Saturday, October 8, 2016

የትግራይ ተወላጆች ቢሾፍቱን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ



Bishoftu, Ethiopia
በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ዛሬ (8 ኦገስት) ሙሉ በሙሉ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማረጋገጥ ችለናል።
የትግራይ ተወላጆቹ ከተማዋን ለቅቀው የወጡት በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የአካባቢው ሕዝብ ከጫፍ እስከጫፍ ነቅሎ በወውጣት እያካሀደ ባለው ሕዝባዊ አመጽ ሊመጣ ካለው አደጋ ለማምለጥ ነው ተብሏል። ህወሃት በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በከተማዋ ያሉ ሁሉ ሲቃወም የትግራይ ተወላጆች ግን ዝም ማለታቸው ሕዝቡን በእጅጉ እንዳስቆጣው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የትግራይ ተወላጆቹ ሃብት ንብረታቸውን እየጣሉ ከተማዋን ለቅቀው ወዴት እንደሄዱ የታወቀ ነገር የለም።
ላለፉት አራት ቀናት በደብረዘይት እንደ አብዛኞቹ ከተሞች የንግድ እና የስራ እንቅስቃሴ ቆሟል። ሱቆች ተዘግተዋል፣ ሕዝብም ከቤቱ አይወጣም። አልፎ አልፎ የከባድ መሳርያ ድምጽ የሚሰማ ሲሆን መንግስታዊ ተቋማት እና ከህወሃት/ኦህዴድ ጋር ንክኪ ያላቸው ተቋማት ወድመዋል።
በናዝሬት መግቢያ የምትገኘው ዱላላ ማርያም ወረዳ የህወሃት/ኦህዴድ ንብረቶች እና ጽ/ቤቶች ወድመዋል። ሊበን ጭቆላ ወረዳ አመራሩ ተነስቶ ወረዳው በሕዝብ እየተመራ ይገኛል። ወንጂ የስኳር ፋብሪካው ብቻ ሳይሆን አገዳውም ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች አረጋግጠዋል።
ከዱከም አንስቶ እስከ አገረማርያም የሚወስደው የጦር ቀጠና በመምሰሉ ምንም አይነት ተሽከርካሪ ላለፉት 6 ቀናት እንዳላዩ እማኞች በስልክ ተናግረዋል። ከደቡብ መስመር አንጻራዊ ሰላም የሚታየው በአዋሳ ከተማ ብቻ ነው።
በዲላ እና ወንዶገነት የህወሃት ባልሰልጣናት መኖርያ ቤቶች አጋይቶባቸዋል። ባለስልጣናቱ እና ከድሬዎቹ በሙሉ ከተማዎቹን እየለቀቁ ወደ አዋሳ ከተማ ገብተዋል።
በዲላ መስጊዶች እና አብያተ-ክርስትያናት በዛሬው እለት ባልታወቀ ሃይል ወድመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የህወሃት ካድሬዎች ሆን በለው የሃይማኖት ጸብ ለመቀስቀስ እንዳቃጠሉት ነው የሚናገሩት።
ደምቢዶሎ እና ምእራብ አርሲ የጦር ቀጠና ሆነው መሰንበታቸውን እና በጦርነቱ በርካታ ሰዎች ማለቃቸን የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

“… ህውሓት/ኢህአዴግ ባደረሰው አሰቃቂ እልቂት በጣም አዝነናል የሽግግር መንግስት በአፋጣኝ ይቋቋም! …”



