Wednesday, November 30, 2016

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ መታሰራቸው ታወቀ

  


merera-1
ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፕሬዚደንት ዶ/ር መረራ ጉዲና
የአይን ምስክሮች እንደገለጹት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቁጥጥር ስር የዋሉት በምን እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን ዶር መረራ እንዲታሰሩ ሰሞኑን በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ ታውቋል። በአውሮፓ ህብረት ግብዣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከአትሌት ፈይሳ ለሊሳ ጋር ብራሰልስ የተገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጥሰዋል የሚል ቅስቀሳ ሲደረግባቸው ቆይቷል። ለዚህም ይቀርብ የነበረው ምክንያት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአንድ መድረክ መገናኘታቸውና ጎን ለጎን መቀመጣቸው መሆኑን መረዳት ተችሏል። ዶ/ር መረራ ጉዲና አውሮፓ የተጋበዙትም በአንድ መድረክ የተገኙትም በአውሮፓ ፓርላማ ግብዣ ሆኖ ሳለ፣ በጉዳዩ ተጠያቂ መደረጋቸውና በዚህም መወንጀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ዶ/ር መረራ ጉዲናን የያዟቸው ወገኖች ወዴት እንደወሰዷቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት ምስክርነት መንግስትን አለማስደሰቱን ለማወቅ ተችሏል። ምንጭ፦ ኢሳት

ፌዴራል ፖሊሶች በየቦታው በገፍ እየታሰሩ ነው።ቆንጅት ስጦታው



~ከኮማንድ ፖስቱ በኋላ ፌዴራል ፖሊሶች በየቦታው በገፍ እየታሰሩ ነው። በተለይ በህዝባዊ አመጹ ጊዜ ያልተኮሱ-ለመተኮስ አስበው መሳሪያቸው እምቢ ያላቸው ሁሉ፣ ፌስቡክ ላይ ጸረ ወያኔ ጽሁፎችን ሸር እና ላይክ አድርገዋል የተባሉት ሁሉ ወደ ወህኒ ወርደዋል።
~ ባሁኑ ሰዓት የትም ለመሄድ ፈቃድ ተከልክሏል። ሌላው ቢቀር ከካም ውጭ ካደሩ ከአሸባሪዎች ጋር ስትመክር ነው ያደርከው ተብሎ ወህኒ እየተወረወረ ነው።
~ከኮማንድ ፖስቱ በኋላ በአዲስ አበባ በየጊዜው ሲደረግ የነበረው የፖሊሶች ስብሰባ ቀንሷል።ምክንያቱ ደግሞ ከ50% በላይ ፌዴራል ፖሊሶች ከአዲስ አበባ ስለወጡ ነው።
~ዛሬ ቦሌ ኤርፖርት ዙሪያ ለየት ያለ ጥበቃ ነበር።



የሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተዛወሩ EthiopianReporter.com



የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ቱሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡
በኦሮሚያ ክልል አዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፊርማ ሰኞ ኅዳር 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በወጣ ደብዳቤ፣ አቶ አህመድ ቱሳ ለአምስት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሦስት ዘርፎችን በማደራጀት ሹመት ሰጡEthiopianReporter.com

    


– አቶ ሱፊያን አህመድ – የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ
– ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ – የኢንዲስትሪ ዘርፍ አስተባባሪ
– አቶ ሙክታር ከድር – የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጽሕፈት ቤታቸውን በማደራጀት አዳዲስ ሹመቶችን መስጠታቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

Tuesday, November 29, 2016

የደፈረሰው ፖለቲካችን የወያኔና የተቃዋሚዎች ስርስር የግብጽና ኤርትራ የኮማንድ ፖስት ምስረታ እቅድ በጆሮ የሰማናቸው ናቸው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)



