Wednesday, August 2, 2017

ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን ወደ ኋላ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ source abbay media

ታዋቂው ፖለቲከኛና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን ወደ ኋላ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ።
በዘረፋ የታሰሩ እንዲሁም ነፍስ ያጠፉ ግለሰቦች ላይ የማይፈጸም ድርጊት ዶክተር መራራ ላይ መከሰቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን ወደ ኋላ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት የማቅረቡ ርምጃ እሳቸውን በማዋረድ የደጋፊዎቻቸውን ቅስም ለመስበር ነው የሚለው የበርካቶች እምነት ነው። ርምጃው ደግሞ ቁጣን የሚቀሰቅስ መሆኑን የፖለቲካ ምሁራን ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ይዘው የቆዩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ዶክተር መራራ ጉዲና በአውሮፓ ሕብረት ግብዣ ቤልጂየም ብራስልስ መገኘታቸውን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሰሃል በሚል መታሰራቸው ሲታወስ ቆይቶ ክሱ ወደ አሸባሪነት መለወጡ ይታወቃል።
ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያስተማሩትና ከዛሬ 40 አመት በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትግል ውስጥ ተሳታፊና የለውጥና የመብት አቀንቃኝ የሆኑት ዶክተር መራራ ጉዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያለጊዜያቸው በጡረታ እንዲወጡ ያደረጋቸው ሲሆን አስፈላጊውን መመዘኛ አሟልተው የፕሮፌሰርነት ማእረግ እንደተነፈጉም ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል።
ለረዥም ጊዜ ከኖሩበት ቤት መባረራቸውንም ተከትሎ አዲስ አበባ ጫፍ ላይ ተጀምሮ ወዳላለቀ ቤት መግባታቸውን ማስታውስ ተችሏል።
ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን በካቴና ወደኋላ ታስረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 25/2009 እንደሆነም ታውቋል።
በነፍስ ማጥፋት፣በዘረፋ፣እንዲሁም በተራ ስርቆትም ሆነ በሌላ ወንጀል እንዲሁም በፖለቲካ ጭምር የታሰሩ በአብዛኛው በካቴና በማይታሰሩበት ሁኔታ እኚህን ታዋቂ ምሁርና ፖለቲከኛ በካቴና አስረው ፍርድ ቤት ያቀረቡበት ምክንያት አልታወቀም።

