Friday, September 23, 2016

የመምህራን ተቃውሞ በማስጠንቀቂያ በከባድ ትችትና በእንቅልፍ ታጅቦ ቀጥሏል።  


Minilik Salsawi's photo.
የመምህራን ተቃውሞ በማስጠንቀቂያ በከባድ ትችትና በእንቅልፍ ታጅቦ ቀጥሏል።
#Ethiopia #EthiopiaTeachers #EthiopiaProtests #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኣዲስ ኣበባና በኣንዳንድ ክልሎች የሚካሄዱ የወያኔ መጭው ያስፈራኛል ለመምህራን የሚሰጥ ስልጠና ቀመስ የሆነ ስብሰባ በተቃውሞ እየታሸ መምሕራን ለወያኔ ኣገዛዝ በሚሰጡት ማስጠንቀቂያና የሰላ ትችት ታቦ መዋሉ ሲታወቅ በተወሰኑ ኣደራሾች የመድረክ መሪዎችን ያስደነገጡ ቡድናዊ ተቃውሞዎች ተነስተው እንደነበር ተጠቁሟል።
ከኣዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስንጀምር በዛሬው እለት የዩንቨርስቲው መምህራን መስከረም 12 2009 ዓ።ም በዋነኝነት ያነሷቸው ሦሰት ጉዳዬች፥፡
* ኦሮምኛ እንደ አንድ የቋንቋ ትምህርት በአዲስ አበባ ከተማ እና በአማራ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መስጠት እንዲጀመር ጠይቀዋል፥፥
* 1 ለ 5 የተባለው አደረጃጀት የዩኒቨርስቲውን የመማር ማስተማር ሂደት ወደ ሗላ እየጎተተ መሆኑን አስረድተዋል፥፥
* የዩኒቨርስቲው ከማንኛውም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ የመሆን መሠረታዊ መርህ እንዲከበር ጠይቀዋል።
Minilik Salsawi's photo.
በደብረ ብርሃን ከተደረጉ የመምህራን ስልጣናዊ ስብሰባዎች ኣብዛኛዎቹ እየተበተኑ ሲሆን በኣንዱ ኣደራሽ ግን ኣንዲት እንስት መምህር በሰጠችው ኣስተያየት የተነሳ የመድረኩ መሪዎች በእምባ ታጅበው ስብሰባውን መበተናቸውን ከተሳታፊዎች የተላከ መረጃ ጠቁሟል፤ ዝርዝሩ ከዚህ ሊንክ ይገኛል። http://www.mereja.com/amharic/514976
Minilik Salsawi's photo.
በኣዲስ አበባ ኣንሰበሰብም ያሉ በገርጂ በኣዲሱ ገበያ በመካኒሳ በኣራዳ ኣከባቢ ያሉ መምህራን ከሰዓት በኋላ ያለው የኣበል ክፍያ እንደሚቆረጥ ቢነገራቸውም የሙሉ ቀኑንም ውሰዱት ኣንፈልግም በማለት ኣተካራ ገጥመው ሳይስማሙ የከሰዓት በኃላው ስብሰባ መበተኑ ታውቋል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቡድን እንዲወያዩ የተደረጉ መምህራን የጋራ ኣቋም በመያዝ የመድረኩን መሪዎች ግራ ኣጋብተው ኣሳፍረው ዝም ኣሰኝነዋል። ሁለት ሺህ መምህራን ኣበል ኣልተከፈላቸውም። የሚለው መረጃ መውጣቱን ተከትለው ድሮም ኣገዛዙ ኣጭበርባሪ ነው የከፈሉንም በተዘዋዋሪ ይወስዱታል በማለት መምህራኑ ተናግረዋል።ከኣበል ጋር በተያያዘ ከባድ ፍጥጫ መጀመሩ ሲታወቅ መምህራኑ ለወያኔ የሚሆን መልስ ኣናጣም
በማለት በግልጽ ዝተዋል።
Minilik Salsawi's photo.
በቦሌ ኮሚኒቲ ስኩል በተካሄደው ስብሰባ ስብሰባው ኣሰልቺ ከመሆኑ የመጣ ኣብዛኛው መምህራን በተለይ ሴቶቹ ከመተኛት ኣልፈው ሲያንኮራፉ እንደነበር የሚናገሩት ተሳታፊዎች በኣብዛናው መድረክ ወያኔ ሙድ መያዣ መሆኑንና ከልቡ ስብሰባውን የሚከታተል እንደሌለ ታውቋል፤ የመድረኩ መሪዎች በድካም ሲንገላጀጁ የተከፈተው የኣዲስ ኣበባ መስተዳደር የትምህርት ቢሮ የፕላዝማ ቲቪ ስርጭት ላይ እንደተለመደው የቀድሞ መንግስታትን በማጣጣል ስለ ወያኔ ጻድቅነት ሊሰብኩ ማንም ኣዳማጭ ባለመኖሩ እንዲዘጋ መደረጉ ታውቋል። እንዲሁም መምህራኑ ለምሳ ከወጡ በኋላ ኣንገባም በማለት መሰላቸታቸውን ኣሳይተዋል።
=============================
ይቀጥላል።

