Tuesday, June 27, 2017

ንዳርጋቸው ጽጌ የጽናታችን እና የቁርጠኝነታችን ዓርማ ነው! (አርበኞች ግንቦት 7) source satenwe




የንቅናቄያችን መስራችና ዋና ጸሀፊ የነበረው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በዘረኛው የህወአት አገዛዝ ከየመን አየር ማረፊያ ታግቶ እስር ቤት ከተወረወረ እነሆ ጁን 23 2017 ዓም 3 አመት ሞላው።
ህወአት አንዳርጋቸውን ባገተበት ወቅት የንቅናቄያችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ይሽመደመዳል የሚል ተስፋና እምነት ነበረው። ይህንን እምነቱን ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በሚፈጸምበት ሰቆቃ ውስጥ ሆኖ እንዲያረጋግጥለትና ነጻነት ናፋቂ የሆነው ህዝባችን ተስፋ እንዲቆርጥ ብዙ ጥሯል፣ ደክሟል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በሚከፍለው ግብር የሚተዳደረው የአገራችን ዋናው ቴለቪዥን ጣቢያና ህወሃት ህዝባችንን በፕሮፖጋንዳ ለማደንዘዝ ያቋቋማቸው ሌሎች ሚዲያዎ በሙሉ በመረባረብ ከጓዳችን መታገት ጋር ተያይዞ ግንቦት 7 አከርካሪውን ተመቶአል፤ ሌሎች የንቅናቄው አመራሮች የአውሮጳና የአሜሪካ የምቾት ኑሮዋቸውን ትተው ወደ በረሃ የመሄዳቸው ጉዳይ የማይታሰብ ነው የሚል ከንቱ ትንበያ ከማራገብ አልፈው የህዝባችንን ቅስም ለመስበር ያመቸናል የሚሉትን የፈጠራ ድራማዎችን በማቀነባበርና በማሰራጨት ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ብቻ ሳይሆን ግምቱ የማይታወቅ የአገራችንን ሃብትም አባክነዋል።
ህወሃት ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብና በጠመንጃ ሃይል በተያዘ ሥልጣን ልቡ ያበጠ እብሪተኛ ድርጅት መሆኑን በገሃድ ያስመሰከረው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌን ለማገት ከተጓዘው ርቀት እና ከወሰደው የድፍረት እርምጃ በተጨማሪ ለነጻነት የሚደረገው ትግል አብቅቶለታል ብሎ ለመደምደም ያሳየው ጥድፊያ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ትግል ፤ ለፍትህ ለእኩል ነትና ለአገር ባለቤትነት የሚደረግ ትግል መሆኑ መረዳት ያልቻለው የህወሃት አገዛዝ ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ ከአፍላ የወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ የቆመለትና ዋጋ እየከፈለለት ያለው ይህ ክቡር አላማ ከግለሰብ ተክለ ሰውነት በላይ ግዙፍ እንደሆነ አንዳርጋቸውና የትግል ጓዶቹ ጠንቅቀን እናውቃለን።
ወያኔ አገር ውስጥ ያሉትን ተቃዋሚዎች እግር በእግር እየተከተለ ለማዳከም በየቀኑ የሚወስደው የእስር፤ የእንግልትና የግዲያ እርምጃ አልበቃ ብሎት ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌን ከባህር ማዶ አግቶ ለመውሰድ ለየመን ጸጥታ ሃይል በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍሎአል። በዚህ የወያኒ የእብሪት እርምጃ የተበሳጨው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘር፤ ቋንቋና ሃይማኖት ልዩነት ሳያከፋፍለው ‘”እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” በሚል ቁጣ ተነስቶ በአምባገነንነትና በዘረኝነት ላይ የሚደረገውን ትግል ወደ ሌላ ምዕራፍ እንዲሸጋገር አድርጎታል። ከዚህም በተጨማሪ ህወሃት ከአንዳርጋቸው መታገት በኋላ በአመራር እጦት ይበተናል ያለው የነጻነት ትግል ከኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ጋር በተደረገው ውህደትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመታገል በተፈጠረው ጥምረት መክሸፉን አስመስክሯል።
ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በታገተ ሰሞን የንቅናቄያችን አመራር ወደ ምድር ወርዶ ትግሉን ለመምራትና ለመታገል ያስተላለፈውና እየተገበረው ያለው ውሳኔ በጠላት ካምፕ ከፍተኛ መደናገጥን ሲፈጥር በወገን ካምፕ በኩል ከፍተኛ ተስፋንና አለኝታነትን የጫረ ሆኖአል።
የንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 አባላት እና ደጋፊዎች በየምንሰበሰብባቸው የስብሰባ አዳራሾችና በየምንሰማራባቸው የትግል መስኮች እየዘመርነው ያለው የ”ላንቺው ነው አገሬ” ግጥም ደራሲ የሆነው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ የምንታገልለትን አላማ በአጭሩ እንዲህ ሲል በስንኞቹ አስቀምጦአል።
በባርነት ሸክም ጀርባሽ የጎበጠው፣
በባለጌ መዳፍ ክብርሽ የጎደፈው፣
የስቃይሽ ስቃይ ሰማይ የነደለው፣
ዓይንሽ እስኪጠፋ ደም ለምታነቢው፣
ላንቺ ነው ሀገሬ ህይወት የገበርነው፣
ላንቺው ነው ሀገሬ እኛ የምንሞተው።
ለናዱት አንድነት ላረከሱት ሀገር፣
ለቀሙን ነጻነት ለጫኑብን ቀንበር፣
መልሱ ሆኖ መጥቷል ደረትን ለአረር፣ እያለ ይቀጥላል።
ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ ይህንን ግጥም በደረሰበት ወቅት በእአምሮ ውስጥ ይመላለስ የነበረው አገራችን የገባችበት አዘቅትና የህዝቦቿ ጉስቁልና እንደሆነ መገንዘብ ከባድ አይሆንም። ይህንን ለመለወጥ ደግሞ ትግሉ የሚጠይቀው ቁርጠኝነትና የመንፈስ ጽናት ደረጃ እስከምን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦአል።
መላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች መሪያችን አንዳርጋቸው ጽጌ በጠላት እጅ የወደቀበትን ሶስተኛ አመት ስናስታውስ እርሱና ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላቶቻችን እስከዛሬ የከፈሉትንና በመክፈል ላይ የሚገኙትን መስዋዕትነት እያሰብን ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለለትን የነጻነት ትግል ከዳር ለማድረስ ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ በመግለጽ ነው ።
ዛሬ በየእስር ቤት ውስጥ ሆነው በንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ሥም የተለያየ መከራና ስቃይ በመቀበል ላይ ያሉትም ሆኑ በትግሉ ላይ እያሉ ውድ ህይወታቸውን ለዚህ ክቡር ዓላማ የገበሩ ወገኖቻችን የሚካሱት እነርሱ ዋጋ የከፈሉለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ባለን ጽናትና ቁርጠኝነት ብቻ ነው።
የጀመርነው ትግል ምንም አይነት ዋጋ ቢያስከፍለን የኋላ ኋላ በአሸናፊነት እንደሚደመደም ምንም አይነት ጥርጣሬ የለንም። መታሠር፣ መገረፍና መገደል የነጻነት ትግል ማደናቀፍ የሚችል ቢሆን ኖሮ የህወሃት የመንፈስ አባት የሆነው ፋሽስት ጣሊያን እስከዛሬዋ ደቂቃ ድረስ በባርነት ሲገዛን ይኖር ነበር።
ውድ ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ እና በተለያየ የወያኔ ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ ፍዳችሁን እያያችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን ሆይ! የታሠራችሁበት የብረት ሰንሰለትና የታገታችሁበት የእስር ቤት በሮች የሚበረገዱበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን እኛ የትግል ጓዶቻችሁ እናረጋግጣለን። በአረአያነት ያስተማራችሁን ጽናታችሁና ቆራጥነታችሁ በደማችን ውስጥ ነፍስ እንደዘራ አትጠራጠሩ።
ዘለአለማዊ ክብር ለነጻነት ስሉ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን ሁሉ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Monday, June 26, 2017