የደፈረሰው ፖለቲካችን የወያኔና የተቃዋሚዎች ስርስር የግብጽና ኤርትራ የኮማንድ ፖስት ምስረታ እቅድ በጆሮ የሰማናቸው ናቸው::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ተልባ በጥባጯ እያለች ጎበን በጣሿ ምች የተመታችበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኣሁንም ምኑንም ሳይመልስ ምናምኑን እንዳግበሰበሰ ቀጥሏል። ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱም ግፊቱ ቀጥሏል።የሚገርመው እያሰረ እየገደለ እያፈነ እያሳደደ ያለው አካል ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ስለ ሰብዓዊ መብት ለመነጋገር ሶስት ቀን ስብሰባ የሚቀመጥበት ግርግር ምን ያህል በሕዝብ ላይ እየተቀለደ እንዳለ እያየን ሲሆን ኮማንድ ፖስቱ እየሰራ ያለው ግፍ እና በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋ ለመደገፍ ካልሆነ በቀር በፍጹ ስለ ሰብዓዊ መብት የሚቆረቆር ይገኛል ማለት ሞኝነት የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ስልጣን ኣካፍሉን ለማለት ካልሆነ በቀ ስብሰባው ከጭብጨባ የሚዘር ፋይዳ ኣይሰራም ወያኔ ተቃዋሚዎችን ተርታ የምጸበስበው አንድም ለማዘናጋት ኣሊያም አዲስ የፖለቲካ ፍጆታና ሴራ ከማለም የዘለለ ስራ የለውም። የሚገርመው ግብጽና ኤርትራ በካይሮ አሸባሪነትን የሚቆጣጠር በቀይ ባህርና ለምስራቅ ኣፍሪካ የሚያገለግል ኮማንድ ፖስት ሊመሰርቱ ነው።ይህ ኮማንድ ፖስታችው እኮ ስንቱን አስቀና ሆሆሆ…ወያኔ ጠላቶቼ የሚላቸው ሁለት ሃገራት እንኳን እንዲህ ብለው ይቅርና እንዲሁም በነጻ ወንጀል ለማሸከም ኣይቦዝንም ቢሆንም ከጀርባ ያለውንም የፖለቲካ መነባነብ ሰከን ብሎ ማዳመጥ ይበጃል ወዳጆቼ። በአንድ ጉዳይ የፈዘዘ ደንዝዞ ይቀራል። ነቃ እንበል !! እንብሰል !! አንዘናጋ !! ይህን ስል ደግሞ ወዲ ሳልሳዊ ሻእቢያና ወያኔ የተጠና ፖለቲካ ያሴራሉ ብሏል ብለህ መርዝ ምላስህን ዘርጋው አሉ:: #ምንሊክሳልሳዊ

የአማራ ህዝብ የተጋረጡበት አደጋዎች ባለ ፈርጀ ብዙ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ – ኄኖክ የሺጥ



