Tuesday, January 24, 2017

ግንቦት ሰባት ፥ ኢሳት እና ትግሉ – (ኄኖክ የሺጥላ)



ግንቦት ሰባት ፥ ኢሳት እና ትግሉ (ኄኖክ የሺጥላ)
ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያስታርቅ ነገር እስከ አሁን አልገጠመኝም! ከግንቦት ሰባት ጋር ያጋጨኝ ነገር ፥ ከወያኔ ጋር ያጋጨኝ አይነት አይደለም! ግንቦት ሰባት የከሸፈ ፥ አቅም የሌለው ፥ አቅመ ቢስነቱን እያወቀ በደረቁ የኢትዮጵያ ህዝብን ለማጭበርበር ደፋ ቀና የሚል ድርጅት ስለመሆኑ ከማንም በላይ ደጋፊዎቹ እና መሪዎቹ በደንብ ያውቃሉ። ግንቦት ሰባት በአባላቱ ላይ ሳይቀር ፕሮፖጋንዳ የሚሰራ ድርጅት ነው። አሁንም በመላው አለም ላይ ሊያደርጉት ያሰቡት ጉዞ ፥ ከጭንቀት የመነጨ ፥ አባላትን ለማረጋጋት ታስቦ የተዶለተ ተራ የፖለቲካ ቁማር ስለመሆኑ ፥ ከስብሰባው ቀድሜ ፥ በስብሰባው ላይ ፥ ይህ ነው የሚባል የረባ ነገር እንደማያስተላልፉ መናገር እችላለሁ!
ችግሩ የግንቦት ሰባት መክሸፍ አይደለም ። ችግሩ ግንቦት ሰባት በኤች አይቪ እንደተያዘ ክፉ አባወራ ማሰቡ ነው እንጂ ! በዚህም ድምዳሜው ፥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የኢሳትን ተአማኒነት ፥ እና የኢሳትን የህዝብነት ለድርጅቱ ተክለ ሰውነት ሲባል እንዲረግፍ እያደረገ ያለ ድርጅት ነው ! እኔን ከያዘኝ ኢሳትም ይማቅ አይነት ነገር! ይህ ግንቦት ሰባትን ከወያኔ ጋር የሚያመሳስለው አብይ ጉዳይ ይመስለኛል። ግንቦት ሰባት ደጋፊዎቹን ያለ ምክንያት የመደገፍ ጥቅምን አጥምቆዋቸዋል ። ሃሳብን መሞገት ሲያቅታቸው ፥ ባለቻቸው ሚጢጢ ትልቅነት ግዝብዝ ሲሆኑ ታስተውላለህ ።
ለምሳሌ
የዛሬ ሁለት ሳምንት እዚህ ሳን ሆዜ የሚኖር የግንቦት ሰባት በከተማው ሁለተኛ ሰው የሚያስተዳድረው ሆቴል አለው። ይህ ሰው ጥሩ ወዳጄ የነበረ ነው። የግንቦት ሰባት አባል በነበርኩበት ወቅት ከዚሁ ሰው ጋር ነው ሎስ አንጀለስ ድረስ ተጉዘን የኤፍሬም ማዴቦን « አማራ ምን አባቱ !» አይነት ንግግር የሰማነው። ያም ሆኖ ከግንቦት ሰባት ራሴን ካገለልሁ በኋላ ከዚህ ሰው ጋር ያለኝን ሰዋዊ ወዳጅነት ያለ ምክንያት ወይም የግንቦት ሰባት አባል ስለሆነ ማቋረጥ አለብኝ ብዬ አላስብም ነበር ። ስለዚህም የዛሬ ሁለት ሳምንት ከወዳጆቼ ጋር በሆቴሉ ሄደን ምሳ ለመብላት ( በቁጥር ስምንት ስለሆነን ) በቅድሚያ ወንበር ለመያዝ ደወልሁለት ። ምንም ችግር የለም አለኝ። ከሰዓታት በኋላ ደውሎ « ድርጅቴን ግንቦት ሰባትን ስለጎዳህብኝ አንተ ምግብ ቤቴ መጥተህ እንድትመገብ አልፈልግም !» የሚል መልስ ሰጠኝ ። በመጀመሪያ ሰውን በፖለቲካ አቋሙ አላስተናግድም ማለት የሚያስከስሰው ነገር እንደሆነ እንኳ በቅጡ የሚያውቅም ሰው አለመሆኑ ገረመኝ ፥ በሁለተኛ ደረጃ እዚህ ድረስ እስኪበሰብሱ ድርጅት ማፍቀራቸው አዘንኩላቸው ። ይህም ከወያኔ ማንነት ጋር ፍፁም አንድ ነው !