“… ህውሓት/ኢህአዴግ ባደረሰው አሰቃቂ እልቂት በጣም አዝነናል
የሽግግር መንግስት በአፋጣኝ ይቋቋም! …”
“””””””””””””””””””””
‘ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ህውሓት ባዘጋጀው ወጥመድ መግባት የለባቸውም !’
በዳያስፖራ ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ (3ኛ) መግለጫ
27 መስከረም 2009
==========
ባሳለፈነው እሁድ (22.01.2009) ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ዜጎች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ በደማቅ ሁኔታ በመከበር ላይ በነበረው የኢሬቻ በዓል ላይ፣ ዜጎች በአፋኙ “መንግስት” ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ባዶ እጃቸውን አጣምረው በሰላማዊ መንገድ በማሰማታቸው ምክንያት፣ ሰብአዊነት በጎደለውና ጭካኔ በተሞላበት የህውሓት/ኢህአዴግ አሰቃቂ እርምጃ የብዙኃን ህይወት ተቀጥፏል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በቪኦኤ ቀርበው እንደገለፁት፣ የህውሓት/ኢህአዴግ ታጣቂዎች በፈፀሙት በዚህ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ምክንያት 678 ዜጎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ400 በላይ ሰዎች በሞትና በህይወት መካከል ይገኙ የነበረ ሲሆን ትክክለኛ የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይም ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል።
እኛ ስማችን ከታች የተዘረዘረው የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን፣ ጭካኔ በተሞላበት በዚህ አረመኔያዊ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ ማዘናችንን ለመግለፅ እንወዳለን። የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ ቃላት ያጥሩናል።
ህውሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነቱን ለማስጠበቅ ሲል በዜጎች ላይ ያለውን አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመሄድ፣ ዛሬ ህዝብን የሚያስተዳድር መንግስት ሳይሆን ህዝብን የሚያሸብር ወንበዴ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረበት ዘግናኝ እልቂት ለማየት በቅተናል። በተለይ ደግሞ ይህን የሚያደርገው ህውሓት፣ የተለያዩ የብሔር ትንኮሳዎችን እያራገበና ከመቼውም በላይ በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደና ጥላቻን እየበተነ ባለበት በዚህ ወቅት በመሆኑ ሀዘናችንን የከበደ አድርጎታል።
ቀደም ሲል ባወጣነው የጋራ መግለጫ እንደጠቀስነው፣ ህውሓት/ኢህአዴግ ከስልጣኑ ወርዶ የሽግግር መንግስት ባገሪቱ ካልተመሰረተ፣ ስልጣን ላይ በሚቆይበት እያንዳንዱ ተጨማሪ ቀን በዜጎች ላይ የባሰ እልቂትን እያስከተለና የአገሪቱን ህልውና ይበልጥ አደጋ ላይ እየጣለ መዝለቁ አይቀሬ ነው።
ህውሓት/ኢህአዴግ ከህዝብ ራሱን ነጥሎ በትምክህትና በጉልበት ረግጦ ለመግዛት የሚሞክረው አካሄድ መቼም ቢሆን ሊሳካለት እንደማይችል ተረድቶ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ቢሰራ ለሁሉም የሚበጅ ነውና በድጋሚ ለመምከርና ለመዘከር እንወዳለን።
ህውሓት/ኢህአዴግና የኢትዮጵያ ህዝብ የገቡበት ቅራኔ ከዚህ ብኋላ በሌላ በማንኛውም መንገድ ሊታረቅ የሚችል ቅራኔ ባለመሆኑ መፍትሔው የሽግግር መንግስት በመመስረት ህዝብ በነፃና ገለልተኛ ምርጫ ይሆነኛል የሚለውን ስርዓት እንዲመርጥ መንገድ ማመቻቸት ብቻና ብቻ ነው የሚለው እምነታችን አሁንም ፅኑ ነው።
ይህ እንዳለ ሆነ፣ ካለፈው ባህሪው ተነስተን ህውሓት/ኢህአዴግ በጎ ፈቃደኝነት ይኖረዋል ብለን ለማመን ስለምንቸገር፣ ይህን የማሳከት ሃላፊነቱና የዜግነት ግዴታው የተጣለው በመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ላይ መሆኑን በፅኑ እናምናለን።
በመሆኑም በመላ አገሪቱ ለነፃነቱ በጋራ እየተነሳ እንዳለው ህዝባችን፣ በተለያዩ የተቃውሚ ጎራ፣ የሲቪክ ተቋማት፣ የእምነት ተቋማት፣ እና የሙያ ማህበራት ስር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን (በተለይም በመሪነት ደረጃ የተቀመጥን ዜጎች) ጊዜያዊ ልዩነታችንን ወደጎን ብለንና የጋራ መድረክ በማዘጋጀት ሁሉንም ያቀፈና ያሳተፈ የሽግግር መንግስት የመፍጠር ሂደት ከወዲሁ እንድንጀምር በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