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህወሀት/ኢህአዴግ የአንድ ዓመት የአገዛዝ ጉዞ በተመለከተ ውይይት አደረገ!!!

“ህወሀት በራሱ ጠመንጃ ወደራሱ አነጣጥሮ እንደቆመ 2009 ዓ.ም ጥሎት ሂዷል፡፡”ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
“ህወሃት ዓመቱን በከንቱ ያሳለፈው ከክህደት በመጀመሩ ነው፡፡” አቶ ወረታው ዋሴ
“የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሃት ምንም ሳይጠብቅ እንደሌለ ቆጥሮ ከገባበት ውስብስብ ችግር ለመውጣት በራሱ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡”ወ/ሮ መዓዛ መሀመድ

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህወሀት/ኢህአዴግ የአንድ ዓመት የአገዛዝ ጉዞ በተመለከተ ውይይት አደረገ!!!
(በሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ አገዛዙ በ2009 በጀት ዓመት መጀመሪያ እና መጨረሻ ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አደረገ፡፡ በውይይቱ ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ተነስተው በመድረኩ መሪዎች በአቶ ወረታው ዋሴ፣በኢ/ር ይልቃል ጌትነትና ወ/ሮ መዓዛ መሀመድ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
አገዛዙ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ብዙ ነገሮችን ለመፈፀም ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆነም
በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የሞቱ ሰዎችን በተመለከተ ተገቢው አንድም የመንግስት አካል ተጠያቂ አልሆነም፡፡
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ አላገኘም፡፡
ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ማግኘት የሚገባውና በህገ መንግሰቱ የተሰጠው የመብት ጥያቄ መልስ አልተሰጠም፡፡
በኢትዮጵያ የስራ አጥነት፣የኑሮ ውድነት እና መረን የለቀቀው ሙስና ጉዳይ መፍትሔ አላገኘም፡፡
ከተቃዋሚዎች ጋር አደርገዋለሁ የተባለው ድርድር ቀለብ ከሚሰፍርላቸው ጋራ የሚደረግ አሰልቺ ትያትር ሆኖ አልፏል፡፡
የህሌናና የፖለቲካ እስረኞች አሁንም በር እንደተቆለፈባቸው ናቸው፡፡ይባስ ብሎም በሃገራችን ምንም ዓይነት የህሊናና የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት አገዛዙ በህዝብ ቁስል ላይ መሳለቁን ቀጥሎበታል፡፡
እነዚህን ሁሉ ችግሮች በቀላሉ መፍታት ሲችል በተቃራኒው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ዜጎችን ማሳደድና ማፈን፣በየጦር ካምፑ ማጎር ዋነኛ የበጀት ዓመቱ ስራው አድርጎት አንድ ዓመት የኢትዮጵያውያን የመከራ ጊዜ አልፏል፡፡
በአጠቃላይ ባሳለፍነው የበጀት ዓመት ሀገራችን ከመቸውም ጊዜ በባሰ በከባድ ችግር ውስጥ ወድቃለች፡፡ይህ ሊሆን የቻለበት ዋናው ምክንያት አገዛዙ ለመጭው 25 እና 30 ዓመታት ያለምንም ተቀናቃኝ ስልጣን ላይ እቆያለሁ በሚል አቅዶ ስለነበረ እና ይህንን ህልሙን ወደ ቅዠት የለወጠ የህዝብ ተቃውሞ በመነሳቱ ነው፡፡ ባላሰበው ሰዓት ስልጣኑ አደጋላይ በመውደቁ ይህንን ሀቅ አምኖ ለመቀበል ባለመፈለጉ የሆነውን ሁሉ በክህደት በመጀመሩ ለተፈጠሩትና ለአንዣበቡት ችግሮች ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳይሰጥ አገዛዙ በራሱ ጠመንጃ ወደራሱ አነጣጥሮ እደቆመ እድሉን ሳይጠቀምበት 2009 ዓ.ም ጥሎት አልፏል፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ የተፈጠሩትን ችግሮች ካመነና የህዝብን ጥያቄ መመለስ ከጀመረ ውጤቱ ከስልጣን ወደኋላ ማፈግፈግና ለህዝብም ድል እዲጣፍጠው እና የበለጠ ግፊት በማድረግ ለስልጣናችን አደጋ ይሆናል ብሎ በማሰብ በራሱ አደርገቸዋለሁ ብሎ ቃል የገባቸውን ተግባራት እንኳ አንዱንም መፈፀም ሳይችል ራሱም ተጨንቆ የኢትዮጵያን ህዝብም እያስጨነቀ አንድ ዓመት የመከራ ዘመን አልፏል፡፡በዚህም ምክንያት ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ ፍርሃት ተከቦ በኢትዮጵያ የወደፊት ፖለቲካ ውስጥ በየትኛውም መመዘኛ የመፍትሔ አካል የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ለሀገራችን ብቸኛ የመፍትሔ አካል መሆናችንን ተገንዝበን ከአለፉት ዓመታት ድክመትና ጥንካሬ ግንዛቤ በመውሰድ የኢትዮጵያ ወጣቶች የደም ዋጋ የከፈሉበትን የነፃነትና የእኩልነት ትግል ከግብ ለማድረስ ጠንክረን ለመስራት እና የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈለ የህሌና ዝግጅት ማድረግ እንዳለብ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ የእለቱን ስብሰባ አጠናቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሁለት አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች ደረሱ * በሁለት የመኪና አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ source zhabesha

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እንደዘገበው በኦሮሚያ ክልል ዛሬ በደረሱ ሁለት የትራፊክ አደጋዎች የ28 ህይወት አለፈ።
ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ 60 መንገደኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በምዕራብ ሀረርጌ ሂርና ከተማ ሲደርስ ፍሬን አልታዘዝ በማለቱ ነው በአከባቢው ለነበሩ 14 ወንድ እና ስምንት ሴት እግረኞች ሞት ምክንያት የሆነው።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የሰሌዳ ቁ.ኮድ 3-50262 ኢት የሆነው ተሽከርካሪ ቆመው በነበሩ ሶስት ሚኒባስ፣ አራት ባጃጆችና አራት አይሱዙ መኪኖች ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ንጉሴ ግርማ እንደገለጹት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም። አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ከደምቢዶሎ ወደ አዲስ አበባ አስክሬን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ሃይሩፍ ሚኒባስ በምዕራብ ወለጋ ጉቴ ወረዳ ገባ ሰንበታ ሲደርስ ገደል ውስጥ ገብቶ 6 ተሳፋሪዎች ላይ የሞት አደጋ አድርሷል ያለው ኢቢሲ በአደጋው አንድ አባት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ሂወታቸው አልፏ ል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ሹፌሩ ካለ እረፍት ለ3 ቀናት ሲያሽከረከር እንደነበረ ገልጸው ፖሊስም በስፋት በማጣራት ላይ ነው ሲል ኢቢሲ ዘገባውን ቋጭቷል::