የአማራው ነገድ ኢትዮጵያዊ ብኩርናው ላይ መቼም ቢሆን አይደራደርም! [በወንድወሰን ተክሉ] source abbay media

ለዶ/ር አቤል ዮሴፍ መልስ የተጻፈ
[በወንድወሰን ተክሉ]
ውድ የአማራው ነገድ ሆይ ከአይሁዶቹ ታሪክ የምንማረውን እና የማንማረውን ለይተን እንወቅ
**አንድ- የዶ/ሩ የወቅቱ የነገደ አማራ አደረጃጀት ንጽጽር ከጀርመኖቹ አይሁዶች ጋር ያቀሩቡት ተወራራሽነት እና ተያያዥነት በሌላቸው ጉዳዮች የመሆኑ ፋላሲ።
በቅድመ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ያሉ አይሁዳውያን በ1880ዎቹ መገባደጃ ላይ በአሜሪካዊው አይሁድ ሄርዝል የተቃቃመውን ዓለም አቀፍ የአይሁዳውያንን ማህበር በሁለተናዊ መልኩ ከመቀላቀልና እና ተደራጅተው ከመታገል ይልቅ ከአምስት እስከ አስር ትውልዳቸው በተወለደበት “ሀገራቸው” ሆላንድ፣ሩሲያ፣ፈረንሳይ..ወዘተ ይበልጥ ይሰማቸው ነበርና ድጋፋቸው እጅግ ውስን ወይም ከእነ አካቴውም ገለልተኛ ሆኖ ይታይ እንደነበረ ግልጽ ነው።
የናዚው ሂትለር ሰይፍ ይህንን ቸልተኝነት፣ዳተኝነትና ገለልተኝነትን ጠራርጎ ሊያጠፋባቸው ያስቻለን ሁሉን አቀፍ ጥቃት/ፍጅት/በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ በመፈጸሙ ሁሉም አስበውትና አምነውበት የማያውቁትን የጽዮናዊነትን መንፈስና እምነት እንዲላበሱ በማድረግ በ1948 ለተቃቃመችው አይሁዳዊታ የእስራኤል ሀገር መመስረት የማእዘን ድንጋይ ሚናን በመጫወት ታላቅ ተጋድሎና መስዋትነትን ሊከፍሉ ችለዋል።
ይህ የእነሱ ታሪክ ነው።የአማራው ወቅታዊም ሆነ የወደፊት ህልውናዊ እጣፈንታው ከአውሮፓውያኑ አይሁዶች ቅድመ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር አንዳችም አይነት ተዛማችነትን የምንይበት ክስተት ስለመኖሩ ያየነውና የኖርነው ነገር እንደሌለ የገሃድ እውነታ ነው። አይሁዶቹ ከሁሉም በላይ ጭፍጨፋውና ጥቃቱ [In Human Discrimination ]የተፈጸመባቸው የራሳቸው በሆነው ምድር/ሀገር ሳይሆን እንደ መጤ በሚቆጥራቸው የሰው ሀገር ሲሆን በቅድመ ጭፍጨፋው ከአይሁድነታቸው ይልቅ ጀርመናዊነታቸውን፣ሆላንዳዊነታቸውን፣ፈረንሳዊነታቸውን..ወዘተ ይበልጥ የመረጡበት ሁኔታ ከአምስትና ከዚያ በላይ ትውልድ በተወለደበት ሀገር የዜግነት እና የሀገራዊ ብሔርተኝነት ስሜታቸው ማየሉ ሳይሆን ጥፋት የሚሆነው ያንን ስሜትና እምነት ባይኖራቸው ነበር እንደጥፋት የሚቆጠረው።
አይሁዶቹ በየሀገራቱ እንደዜጋ ሳይሆን እንደመጤ በዝባዥና ዘራፊ ተደርገው ታዩና ለጥቃት ተጋለጡ።በማን ሀገር? በ”ሰው” ሀገርና ምድር ማለት ነው።መገለሉ መጠቃቱና እንደመጤ መታየቱ በጀርመን ብቻ የተፈጸመ ሳይሆን እንደየ ደረጃው በተበተኑበት ምድር ሁሉ የተፈጸመ ነበር።
የነገደ አማራው ታሪክ ከአይሁዳውያን ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ክስተት ተፈጽሞበታልን?
በፍጹም።ምንም የሚያመሳስለን ክስተት በታሪካችንም ሆነ በአሁኑ ሰዓትም አልተፈጸመብንም-ሊፈጸምብንም አይችልም።
በእርግጥ ነገደ አማራ ህልውና ላለፉት 40ዓመታት በጥቃት ስር ያለ ነገድ ሲሆን የጥቃቱ መጠን እና ይዘት በዘመነ ህዋታውያን አድጎና ተለውጦ ለህልውናው መጥፋት ስጋት ደረጃ መድረሱ እውነት ነው።
ማንም ሊያስተባብለው የማይቻለው እውነታ የነገደ አማራ ህልውና በከፍተኛ አደጋ ላይ የመገኘቱ እውነታ ሲሆን ይህ ጥቃት እየተፈጸመ ያለው ግን እንደ አይሁዶቹ በሰው ሀገር እንደ መጤና ዘራፊ በሚያያቸው ህዝብና ስርዓት ሳይሆን አማራው ከ3400ዓመት በላይ እትብቱ በተቀበረበት የግል እርስቱና ሀገሩ ላይ በአቻ የሀገሩ ተወላጅ የመሆኑ እውነታን የተለያዩ ክስተቶች እንደሆኑ እናያለን።
አማራው በምድሩ ነው የተጠቃው-እየተጠቃም ያለው። አይሁዶቹ በመጤነታቸው በሰው ሀገር የተጠቁ ሲሆን አማራው ግን በራሱ ምድር በታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያን በመመሰረት፣በመጠበቅ ሂደት ውስጥ ነገዱ በሀገሪቱ ውስጥ በመሰረተው ፓለቲካዊ የስልጣን የበላይነት፣የባህል፣የቃንቃ፣የኢኮኖሚ የበላይነቱን ሚናን በእጅጉ በጠሉና በቀኑበት አቻ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሃይሎች የተከፈተበት ጥቃት እንደሆነ እናያለን።
በኢትዮጵያዊው የአማራ ነገድ ላይ የጠላትነትን መንፈስና እምነት ምንጩ የደደቢት በረሃ ተወላጁ ህወሃት እና ህወሃት ብቻ እንደሆነ ከሁሉም በፊት በጥልቅ ልንረዳውና ልናውቀው ይገባል።
የአማራው ነገድ ከህወሃት በስተቀር በሌሎች ሃይሎች ተጠቅቶ አያውቅም እያልኩ እንዳልሆነ ከግንዛቤ ሊያዝልኝ ይገባል።ምንም እንካን የኦ.ነ.ግ ኦ.ብ.ነ.ግ እና ሻእቢያ ሃይሎች ለአማራው ነገድ ፍቅር ያላቸው ሃይሎች ናቸው የሚያስብል የጥላቻ ስሜትና ቅስቀሳን የሚያደርጉ መሆናቸውን ብናውቅም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በድርጅቱ መተዳደሪያ ፕሮግራም ላይ “ጨቃኛ የአማራ ብሔር የመደብ ጠላታችን ናት”ብሎ አርቅቆና አጽድቆ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሃይል የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻውም ህወሃትና ህወሃት ብቻ እንደሆነ እናውቃለን።