ዛሬ ድርጅቴን ስለተናገርክብኝ እቤቴ አትበላም ያለኝ ሰው ነገ ስልጣን ቢይዝ ፥ ሃገር መግባት አትችልም ስላለማለቱ ዋስትናው ምንድን ነው ! እንግዲህ ይህ ሰው ራሱ በሳን ሆዜ የኢሳት የገቢ አሰባሳቢ አካል ነው ። አሁን በዚህ ሰው መነፅር ኢሳትን እንድናይ የሚያደርጉን ግንቦት ሰባቶች ናቸው ! የኢሳትን ህልውና የሚፈታተን ርካሽ ነገር የሚፈፅሙትም ፥ ኢሳት ያገኘው ህዝባዊ ተቀባይነት በመጠቀም ፥ ከነሱ ጋር በ አልቦነታቸው ምክንያት የሚጋጨውን ( ወይም የሚጠይቀውን ) ሰው ሁሉ ግጭቱን ወደ ኢሳት እያዞሩ ፥ በቀጥታ ፀቡን ከኢሳት ጋር እንድናደርግ የሚያደርጉን !
ይህ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ወደፊት ልክ ዛሬ የግንቦት ሰባት ህልውና አደጋ ላይ እንደወደቀው ( ከስሩ እንደተሽመደመደ ) ሁሉ ፥ የኢሳትም ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም ! ትንቢት አይደለም ግን I can see it!
በቀጣይ ግንቦት ሰባት እንደ ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው ነገር ፥ ሆድ አደር እና ምልምል የአማራ ልጆችን በማሳመን ፥ የአማራ ማህበር እየፈጠሩ ፥ አማራን እንዲሰበስቡ የማድረግ ስራ ነው ። ይህ ለግንቦት ሰባት ለጊዜው የሚፈልገውን የሰው እና የቁስ ሃይል ያመጣለት ይሆናል ፥ ኋላ ላይ ግን ማቆም እና መቋቋም የማይችለው ጉልበት ተፈጥሮ እነዚህ በስውር የተቋቋሙ የአማራ ሃይሎች ተገንጥለው እንደሚወጡ ለመገመት ብዙ ማወቅ አይጠይቅም ! ወያኔ ትግሬ በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ብአዴን የሚባል ቡድን መስርቶ አማራውን ለመቆጣጠር የሄደበት መንገድ ፥ ዛሬ ለወያኔ ከፍተኛ ስጋት እና የውስጥ አርበኛ በመሆን የቁም ስቅሉን የሚያሳዩት እነማን እንደሆኑ ፥ እነማን መረጃ እንደሚሰዱልን የታወቀ ነገር ነው !
ባጭሩ ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያስታርቁኝ ( እኔን እና የአማራ ወጣቶችን ማለቴ ነው ) የሚከተሉት ይሆናሉ ብዬ እገምታለሁ
1ኛ ግንቦት ሰባት አቅም የሌለው አየር ወለድ ድርጅት መሆኑን አምኖ የትግል ስልት ለውጥ ማድረግ
2ኛ አማራን ለስልጣን መወጣጫነት ለመጠቀም ከማሰብ እና አማራን አዚህ ደረጃ ከመናቅ መውጣት
3ኛ ስለ አንድነት እየሰበከ እራሱ በብሄር የተደረጃ ድርጅት ነውና ፥ ይህንን መዋቅሩን ቀይሮ ሁሉ አቀፍ ህብረ ብሄራዊ ማዕከላዊ መዋቅር ያለው ድርጅት ለመሆን መንገድ መክፈት
4ኛ ላምባልዋለበት ኩበት መልቀሙን ማቆም! የአማራ ትግልን የኔ ነው ብሎ መታበዩን መግታት
5ኛ ከምንም በላይ በህዝብ ገንዘብ የቆመውን ኢሳትን የህዝብ እንዲሆን መፍቀድ! ለድርጅት ተክለ ሰውነት ሲባል የኢሳትን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ተራ ጉንጭ አልፋ ፕሮፖጋናዳ በኢሳት እንዲሰራ ከማድረግ መቆጠብ
እና ሌሎች !
ኄኖክ የሺጥላ