ብሄርተኝነት ወደ ዘቀጠ ዘረኝነት ይወስዳል ፤ ዘረኝነት ደግሞ ወደ ውድቀት ይመልሳል

በቶማስ ሰብሰቤ
በብሄር ፖለቲካ ብሄርተኝነት አዎንታዊ ከመሆን ይልቅ ለዘረኝነት ቅርብ ነው።በተለያያ የማህበረሰብ የእውቀት፣የአስተሳሰብና የባህል ልዮነት ውስጥ ለብሄርተኝነት ትልቅ ቦታ መስጠት ዘረኝነት በማሳደግ ወደ ለየለት ዝቅጠት ማምራት ነው።ብሄርተኝነት ውስንነት ላይ መሰረት አለው ፣ ውስንነቱ ደግሞ በዛች በምታስባት ነገር ላይ ይበልጥ ትኩረት እንድሰጥ ያስገድድሃል።የበላይነትና ሌላውን እንደ ራስ ያለማየት ሰወኛ ያልሆነ ባህሪ ያመጣብሃል።
ስለ ራስ ብቻ ብዙ እንድትጨነቅ አድርጎ ትልቁ ነገር እንዳታይ ያደርግሃል።ሰው በተፈጥሮው ስለ ራሱ ብቻ እንዳያስብ ፣እንዳይጨነቅና እንዳይኖር የተፈጠረ ስለሆነ ማስብ የተቸረው እንስሳ ነው።ብሄርተኛ ስትሆን ደሞ ለሰው የተቸረው የማስብ ፀጋ ሳታውቀውም ከሰውነት እንደ ፀጉር ያልቃል ያኔ የዘረኝነት መንገድ ትጀምረዋለህ ፤ ያኔ ስለ አንድ ጠባብ ነገር እየተጨነክ ትልቁን ነገር ትስተዋለህ።
ዘረኝነት የብሄር ፖለቲካ የበኩር ልጅ ነው።ዘረኝነት ከአንድነት ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰው ተፈጥሮ ጋር የተጣላ ነው።ባለፉት 26 አመታት ያለው የብሄር ፖለቲካ በትንሹ እንኳን ካስተዋልነት ከእንድነት ጋር ብቻ ሳይሆን የተጣላነው ብዙዎች ከሰውነት ሰበዓዊ ፍጥረት ደረጃ ወርደው በተጨማለቀ በዘረኝነት ዝቅተጥ ውስጥ ገብተዋል።ከደርግ ውድቀት በፊትና በኋላ የመጣው ብሄርተኝነት የመልክ ፣የአካሄድና የስልት ልዮነት ይኑረው እንጂ በባህሪውና አላማው ተመሳሳይ ነው።
ከደርግ ውድቀት በፊት ያለው የሻቢያ፣የህውሃትና የኦነግ ብሄርተኝነት ጥላቻና ራስን በራስ ማስተዳደር ላይ መሰረት ያደረገ ነበር።ሻቢያም ሆነ ህውሃት ለህዝቦቻቸው ፀረ አንድነት ፣ ሌላውን የመጥላት ፖለቲካ ፣ በሀሰት የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ የትግራይና የኤርትራ ህዝብ በሌላው ኢትዮጰያዊ በተለይ በአማራው መደብ ጭቆና እንደደረሰበት ፣ ከማንም በላይ ራሱን እንዲወድ አድርጎ የተነገረው ወቅት ነው።ሻቢያም ሆነ ህውሃት ጠንካራዉን የደርግ መንግስትን ለመጣል በጥላቻ ብሄርተኝነትና በዘረኝነት ህዝባቸው አነሳስተው ሻብያ ሀገር መስርቷል ፤ ህውሃት መንግስት ሆኖል።
ይህና ሌሎች ውስብስብ ጥላቻ ፣ ሸፍጥና የጠነባ ህዝብን ከህዝብ ያቃቃረ ዘረኝነት ከተሰራ በሃላ የመጣው ስርዓትም ደሞ የብሄርተኞች የፖለቲካ ዳማ ይዞ ከደርግ ውድቀት በኋላ አለ።ህውሃት ቅደመ ስልጣን በጥላቻ ሲያብጠለጥለው የነበረው አማራ “ትምክተኛ” ፤ ሌላውን ተቀናቃኝ ኦሮሞ “ጠባብ ” ብሎ ሁለቱ ትልልቅ ብሄሮች የመብት ጥያቄ ካነሱ ለማደፈ በዚህ ስልት እየኖረ ነው።በተለይ አማራና ኦሮሞ ህውሃት ከመንበረ ስልጣኑ በፊትና በኋላ ያሰመረባቸው ብሄሮች ቢሆኑም ሌላው ኢትዮጵያዊም ከአንድነት ይልቅ ልዮነት ፣ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅና በጠባብ ነገር ብዙ ጊዜ እንዲፈጅ የመጣ ሰርዓት ነው ብሄርተኝነት።
መንግስቱ ኋይለ ማሪያም በብሄርተኝነትና ገንጣይነት ህውሃትና ሻቢያ ሲያስቸግሩት ብዙ ይናገር ነበር።ጓድ መንግስቱ በንቀት ” ሰሜን ኢትዮጵያ የሻቢያና የወያኔ መደበቂያ ሳይሆን መቀበሪያ ይሆናል” ይሉን ነበር።የተናቀ ያስረግዛል ይሉት ፕሬዘዳንቱን አፍንጫቸው ድረስ መተው አባረው ይኸው ዛሬ እነሱንም ባለ ጊዜ ሲሆኑ “ብሄርተኝነት ወደ ዘቀጠ ዘረኝነት ይወስዳል ፣ዘረኝነት ወደ ውድቀት ይመልሰናል” ስንላቸው እንደ ፕሬዘደንት መንግስቱ ይንቁናል።