ህወሃት እንደ ነገደ አማራ ኢትዮጵያዊ ነው ሃይል ነው።ግን ጸረ-አማራ ሆኖ እራሱን በአማራ ጠላትነት ያደራጀና ለመንግስትነት የበቃ ሃይል ነው። ባለው የጸረ አማራ እምነቱ እና ባለው የአናሳ ነገድ ተወላጅነቱ የተነሳ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት 81 ነገዶች ውስጥ በሕዝብ ብዛቱ በሁለተኛ ደረጃ ያለውን የአማራ ነገድ ተጽእኖ ብቻውን መመከት አይቻለውምና ሌሎችም ነገዶች ጸረ-አማራ እምነትና አመለካከት እንዲኖራቸው ለማድረግ ላለፉት ሁለት ዓስርተ ዓመታት ውስጥ በመንግስታዊ አቅሙ ከፍተኛ የሆነ ፕሮፖጋንዳን ዘራ። አማራውን እንደ ጨቃኝና በዝባዥ በማድረግ ከፍተኛ ቅስቀሳን አደረገ።ሌሎችንም በጸረ አማራነት አደራጅቶ አስታጠቀ ብሎም አማራውን እራሱም መትቶ በሌሎችም አስመታ። የህወሃት ጸረ-አማራ ፕሮፖጋንዳ ሰለባ በመሆን ጸረ አማራ አቃም ያሳዩና ብሎም ያራመዱም ይኖሩ ይሆናል ግን ጸረ አማራነታቸው የራስ ወለድ የሆነ ሳይሆን ህወሃት ወለድ በመሆኑ ለጠላትነታቸው መሰረት ያላቸው ሆነው አናያቸውም።
ይህ ክስተት የነገደ አማራውን ክስተት ከአውሮፓውያኑ አይሁዶች ክስተት ጋር ፈጽሞ የማይገናኝበትን ሂደት ያየንበት ነው።
**ሁለት-የአማራው ነገድ አደረጃጀት ከዚህ በፊት የተደራጁትን እንደነ የጎንደር ህብረት፣የጎጃም ህብረት፣የወሎ ህብረት፣የሸዋ ህብረት እና በኢትዮጵያዊነት ስር የተደራጁትን ሃይሎች እንደ የአማራው ጠላትና ጸረ-አማራዊ ሃይል አድርጎ የሚያይ ከሆነ መሰረት በሌለው ዓየር ላይ እራሱን ለአማራ ተቆርቃሪ ድርጅት አድርጎ የሚያይ መፍትሄ ያለው ተደራጅ ሃይል ሳይሆን በቅዥት አለም የሚቃዥ አሊያም የአማራውን እውነተኛ የመደራጀት ግብን ለማጨናገፍ የተነሳ ቅቡል ሃሳብ ነው ብዪ ለመናገር እችላለሁ።
እስቲ ከምን እሳቤና ፍልስፍና ነው ለአማራው ነገድ ተቆርቁሬያለሁ ብሎ እራሱን እያስተዋወቀ ያለ ግለሰብም በሉት ቡድን ወይም ድርጅት በጎንደር፣በወሎ፣በጎጃም፣በሸዋ ያሉትን አማሮች ከደረሰባቸው ጥቃት ለመታደግ ተደራጅተው የበኩላቸውን ታላቅ ተጋድሎን እና ድጋፍን እያበረከቱ ላሉት የጎንደር ህብረት፣የጎጃም ህብረት፣የሸዋ ህብረት እና የወሎ ህብረትን የአማራው ነገድ ጠላቶች ናቸው ለማለት የተቻለው?
ዶ/ር አቤል ዮሴፍ በሚያስደንቅ ድፍረት እነዚህን ድርጅቶች የወያኔን አላማ አስፈጻሚዎች ናቸው እስከማለት የወረደ አመለካከት አራምዳል። በእርግጥ እሱ አማራ ከሆነ ከአንድ አማራ በሌላው አማራ ላይ ሊሰነዘር የማይገባን ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም መፍትሄ አቅራቢ ሳይሆን ልዩነትን እና ክፍፍልን ፈጣሪና አስፋፊ ሆኖብኝ ታይቶኛል።
በአስቸካይ መቆም አለበት። ራእይ አለኝ ባይ አማራ ሌላውን አማራ ካልተከተልከኝ ይሁዳ ነህ የሚል እንጭጭ ድምዳሜን ከመስጠት መቆጠብ ይጠበቅበታል።
እንደ ባለራእይነቱ ደግሞ ራእዩን በጥራትና በትጋት ማስተማር እንጂ መጫን ከቶም አይገባውም። ከሁሉ በፊት የአማራው መደራጀት በጸረ የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች፣በጸረ ኢትዮጵያዊነትና ብሎም ለአማራዊው ሀገር ምስረታ ላይ መሰረት ያደረገ ከሆነ የሚካበው ድርጅት ከእንባይ ካብም የባሰ መሰረት የለሽ እንደሆነ ወደደም ጠላም ማወቅ አለበት። ዶ/ር አቤል ዮሴፍ በጎንደር ህብረት፣በአግ7 እና በኢትዮጵያን አንድነት ላይ ያላቸው የጠላትነት አመለካከትና አቃም ሎጂካል ሆኖ አላየሁትም-ምክንያታዊነት ያለው ሳይሆን ስሜታዊነትና ብሎም ግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ እንጂ የአማራውን ነገድ ጥቅምና ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እንዳልሆነ ልረዳ ችያለሁ።
**ሶስተኛ-ኢትዮጵያዊው የአማራ ነገድ ከአይሁዶቹ የሚማረው እውነታ ምንድነው?
በወርሃ ግንቦት 1948 እስራኤል የተባለች የአይሁድ መራሽ መንግስት በቀድሞዋ ፍልስጥኤም በተመስረተች ማግስት የዓረብ ሀገራት በአጭሩ ለመቅጨት ከየአቅጣጫ ወረራ ፈጸሙ። አዲሲታ ሀገርም ምድራችን ብለው ያመኑበትን የከነዓንን ምድር አሳልፎ ላለመስጠት ተፋለሙ። ሁሉንም መስዋእትነትን ከፍለው ምድራችን ያሉትን የከነዓንን ምድር እስራኤል በሚል መጠሪያ የሰየሙትን ሀገር ተከላከሉ። አይሁዳውያኑ በጀርመን እና አውሮፓ እያሉ እጅግ ዘግናኝ የሆነ አሰቃቂ ጥቃት ቢደርስባቸውም እራሳቸውን ለመከላከል ያደረጉት ፍልሚያ አልነበረም። ያሉት በሰው ሀገር ነውና።
ኢትዮጵያዊው አማራ ከአቻው የኦሮሞ ነገድ እና ሌሎች ጋር የኢትዮጵያ የበኩር ነገድ የሆነ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በመገንባት ደረጃ ከ3ሺህ በላይ በፈጀው ተጋድሎና ግንባታው አማራ በታሪክ ተጽፎ ያለን ታላቅ መስዋእትነትን የከፈለበት ውድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ነች።
ይህ ታላቅ ሚናውም እንደ ህወሃት ያሉትን ጠባብ ሃይሎች በነገዱ ላይ የመረረ ጥላቻና የጠላትነት መንፈስ እንዲያውጁ አድርጎዋቸዋል። አማራው ነገድ ልክ እስራኤላውያኑ በእርስታቸው ከነዓን ምድር እየተጋደሉና እየተማማቱ እንዳለው እሱም በኢትዮጵያዊነቱ በኢትዮጵያ ደረጃ ያለውን ሚና እና ድርሻውን ለግዜውም ቢሆን መንጠቅ ለቻለው የህወሃት ሃይል አሳልፎ በመስጠት ኖሮበትና ዓይቶትም ሆነ አልሞት የማያውቀውን የአማራ አነስተኛ ግዛት ሀገር እፈጥራለሁ ብሎ ሊማማት አይችልም -አይገባውምም።
እኛ የበኩር ልጆች ነን-ብኩርናችንን ደግሞ ልክ እንደ ኤሳው በምስር ወጥ እንደሸጠው እኛም ኢትዮጵያዊ ብኩርናችንን በአባት አማራ መሰል ክልላዊ ሀገር ልንሸጥ አንችልም-አይገባንምም።
[ይቀጥላል]

የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ውሎ source zahabsha

 

     


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት እንደዘገበው:  ዶ/ር መረራ ለዛሬ ሃምሌ 25/2009 ተቀጥረው የነበረው በክሱ ላይ በማስረጃ ዝርዝር የተጠቀሱ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ዝርዝር ለተከሳሽ (ዶ/ር መረራ) ማሳወቅን ወይም አለማሳወቅን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤትን ምላሽ (ትርጓሜ) ለመስማት ነበር።
ሆኖም የ19ኛ ችሎት ዳኞች ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ምላሽ እንዳላገኙ በመግለፅ፤ ፌደሬሽን ምክር ቤት ለህገመንግስት አጣሪ ኮሚቴ ትርጓሜውን እንዲሰራ የላከው ደብዳቤ ግልባጭ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።

የዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቃዎች የሚከተለውን ሃሳብ አንስተው ተከራክረዋል። ደንበኛችን ከታሰሩ 9ወር ሆኗቸዋል፤ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸው እየተከበረ አይደለም፤ ፌደሬሽን ምክር ቤት የተላከው የትርጉም ጉዳይ ፍ/ቤቱ በራሱ የሚወስነው ነገር ስለሆነ ችሎቱ ራሱ ቢወስን፤ ተመሳሳይ ወንጀሎችን የሚያየው 4ኛ ችሎት ተመሳሳይ ጉዳዮችን ችሎቱ በራሱ ነው የሚወስነው፤ ደንበኛችን ከቆዩበት ጊዜ አንፃር፣ ከእድሜያቸው፣ ካበረከቱት አስተዋፅኦ እና ከጤናቸው አኳያ ክሳቸው በክረምትም እንዲታይ እና አጭር ቀጠሮ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የዶ/ር መረራ ጠበቃ ዶ/ር ያእቆብ ሃ/ማርያም፤ “የታደሰ የጥብቅና ፈቃድ እና ውክልና እያለኝ ወህኒ ቤቱ ደንበኛዬ ዶ/ር መረራን እንዳላገኝ ከልክሎኛል። ስለሆነም ፍርድ ቤቱ በህገመንግስቱ አንቀፅ 21 መሰረት ደንበኛዬን እንዳገኝ ለወህኒ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ አመለክታለሁ።” ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
ዳኞችም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተዋል። የምስክሮች ጥበቃ አዋጅ እና በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 32 ላይ የተደነገገው ህገመንግስታዊ ትርጉሙ አሻሚ መሆኑን የገለፁት ዳኞች፤ ተከሳሽ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የመቅረብ ያለመቅረብን በተመለከተ ያቀረቡትን መቃወሚያቸውን ውድቅ ሚያደርጉ ካልሆነ በስተቀር የፌዴሬሽን ምክርቤትን ትርጓሜ መጠበቅ ግድ መሆኑን ገልፀዋል። 4ኛ ችሎት ተመሰሳሳይ ጉዳዬችን በራሱ ይሰራዋል የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ፤ ለሌሎች ችሎቶች ገዢ የሚሆነው ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው ውሳኔ ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል— ዳኞቹ። ክሱ በክረምት እንዲታይ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ የፍርድ ቤቱ የእረፍት ጊዜ በመቃረቡ እና የዛሬ አመት ክስ የተመሰረተበት መዝገብ ጉዳይ እስከ ነሃሴ 12, 2009 ስለሚያዩ፤ የእነ ዶ/ር መረራን መዝገብ በክረምት ማየት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት የፌዴሬሽን ምክርቤትን ምላሽ ለመጠባበቅ ለጥቅምት 6/2010 ቀጠሮ ሰጥተዋል። የጠበቃ ዶ/ር ያእቆብን አቤቱታ በተመለከተም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ደንበኛቸውን እንዲያገናኟቸው ትእዛዝ እንዲወጣ ተብሏል።

Monday, July 24, 2017

አቶ አርከበ እቁባይ ለህክምና ጀርመን መግባታቸው ተሰማ source zhabesha


(ዘ-ሐበሻ) የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከፍራንክፈርት እንደገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ታመው ጀርመን ፍራንክፈርት በህክምና ላይ ይገኛሉ::
አቶ አርከበ እቁባይ የህመማቸው ምንነት ያልታወቀ ሲሆን ፍራንክፈርት ኤርፖርት የሚሰሩ ወገኖች በዊልቸር ሲሄዱ እንዳዩዋቸውና ህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸውልናል::
አንዳንድ ምንጮች አቶ አርከበ የደረሰባቸው አደጋ ከደረጃ ወድቀው ነው ሲሉ ይናገራሉ::

Tuesday, July 18, 2017

ለመተራመስ መቸኮል ምንድነው? (ዮሃንስ ሰ. )