የአማራ ህዝብ የተጋረጡበት አደጋዎች ባለ ፈርጀ ብዙ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ
1) የአማራ ህዝብን በአንድነት ለማደራጀት እና በህብረት እንዲቆም እየተደረገ ላለው ጥረት ከዚህ በፊት አማራ አይደለንም ሲሉ ያልተሰሙትን የአማራ ህዝብ ክፋይ የሆኑትን አካሎች ፥ እንደ አገው እና ቅማንት ያሉ ማህበረሰቦችን ( ህዝብ ባልወከላቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት ) አማራ አይደለንም የሚል ወያኔያዊ አጀንዳ እንዲያነሱ በማድረግ እና የአማራ ህዝብ ህብረት የነርሱ ህልውና ላይ አደጋ ሊጥል የሚችል ጠንቅ እንደሆነ በመስበክ አማራውን እንደ ቁጠባ ቤት በተርታ በመከፋፈል በአንድነት እንዳይቆም የማድረግ ስራ እና ሴራ
2) አማራን በአረንጓዴ ፥ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ አላማችን እያታለሉ ፥ አማራ የሚያምርበት ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት ፥ በኢትዮጵያዊነቱ የማይታማውን የአማራ ህዝብ ፥ ለተራ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል ብቻ ፥ የአማራ ህዝብ ስቃይ በገሃድ እየታየ « ኢትዮጵያዊነትህን እንዳትለቅ ብቻ ሳይሆን ፥ ኢትዮጵያዊነትህን ይዘህ ጥፋ» በሚል ሰበካ የአማራን ህዝብ ተክለ ሰውነት ማቀጨጭ እና ጥሪቱን መሞለጭ!
3) በኖርንበት እና ባየነው ፥ ምስክርም በምንሆንበት 25 አመት የወየኔ ዘመናት ፥ አንድም ኢትዮጵያዊ ( ከአማራ በስተቀር ) ከየትኛውም ክልል ሳይባረር ፥ አመራ ግን በዘሩ ሲባረር ፥ ስለዘሩ ሲሳደድ እና በዘሩ ምክንያት ሲገደል እያየነው ፥ ይህንን ህዝብ ለመታደግ የሚደረገውን ርብርብ በዘረኝነት በመፈረጅ ፥ ታሪክን ተገን አድርጎ ፥ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ በማይወክል መልኩ አማራ ራሱን ጨፍልቆ ፥ ከሱ በቁጥርም ይሁን በእውቀት እጅግ ባነሱ አካሎች ተወክሎ ፥ ከስራቸው እንዲንደፋደፍ ፥ ስለት እና ምልጃ እንዲያቀርብ ፥ ራሱን ክዶ ፥ በራሱ በአማራ አጋፋሪዎች በተደረገ የኤሌሎች በአለ ሲመት ላይ አክሊል አቅራቢ ፥ ምንጣፍ አንጣፊ ፥ የዙፋን እግር ወልዋይ እና ሰረገላ ገፊ እንዲሆን እየቴሰረ መሆኑ