Sunday, January 22, 2017

ብርቱ ሚስጥር በጋምቤላ ፍጅት ሲጋለጥ! የጋምቤላ ታጋች ህፃናት ለፖለቲካ ፎጆታ እየሆኑ ነው! ሙሉነህ ዮሃንስ



ብርቱ ሚስጥር በጋምቤላ ፍጅት ሲጋለጥ!
የጋምቤላ ታጋች ህፃናት ለፖለቲካ ፎጆታ እየሆኑ ነው!
ህፃናቶቻቸውን እና እንስሶችን እንደፈለጉ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት የሚነጥቁባቸው ዞን ውስጥ ከፍተኛ ሹመኛ የሆነ ሰው ነው ያደረሰን።
ሚስጥሩን በደረስኩበት መረጃ መሠረት ገና ከዚህ በላይ የወረዳው ሰው ሁሉ ሊወሰድ ይችላል ይላል፡፡ ምክንያቶቹን እንዲህ ዘርዝሮ ልኮታል፡-
1. ለም የእርሻ መሬት ከእኛ እስከ አጎራባች አለ ይህን በሚያርሱ የወያኔ ኢንቨስተሮች ለበርካታ አመታት ከህይወት እስከ ንብረት መስዋትነት አስከፍሏቸዋል።
2. #ወያኔን ሊያሰጋ የሚችል ሁሉ እስካሁን በሙሉ ሃይል በየቦታው ባይንቀሳቀስም በወታደራዊ ጥናታቸው መሰረት ያሰጋልና ስለሚሉ እስከዛው እኛም የስጋት ምንጭ ተደርገን ስለምንቆጠርና ለጥቃትም በቀላሉ ተጋላጭ ስለሆንን ዘራችን የሚጠፋበት አደጋ ውስጥ ገብተናል።
3. ከደቡብ ሱዳን ውሎገብ የፈለግነውን የጦር መሳርያና የእለት ፍጆታ ሸቀጥ ያለስጋት እናስገባ ነበር። ያንንም ለማስቀረትና እኛል ለመፍጀት ነው።
4. የወያኔ ሴረኛ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር በጥበብ በመመሳጠር በግጦሽ በማመሳሰል ምንም የማያውቀውን ህዝቡን እያስገደለ ነው።
5. ለወረዳው ቅርብ በሆነ ሁኔታ የሠፈረው በትግራይ ኃላፊዎች ብቻ እንደፈለጉ የሚያዙት ልዮ ኃይል፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ሽምቆች እንዲሁም መከላከያም አለ። የመጀመርያዋ ጥይት ሳትጮህ ለመከላከያ አዛዡ ተደውሎ ነበር እንደርሳለን ብለው አውቀው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ፡፡
6. ቢያንስ በቅርብ ርቀት አስተማማኝ የአየር ኃይል አለ። ታድያ በትንሽ ደቂቃ ብቻ እስከ ወረዳው መድረስ ይችል ነበር ግን አልሆነም። ለምን አትበሉ። ዘር ፍጅቱ በወያኔ የተቀነባበረ ነው።
7. መሬታችንን ያለግብር የሚያርሱት የትግራይ ዜጎች ቢሆኑ ኖሮ የተጠቁት 57ቱ ወገኖቻችን ሳይመለሱ ተጨማሪ 16 ህፃናት መወሰዳቸው ሌሎችም ሊሞቱ ቀርቶ ደቡብ ሱዳንን በጨፈለቀ ነበረ፡፡
8. #በመጨረሻም የሱማሊያን አልሻባብ ተሻግሮ ለመግጠም ሰራዊት የሚልክ እንዲሁም አልፎ ላይቤርያና ሱዳን ሄዶ ሰላም አስከብራለሁ እያለ ኃይል የሚገብር የወንጀለኞች ጥርቅም ለራሳችን ዜጎች መሆን ሳይችል ይብስ ብሎ በአስቸኳይ አዋጅ ስም ሰላማዊ ህዝብ ሲያሸብርና ሲጨፈጭፍ ማየት እጅግ ያማል።
9. አሁን እኛም በስለናል። በተለይ የእኛን ወጣቶች በገፍ ለውትድርና የማያውቁትን ገጠራማው አካባቢ የሚመለምለው እንዳይሳካ ተግተን እየሰራን ነው። ለነፃነታችን መከበር ደቡብ ሱዳንን ሣይሆን ህዋህትን/ወያኔን ከአጋሮች ጋር ተደራጅተን እንታገላለን፡፡
ድል ለጭቁኑ ህዝብ! በማለት ይህን ብርቱ ሚስጥር ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለአለም እንዲታወቅ በአስቸኳይ ይድረስልን ብሏል።
ማሳሰቢያ፡-
ይህን ወደእንግሊዝኛና ወደተለያዪ ቋንቋወች በመተርጎም በቶሎ ስራ ልትጋሩ የምትችሉ በፍጥነት በውስጥ መስመር አግኙኝና የህዝባችንን ብሶት እናስተጋባ ለጋምቤላ ወገኖቻችን እንድረስላቸው።
አሁንስ ያማል!
ሙሉነህ ዮሃንስ