1. የዞረበት ዘመን…
• ተመራቂ ወጣቶች ሲበራከቱ፣ መፍራትና መጨነቅ ሳይሆን፣ ‘ብሩህ ዘመን እየመጣ ነው’ የሚል ስሜት
ሊፈጠርብን ይገባ ነበር። ግን፣ በዓመት ለ1 ሚሊዮን ወጣቶች፣ በየት በኩል ተጨማሪ የስራ እድል ይከፈት ይሆን?
2. የዞረበት አገር…
• ለተመራቂ ወጣቶች ብዙ ሺ የስራ እድል የሚፈጥሩ፣በዚህም ከአደጋ የሚያድኑን ኢንቨስትመንቶች
እንዲበራከቱና እንቅፋት እንዳይገጥማቸው ከመጣርና ከመዝመት ይልቅ፤ በኢንቨስትመንቶች ላይ እንዘምታለን።
በ1 ዓመት……
====================================
በዲግሪ ተመርቀው ስራ የሚፈልጉ ወጣቶች              120 ሺ
====================================
ከቴክኒክና ሙያ ተመርቀው ስራ የሚፈልጉ ወጣቶች     400 ሺ
====================================
10ኛ ክፍል አጠናቅቀው ስራ የሚፈልጉ ወጣቶች          500 ሺ
====================================
የተማሩ-የተመረቁ ስራ ፈላጊ ወጣቶች – የ1 ዓመት     ከ1 ሚሊዮን በላይ
===================================
ይሄ በየዓመቱ ነው። ከ10ኛ ክፍል እስከ ዲግሪ ድረስ የተማሩ 1 ሚሊዮን ወጣቶች፣ በየዓመቱ ስራ ይፈልጋሉ።
ስለ ትምህርትና ስለ ተመራቂዎች ስናወራ፣ የእውቀትን ሃያልነትና የወጣትነትን የስራ ብርታት እያሰብን ስሜታችን በብሩህ ተስፋና በጉጉት የተሞላ መሆን ነበረበት። እንዲሆን ማድረግም ይቻላል። ሕይወትን የሚያሻሽል፣ ድንቅ የብልፅግናና የስልጣኔ ለውጥ የምናመጣበት የስኬት ጎዳና ሊሆንልን ይችላል – ትክክለኛውን የመፍትሄ ሃሳብ ከጨበጥን።
አሁን ግን፣ የዞረበት ዘመን ሆነና፤… የተመራቂ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ የመምጣቱን ያህል፣… ሃሳባችንም ጭንቀትና ፍርሃት ያጠላበት ሆኗል (ለማሰብ ፈቃደኛ ከሆንን ማለቴ ነው)። በአንድ በኩል፣ የስራ እድልና ተስፋ ብዙም የለም። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የተማሩና የተመረቁ 1 ሚሊዮን ተጨማሪ ወጣቶች፣ በየዓመቱ!
መዘዞቹ፤… የስራ እጦትና የኑሮ ችግር፣ ቅሬታና ስደት፣ ቀውስና ትርምስ… ያስጨንቃሉ! ያስፈራሉ።
አዎ፤ “ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም” ብለን ራሳችንን ለማታለል እንሞክር ይሆናል። በእርግጥም፣ የስራ እጦትና የኑሮ ችግር፣ ለዓመታት አብረውን ኖረዋል። በዓመት 100ሺ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች፣ በጂቡቲና በሶማሊያ አቅጣጫ ሲሰደዱ አይተናል – ለዚያውም በጦርነት በምትታመሰው በየመን በኩል። ቅሬታና ቀውስም ከዓመት ዓመት ሲከማች፣ ዓመፅና ትርምስም… በየጊዜው ሲፈነዳ ተመልክተናል (የአምናው አስፈሪ ቀውስ ጭምር)። ነገር ግን፣ የእስከዛሬዎቹ ቀውሶችና ትርምሶች፣ ከወደፊቱ አደጋዎች ጋር ሲነፃፀሩ፣… ኢምንት ናቸው፤ ወይም የሕፃናት ጨዋታ ቀልለው የሚታዩ ይሆናሉ።
አዲስ የተፈጠረ ነገር አለ?
እስቲ ጥቂት መረጃዎችን ልጥቀስላችሁ።
1. የቴክኒክና ሙያ
ከ10 ዓመት በፊት፣ የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ቁጥር፣ 80ሺ ገደማ ነበር።
ዛሬ፣ 400ሺ ደርሷል – በየዓመቱ።
2. የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች
ከ20 ዓመት በፊት፣ እስከ 1990 ዓ.ም ድረስ፣… የየዓመቱ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ቁጥር፣ ከ2500 ገደማ አይበልጥም ነበር። እስከቅርብ ጊዜ ድረስ፣ ማለትም ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እንኳ፣ የዲግሪ ተመራቂዎች ቁጥር 7ሺ አይሞላም ነበር። በአስር ዓመት ውስጥ፣ በዲግሪ የሚመረቁት ወጣቶች ከ50 ሺ አይበልጡም ነበር።
በአማካይ በዓመት 5ሺ ያህል ማለት ነው!
ዛሬስ? በዓመት 120ሺ ወጣቶች ይመረቃሉ። ከ20 እጥፍ በላይ እንደሆነ ልብ በሉ።
3. የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
የዛሬ 20 ዓመት ጠቅላላ የዩኒቨርስቲ የዲግሪ ተማሪዎች ቁጥር፣ 20ሺ ነበር።
ዛሬ፣ ከ1 ሚሊዮን በላይ ነው። 50 እጥፍ ማለት ነው። ታዲያ፣ ምንም አዲስ ነገር አልተፈጠረም? ተፈጥሯል እንጂ። አዎ! የትምህርቱ ጥራት ራሱ፣ በጣም አሳሳቢ መሆኑ ባንዘነጋም፣ የተማሪዎችና የተመራቂዎች ቁጥር በሃምሳ እና በሃያ እጥፍ መጨመሩን፣… እንደ ስኬት ልናየው ይችላል። ያው፤ የመማርና የማወቅ እድል ያገኘ ወጣት በርክቷል፤.. ቁጥሩ፣ በእጅጉ ጨምሯል።
ታዲያ፣ በዚያው ልክ…
“ለትምህርቴ የሚመጥን፣ ደህና የስራ እድልና የኑሮ ደረጃ ማግኘት አለብኝ” የሚል አወንታዊ ስሜት የተላበሰ ተመራቂ ወጣትም፣ ቁጥሩ በእጅጉ ጨምሯል።
ተምሮ የተመረቀው ወጣት፣ በአብዛኛው… “ይገባኛል” ብቻ ሳይሆን፤ “ይግገባኛል” ባይ ነው። “ገብቶኛል፣ አውቄያለሁ” ብቻ ሳይሆን፣ “ለኔ ተገቢ የሆነው የስራ አይነት፣ ኑሮን የሚያሻሽል መሆን ይገባዋል” የማለት ዝንባሌን፣ ወይም ‘የይገባኛል ስሜት’ን የያዘ ነው – አብዛኛው ተመራቂ ወጣት።
በሌላ አነጋገር፣ እንደድሮው፣… ነባር የድህነት ኑሮን አሜን ብሎ ለመቀበል፣… በዝምታ ለመሸከምና እንደ እጣፈንታ እድሜውን በችጋር ለመግፋት፣ ብዙም ፈቃደኛ አይደለም። ይሄ ሁሉ፣ ጥሩ ለውጥ ነው።
ችግር የሚፈጠረው፤ ኑሮን የሚያሻሽል ዘዴና የስራ እድል ሲያጣ ነው። ያኔ፣… አንዳንዱ፣ በስሜትም ሆነ በስሌት ከስደት ጎርፍ ጋር ይቀላቀላል። አንዳንዱ፣ እዚሁ ሆኖ፣ መሰናክል በበዛበትና ተዘጋግቶ መፈናፈኛ በሚያሳጣ አገር፣ የቻለውን ያህል ለመንቀሳቀስ ይፍጨረጨራል፤ ይለፋል – ሌላ ጥሩ አማራጭ በማጣት። አንዳንዱ፣ አየርባየርም እየተቅለበለበ አልያም ከስር እየተሽሎከለከና እየሰረሰረ፣ የማምታታትና የማጭበርበር አቋራጭ መንገድ ለማግኘት ይቅበዘበዛል።
ከፊሉ ተስፋ ቆርጦ፣ ይላወሳል።
ከፊሉ ደግሞ፣ በቅሬታና በእሮሮ ተወጥሮ፣ “አንዳች ለውጥ” ይመጣ እንደሆነ ለማየት፣ ግራ ቀኝ ይወራጫል፣ ፊትና ኋላ እየተፈናጠረ ይደናበራል። ያምፃል፣ ይራበሻል።
አላወቀም እንጂ፣ ‘አንዳች ለውጥ’ ለማየት እየተደናበረ ሲራበሽ፣… ረብሻ የሚናፍቁ ነውጠኞች ይመቻቸዋል። ነውጠኞቹ፣ ሰበብ አያጡም። በዘር አልያም በሃይማኖት ማቧደን፣ በአገር አልያም በብሔርብሔረሰብ መፈክር፣ በባለስልጣንነት አልያም በተቃውሞ መሪነት፣ ሰማይ ምድሩን ያምሱታል። ባለፈው ዓመት እንዳየነው፣ የዘመናችን ቀውሶች በምን ሰበብ እንደሚጀመሩ፣ በየት አቅጣጫ ተባብሰውና ተቀጣጥለው አስፈሪ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው። በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር ምንድነው?
የተጠራቀመ የኑሮ ቅሬታ ሲበዛና ትክክለኛ የመፍትሄ ሃሳብ ሲታጣ፣ ቀውስ መፈጠሩ አይቀሬ ነው – ቀውሱን የሚለኩስ ሰበብ ሞልቷል።