4) የአማራ ህዝብ ከብቱን ሽጦ ፥ ደሙን ገብሮ ፥ ልጆቹን ሰውቶ የሚያደርገውን ትግል በጠራራ ፀሃይ ፥ ባልተወከሉ ታጋዮች ትግሉን ተቀምቶ ፥ ለሞቱ ስም ተሰጥቶት ፥ ለትግሉ የሃሰት ዜና ተሰርቶለት ፥ ባልዋለበት ውሎ እና ላልቆመለት አካል ቆሞ ፥ የክብር ሞቱ መነገጃ እና መወስለቻ ሆኖ እያየም ፥ ስድብ እና ክብረ ነክ የሆኑ ትችቶችን ፈርቶ ፥ ከጥቂቶች እውነት ይልቅ ለብዙሃን ነውር ገብሮ ፥ እውነቱን እያወቀ ፥ የሆነውን እያየ ፥ ሞቱን አማራ ለነፃነቱ ሲል ያደረገው እንደሆነ ያልመሰከረ እና ያልተናገረ አማራ ባለበት ዘመን መፈጠራችን እና መኖራችን
5) ከትግሉ ባሻገር ትግሁ አማራ ማንነቱን ጥያቄ አድርጎ ሲነሳ ፥ ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም በሚል የፋኖ መለከት የተቀጣጠለው ትግል ፥ በውጭ ሃገር አርባ ስም ተሰጥቶት ፥ የትግሉ አብሪ ጥይት አማራነት እንደሆነ እየታወቀ ፥ የጎጃም ገበሬ ለጎንደሩ ገበሬ መገደል ባህር ዳር ላይ ሲሞት የሞተው ጎጃሙን እና ጎንደሩን አንድ ያደረጋቸው አማራ መሆናቸው ፥ ባንድነትም ያቆማቸው ይኸው አማራነታቸው እንደሆነ ለሳር ለቅጠሉ ሳይቀር ግልፅ በሆነበት ሰዓት ፥ ይህ የአማራ ትግል ሰላም የነሳቸው ፥ ሲቻል የአማራ ህብረትን ኒዩክሊየር ቦምቦ አስመስሎ በመሳል ሳይቻል ደሞ አማራን በምክንያት በመሰነጣጠቅ ፥ ጎንደር ህብረት ፥ ጎጃም ህብረት ፥ ወሎ ህብረት ፥ ሸዋ ጅብረት እያሉ ሃይሉን ለመበታተን ፥ ገባሪነቱን ዘመን ተሽጋሪ ለማድረግ ፥ ሃይሉን ለመፈረካከስ ፥ የህብረት ክሩን ለመበጠስ ፥ የአንድነት ዋልታውን ለመከስከስ እየሄዱበት ያለው መንገድ በራሱ በአማራው ተወላጅ ሳይቀር በከፊልም ቢሆን ተቀባይነት ማግኘቱ ይመስለኛል ።
ጥያቄ አለኝ ፥ የጎንደርን አማራ በጎንደር ህብረት ፥ የጎጃሙን በጎጃም ፥ የወሎውን በወሎ ፥ የሸዋውን በሸዋ ጠቅልለን ፥ ሰብረን እና ሰንጥቀን ከጨረስን ወዲያ ፥ በሃረርጌ የሚኖሩን የወሎ አማሮችን የሃገረርጌ ወሎዬውች ፥ በጅማ የሚኖሩ የጎንደር አማሮችን የጅማ ጎንደሮች ፥ የ ወለጋ ጎጃሞች ፥ የአዲስ አበባ ሸዋዎች ብለን ሌላ የአማራ ህብረት ልንፈጥር ነው ?
አማራ እንዲበረታ አማራ በህብረት ይቁም! የአማራ ድል በአማራ ህብረት ብቻ የሚገኝ ነው! የብሄር ፖለቲካ የነገሮች ሁሉ መለኪያ በሆነበት ዘመን ፥አማራ አይደራጅ ማለት አማራን በጀርባው በኩል እንደ ማረድ ነው !
አማራ ንቃ!
ኄኖክ የሺጥላ