አቶ ጁኔዲን ሳዶ ለመጀመሪያ ጊዜ ህወሓት ላይ ቦምብ ወረወረ።



Image result for junedin sado
አቶ ጁኔዲን ሳዶ
አቶ ጁኔዲን ሳዶ ለመጀመሪያ ጊዜ ህወሓት ላይ ቦምብ ወረወረ። #VOAafaanOromoo
“የኦሮሞ ህዝብ ይህ ስርዓት የኛ ስርዓት አይደለም እያለ ሲጮህ አሳምኜ እንዲቀበሉ ማድረጌ የኦሮሞን ህዝብ እጅና እግሩን አስሬ እሳት ውስጥ እንደጨመርኩ ይሰማኛል፣ ይህን በማድረጌ የኦሮሞን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
ኦህዴድ ስልጣን የለውም፣ የራሱ አጀንዳ የለውም፣ የኦህዴድ ፕሮግራም የተፃፈው በህወሓት ነው። የኦህዴድ ፕሮግራም የህወሓት ፕሮግራም ኦሮሚኛ ቅጂ/version ነው። የኦሮሞ ጥያቄ በኦህዴድ ሊፈታ አይችልም። ማስተር ፕላን የኦህዴድ አይደለም።
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደር ነው። የኦሮሞ ጥያቄ የሀገር ባለቤትነት ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ጥያቄ የነፃነት ጥያቄ ነው።
ግንዱን ትቶ ቅርንጫፎቹን ማራገፍ ፋይዳ የለውም። ችግሩ ያለው ግንዱ ላይ ነው። የህወሓት ስርዓት መወገድ አለበት።”