እንደሚባባስና መያዣ መጨበጫ እንደሚያጣም፣ አያጠራጥርም። ውጥንቅጡ እየወጣ፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳይ እየደረሰ፣ ብዙም ሳይቆይ ወደ አስፈሪ ትርምስነት ይንደረደራል። ትክክለኛ የመፍትሄ ሃሳብ እስካላወቅን ድረስ፣ የቀውሱ መልክ እየተዘበራረቀ አገሬውን በነውጥ ለማዳረስ ከተስፋፋ በኋላ፣ ከመንታ አማራጮች ውጭ መሄጃ መንገድ ይጠፋል። ወይ፣ በበርካታ አገራት እንዳየነው፣ ‘ምንነቱ ያልታወቀ አንዳች ለውጥ ለማምጣት’ እየተደናበርን፣ አገሬው ወደለየት ትርምስና ለዓመታት መውጫ ወደሌለው እንጦሮጦስ ይወርዳል። አልያም፣… ‘ከትርምስ አድናችኋለሁ’ የሚል መንግስት፣ ከወትሮም በላይ በጉልበት የመግነን እድል ያገኛል። ይህም በበርካታ አገራት ታይቷል። ከእያንዳንዱ ቀውስና ብጥብጥ በኋላ፣ በጉልበት መግነን የሚፈልጉ ባለስልጣናት፣ እንዳሻቸው የመሆን ተጨማሪ ስልጣን ያገኛሉ – አገርን ለማረጋጋትና ከትርምስ ለማዳን።
በእርግጥም፣ ፈላስፋዋና ደራሲዋ አየን ራንድ እንደገለፀችው፣ ትክክለኛ የመፍትሄ ሃሳብ ሲጠፋ፣ መንታዎቹ የጥፋት አቅጣጫዎች… በአንድ በኩል ወደለየለት ትርምስ የሚያመራ አመፅ፣ በሌላ በኩል እየገነነ የሚሄድ መንግስት ናቸው። ደግሞስ፣ ትክክለኛ የመፍትሄ ሃሳብ ለመያዝ ያልቻለ ሰው፣ ምን ሌላ አማራጭ አለው? ያው፣ በትርምስ ዓመፅ ስንደናበር፣ በስልጣን መግነን ለሚፈልግ መንግስት እንመቸዋለን – “አገር ለማረጋጋት፣ በስልጣን መግነን ያስፈልጋል” ይላል። መንግስት በገነነ ቁጥር ደግሞ፣ የትርምስ ዓመፅ ማቀጣጠልና አገር-ምድሩን ማደበላለቅ ለሚፈልግ ነውጠኛ ይመቸዋል – “አንዳች ለውጥ ለማምጣት እንታገል” ይላል – (ምንነቱ የማይታወቅ ‘አንዳች ለውጥ’ ማለት፣ ከትርምስ ውጭ ትርጉም ባይረውም)። የትርምስ ዓመፅና ገናና መንግስት… እነዚህ ሁለቱ፣ እርስበርስ ‘ተመጋጋቢ’ ናቸው።
ለዚህም ነው፣ መፍትሄ ሃሳብ የሌለና የማይገኝ በመሰለበት በዛሬው ግራ የተጋባ ዘመን፣ መጠኑ ቢለያይም፣ በየአህጉሩ የአለማችን አገራት እየተቃወሱ የሚገኙት። አንዳንዶቹ፣ ለይቶላቸዋል – መውጫ በሚያሳጣ ትርምስ እየተጫረሱ ናቸው (ከሶማሊያ እስከ ሶሪያ፣ ከየመን እስከ ሊቢያ ወዘተ…)። አልያም መፈናፈኛ የሚያሳጣ መንግስት ከቀን ወደ ቀን እየገነነባቸው ነው – (ከግብፅ እስከ ራሺያ፣ ከቬኔዝዌላ እስከ ፊሊፒንስ… ወዘተ)። የኛ አገር፣… ሁለቱንም የጥፋት መንገዶች እየሞካከረች፣ በየጊዜው የትርምስ ዓመፅንም እየቀመሰች፣ ከዚሁ ጎን ለጎን መንግስት እየገነነ የሚመጣበትንም ጊዜ እያየች ቆይታለች። ግን፣ ገና አልለየላትም። ይሄ፣ መፅናኛ ሊሆን ይችላል። ለጊዜ ብቻ!
ለማለት የፈለግኩትን በአጭሩ ለመግለፅ ይህንን እላለሁ፡
የኑሮ ቅሬታ በበዛበትና ትክክለኛ የመፍትሄ ሃሳብ የመያዝ ፈቃደኝነት በጠፋበት ዘመን፣… በተለይ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ኋላቀርና ድሃ አገራት ውስጥ፣… በነውጠኛ የትርምስ ዓመፅ እንዲሁም እየገነነ በሚሄድ መንግስት… ወደለየለት ጥፋት የመማገድ አደጋ እንደሚያጋጥም አትጠራጠሩ።
ታዲያ፣ ከዚህ አስፈሪ አደጋ ለመዳን፣ መጣጣር የለብንም?
ትክክለኛ የመፍትሄ ሃሳብ ለመጨበጥ፣ መመርመርና ማሰብ የለብንም?
እስከዚያው፣ የአደጋውን ፍጥነትና ጉዳት ለመቀነስ፣ የቻልነውን ያህል መሞከር፣… በተለይ ደግሞ፣ እስካሁን የዘረጋናቸውን መሰናክሎችና የተከልናቸው ጋሬጣዎችን በማስወገድ፣ ዜጎች ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ መንገዱን ለመክፈት መረባረብ የለብንም?
(በተቃራኒው፣ ‘የካርቦን ልቀት’ ለመከላከል በሚል አስቂኝ የተሳከረ የቅዠት ሃሳብ፣ የፋብሪካዎችና የስራ ግንባታዎች ሲታገዱ ዜና እንሰማለን – በአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አማካኝነት)።
የተማሩ ተመራቂ ወጣቶች፣… የየራሳቸውን ሕይወት በየራሳቸው ጥረት ከማሻሻል የበለጠ አንዳችም ቅዱስ ተግባር እንደሌለ እንዲገነዘቡና፣ ለስራ ፈጠራ እንዲተጉ ማነሳሳትና ማበረታታት የለብንም?
(ተማሪዎች ለስራ አለም እንዲዘጋጁ ከማድረግ ይልቅ፣ ‘የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የሚስተካከል ቅዱስ ነገር የለም’ በሚል መፈክር፣ 8 ሚሊዮን ተማሪዎች ለወደፊት የስራ ዓለም ምንም ፋይዳ በሌለው የክረምት ስምሪት እንዲጠመዱ ‘ትልቅ’ ዘመቻ ሲካሄድ እናያለን)።
ስራ የመፍጠር ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ወጣት ተመራቂዎች፣ በጥረት አለማቸውን እንዲያሳኩ መመኘትና በነፃነት እንዲሰሩ ማበረታታት ተገቢ የመሆኑን ያህል፤… በዚያው ልክ ለተመራቂ ተማሪዎች፣ ብዙ ሺ የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ኢንቨስተሮችንም ማድነቅ፣ ማክበር፣ ያለመሰናክል በነፃነት የሚሰሩበት የሕግ የበላይነትን ለማስፋፋት መጣጣርስ የለብንም?
(በተቃራኒው፣ ኢንቨስተሮችንና የቢዝነስ ሰዎችን በጅምላ፣… ‘ኪራይ ሰብሳቢ’፣ ‘አጭበርባሪ’ እያልን ያለፋታ የውግዘት ዘመቻ እናካሂድባቸዋለን። ባሰኘን ጊዜ፣ የዋጋ ቁጥጥር እናውጅባቸዋለን። ባለ10 ፎቅ የቢሮ ሕንፃ የመገንባት ግዴታ ካሸከምናቸው በኋላ፣ ትንሽ ቆይተን ደግሞ፣ የቢሮና የመኖሪያ አገልግሎትን ካላቀላቀልክ፣ ህንፃ መገንባት አትችልም ብለን በድንገተኛ መመሪያ እንጠፍራቸዋለን። እንደ ስኳር ፕሮጀክት በመሳሰሉ የመንግስት ቢዝነሶች አማካኝነት በርካታ ቢሊዮን ብሮች በየዓመቱ ሲባክን ብዙም አያስጨንቀንም፤ በየዓመቱ ተጨማሪ ታክስ በኢንቨስተሮችና በነጋዴዎች ላይ መጫን ግዴታ እንደሚሆን አይገባንም። የሲሚንቶ ቢዝነስ ለዓመታት መንግስት በሞኖፖል (በጉልበት) ስለያዘው፣ ሲሚንቶ ብርቅ የነበረ ጊዜ ሩቅ አይደለም። በስድስት ወር ወረፋም አይገኝም፤ በዚያ ላይ ዋጋው ጣሪያ ሲነካ እናስታውሳለን። የሲሚንቶ እጥረት፣ በኢንቨስተሮች አማካኝነት ነው፣ ‘የድሮ ተረት’ የሆነው፤… ዋጋውም በግማሽ የቀነሰው። በዚህ ምክንያት፤ ስንትና ስንት ግንባታዎች እንደተሳኩ፣ ለስንትና ስንት ወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠ ማሰብ ይቻላል። ታዲያ፣ እነዚህ ፋብሪካዎች ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ማካሄድ ነበረብን? ልንዘምትባቸው ይቅርና፣ ጨርሶ በሕልማችን ዝር ማለት ነበረበት? ‘በግዴታ፣ ለወጣቶች የስራ እድል ስጡ’ በሚል ዘመቻ፣ ለወጣቶች የስራ እድልን የሚፈጥሩ ኢንቨስትመንቶችን መሸርሸር!)
ያስገርማል።
የተማሩና የተመረቁ ወጣቶች ሲበራከቱ፣ መፍራትና መጨነቅ ሳይሆን፣ ብሩህ ዘመን ይመጣል የሚል ስሜት ሊፈጠርብን ይገባ ነበር።
ለወጣቶች ብዙ ሺ የስራ እድል የሚፈጥሩና ከአደጋ የሚያድኑን ኢንቨስትመንቶች እንዲበራከቱና እንቅፋት እንዳይገጥማቸው ከመጣርና ከመዝመት ይልቅ፤ በኢንቨስትመንቶች ላይ እንዘምታለን።
ይሄ፣ ይሄ… ከአደጋው በላይ፣… ይበልጥ ያስፈራል፤ ያስጨንቃል