ለመንግስቱ ውድቀት በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ለህውሃትና ሻቢያ የሰጡት ንቀት ከፍተኛ ቦታ አለው።ህውሃትና ሻቢያ ከውጪ ሀገራት ጋር ያላቸው ግንኙነት በሰፊው አያሳስባቸውም ፤ የሰሩት ህዝብ ለህዝብ የማቃቃር ስራ እንብዛም ቦታ አልተሰጠውም፣ ሁለቱም በተሳሳተ ታሪክ ፣ውንጀላና ጥላቻ ህዝባቸውን ለጦርነት ሲያስነሱ ለፕሬዘደንት መንግስቱና ጓዶች ሰሚ የለውም ነበር ።መጨረሻ የጉዱ ቀን መጣና 4 ኪሎ ቁጭ አሉ።
ዛሬም ህውሃት ኢህአዴግ በእጁ ጠፋጥፎ የሰራው ብሄርተኝነት ወደ ዘረኝነት ተቀይሮ ሊበላው ነው።ያኔ ለስልጣን ማራዘምና ከፋፍሎ ለማስተዳደር ምቹ የሆነው የብሄር ተኮር ፌደራሊዝም ዛሬ ምርጥ የደለበ ዘረኛኒዝም አሳድጎልናል።ኢህአዴግን በትጥቅ ትግል አይወድቅም ፣ ኢህአዴግ በምርጫ አይወድቅም ፤ ኢህአዴግ የሚወድቀው እራሱ ባመጣው የብሄርተኝነትና የዘረኝነት ፖለቲካ ጠርዝ ነው።ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ያደገው ወጣት ስለ ልዮነቱ የዘመረ ነው።
ስለ ራሱ ብቻ እንዲያስብ የተገደደ ፤ ስለ ሌላው ኢትዮጵያዊ የማይጨነቅ ፣ ትልቁ ሀገር ሳይሆን ትንሽየዋ ክልል በዓይነ ህሊናው ያለ ፣ ብሄርተኝነት ዘረኝነት ወልዶበት በዝቃጭ ኢ _ሰበዓዊነት አስተሳሰብ እንዲጫወት ያደረገው ስርዓት ነው።ይህ ስርዓት ደሞ ወደድንም ጠላንም ሁሉም ሀገሬን ከማለት ይልቅ አጉል ውድድር ውስጥ አስገብቷል።ምንም ነገር ሲሰራ እንደ ሀገር ከመቆም ይልቅ በጣም ርካሽ በሆነ በዘር ቆጠራ ፣በዘር ልማት ፣በዘር ባለሞያ ፣በዘር ስልጣን ፣በዘር ሃይማኖት ፣በዘር ማህበርና በዘር ባህል አጉል በዘረኝነት የተጨመላለቀ አካሄድ ላይ ነን።
ይሄ ትውልድ የኢትዮጵያ መሬት በሱዳን ከመወሰድ ይልቅ ሲዳማ ከወላይታ የወሰደው መሬት ይሰማዋል።ልክ ሎሬት ፀጋዮ ገብረ መድህን “የዘንድሮ ትውልድ ወኔው የሚመጣው አረቄ ሲጣጣ” ነው እንዳሉት የህውሃት ኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ ወጣት ከሀገሩ በላይ ክልል ሲነካበት እንዲያመው አድርጎ ነው የተሰራው【የተወሰኑ ሀገር ወዳድ ወጣት እንዳለ ሳይረሳ】 ይህ ፅንፈኝነት ደሞ መጀመሪያ አምጪውን ህውሃት ኢህአዴግን ይበላዋል።ዛሬ ህውሃት ኢህአዴግ ፈታዋለው የሚለው ለ26 አመታት የዘራው ዘረኝነት አይደለም ሊፈታው ይቅርና ራሱን ያጭደዋል።
የህውሃት ኢህአዴግ በምርጫ ሳይሆን ባመጣው የዘር ፖለቲካ ይወድቃል ፣ህውሃት ኢህአዴግ በትግል ሳይሆን ውሃ አጠጥቶ ባሳደገው ብሄርተኝነትና ዘረኝነት ይወርዳል።ይህን ስል ካሳቀ ደሞ ጓድ መንግስቱ ያኔ የናቀ ትዝ ይበልህ።የአንድ ብሄር ተጠቃሚነትና ህውሃት ኢህአዴግን የደገፈ በማህበራዊ ፣ፖለቲካዊና ፣ኢኮኖሚያዊ ዘርፋ ላይ በሃገሪቱ የበላይ ተጠቃሚ ሲሆን ጪሰኛው መቆጣቱ አይቀርም።
የሀገሩቱ የሲቪክ ማህበራት በማዳከም ፣ የውጪ ግንኙነት የበላይነት ፣የንግድ የበላይነት ፣የወሳኝ ስልጣን የበላይነት ፣ የተደማጭነትና የተፈሪነት የበላይነት የወሰደው የህውሃት አመራር ዛሬ የደህነንነት መስሪያ ቤቱን ፣መከላከያውንና ሀገሩን ስለተቆጣጠረ እድሜ ያለው ይመስላዋል።ነገር ግን ህዝብ ከማንም በላይ ነው።ህዝብ በሀገሪቱ ያለው የብሄር ፖለቲካ መጠቃቀም ከማንም በላይ አይቶ “በቃኝ” ብሏል።ከዚህም አልፎ ዘረኛ ፣ብሄርተኛ ትውልድ ተፈጥሯል።ዘረኝነት የዘቀጣ፤ ብሄርተኝነት ርካሽ ፖለቲካ ቢሆንም ፤ ዘረኝነትና ብሄርተኝነት አምጪውን ኢህዴግን ሲበላው ማየት ያስደስታል።