Thursday, September 22, 2016

ከእኛ በላይ ፉጨት ….. አፍ ማሞጥሞጥ! ከናሆም ግርማ


ከእኛ በላይ ፉጨት ….. አፍ ማሞጥሞጥ! ከናሆም ግርማ

… ጅብ ብዙ ወለደች አሉ። ታዲያ ልጆችዋን አስቀድማ ስትጓዝ አንዳቸውም ሳይቀሩ ያነክሳል በሁኔታው በጣም አዝና ‘’ አያችሁ ልጆች ሁላችሁም ታነክሳላችሁ እናም ከእንግዲህ አረማመድ ከእኔ መማር አለባችሁ’’  ብላ ከፊታቸው ቀድማ ልታሳያቸው ሞከረች። ከእነርሱ በባሰ ሁኔታ ማነከሷን ያዩ ልጆች ….. ‘’ በነገርሽን ይበቃ ነበር’’ አሏት አሉ።
በዚህ በምኖርበት የምዕራቡ አገር ተወላጅ የሆነ አንድ ወዳጄ አንድ ቀን ‘’ለምንድን ነው ከሁሉም ስሞቻችሁ ጎን ’’ዲሞክራሲያዊ የሚል ቃልን የምታስቀድሙት ብሎ ይሽው እስከዛሬ ልመልሰው ያልቻልኩትን ጥያቄ እንደጠየቀኝ አስታውሳለሁ። አብዮታዊ
ዲሞክራሲያዊ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሀዊ፣ ዲሞክራሲያዊ… ኧረ ስንቱ በስሙ ውስጥ ካለው ትርጓሜ እና ተግባራዊነቱ አንፃር በአለም ከመጨረሻዎቹ አስር አገራት አንዱ ሆነን ሳለን የሀገራችን ፓስፓርት /passport/ እንኳን ሳይቀር በፊቱ ገፅ ላይ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ተብሎ መገሸሩ እጅግ አስገራሚም አሳፋሪም ነው።
ከእኛ በላይ ፉጨት አፍን ማሞጥሞጥ ነው እንዲሉ ከክፋታቸው ይልቅ በጎነታቸውን ያጎላላቸው ይመስል ዛሬ የኢትዮጵያን የመገናኛ ብዙሀን ዜና ትእግስቱ ኖሮት ለአስር ደቂቃ ያደመጠ አንድ ሰው ሰላሳ ወዳጆቹን በየ እስርቤትና በየመቃብሩ እንዳልሸኘ ሁሉ ሰላሳ ግዜ ዲሞክራሲያዊ ውይይይ፣ ዲሞክራሲያዊ ልማት፣ ዲሞክራሲያዊ ትግል፣ ዲሞክራሲያዊ ምክክር፣ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ….. ወዘተ የሚሉ ቃላትን መስማቱ አይቀሬ ነው ሌላው ቀርቶ 95 ሚሊዮን ህዝብን ይወክላል ብለው በሚዘምሩት ብሄራዊ መዝሙር ውስጥ እነ ዲሞክራሲ እነ ፍትህና የህዝብ ክብር የተሰኙ ቃላቶች ተሰልፈው ሲዜሙ ምን ያህል ወያኔ በዜማ እና በአሽሙር እያላገጠበት መሆኑን መረዳት ይቻላል።
በአሜሪካን የሚገኘው የአልበርት አነስታይን ተቋም በየወቅቱ የዲሞክራሲን ፅንሰ ሀሳብ በተለይ ሰሶስተኛው ዓለም አገሮች ከአምባ ገነንነት ወደ ዲሞክራሲ ሽግግር በሚል በተለታዩ ጊዜ የፅንሰ ሀሳብ ንድፎችን እየነደፈ ያስነብባል። እናም ታዲያ እ.ኤ.አ በሜይ 2010 በአራተኛ ህትመቱ ላይ በተለይ በአለም ታሪክ የሰው ልጆችን በደቦ በመግደል ወደር ያልተገኘለትን ጨካኙን ሂትለር ግራዚያኒን ጠቅሶ ሰውዬው ሰላም ነፃነትና ፍትህ የተሰኙ ቃላቶችን በንግግሩ ውስጥ በመጠቀም ወደር ያልተገኘለት እንደነበረ ያስነብበናል።
ታዋቂዋ የእንግሊዝ ገጣሚና አክቲቪስት አላይስ አስዋርድ /Alice osward/ ደግሞ ዲሞክራሲን በመልካም ዝናብ ትመስለዋለች። በተመጠነ ጠብታ፣ በሁሉም ስፍራ በእኩልነት ከላይ የሚወርድ ቢመስልም በጎ ሀገራት በሌሉበት ሀገራት ላይ ስሙ ብቻ ስለሚገን ጎርፍ ሆኖ ብዙሀኑን ጠራርጎ መጨረሱ አይቀሬ ነው ትለናለች።
ታዲያ ዛሬ ሀሳብን ለምን ተናገርክ ተብሎ በየጎዳና በጥይት የሚቆላው ወገናችን የተፃረረው የትኛው ዲሞክራሲ ህገ መንግስት እንደሆነ ከቶም ሊገባን አልቻለም። ምክርና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው እንዲሉ የዛሬው መንግስት ተብዬው ምክሩንም ቡጢውንም እራሱ እየሰጠ ዲሞክራሲ ዘንቦልሀልና እምልህን ብቻ አድምጥ ብሎ በግድያና በእስር ጎርፍ መጥረጉ በእጅግ ያሳዝናል።
መቼም የወያኔ ዲሞክራሲ ቃሉ ሲፈታ ከሰሙ ይልቅ ወርቁ ይልቃልና መንገድ በተቆፈረለት ጉድጓድ በተቀለሰለት መንገድ፣ በተማሰለት ቦይ መፍሰስ ብቻ ግድ ሆነ። በመሆኑም በቃኝ ያለ ህዝብ፣ ተበደልኩ ያለ ወገን ቀለቡ ጥይት እንጂ ከቶም ሰሚ ጆሮ አይደለም። ዲሞክራሲ ለወያኔ፣ ነፃነት ለህወሀት ሰሙ ነው እንጂ ወርቁ እኔ ያልኩትን ተቀበል፣ እኔ ያልኩህን ስማ፣ ያለ እኔ ማንም አያውቅልህም ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው። የአገዛዙ ተጠቃሚና ባለ ካዝናዎች እንደ መሪያቸው የሚያነክሱና ራስ ወዳዶች የራሱ ብሄር ዘሮች መሆናቸው እንኳንስ ሰፊው ህዝን አለም ሁሉ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
ለአንድ ሀገር ማንነቱ በውስጡ ያለው ህዝብ ነው። ሀገር ያለ ህዝብ ህዝብ ደግሞ ያለሀገር አይኖርም። በመሆኑም የአንድ ሀገር ምሉእነት አገሩቷ በእኩልነት የሁሉም መሆን የቻለች ጊዜ ብቻ ነው። ወያኔ የመረጠውን ዘርና የተመቸውን አካል ብቻ ይዞ አገርን አስተዳድራለሁ ሊለን አይችልም። መሆኑም በዲሞክራሲ ስም ብቻ ሰፊውን ህዝብ የሚበላ በልቶም የሚጨርስ የአገዳ ትል እንጂ ከቶም ለህዝባችን የሚበጅ መንግስት እንዳልሆነ ልብ ሊሉ ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች


በጎንደር መስቀል አደባባይ ደመራ እንዳይከበር ታገደ፤



በጎንደር መስቀል አደባባይ ደመራ እንዳይከበር ታገደ፤
የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በወያኔዎች ትእዛዝ በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል በዚህ ዓመት እንዲዘለል ወሰነ።
ሀገረ ስብከቱ በአደባባይ ይከበር የነበረውን የደመራ በዓል በየአጥቢያዎች ብቻ እንዲከበር ዛሬ መመሪያ አስተላልፏል። በጎንደር በደማቅ ከሚከበሩ በአላት አንዱ የመስቀል ወይም የደመራ በአል ነው።
Image result for Gonder Demera celebration

Wednesday, September 21, 2016

በጎንደር እና በባህር ዳር የተጠራውን የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ተከትሎ ለንግድ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።



በጎንደር እና በባህር ዳር የተጠራውን የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ተከትሎ ለንግድ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።
በጎንደር እና በባህር ዳር የተጠራውን የቤት ውስጥ መቀመጥ ኣድማ ከኣቅሙ በላይ የሆነበት የወያኔው ኣገዛዝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በሚል በየንግድ ድርጅቶች በተዘጎ በሮቻቸው ላይ ማስታወቂያ መለጠፉንና ድርጅቶን ካልከፈቱ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሰምቷል።
የሕዝብ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ በጉልበት ለመቀልበስ የሚሮጠው የወያኔ ኣገዛዝ ሕዝቡ ትእግስቱ ስላለቀ ስልጣኑን እንዲለቅ በተደጋጋሚ ኣድማዎች ተቃውሞውን እየገለጽ ይገኛል።የባህርዳርና የጎንደር ኣድማው ቀጥሎ ያለ ሲሆን የኣማራው ሕዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ሕወሓት ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ስልጣኑንም ለሕዝብ እንዲያስረክብ እንዲሁም የወልቃይት ምድርና ሕዝብ ማንነቱ ታውቆ በትግራይ ክልል የተነጠቀው መሬት እንዲመለስ በመታገል ላይ ይገኛል።

የኣማራ ክልል ኦዲተር ጽ/ቤት ሃላፊ በብር ሸለቆ የታሰሩ የኣማራ ወጣቶች ላይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል።  