በኦሮሚያ ወረዳዎች የተነሳዉ ህዝባዊ የግብር ይቀነስ ጥያቄ ምላሹ ጠመንጃ ለምን ሆነ ? source zhabesha


በአንቦ፣ወሊሶ ፣በጉደር፣ጊንጪ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ግብርን በመቃወም ህዝብ ጥያቄ ማቅረቡ ለምን ወንጀል ይሆናል? ለምንስ በጥይት ያስደበድባል?
ያልተጻፈዉ የወያኔ ህግ ብዙ ነዉ::ምንም ጥያቄ ህዝቡ ቢጠይቅ በጥይት ይደበደባል:: አስደብዳቢዎቹ ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ ስም የኦሮሞ ብሄረተኘነትን እናራምዳለን እያሉ የሚያናፉት እነ ኦህዴድ ናቸዉ::

አንድ ጊዜ በወልመራ ወረዳ የሚኖሩ ገበሬ የኦህዴድ ካድሬዎችን እንዲህ ሲሉ አፋጠዋቸዉ ነበር::”እናንተም ገደላችሁን ወይም ትግሬም ገደለን ያዉ ለእኛ ሞት ነዉ::ኦህዴድ ለምንድን ነዉ ከኦሮሞ ህዝብ ጎን ቆሞ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ የማያደምጠዉ?የወያኔን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከምትራወጡ የህዝብ ጮህት ለምን አትሰሙም::”
ዛሬ የኝህ አርሶ አደር ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነዉ::
በኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ ከመቶ በላይ በብሄር የተደራጁ ፓርቲዎችን ወያኔ ቀፍቅፋለች::እነዚህ በዬብሄሩ የተደራጁ ፓርቲዎች ግን ዋና ስራቸዉ በስሙ የተደራጁትን ህዝብ ማስፈጀት እና ማሳረድ ነዉ::የወያኔም ዋናዉ ግቡ የገደለህ የራስህ ብሄር ድርጅት ነዉ ብሎ እጁን በዉሃ ታጥቦ በመጨረሻዋ ሰዓት ፊቱን አዙሮ እብስ ማለት ነዉ::
ህዝብ ከህዝብ ቢተላለቅ: ኢትዮጵያ በሳት ብትያያዝ: ብሎም አጠቃላይ የሰበአዊነት ቀዉስ በዚያች ሀገር ዉስጥ ቢፈጠር ወያኔ ግድም አይሰጠዉ::ስልጣን ላይ እስካለ አንዴ በግብር: አንዴ በኢንቨስትመንት: አንዴ በድብቅ የሚዘርፈዉን ሀብት ማግበስበሱ ብቻ ነዉ አንድ ቁጥር አላማዉ::
አምቦ የአውቶቡስ መናኸሪያ እንዲህ ተጨናንቋል::

በኦሮሚያ ወረዳዎች የተነሳዉ ህዝባዊ የግብር ይቀነስ ጥያቄ ምላሹ ጠመንጃ ለምን ሆነ ? ብለን የጠየቅን እንደሆነ መልሱ አንድ ነዉ::ከወያኔ ባህሪ የሚመነጭ ነዉ::ይሄ ጥያቄ በየትኛዉም የሀገሪቱ ክፍል ቢነሳ መልሱ ጠመንጃ ነዉ::በየትኛዉም የሀገሪቱ ወረዳ ወይም ቀበሌ እንዲህ አይነት የእዉነት ህዝባዊ ጥያቄ ከተነሳ መልሱ የሚሆነዉ ጠመንጃ ነዉ::