Friday, June 9, 2017

በኢትዮጵያ በድጋሚ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ተከሰተ      soure zehabesha

 






በኢትዮጵያ ያለው የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሔዱ ተጠቆመ፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃውን ይፋ ያደረገው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ የግንቦር ወር የዋጋ ግሽበት 8 ነጥብ 7 ሆነ መመዝገቡን ገልጿል፡፡ ይህም ካለፈው ሚያዝያ ወር ጋር ሲተያይ፣ በሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበት መስተዋሉን ያሳያል ብሏል፡፡ የዋጋ ጭማሪው ከየካቲት ወር ጀምሮ እስከ ግንቦት ወር ድረስ በተከታታይ የተከሰተ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የንግድ ስርዓት ላይም ቀውስ መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡

‹‹ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ለግሽበቱ መጨመር ምክንያት ነው፡፡›› ያለው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ ‹‹በተለይም ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እና ማሽላ ዋጋቸው ከፍተኛ ጭማሪ›› ማሳየቱን አስታውቋል፡፡ ጭማሪው በየጊዜው እየተከሰተ መምጣቱ በህዝብ ኑሮ ላይ ጫና ማሳደሩን የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ እንዲህ ዓይነት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሚታይበት ሁኔታ ውስጥ፣ ደሞዝ ቢጨመር እንኳን ግሽበቱን ለመቋቋም እንደሚያስቸግር ታዛቢዎቹ ይናገራሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት እቃዎች እንዲሁም ማስጌጫዎች ላይም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉን ከኤጀንሲው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ‹‹ምግብ ነክ ሸቀጦች ግሽበት ካለፈው ሚያዚያ ወር ጋር ሲነፃፀር ከ12 ነጥብ 2 ወደ 12 ነጥብ 3 በመቶ ጨምሯል፡፡›› ሲል በሪፖርቱ ላይ የገለጸው ኤጀንሲው፣ ‹‹ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ግሽበት ደግሞ ሚያዚያ ወር ላይ ከነበረት 4 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 4 ነጥብ 7 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡›› ሲል አስታውቋል፡፡
Source: BBN news June 8, 2017





Wednesday, June 7, 2017

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ለሕዝባቸው ነጻነት፤ ለአገራቸው አንድነት ለሚያስቡ ወገኖች ባለ5 ነጥብ መልክት አስተላለፈ source zehabesha


የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የአመራር ጉባኤ አካሄደ
የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የተመሰረተበትን ዓላማ ከወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ለማራመድ፤ ባለፈው ዓመት ካከሄደው የአባላት ኮንግረስ በኋላ ስላከናወናቸው ተግባራት ለመገምገም፤ መጪውን አንድ ዓመት ሊያከናውን ስለሚገባው ተግባራት እቅድ ለማውጣት ለሶሥት ቀናቶች በሰሜን አሜሪካ ችካጎ ከተማ ጉባኤ አካሂዷል።
በዚህ ጉባኤ የአመራር አባላት በኑሮ ምክንያት የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች ወደ ጎን በመተው በአካል ተገናኝተው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ያካበቱትን ልምድ ለትግል አጋሮቻቸው ለማካፈል በግል ህይወታቸው ያላቸውን የኑሮ ጫና ወደ ጎን በመተው አውሮፓ ካናዳ እና ሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የድርጅቱ አመራር አባላት ሙሉ በሙሉ በአካል ተግኝተው፤ ስለ ድርጅታቸው መክረዋል።
ከተወያዩባቸው አጫጭር አጀንዳዎች ውስጥ፦
1. ድርጅታቸው ስላከናወናቸው እና ለወደፊት ሊያከናውን ስለሚገባቸው ተግባራት በተለያዩ ኑእስ አጀንዳዎች በመከፋፈል፤
2. ወያኔ በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በጎንደር ክ/ሀገር እና በደቡብ የኦሮሞ ማህበረሰብ ወገኖቻችን ላይ እያከናወነ ያለውን የግፍ ጭፍጨፋ እና መሬታችን ለሱዳን አሳልፎ ለመሥጠት የሚያደርገውን ድብቅ ሴራ፤
3. ሕዝባችን ከጭፍጨፋ፤ አገራችንን ከመከፋፈል አደጋ ለማዳን ከግፈኛው የወያኔ ሥራዓት ለማላቀቅ ሊደረግ ስለሚገባው የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት፤ ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት አጀንዳዎች ዙሪያ የመከረ ሲሆን፤ በቀዳሚ አጀንዳው እንደተመለከተው፤ ማንኛውንም ዓይነት ተግባራት እንደ ድርጅት ውጤታማ ለማድረግ፤ በቅድሚያ የድርጅታዊ አሰራር እና ጥንካሬን ተገቢውን ትኩርት በመስጠት በጥንካሬ ላይ መተኮር ስላለበት በመምከር፤ የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፤ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ በቀጣይ ሊያከናውን ያቀዳቸውን የፖለቲካ እና የማህበራዊ እንቅሥቃሴዎች፤በዞን እና በቀጠና ከፋፍሎ የበለጠ ጠንክሮ መሥራት ስላለበት ተግባሮች በጥልቀት መርምሮ የውስጥ መመሪያዎቹን አጽድቋል።
በተከታታይ ደግሞ፤ ወያኔ አገራችን ኢትዮጵያን ለዘለዓለም ቀጥቅጦ ለመግዛት ባለው የተፈጥሮ ባህሪው ምክንያት፤ ወገኖቻችን የጠየቁትን ዲሞክራሲያዊ እና ሰበአዊ መብት በኃይል ለመጨፍለቅ፤ በህይዎት እና በንብረት ላይ እያደረሰ ያለውን ጭካኔ የተሞላበት ወታደራዊ እርምጃ ገምግሟል። በተለይ በአሁኑ ወቅት በደቡብ (በኦሮምያ)፤ በጎጃም እና በጎንደር ክ/ሀገሮች እያደረሰ ያለው ገደብ የሌለው ጭፍጨፋ ፈጽሞ ህዝባዊ ትግሉን በእልህ የበለጠ ሊያቀጣጥል የሚችል መሆኑን በሁሉም አካባቢዎች በተግባር እየተፈጸሙ ያሉትን ሕዝባዊ እንቅሥቃሴዎች ገምግሟል።