Wednesday, January 18, 2017

በስናይፐር የታጄበ ጥምቀት በጎንደር ቆንጅት ስጦታው



በስናይፐር የታጄበ ጥምቀት በጎንደር
( የጎህ ጋዜጠኛ ዞብል)
ከጎንደር ታቦቱን ከመቅደሱ ገብተው መሼከም እስኪቀራቼው ድረስ የመንግስት ወታደሮች ካህናቱን ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ እያሉ ያጣድፏቼው ነበር።
ታቦት በራሳቼው ላይ የተሼከሙ አባቶች ሁለት እጆቻቼው ታቦቱን ቢደግፉም እንባዎቻቼው በጎንደር
አስፋልት ላይ ጠብ፣ ጠብ፣ እያሉ ሲፈሱ ከበርካታ ካህናት አይኖቼ ቀረብ ብዮ አስተውያለሁ፣ መስቀል ኃይልነ ብላ የምታምን ቤተክርስቲያን ዛሬ ስናይፐር ኃይልነ የሚል መንግስት በስናይፐር የጎንደር ታቦቶች እንዲታጄቡ አደረገ። ድሮ በኦሞ መንገዱ ታጥቦ ምንጣፍ እየተነጠፈ እላዩ ላይ የሰላም ምልክት ቄጠማ የሚጎዘጉዙት ወጣቶች ዛሬ በብአሉ ስፍራ የሉም። በምትካቼው ካህናተ እግዚአብሔርን በግልምጫ እና
በስድብ የሚያዋርድ ሰራዊት ከህዝቡ በላይ ተገኝቷል። ታቦት ተሼካሚውን ካህን ተጎንብሶ አንድ ባለ ስናይፐር
“ቶሎ ቶሎ ሒድ ምን ይገትርሐል ” በማለት ሲናገር የተመለከቱ አንዲት መነኩሲት ምነው የአባቶቻችን አምላክ እንዲህ ፈጽሞ ረሰን ፣ አርባ አራቱ ታቦቶቻችን ከመዋረዳቸዉ በፊት ምን አለበት እኛን በሞት ቢጠራን በማለት ጮክ ብለው በመናገር ምርር ብለው ሲያለቅሱ ብዙ እናቶች በዋይታ አጄበዋቼው ነበር። “የምን ለቅሶ ነው ዝም በይ” ተብለው እኒህ እናት በታጣቂ ሲንገላቱ ህዝቡ መሀል ገብቶ ከባለ መሳሪያው አስለቅቋቼዋል።
ጎንደር ከወትሮው በተለየ መልኩ የጥምቀት ባዕል ሳይሆን ዘመድ አልባ አስከሬን የሚሼኝ በሚመስል መልኩ ፀጥ እረጭ ብላ በዓለ ጥምቀቱን በግዳጁ ስታከብር ፣ ታቦታቱን ወደ ማደሪያው በፌደራል፣ በመከላከያና በወያኔ ካድሬ ተከቦ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከተማዋ ነዎሪዋቾን በተፈጥሮ አደጋ የተነጠቀች እስኪመስል በዓለ ጥምቀቱ የሰው ድርቅ መትቶት በደበዘዘ መልኩ አልፉል። ባከታሪኩ ጄግናው የጎንደር ህዝብም የተማማለበትን ጥምቀተን እንደወትሮው በድምቀት አናከብርም ያለውን ቃሉን በሚገባ አክብሯል!!!!