ለምን? ወያኔ ህዝባዊ መሰረት ስለሌለዉ ህዝባዊ ጥያቄዎችን ማስተናገድ አይችልም::ገዳይ እና አስገዳይ አድርጎ የመለመላቸዉ እና በዬብሄረሰቡ ስም ያደራጃቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ህዝባዊ መሰረት ስለሌላቸዉ የህዝቡን ጥያቄ የሚያደምጡበት ጆሮም የላቸዉም::የወያኔን ትዕዛዝ ተቀብለዉ ህዝቡን ለመግደል ግን ቁርጠኛ ናቸዉ::
በእጅጉ የሚያሳዝነዉ ደግሞ በተቃዉሞ ጎራዉ የተሰለፈዉ ሀይልም ከግል ስሜቱ እና የፖለቲካ እይታዉ ከረጢት ዉስጥ ወጥቶ በጋራ በመምከር ሀገራዊ መፍተሄ የሚያመጣ እርምጃ ላይ ላለመስማማት ያለዉ ቁርጠኛ አቋም ነዉ:: ህዝቡ ግን ብዙ ህዝባዊ ጥያቄዎች አሉት::እያንዳንዱን ህዝባዊ ጥያቄዉን ባነሳ ቁጥር ደግሞ በወያኔ የሚያስገድለዉ ነዉ::

አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝባዊ ጥያቄ ግን በአንድ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚፈታዉ እና ህዝቡም እፎይታ አግኝቶ ወደ ብልጽግና መገስገስ የሚችለዉ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በእዉነት መፍጠር ከተቻለ ብቻ ነዉ:: ወደዚህ ግብ የሚሰሩ ተቃዋሚ ሀይላት እስካልተፈጠሩ ድረስ ኩነቶች ይቀጥላሉ::
ለጊዜአዉ እንኳን በጠባብ ፍላጎት አብጠዉ የሚመጡ ሀይላት አሸናፊ ቢሆኑም አስተማማኝ እና ሁል አቀፍ ህዝባዊ ምላሽ መስጠት አይችሉም::ትርምስ እና ትርምስምሱ ይቀጥላል::ህዝብ ግን ከዚህ መከራ የግድ መዳን አለበት::ኢትዮጵያ ከዚህ ሁሉ ህመም መዳን አለባት::

Thursday, July 13, 2017

ፍርድ ቤቱ በእነ ጉርሜሳ አያና መዝገብ ላይ ብይን ሰጠ • 5 ተከሳሾችን በነፃ አሰናብቷል • አቶ በቀለ ገርባ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ተከላከል ተብሏል source mereja.com

ፍርድ ቤቱ በእነ ጉርሜሳ አያና መዝገብ ላይ ብይን ሰጠ
• 5 ተከሳሾችን በነፃ አሰናብቷል
• አቶ በቀለ ገርባ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ተከላከል ተብሏል
(በጌታቸው ሺፈራው)

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሀምሌ 6/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት በእነ ጉርሜሳ አያና መዝገብ በተከሰሱት 22 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ ሁለት ክስ ቀርቦባቸው የነበር ሲሆን ከ1ኛ እስከ 13ኛ ያሉት ተከሳሾች ኦሮሚያ ውስጥ ተከስቶ በነበረው ህዝባዊ አመፅ ‹‹በቀጥታ በመሳተፍ፣ ከውጤቱም ተካፋይ ለመሆን›› የሽብርተኝነት ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በፀረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 3 ስር የተደነገገውን ተላልፈዋል ተብለው ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ በሁለተኛ ክስ ከ14ኛ እስከ 22ኛ ያሉት ተከሳሾች በማንኛውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ በሚል በፀረ ሽብር አዋጁ አንቀፅ 7(1) ስር ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በቀጥታ በሽብር ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው ተከሰው ከነበሩት መካከል 1ኛ ተከሳሽ ጉርሜሳ አያና፣ 2ኛ ተከሳሽ ደጀኔ ጣፋ፣ 3ኛ ተከሳሽ አዲሱ ቡላላ፣ 5ኛ ተከሳሽ አብደታ ነጋሳ፣ 6ኛ ተከሳሽ ገላና ነገራ፣ 8ኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ፣ 11ኛ ተከሳሽ በየነ ሩዳ እና 12ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ሊበን ተመስርቶባቸው ከነበረው በቀጥታ የሽብር ወንጀል መፈፀም በሽብርተኝነት ድርጅት ውስጥ መሳተፍ ወደሚል ተቀይሮ ከፀረ ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3 በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 7(1) ስር ተቀይሮ ይከላከሉ ሲል ክሳቸውን አሻሽሏል፡፡
በተመሳሳይ አቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀረበው ማስረጃ የሽብር ወንጀልን የሚያቋቁም ስላልሆነ ከፀረ ሽብር አዋጁ ወጥቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀፅ 257 (ሀ) ስር የተደነገገውን ግዙፍ ያልሆነ መሰናዳትና መገፋፋት ክስ ተቀይሮ እንዲከላከል በይኗል፡፡ በሌላ በኩል በ1ኛ ክስ በጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 3 ስር ተከሰው ከነበሩት መካከል 7ኛ ተከሳሽ ጭምሳ አብደሳ፣ 9ኛ ተከሳሽ ፍራኦል ቶላ፣ 10ኛ ተከሳሽ ጌታቸው ደረጀ እና በማንኛውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ ክስ ተመስርቶበት የነበረውና በዜግነት ኬንያዊ የሆነው 22ኛ ተከሳሽ አልካኖ ቆንጨራ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ወስኗል፡፡
በዚሁ መዝገብ በማንኛውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት 14ኛ ተከሳሽ ደረጀ መርጋ፣ 15ኛ ተከሳሽ የሱፍ አለማየሁ፣ 16ኛ ተከሳሽ ኢካ ተክሉ፣ 17ኛ ተከሳሽ ገመቹ ሻንቆ፣ 18ኛ ተከሳሽ መገርሳ አስፋው፣ 19ኛ ተከሳሽ ለሚ ኢዴቶ፣ 20ኛ ተከሳሽ አብዲ ታምራት እና 21ኛ ተከሳሽ አብዲ ኩምሳ ተከሰውበት የነበረውን አንቀጽ 7(1) ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ ይከላከሉ የተባሉበት አንቀፅ ዋስትና የሚያስፈቅድ በመሆኑ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው በኩል ጥያቄ አቅርበው የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ‹‹በፅሁፍ አስገቡ›› ሲል ለጥያቄው ውሳኔ ሳይሰጥ አልፎታል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የመከላከያ ምስክር ለመስማት ከነሃሴ 8-12/2009 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