ወያኔ ሰንጎ የያዘውን ሕዝባዊ ማእበል ለማዳፈን ጊዚያዊ የወታደራዊ አስተዳደር ቢያውጅም፤ እየታየ ያለው ሕዝባዊ ምላሽ ግን፤ ወታደራዊ አስቸኳይ አዋጅ ከምንም የማያስጥለው ህዝባዊ ብሶት የወለደው የለውጥ ማእበል መሆኑን ነው። በአኳያው፤ ይህን የተቀጣጠል ሕዝባዊ ትግል በተቀነባበረ እና በጠነከረ መልኩ በማቀናጀት ለአንዴ እና ለመጨረሻ የወያኔን ግፈኛ ሥራዓት አስወግዶ፤ በምትኩ የዜጎቿ ነፃነት በእኩልነት የተመሰረተባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመገምባት፤ ሁሉም ተቀዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ መሥራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን እና በዚህ ዙሪያ የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ሊያበርክት የሚገባዊ ድርሻ መክሯል።
በመጨረሻም በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ የአቋም መልክቱን ለሕዝባቸው ነጻነት፤ ለአገራቸው አንድነት ለሚያስቡ ወገኖች አስተላልፏል።
1. ድርብ ሱሪ — አያስጥልም እንዲሉ፤ ወያኔ ብሶት የወለደውን ሕዝባዊ የለውጥ ፍላጎት እና እንቅስቃሴ በኃይል መጨፍለቅ እንደማይቻለው አምኖ፤ አገራችንን ወደከፋ ጥፋት ከሚውስድ የአደጋ ጉዞ እንዲታቀብ እና የወታደራዊ አዋጁን አንሥቶ አገሪቱን በተረጋጋ መንገድ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥራዓት ለሚያሸጋግር ጊዚያዊ መንግሥት እንዲያስረክብ፤
2. ሕዝባዊ መነሳሳቱን አቅጣጫ ለማስቀየር በስፖርት እና በንግድ እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች የሚገናኘውን ንፁህ ዜጋ ምክንያት እየፈጠረ የሚጭረውን የጎሳ እሳት እሱን ጭምር የሚያቀጥለው መሆኑን አምኖ ከቀጣይ ትንኮሳ እንዲታቀብ። በተለይ በመቀሌ ስታዲዮም በወያኔ ካድሬዎች የተለኮሰውን እና ቂም የቋጠረውን አጸያፊ ድርጊት በአድሎአዊ ፍርድ ሌላ ጦስ ለመፍጠር ከመጣር ይልቅ፤ ሚዛን ባለው መልኩ ለተደበደቡት የጣና ማዕበል የእግር ኳስ ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጣቸው፤
3. በሁሉም ወገኖች ተቀባይነት አጥቶ የነበረውን በስፋት እና በውህደት የሚኖረውን የጎንደር ክ/ሀገር ሕዝባችን “ቅማንት እና አማራ” በሚል በአንድ ወቅት ተለኩሶ፤ በኋላም ደብዝዞ የነበረውን አደገኛ ከፋፋይ ሂደት እንደገና ነብስ በመዝራት ወያኔ እያካሄደ ያለውን የቅማንት ካድሬዎች ሥልጠና እንዲያቆም፤ የጎንደር ሕዝብም፤ በድብቅ ወያኔ እየቀበረ ያለውን አደገኛ የዘር ቦምብ በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ ሳይፈነዳ በራሱ ካድሬዎች እግር ተረግጦ እንዲፈነዳ በአስቸኳይ የተለመደ የአንድነት ክንዱን እንዲያጠነክርና የእምቢታ ድምጹን እንዲያሰማ፤
4. የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ ደግሞ የጎንደር ሕዝብ ወያኔ ውስጥ ውስጡን ሲጎነጉን የነበረው የአገራችንን መሬት ለሱዳን ቆርሶ የመሥጠቱ ፍጻሜ ላይ ለማዋል ቀን ከሌት እየሰራ እንደሆነ አውቆ በድንበር ዙሪያ እየተዋደቁ ያሉ ወገኖቻችንን የሞራል እና የቁሳቁስ እርዳታ እንዲያደርግ፤
5. በመጨረሻም፤ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እና ሌሎችም በሕዝባችን እና በአገራችን ዙሪያ የተጋረጡ አደጋዎችን ለማክሸፍ ሁሉም የተቀዋሚ ድርጅቶች ልዩነታቸውን አቻችለው፤ የአገራቸውን ጥቅም አስቀድመው በጋራ አብረው ይህን አስከፊ ሥራዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ እንዲያስወግዱ ጥሪውን አሥተላልፏል።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት።