ልዩ ልዩ ዜናዎች – Finote Democracy- EPRP Radio – ፍካሬ ዜና ምኒሊክ ሳልሳዊ



ልዩ ልዩ ዜናዎች – – Finote Democracy- EPRP Radio – ፍካሬ ዜና
 ኢትዮጵያ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት በተለያዩ በሽታዎች ከሚቀጠፉባቸው ሀገራት ግንባር ቀደምትነቱን መያዟ ታወቀ፡፡ ከሰላሳ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ህፃናት የሚሞቱት በተቅማጥና በሳምባ ምች መሆኑም ተነግሯል፡፡ ወያኔ በየጊዜው የህፃናትና የእናቶች ሞትን መቀነስ መቻሉን ቢያቀርብም ሐቁ ግን በወሊድ የሚሞቱ ህፃናት ቁጥር በእጅጉ የጨመረ መሆኑንና ስድስተኛ ልደተቻውን ሳያከብሩ በሞት የሚነጠቁ ሕፃናትም ቁጥር እየናረ በመሄድ ላይ
እንደሆነ ታውቋል፡፡
 የተለያዩ የነዳጅ ምርቶች ማለትም ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ጋዝ በማቅረብ በኩል ግዙፍ መሆኑ የሚነገርለት የቻይናው ፔትሮቻይና የተባለ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ ማሸነፉ በይፋ ተነገረ፡፡ ይህ በዓለም ግዙፍ ከሆኑት አስሩ ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ድርጅት ከአመታት በፊት ይህንን እድል ለማግኘት ከወያኔ ቁንጮዎች ጋር ውስጥ ውስጡን ይሠራ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ኩባንያ እስካሁን ነዳጅ ያቀርብ የነበረውን ቪቶል ኦይል የተባለን የባህሬን ኩባንያ ገፍተሮ መግባቱ ቻይናና ወያኔ እጅና ጓንት መሆናቸውን የሚያሳይ እንደሆነ የፖለቲካ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡
 በአማራ ህዝብ ላይ የተጫነው ብአዴን የተባለው የ ወያኔ ቡድን፣ ተከስቶ የነበረውን ሕዝባዊ አመጽ በማጣጣል ለወልቃይት ጥያቄ የተድበሰበሰ ምላሽ በመስጠት በመጠናቀቁ ሕዝቡን ክፉኛ ያበሳጨና ጥርሱን ያስነከሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው በማንም ወገን ሳይሆን በወልቃይትና በጎንደር ሕዝብ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሆኖ ሳለ የአማራ ፕሬዚደንት ተብየው ገዱ አንዳርጋቸው ይህ ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው በትግራይ ገዥዎች ብቻ እንደሆነ መናገሩ ሕዝቡ እያካሄደ ላለው ሕዝባዊ አመጽ ነዳጅ ሆኖ እንሚያቀጣጥለው ለማወቅ ችለናል፡፡ በጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ በጎበዝ አለቆች እየተመራ ከወያኔ ነፍሰ-ገዳዮች ጋር ፍልሚውን እያደረገ እንደሚገኝ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚደርሱን ዜናዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡
 በቅሊንጦ እስር ቤት እሳት አያይዛችኋል የተባሉ 38 እስረኞች ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ተነግሯል። በክሳቸው ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከል አመጽ ማስነሳት፤ የአሸባሪ ድርጅቶች አባሎች በመሆን ሌሎች ሰዎችን መመልመል የሚሉት የተጠቀሱ ሲሆን እሳቱ ከመነሳቱ በፊትም ያልተግባቧቸውን ሰዎች ይደበድቡ እንደነበር ተጠቅሷል። በቅሊንጦ የተካሄደው የእሳት ቃጠሎ በወያኔ አገዛዝ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ አመጽ መልኩን እንዲቀይር ያደረገው እኩይ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከእሳቱ በፊት የተኩስ ድምጽ እንደተሰማ የአይን እማኞች ከመመስከራቸውም በላይ በእሳት ቃጥሎ ምክንያት ከሞቱት ዜጎች መካከል
የተወሰኑት በጥይት ተመተው እንደሞቱ የአስከሬናቸው ምርመራ አረጋግጧል።
 በጋምቤላ ታግተው የነበሩና ቪንቴጅ ኤር ራለይ በሚል ስም የሚታወቁ የትናንሽ ሲቪል አውሮፕላኖች አብራሪዎች ተለቀው ጉዟቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ የቀጠሉ መሆናቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። የወያኔ አገዛዝ ሰዎችን ያገተበት ምክንያት የአየር ወሰንን አለፈቃድ በመጣሳቸው መሆኑን ጠቅሶ ከማክሰኞ ኅዳር 13 ቀን ጀምሮ ከጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳይወጡ ያደረገ መሆኑን ገልጿል። ሰዎችን ለማስፈታት በርካታ የምዕራብ አገሮች
ዲፕሎማቶች ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ይታወሳል።
 ባለፈው ሳምንት አንዲት ኢትዮጵያዊት 3.1 ኪሎግራም የሚመዝን ወርቅና $10, 000 ዶላር ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የሌሎች አገሮች ገንዝብ ኖቶች ይዛ ወደ ህንድ ለመግባት ስትሞክር ዴልሂ የኢንድራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፈታሾች ተይዛ የታሰረች መሆኑ ተዘግቧል። የህንድ ባለስልጣኖች በሰጡት መግለጫ ግለሰቧ ከሁለት ወር በፊት ተመሳሳይ ሙከራ ስታደርግ ተይዛ በዋስ የተለቀቀች መሆኑን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት የያዘቻቸው ንብረቶች በሙሉ የተያዙ መሆናቸውንና እሷም ወደ እስር ቤት መላኳን ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄዱ የነበሩትን ሕዝባዊ አመጾች በመሸሽ በርክት ያሉ የወያኔ ባለስልጣኖች የዘረፉትን ሀብት በተለያዩ መንገዶች ሲያስወጡ የነበሩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በህንድ ባለስልጣኖች በቁጥጥር ስር የዋለችው ሴት ምናልባት ከወያኔ ባለሥልጣናት መካከል አንዷ ወይም የነሱ ተባባሪ ልትሆን ትችላለች የሚል ግምት እየተሰጠ ነው።
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
Vm
http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
00:00
R
p

To Listen PART 2: http://www.finote.org/TodayPart2.mp3
Vm
P