የኣማራ ክልል ኦዲተር ጽ/ቤት ሃላፊ በብር ሸለቆ የታሰሩ የኣማራ ወጣቶች ላይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል።
ደሴ ጥላሁን ይባላል፤ የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሃላፊ ነው። ተወልዶ ያደገው ደቡብ ጎንደር ስማዳ የሚባል ቦታ ነው። ሰውየው አማራ ቢሆንም የሚሰራው ስራ ግን ትግሬዎች ከሚሰሩት አይተናነስም። የመ/ቤቱን መኪና ለአጋዚዎች መበስጠት የባ/ዳርን ወጣት እያሳፈሰና እያስገደለ ይገኛል።
ከአጋዚዎች ጋር በመሆን መንግስት የሰጠውን ካላሽ መሳሪያ በመጠቀም ቤት ለቤት እየዞረ ወጣቱን የሚያሳድድ በተለይም የቀበሌ 11 ወጣቶችን ያሳሳረና ያስጨፈጨፈ ወንጀለኛ ነው። ግለሰቡ አሁንም ብርሸለቆ ተብሎ በሚጠራው የወያኔ ማጎሪያና መረሸኛ ጣቢያ ከሁሉም የጎጃም አካባቢዎች ባ/ዳርንም ጨምሮ የተያዙ ወጣቶችን ሌሊት ሌሊት እንዲሰቃዩ በማድረግና ቀን ላይ ደግሞ የፖለቲካ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ስልክ ቁጥሩ 091834 0046 ነው። ይህንን ወንጀለኛ ነፍሰ በላ ለአማራ ተቆርቋሪ ነኝ የሚል ግለሰቡ ሁሉ እንዲያውቀው ይሁን!»

ኮማንደር ውበት አለ የባህር ዳር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ የባህር ዳርን ወጣቶች የሚያሰቃየው አውሬ


ኮማንደር ውበት አለ የባህር ዳር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ የባህር ዳርን ወጣቶች የሚያሰቃየው አውሬ የቤት ለቤት አፈናው እና አፈሳው ቀጥሏል:: በተለያዮ ጣቢያዎች እስከ ሰኞ 09/01/2009 የታሰሩትን የባህር ዳር ወጣቶች ሌሊት 7:00 ስአት ይኸው ኮማንደር ውበት አለ የባህር ዳር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ በመደብደብ አስጭኖ ሰባታሚት ከሚገኜው ውሃ መብራት ከሌለው ማረሚያ ቤት አስግዟል ::
ገዳይን የማጋለጥ ዘመቻ መድረሻ ያጣ የባህር ዳር ወጣት ድምጽ ኮማንደር ውበት አለ የባህር ዳር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ ከከተማዋ ህዝብ በቀማው ብር ቀበሌ 14 ባለእግዚአብሄር አካባቢ በሰራው ዘመናዊ ባለ 1 ፎቅ መኖሪያ ቤት ሆኖ ተእዛዝ በመስጠት የከተማችን ህዝብ ያስጨፈጨፈ ያስጨረሰ ባንዳ ሲሆን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ደግሞ የከተማዋን እና አካባቢዋን ከ2000 በላይ ወጣት እያሳፈሰ በማስወሰድ ከ600 በላዬን ብርሸለቆ በማስወሰድ ከቤተሰብ እና ከጠያቂ አርቆ እያሰቃየ ያለ እና ቀሪዎችን ዲዛይን ቢሮ ጉን አጉሮ በማሰቃየት ላይ ያለ ነፍሰ በላ የህዝብ ደም ይቅር የማይለው አውሬ እና ጨካኝ ነው ::
ይህን ግለሰብ እኛ የከተማዋ ወጣቶች የምንበቀለው በሞቱት እና በመሰቃየት ላይ ባሉ የከተማችን ወጣቶች ስም መሆኑን እናሳውቃለን :: ለፍትህ ለዲሞክራሲ ለተጨቆኑት መጣሁ ያለው መንግስት ይሄው ዛሬ በአደባባይ እየቀጠፈን ነው :: ክብር ለሰማእቱ መፈታት ለታሰሩት ገዳይን አስገዳይን የማጋለጥ ዘመቻው በመረጃና በማስረጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል መደረሻ ያጣው የባህር ዳር ወጣት በተለያዮ ጣቢያዎች እስከ ሰኞ 09/01/2009 የታሰሩትን የባህር ዳር ወጣቶች ሌሊት 7:00 ስአት ይኸው ኮማንደር ውበት አለ የባህር ዳር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ በመደብደብ አስጭኖ ሰባታሚት ከሚገኜው ውሃ መብራት ከሌለው ማረሚያ ቤት አስግዟል ::