ከዚህ በተጓዳኝ ግልፅ ለማድረግ የምንፈልገው አንድ ነገር አለ። ይኸውም ህውሓት በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግደውና በትግራይ ህዝብ ስም ጥላቻ የሚነዛው አልበቃ ብሎት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን በማታለል ከቤት ንበረታቸው እያፈነቀለ ወደ ትግራይ ለማጓጓዝ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከታማኝ ምንጮች ለመረዳት ችለናል።
ይህንን ሴራውን ለማሳካት በትግራይ ተወላጆች ላይ ሃላፊነት የጎደለው እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ሁሉ ጥቆማዎች ደርሰውናል። ይህን የአቋም መግለጫ በምናዘጋጅበት ሰዓት አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ከኦሮሚያ ክልል መውጣት መጀመራቸውን አረጋግጠናል።
የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን በህውሓት ፕሮፓጋንዳና ሽንገላ ተታለው ለዓመታት ጎጆ ቀልሰው ከኖሩበትና ጥረው ግረው ካፈሩት ቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው፣ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው በመነጠል አፋኙና ነፍሰ በላው የህውሓት ቡድን ባዘጋጀላቸው ወጥመድ እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ እንወዳለን።
ዛሬ ለትግራይ ህዝብ ከህውሓት በላይ ሌላ ጠላት እንደሌለው እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ሊያውቀው ይገባል። በህውሓት ስር ያሉ ወሮበላዎች ለትግራይ ህዝብ ቀርቶ አብረው ለታገሉ ጓዶቻቸውና ለቤተሰቦቻቸውም ምህረት የማያውቁ አረመኔዎች መሆናቸውን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘብ ይገባል።
በሁሉም የአገሪቱ ክፍል የምትኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን ህውሓት ባዘጋጀላችሁ ወጥመድ ሳትገቡና የህውሓትን ህልም አሳክታችሁ ራሳችሁን መቋጫ ለሌለው ሰቆቃ ሳትዳርጉ በፊት፣ በያላችሁበት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ጋር በጋራ በመቆም ለነፃነታችሁ እንድትታገሉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሁሉም ነፃ ካልወጣ ማንም ነፃ ሊወጣ እንደማይችል ተገንዝበን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጎን በጋራ በመቆም ለነፃነት የሚደረገውን ትግል በያለንበት እንድንቀላቀል በድጋሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በአገሪቱ በሁሉም አቅጣጫ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣ ለዘመናት በመካከላችሁ አብረዋችሁ የኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችሁ ከማንኛውም ኃይል ሊደርስባቸው ከሚችል ጥቃት የመጠበቅ አደራ ተጥሎባችኋል።
አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ ዜጋ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወገኑ በአፈናና በጭቆና ስር የሚኖር ወንድማችሁ በመሆኑ፣ በተለይ ህውሓት ህልሙን ለማሳካት ሊፈፅምባቸው ከሚችል ደባ ለመጠበቅና ለነፃነት ትግሉ ከጎናችሁ ለማሰለፍ የዜግነት ግዴታችሁን እንደትወጡ እንማፀናለን።
በማጠቃለል በቢሾፍቱ በደረሰ አሰቃቂ እልቂት ልባችን የደማ መሆኑን በድጋሚ እየገለፅን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና በአጠቃላይ ሀዘን ላይ ለተቀመጠው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው እግዚአብሔር መፅናናቱን እንዲሰጥልን፣ የሙታንን ነፍስ በሰላም እንዲያሳርፍልን እንመኛለን።
እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎብኘን፤ አገራችንንም ይባርክልን።
አሜን!
የስም ዝርዝር
1. ህይወት ተሰማ
2. ሓረገወይኒ:ገ/ኢየሱስ
3. ሕሉፍ በርሀ
4. ሜሮን አብርሃ
5. ሲራክ ኣማረ
6. ስልጣን ኣለነ
7. በላቸው ለማ
8. በየነ ገብራይ
9. ብሩክ እንግዳ
10. ተስፋዬ መሓሪ
11. ተስፋይ ኣፅብሃ
12. ታደሰ በርሀ
13. ታደሰ ገብረእዝጊ
14. ነጋሲ በየነ
15. ናትናኤል ኣስመላሽ
16. አሰር አሉላ
17. አባይ ኪሮስ
18. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
19. ኣብራሃ በላይ
20. ኣብርሃም ኀይለ
21. ኤልያስ በየነ
22. ኪዳነ ኃይሌ
23. ኪዳነማርያም ፀጋይ
24. ካሕሳይ በርሀ
25. ዘልኣለም ንርአ
26. ዮሃንስ በርሀ
27. ዮሴፍ ብርሃነ
28. ዮናስ ሓጎስ
29. ዮናስ መብራህቱ
30. ደስታ ኣየነው
31. ገብረኪዳን ዳዊት
32. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
33. ጥላሁን አረፈ
34. የማነ ምትኩ
35. ሸዋዬ ሽፈራው
36. ደረጀ ገ/ሂወት

