥያቄያቸውን ለጠ/ሚ ሀይለማሪያምና ፌደራል መንግስት ማቅረባቸውንና በጎ ምላሽ እንደሚጠብቁ ገልፀዋል … ሁለቱ የፕሮግራሙ ይዘቶች … 1~ ትግራይ የጦርነት ቀጠና ሆና በልማት እየተጎዳች ስለሆነ ከፌደራል መንግስት ድጎማ እንድደረግላት የሚጠይቅ ሲሆን… … 2~ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የምትከተለው No war No peace ፖሊሲ ተቀይሮ ወደ ጦርነት እንድገባ የሚገፋፋ አንድምታ ያለው ነው ። … በሁለቱም ጉዳዮች ላይ ያለኝን አመለካከት አጠር በማድረግ ላስቀምጥ: ….. 1~ “ትግራይ በልማት እየተጎዳች በመሆኑ የፌደራል መንግስት ድጎማ ያስፈልጋታል ” ….. እንግሊዛዊው ባለቅኔና ገጣሚ ዊሊያም ሸክስፒር ” ሀምሌት ” በተባለው ዘመን አይሽሬ ተውኔቱ የሰውን ስግብግብነት ፣ አልጠግብ ባይነት ፣ክፋት ፣ ተንኮል እና ፈጣጣነት በአንድ አረፍተ ነገር ገልፆት ነበር … << O shame, where is thy blush ? Proclaim no shame !! …>> ” ሃፍረት ሆይ !! ይሉኝታ ቢስ ሆይ!! ቅላትሽ ወደት አለ? … አንተ ሀፍረተ ቢስ!! እናንተ ይሉኝታ የለሾች! ! ሃፍረት የሌለህ እንደሆንከ አዋጅ ተናገር >> እያለ ይቀጥላል ። እዚህ ላይ የዊሊያም ሸክስፒርን አባባል መጥቀሴ ለእነዚህ ሰዎች ተገቢና ገላጭ አባባል ሆኖ ስላገኘሁት ነው ። … ይች ኢትዮጵያ የምትባል አገር እስከ መቼ ነው የትግራይ ጥገት ላም ሆና የምትኖረው? አሁንም ከመቶ ሚሊዮን ህዝብ አፍ ላይ ተነጥቆ የእነሱ ክልል እንደ ታይዋን እና ሆንግ ኮንግ እንደሆን ይፈልጋሉ ። ብዙዎች በየቀኑ ከኢትዮጵያዊነት መንበር ሸርተት እያሉ ለመሸፈታቸው ዋናው ምክንያት ” ትግሬ እያጋበሰ የሚኖርባት እና ሌላው በችጋር ተጠብሶ የሚያለቅስባት አገር ፣ የተለያዩ ዜጎች እና ክልሎች በእኩል አይን የማይታዩበታ አገር አታስፈልገኝም ” በማለት ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ሌላው ክልል ዜጎች በርሃብ ፣ በእርዛት ፣ በእስር እና በግድያ የሚሰቃዩባት የትራጂዲያ መድረክ ናት ። እንደ ተራ እንስሳ በመከራ የሚጠበሱ ዜጎች ባሉባት አገር ውስጥ የአንድ ክልል ነዋሪዎች ሌላውን ህዝብ << ጥቁር ወተት እና ነጭ ኑግ ውለድ! >> የሚባለው የአልጠግብ ባዮች ልፈፋ በአስቸኳይ መቆም አለበት ። ቪኦኤስ እንደት ስራ ቢያጣ ነው ይሄን አይነት የለየለት የዘረፋ ፕሮጀክት ሊያቀርብልን የቻለው ? የኢትዮጵያ ምዝብርና ግፉእ ህዝብ ለ25 አመታት የተበዘበዘውና የተመዘበረው አንሶ አሁንም አመታት ቢውጡ ከርሳቸው የማይሞላና የማይጠግቡ ቡድኖች ሲሳይ መሆኑ ማብቃት አለበት ። ይሄ ካልሆነ ግን በአገራችን ይሄ አይነት ሰፍሳፋነትና አልጠግብ ባይነት እስካለ ድረስ በአገራችን ሰላም ሊሰፍን አይችልም ። … 2~ የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትሪያ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ በመቀየር አስቸኳይ እርምጃ እንድወስድ ። … በሁለተኛ ደረጃ የአዳነች ፍስሃዬ እንግዶች ያስረዱትና እና ለፌደራል መንግስት አቀረብነው ያሉት ጉዳይ ” ጦርነት ይደረግልን” የሚል አንድምታ ይመስላል። ሀበሻ ሲተርት ” የዘንዶ ጉድጓድ በሞኝ ክንድ ይለካል ” ይላል። እነዚህ ሰዎች እቤታቸው ያለውን የዘንዶ ጉድጓድ በሌላው ኢትዮጵያዊ ክንድ ይለካልን እያሉ እየጠየቁ ይመስላል ። ከአመታት በፊት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶች ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ወደ ጦር ሜዳ ዘመቱ። እነዚህ ወጣቶች ወደ ጦርነቱ ሆ ብለው የገቡት በወቅቱ ገንኖ በነበረው የብሔራዊ ስሜት ማዕበል ተነድተው እና አገራችን ተወረረች ብለው ነበር ።ይሁንና ብዙም ሳይቆይ ተገኘ የተባለው ድል ወደ ምሬት ተለወጠ። ሰዎች በዘር እየተለዩ እየተመረጡ የፈንጅ ማምከኛ እንደሆኑ ተረጋገጠ ።ምሽግ ውስጥ ሆነው የሚዋጉት ወታደሮች ብዙም ሳይቆይ እውነታው ግልጽ ሆነላቸው። የፖለቲካ መሪዎች ጉድ እንዳደረጓቸው፣እንዳታለሏቸውና የጦር መሪዎቻቸውም አሳልፈው እንደሰጧቸው ተረዱ። … ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች “ደስ እያላቸውና በፈቃደኝነት” ለጦርነት የዘመቱት ወድያውኑ ዘመቻው አንድን ቡድን የበላይነት ለመጠበቅ እንደሆነ ተረዱ ። ህዝቡም አወቀ ።የጦርነቱ ነጋሪት ጎሳሚዎች ጦርነት መኖር ያለበት “ተፈጥሮአዊ ግዴታ” ነው ብለው ያመኑ ይመስሉ ነበር ። BBC በተባለው የዜና ማሰራጫ “Human Wave ” በተባለው የጦርነት ስልት ያለቁትን ብሄሮች ስንሰማ የወያኔ መሪዎች ፊል ዊልያምስ የተባሉት ደራሲ “ማህበራዊ ዳርዊኒዝም” ጦርነት የተወሰኑ ዘሮችን ፣ ብሄሮችን ለማስወገድ” የሚያስችል ትክክለኛ መሣሪያ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ተከታዮች እንደነበሩ ተረድተናል ። … ዛሬስ እነዚህ ሰዎች ምን አድርጉ እያሉን ነው? የምን ነጋሪት እየጎሰሙብን ነው? የማሰብ ችሎታ ያላቸው ሰዎች . . . እንዲህ ያለውን እብደት ሊቀበሉ ይችላሉ ወይ? በእርግጥ ዛሬ ሌላ ቀን ነው ። በእርግጥ ልንማረው የሚገባ አንድ ግልጽ ትምህርት አለ። ባለፉት አመታትት የታዩት አሳዛኝ ሁኔታዎች እንዳይደገሙ ከተፈለገ ሊሳሳቱ ከሚችሉት የሰው ልጆች ፍልስፍናዎች ይበልጥ አስተማማኝ የሆነ መመሪያ ያስፈልገናል። ከታሪክ መማር ። “ሰዎች ከታሪክ ሊማሩ ቢችሉ ኖሮ እንዴት ያለ ትምህርት ይገኝ ነበር! ነገር ግን በስሜታዊነትና በወገናዊነት ታውረናል። ተሞክሮ የፈነጠቀልን ብርሃን የጋን ውስጥ መብራት ሆኖብናል!”— ሳሙኤል ቴይለር ኮልሪጅ እንግሊዛዊው ባለቅኔ ሳሙኤል ኮልሪጅ በሰጠው አስተያየት እኔ እስማማለሁ ። ለአንድ የተወሰነ ዓላማ

No comments:

Post a Comment