Sunday, January 15, 2017

በጎንደር ከተማ አመፅና ሁከት አስነስታለች የተባለች ግለሰብ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሠረተባት source EthiopianReporter.com



በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር ከተማ በተለያዩ የዞን ከተሞችና በአዲስ አበባ ጭምር አመፅና ሁከት በማስነሳት፣ የአመፅ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ በማስተባበር ከፍተኛ የሆነ የግልና የመንግሥት ንብረት ላይ ውድመት አድርሳለች የተባለች አንድ ግለሰብ ከሌሎች አምስት ግለሰቦች ጋር የሽብር ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
በቅጽል ስሟ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አላና ፖታሽን በታክስ ማጭበርበር source ethiopian reporter




ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አላና ፖታሽን በታክስ ማጭበርበር ወነጀሉ

-  አላና ፖታሽ ግን በሰላማዊ መንገድ ችግሩን እንፍታ ብሏል
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አላና ፖታሽ የተሰኘውን በአፋር ክልል በፖታሽ ማዕድን ፍለጋ ተሰማርቶ የነበረውን የካናዳ ኩባንያ በታክስ ማጭበርበር ወነጀሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ አላና ፖታሽ የኢትዮጵያ መንግሥትንና አይሲኤል የተባለውን የእስራኤል ኩባንያ ማጭበርበሩን ተናግረዋል፡፡ የአገሪቱ የማዕድን ዘርፍ ስላለበት ሁኔታና እንደ አላናና አይሲኤል ያሉ የማዕድን ኩባንያዎች ሥራቸውን አቋርጠው መውጣት በዘርፉ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአላና ጉዳይ ከታክስ ስወራ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
‹‹የአላና ፖታሽ ጉዳይ ግብር ከማጭበርበር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ኩባንያው ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር መክፈል ያለበት የግብር ዕዳ አለበት፡፡ ያንን ግብር መክፈል አለበት፡፡ መንግሥት ይኼን በሆነው መንገድ በሕግም ፈልጎ ያስከፍላል፤›› ብለዋል፡፡
በቶሮንቶ ስቶክ ገበያ ተመዝግቦ ሲንቀሳቀስ የቆየው አላና ፖታሽ፣ ‹‹አላና ፖታሽ አፋር›› የሚባል እህት ኩባንያ በማቋቋምም በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ የፖታሽ ማዕድን ፍለጋ ሥራ ለስድስት ዓመታት ያህል ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ አላና ፖታሽ አፋር ለማዕድን ፍለጋ ሥራው 90 ሚሊዮን ዶላር ማውጣቱን፣ 3.2 ቢሊዮን ቶን የፖታሽ ክምችት ማግኘቱን በወቅቱ አስታውቋል፡፡
የፖታሽ ክምችቱን ለማልማት 750 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው፣ የፖታሽ ማምረቻ ፋብሪካውን ገንብቶ በዓመት አንድ ሚሊዮን ቶን በማምረት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ430 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት የሚያስችል ዕቅድ ለመንግሥት አቅርቦ ይሁንታን አግኝቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2013 የማዕድን ሚኒስቴር ለአላና ፖታሽ አፋር የከፍተኛ ማዕድን ማምረቻ ፈቃድ ሰጥቶታል፡፡
ይሁን እንጂ በዓለም ገበያ የማዕድናት ዋጋ በመውደቁና አላና ፖታሽ የሚፈለገውን ካፒታል ማሟላት ባለመቻሉ፣ እስራኤል ኬሚካልስ ሊሚትድ (አይሲኤል) ለተባለው ታዋቂ የማዳበሪያ አምራች የአክሲዮን ድርሻውን ሸጧል፡፡ አይሲኤል ቀደም ሲል የአላና ፖታሽ በቶሮንቶ ስቶክ ገበያ 16 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ገዝቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 የተቀረውን 84 በመቶ በ140 ሚሊዮን ዶላር ገዝቶታል፡፡