Friday, October 7, 2016

የወያኔው አገዛዝ ላልተወሰነ ጊዜ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሊዘጋ ነው!!!

የወያኔው አገዛዝ ላልተወሰነ ጊዜ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሊዘጋ ነው!!!

unnamed ግፈኛውን የውያኔን ሥርዓት አልሸከምም ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በአማራ እና በኦሮሞ ህዝብ ፊውታራሪነት ትግሉን ከቀጠለ ዓመታት ሊቆጠሩ ነው። ይህ ግፈኛ ሥርዓት በቢሸፍቱ የእሬቻ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ ወገኖቻችን ላይ በፈፀመው ጭፍጨፋ የመጭረሻውን ቀይ ካርድ ሊመዝ ችሏል። ይህ እኩይ ተግባር ያስቆጣው ህዝብ

Thursday, October 6, 2016

ኃይሉ ሻወል አረፉ – VOA



Hailu Shawel passed away at 80
ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት – መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡
አቶ ኃይሉ ሻወል በሰማንያ ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ ያረፉት በሕክምና ሲረዱ በነበረባት ታይላንድ መሆኑን ለቪኦኤ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አቶ ኃይሉ ሻወልን ለሕልፈት ያበቃቸው የጤና ችግር ምን እንደሆነ ለጊዜው እያጣራን ቢሆንም እራሣቸው በፃፉት መፅሐፍ ላይ እሥር ቤት ሣሉ በገጠማቸው ቅዝቃዜ ምክንያት አከርካሪያቸው ላይ ሕመም ይሰማቸው እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡
ላለፉት ሁለት ዓመታትም በብርቱ ሲታመሙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
የአቶ ኃይሉ ሻወል (ኢንጂነር)አስከሬን ነገ፤ ዓርብ አዲስ አበባ ይገባል ተብሏል።
ተጨማሪ መረጃ ባገኘን ጊዜ ይህንን ዜና እናዳብራለን፡፡ በነገ የአየር ሥርጭታችን ላይ ሥፋት ያለው ዘገባ ለማቅረብ እንጥራለን፡፡

