Sunday, February 5, 2017

9 የየመን ዜጎች ዶናልድ ትረምፕ ባገዱት የጉዞ እገዳ ምክንያት ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደረገ

Yemeni
አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም
ዘጠኝ የመናዉያን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ባወጡት የጉዞ እገዳ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጋቸዉን እና ጎረቤት አገር ወደ ሆነችዉ ጅቡቲ እንዲላኩ መደረጉን አንድ የወያኔ ባለስልጣን አስታወቀ።
የመን አሜሪካ ለደህንነቴ ስጋት ናቸዉ ብላ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ከተጣለችባቸዉ ሰባት አገራት ዉስጥ አንዷ በመሆኗ እነዚሁ ተጓጓዦች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የተደረገዉ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ ቅርብ በመሆኗ እና ጅቡቲ በቀይ ባሕር ለምትዋሰነዉ የመን በ20 ማይልስ ወይም በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ አገር ስለሆነች ነዉ በማለት የወያኔዉ አፈቀላጤ ተናግረዋል።
ወደ አዲስ አበባ የተላኩበት ዋናዉ ምክንያት ተብሎ በወያኔዉ አፈቀላጤዉ ነገሬ ሌንጮ የተገለጸዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዋሽንግቶን ወደ አዲስ አበባ በረራ ስላለዉ ነዉ በማለት ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ሳያነሱ በደፈናዉ መግለጻቸዉ ታዉቋል።
የአሜሪካን ደህንነት ለመጠበቅ በሚል የሰባት አገሮችን የጉዞ እገዳ ያደረጉት ዶናልድ ትረምፕ ምን አልባትም ይኽ ዉሳኔያቸዉ ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ሊጋብዝ እንደሚችል እና በአሜሪካ ባሉ በተለያዩ የፌደራሉ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት የአሜሪካንን ሕገ መንግስት የሚጻረር ነዉ ሲሉም ይደመጣሉ።

No comments:

Post a Comment