በወቅቱ የማዕድን፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስለሽያጩ ቀደም ብሎ አልተገለጸልንም ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰሙ ቢሆንም፣ የአላና ፖታሽ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለሚኒስቴሩ አሳውቀናል ሲሉ አስተባብለዋል፡፡
አላና ፖታሽን ከገዛ በኋላ አይሲኤል የአላና የማዕድን ማምረቻ ፈቃድ እንዲዛወርለት ለማዕድን ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡ ሚኒስቴሩ ማመልከቻውን በመገምገም ላይ ሳለ የፖታሽ ፕሮጀክቱ ሥራ እንዳይቋረጥ አይሲኤል ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች አስገብቶ ሥራውን እንዲቀጥል መፍቀዱን የቀድሞው ሚኒስትር አቶ ቶለሳ ሻጊ ለሪፖርተር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ኃላፊዎች አይሲኤል አስፈላጊዎቹን ሰነዶች አሟልቶ እንዲያቀርብ ጠይቀው ጉዳዩን በማየት ላይ ሳሉ፣ አይሲኤል (አላና ፖታሽ አፋር) ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር በታክስ ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ገብቷል፡፡ ባለሥልጣኑ በአላና ፖታሽ ሊከፈል የሚገባ የዊዝሆልዲንግና የቫት ክፍያ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ በአላናና በአይሲኤል መካከል በተፈጸመው ሽያጭ ውል መንግሥት ሊያገኝ የሚገባውን የካፒታል ዕድገት ግብር በአጠቃላይ 55 ሚሊዮን ዶላር ግብር እንዲከፈል ጠይቋል፡፡
የአይሲኤል ኃላፊዎች በበኩላቸው በአላና ሊከፈል የሚገባ 15 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን የዊዝሆልዲንግና የቫት ግብር ለመክፈል ተስማምተው የነበረ ቢሆንም፣ ባለሥልጣኑ ይህን ሊቀበል አልቻለም፡፡
በግብር ጥያቄው የተደናገጡት የአይሲኤል ኃላፊዎች ሥራቸውን አቁመው ከአገር ወጥተዋል፡፡ በጥቅምት 2009 ዓ.ም. የአይሲኤል ዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያሠራን ስላልቻለ በኢትዮጵያ የጀመርነውን ኢንቨስትመንት ለማቋረጥ ተገደናል፤›› ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን መሠረተ ልማትና የሕግ ማዕቀፍ ሊያቀርብልን ባለመቻሉ፣ የታክስ ባለሥልጣኑ አላና ፖታሽ አፋር ላይ ሕገወጥ የታክስ ጥያቄ በማቅረቡ የኩባንያው ሥራ እንዲቋረጥ ወስነናል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ድርጊት ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ከለላ ውሎችን የጣሰ ነው፤›› ብሏል ቦርዱ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የሰጡት ምላሽ ከአይሲኤል መግለጫ ጋር የማይጣጣም ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት አላና ፖታሽን እንጂ አይሲኤልን እንደማያውቀው ነው የተናገሩት፡፡
‹‹አይሲኤልን በተመለከተ አይሲኤል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተደራደረው ነገር የለም፡፡ አላና ፖታሽ ከሚባል አንድ የፖታሽ ኩባንያ ጋር የኢትዮጵያ መንግሥትን ሳያሳውቁ ከበስተጀርባ ተደራድረው ነው የመጡት፡፡ እኛ አሁንም የምናውቀው አላና ፖታሽን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ተመዝግቦ ሲንቀሳቀስ የነበረው እሱ ነው፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አይሲኤል ከበስተጀርባ ተደራድሮ ከበስተጀርባ እንደሄደ ተናግረዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም እኛ የምናውቀው አላና ፖታሽን ነው፡፡ እኛ አገር ውስጥ ተመዝግቦ የሚሠራው አላና ፖታሽ ነው፡፡ ከቀጠለ ይቀጥላል፣ ካልቀጠለ ለሌላ ኩባንያ እንሰጣለን፡፡ ብዙ ፈላጊዎች ስላሉ ብዙ የሚያሳስበን ጉዳይ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ አላና ፖታሽ አይሲኤልን