ኢትዮጵያዊያን በቢሾፍቱ ለተጨፈጨፉ ወገኖች የሻማ ማብራት ዝግጅት አደረጉ




img_5255img_5255
ቁጥራቸው በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በትናንትናው ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በመሰባሰብ ዋይት ሃውስ ቤተመንግስት ፊት ለፊት ተገኝተው የእሬቻን በዓል ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በማክበር ላይ በነበሩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላትና ሌሎችም ታዳሚዎች ላይ በአጋዚ ጦር ጥይት የረገፉትን ወገኖች በማሰብ የጸሎትና የሻማ ማብራት ዝግጅት አድርገዋል። በዝግጅቱ ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊም ሐይማኖት፣ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የተወከሉ አባቶች ልብ የሚነካ፣ የሚያበረታታና የሚያጽናና መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ጎልቶና ደምቆ የታየበት ከመሆኑም በላይ የህዝቡ ጠላት ወያኔ ብቻ መሆኑ ከተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች በተላለፈው መልክት ተገልጿል። በተለይም የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ድርና ማግ መሆናቸውና እንደማይነጣጠሉ እንዲሁም አንዱ ከሌለ ሌላው እንደማይኖር የተረጋገጠበትና የታየበት መድረክ ነበር። (ስለዝግጅቱ የሚያሳዩ ተጨማሪ ፍቶግራፎች እንለቃለን

እሬቻ ለምን ቁጣ አስነሳ!









ከአማራ ክልል በሁለት መክና ሞልቶ እሬቻን ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጋር እናከብራለን ብሎ ይመጣሉ። ብሾፍቱ ወይም ደብሬዜይት እንደደረሱ የአባ ጌዳ ጽuፈት ቤት ይሄዱና አቶ በዬና ስንበቶን አናግሮ አላማቸዉንም ይነግሩአቸዋል። እሳቸዉም በደስታ ይቀበሉአቸዋል።
የወያኔ አንጀት አረረ፣ ቁጣቸዉንም በአቶ በዬና ሰንቤቶ ላይ አወረዱ። ኦሮሞና አማራ ደግሞ ከመቼ ወድህ ነዉ እሬቻን አብሮ የምያከብሩት አሉአቸዉ። እሳቸዉም ዛሬም ብንጀምር አልረፈደም አሉአቸዉ።
እነዝህ ሰዎች እሬቻ ላይ እንዳይገኙ፤ ከተገኙም ደግሞ ንግግር እንዳያደርጉ በማለት ወያነዎች ጥብቅ ትእዛዝ ሰጡ። አቶ በየናም ይህ የማህበረስብ ጉዳይ እንጅ መንግስትን የምመለከት አይደላም። ስለዝህ የህዝባችን ሀዘን የነሱ ሀዘን ስለሆኔ በደስታችንም ግዜ ከኛ ጋር ተደስቶ ብሄዱ ደስ ይለናል እንጅ ቅር አይለንም እያሉ ይከራከራሉ።

ይሄዳሉ፤ አይሄዱም ንግግር ያደርጋሉ አያደርጉም በምለዉ ጭቅጭቅ ረጅም ግዜ ሄዴ። ቀሮ ደግሞ በሳቸዉ መዘግዬት ምክንያት down down woyane, down down TPLF ማለት ጀመሬ። በስተመጨረሻም እንዳያችሁት፤ በግትርነቱ፤ በጭካነዉ በክፋቱ በአስለቃሽ ጭስ አይናችዉ አዉሮ ጥይት አርከፈከፉባቸዉ፤ ግማሹን ገደል ዉስጥ ጨመሩአቸዉ፤ ግማሹን ሀይቅ ዉስጥ ጣሉአችዉ።
ታድያ የሀዉዘን ጭፍጨፋ ና የብሾፍቱ ጭፍጨፋ ምን ይለየዋል



Image result for irreecha oromo

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች – ፖሊስ እና ሰራዊቱ በሕዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋል (ክንፉ አሰፋ)  