Tuesday, June 6, 2017

ጥብቅ ማስጠንቀቂያ… source zhabesha

ከልዑል ዓለሜ
ከሽሬ ግንባር ለተመዘዛችሁ የህዝባዊ ትግራይ ወያኔ ሐርነት ብርጌድ አባላት እና የ25ተኛ ክ/ጦር አዲስ ምልምል ሐይል ማዘዣ ልዩ ሐይልና በ24ተኛ ክ/ጦር የወታደራዊ ስምሪት እንዲሁም ለጸረ ሽምቅና ለ31ኛ መለስተኛ እግረኛ፣ ከአዲስ አበባ ለተንቀሳቀሳችሁ የመካከለኛዉ እዝ ወታደር ተብዮዎች፣ለአካባቢ ሚሊሻ ለሲቪል ፖሊስ የመረጃ ሰንኮፎች እና ለወታደራዊ ደህንነቶች በሙሉ።
(ፎቶ ከፋይል)
በህዝብ ላይ ከፍተኛ ወረራ ለመፈጸም ከአለቆቻችሁ ትእዛዝ ተቀብላችሁ ወደ አርማጭሆ ጀንበር፣ ቀበሌ እንዲሁም ገደብዬ፣ ዳባትና ጭላ ቀበሌ፣ ሶርቃ፣ ኡማህጅርና ኡመራ፣ ሳንጃ፣ ተከዜ ግንባር ድረስ ለመንቀሳቀስ መዘጋጀታችሁን ተንተርሶ ከዉስጣችሁ የሚገኙ የህዝብ አርበኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይህን ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
በማንኛዉም ወቅት እና ሰሐት ላይ በየትኛዉም ዘመን በተነሱ የህዝብ መነቃቃቶች ህዝብ እንጂ ገዢ አሸንፎ አያዉቅም ይህንንም ምክንያታዊ በማድረግ ይህ ገድሎ አይጠግብ የህወሃት ሰራዊት በህዝባችን ላይ እንዲህ ያለ መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም ሲዘጋጅ ዝም ብለን ለመመልከት ፈጽመን አንደፍርም በመሆኑም የጥይት ሐሩሩ ከዉስጥም እንደሚንቦለቦል በማወቅ ከህዝብ ጋር እንድትቆሙ ማስጠንቀቂያ እንሰጣለን!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