Addis Ababa protest
በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የሕወሃት ቁንጮዎች ትእቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከሕዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል። አብዛኛው የፖሊስ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ “ሕዝብ ላይ አልተኩስም” ማለታቸው የህወሃት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል።
አዲስ አበባ ተቆላልፋለች። በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገባም የሚወጣም የለም። መንገዶች በሙሉ ተዘጋግተዋል። ስልክ እና ኢንተርኔት ጠፍቷል።
በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች ሰኞ መስከረም 23 ቀን የተጀመረውን ሕዝባዊ አመጽ ለማዳፈን በህወሃት የተወሰደው የአፈሳ እርምጃ አመጹን አላቆመውም። ሰኞ ማምሻውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዘጎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ በወሰዳቸው ሳብያ አመጹ በዛሬው እለት ተባብሶ ቀጥሏል። የአካባቢ ፖሊሶችም ከሕዝብ ጋር በመሆን በአመመጹ እየተሳተፉ በመሆኑ የስራአቱን ቁንጮዎች ጭንቀት ውስጥ ከቷቸዋል።
ሰበታ ላይ የነበረው የቱርክ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የሃይል ማመንጫ ኩባንያ በትናንትናው እለት መውደሙን ሮይተርስ ከስፍራው ዘግቧል። በሆለታ በነበረው አመጽ ሚስ ሻሮን ሬይ የተባለች አሜሪካው የግብርና ኤክፐርት መገደልዋንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቦ ነበር። ይህ ዜና በአለም የመገናኛ ብዙሃን ከተሰማ በኋላ ህወሃት የስልክ እና የኢንተርነት አገልሎት እንዲቋረጥ አድርጓል። የአመጹ ዜና ወደ ሌሎች እንዳይሰራጭ ታቅዶ የተደረገው ይህ ድርጊታቸው የህዝብን ቁጣ እያበረታው መጥቶ ካድሬዎችን እየለቀሙ መምታት እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርጓል።
ሕዝብ በጋራ ተነስቶ የህወሃት ተላላኪዎችን እያስጠነቀቀ ሲሆን እንቢ ያሉት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገናል። የወንጂ ስኳር ፍብሪካ ከፉተኛ ቃጠሎ የደረሰበት ሲሆን፣ ኩሪፉቱ የሼክ አላዓሙዲን የከብት ማድለቢያ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። በቀርሳ ወረዳ አንድ የህወሃት ተላላኪ በህዝብ ተገድሏል፣ በሆሮ ጉድሩ እና በጉጂም የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ላይ ሕዝብ እርምጃ ወስዶባቸዋል። በድሬ ዳዋ ዲፖ ጋዝ ስቴሽን ቤሳት ጋይቷል።
የናይጄሪያዊው ኪሎ ዲንጎቴ ንብረት የነበረው ዲንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በህዝባዊ አመጽ መውደሙን የአፍሪካ ሜድያ ኔትወርክ ዘግቧል። ጉጂ ዞን ያለው የሼክ አላሙዲን የወርቅ ማእድን በትላንትናው እለት መውደሙን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ዘግበዋል።
ባዶ እጁን እየወጣ ሲገደል የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ራሱን ራሱን የሚከላከልበት መሳርያ እየያዘ መውጣቱን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአለም ገና ዳሽን ባንክ እና ከገዥው ፓርቲ ጋር ንክኪ ያላቸው መኪናዎች ተቃጥለዋል።
በአርሲ፣ በመቱ እና በጂማ በተማሪዎች የተቀሰቀሰው አመጽ እንደቀጠለ ነው። የጅማ ወህኒ ቤት ተቃጥሎ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ የተደረገው ትላንት ምሽት ላይ ነበር።
አዲስ አበባ ከእሬቻው እልቂት በኋላ የሙት ከተማ መስላለች። የንግድ እንቀስቃሴ በሙሉ ቆሟል። ሱቆች ዝግ ናቸው፣ የህዝብ ትራንስፖርትም የለም። መርካቶም ጸጥ-ረጭ እንዳለች ነው። በዛሬው እለት ታክሲ በከተማዋ ባለመኖሩ አብዛኛው ሰው ስራ አልገባም። ከተወሰኑ የግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ተወስኗል። አንዳንድ የግል ት/ቤቶች ወላጆችንን ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት እንዳይልኩ እየመከሩ ይገኛሉ።
ለአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ያደረገው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው። ሌላዎቹ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪ ገብቶ የመማሩ ጉዳይ የሚታሰብ አይደለም።
በደቡብ ወደ ሻሸመኔ እና ወደ አዋሳ የሚወስደው መንገድ እሁድ ጀምሮ ዝግ ነው። በሰሜን ሱልልታ፣ ለገዳዲ፣ ቦሌ ቡልቡላ፤ በም እራብ በአስኮ፣ በቡራዩ፣ ሰበታ፣ አለምገና፣ ብስራተ-ገብሬል፣ አየር ጤና፣ ወልሶ፣ ወደ ሆሳዕና እና ጅማ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል። በዚያ የሚተላለፍ ተሽከርካሪ ቢገኝ የድንጋይ ናዳ ይወርድበታል።
አጋዚ ይህ ሕዝባዊ አመጽ ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነበት አዲስ አበባን ብቻ ከብቦ እየጠበቀ፣ ንጹሃን ዜጋን በማፈስ ስራ ላይ ተጠምዷል።
ህወሃት በአማራው ሕዝብ ላይ በይፋ ያወጀው ጦርነት አልተሳካም። ራሱን ከመከላከል አልፎ አካባቢውን ከአጋዚ ነጻ እይደረገ ይገኛል። በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር ነጻ ወጥተዋል። የባህርዳር ዩንቨርስቲ እስካሁን እንደተከበበ ነው። የኮሶበር ህዝብ የዳሽን ቢራን ጭኖ የነበረ ከባድ መኪና ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።
በባህር ዳር ወጣቶችን ሲያሰቃይ የነበረ የማንኩሳ ተወላጅ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ተገድሎ መገኘቱ በማህበራዊ ድረ-ገጽ ተዘግቧል።
የህወሃት ባለስልጣናት አሸንዳን በርችት፣ እሬቻን በጥይት ካስተናገዱ በኋላ በወገን ላይ በደረሰው አሰቃቂ እልቂት መላው የአኢትይኦጵያ ህዝብ ብሄራዊ ሃዘን ላይ ነበር።
ብሄራው ሃዘን ላይ የነበረው ህዝብ ወደ ብሀራዊ አመጽ የገባ ይመስላል። ሰላማዊ ሕዝብን እንደ ግራዚያኒ፣ እንደ ሞሶሎኒ በጥይት እና በመርዝ ጭስ ከጨረሱ በኋላ በቴሌቭዥን ወጥተው አዝነናል እያሉ፣ ቁስልን የባሰ ሲነካኩበት ከዚህ ውጭ አማራጭ የለም። ሕወሃቶች ይልቁንም ለራሳቸው ይዘኑ። ሰላማዊውን ህዝብ እየጨረሱ ያሉት ሁሉ በተራቸው የሚያለቅሱበት ግዜ ሩቅ አይደለም። በደም የታጠበ እጃቸው ገና ሳታደርቅ በቴሌቭዥን ወጥተው በሟች አጽም ላይ መቀለዳቸው ሳያንስ በተለመደ የሽብርተኞች ዲስኩር ህዝብ ላይ እጅ መቀሰር ድፍረት ነው።
ግዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል እንጂ እነዚህ ነብሰ-ገዳዮች የእያንዳንዱ ነብስ ዋጋ መክፈላቸው አይቀሬ ነው።
የቢሾፍቱው ግድያ የህወሃት “ጥልቅ ተሃድሶ” ጅማሬ መሆኑ ነው። ግን ህዝብን እየረገጡ ብዙ ሊዘልቁ አይችሉም። ፍም እሳት የሆነ የአመጽ ትውልድ ተፈጥሯል። እነሱ ባሰሩ እና በገደሉ ቁጥር ሚሊዮን ሆኖ የሚነሳ ትውልድ። ምንም ነገር ሳይዝ በድምጹ ብቻ የሚያስፈራ ትውልድ። ህዝብን ጠላት አድርጎ ለመግዛት የሚሞክር ስርዓት ይህንን ሁሉ ህዝብ ከቶውንም ገድሎ ሊጨርስ አይችልም።