እንዳጭበረበረ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡ ‹‹አይሲኤል በራሱ በአላና ፖታሽ የተጭበረበረ መሆኑን አውቆ ነው የሸሸው፡፡ ምክንያቱም እኛ ግብር ይከፈል ስንል እነሱ ከጀርባ የተፈራረሙት ይህን ሁሉ ስለማያካትት፣ ከዚህ ተቋም ጋር መቀጠል አንችልም ብለው ነው የሄዱት፡፡ አሁንም ቢሆን መጥተው ግብሩ ከተከፈለ በኋላ ስማቸውን ለማዛወር ከፈለጉ የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጁ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይኼን ቢሉም የቀድሞ አላና ፖታሽ ማኔጅመንትና ቦርድ አባላትና የአይሲኤል ኃላፊዎች በድብቅ የተደረገ ስምምነት እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት የቀድሞ የአላና ፖታሽና የአይሲኤል ኃላፊዎችን አስደንግጧል፡፡
ከአላና ፖታሽ አፋር መሥራቾች አንዱ የሆኑት አቶ ነጂብ አባቢያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሰዎች ሳያሳስቷቸው እንዳልቀሩ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን እናከብራቸዋለን፡፡ ኢትዮጵያን የምታህል ትልቅና፣ ከአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ላይ የምትገኝ አገር መሪ ናቸው፡፡ አላና ፖታሽን በተመለከተ ግን የቀረበላቸው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚናገሩት በበታቾቻቸው በቀረበላቸው መረጃ ነው፡፡ እኔ የቀረበላቸው መረጃ የተሳሳተ ነው ባይ ነኝ፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ በጣም ቀላል ነው፡፡ አላና ፖታሽንና አይሲኤልን በተመለከተ የተፈጸመው ውል የተመዘገበና በእኛና በመንግሥት እጅ የሚገኝ ለመሆኑ ሰነዶቹን በእርጋታ በመመርመር ማረጋገጥ ይቻላል፤›› ብለዋል አቶ ነጂብ፡፡
አላና ፖታሽ ለአይሲኤል መሸጡ በገሃድ የተካሄደ እንደሆነ፣ በወቅቱ የአላናና የአይሲኤል ከፍተኛ ኃላፊዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ ከቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ከቀድሞ የማዕድን ሚኒስትር አቶ ቶሎሳ ሻጊ ጋር በመገናኘት አይሲኤል በኢትዮጵያ ለመሥራት ስላሰበው ሰፊ ኢንቨስትመንት ማብራሪያ መስጠታቸውን፣ በወቅቱም መሪዎቹ ዕቅዱን በበጎ ሁኔታ መቀበላቸውንና ማበረታታታቸውን ተናግረዋል፡፡
‹‹በድብቅ የተደረገ ድርድር የተባለው እኔ አልገባኝም፡፡ ሁለቱም ኩባንያዎች በስቶክ ኤክስቼንጅ ለሕዝብ ለሽያጭ የቀረቡ በመሆናቸው ማንኛውንም መረጃ መደበቅ አይችሉም፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለአክሲዮኖች ስላላቸው ለእነሱ እያንዳንዱን ነገር ማሳወቅ በሕግ ይገደዳሉ፡፡ ግዢውም ቢሆን በዓለም አቀፍና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሪፖርተርን ጨምሮ ዘግበውታል፡፡ ምኑ ነው ድብቅ?›› ብለዋል፡፡
አይሲኤል አላና ፖታሽን ከመግዛቱ ቀደም ብሎ ጀምሮ ከግብርና ሚኒስቴርና ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ጋር በቅርበት ይሠራ እንደነበር የአይሲኤል ኃላፊዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የአይሲኤል ዋና ባለድርሻና የእስራኤል ቁጥር አንድ ቱጃር የሆኑት ኢዳን ኦፋርና በወቅቱ የአይሲኤል ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ሚስተር ስቴፋን ቦርጋስ፣ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ በማዳበሪያ አጠቃቀም ዙሪያ ለሚካሄዱ ፕሮግራሞች የገንዘብና የባለሙያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ቃለ መጠይቁ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ 600,000 ዶላር መለገሳቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
የታክስ ማጭበርበር ተፈጽሟል ስለተባለው አቶ ነጂብ አይሲኤል አላና ፖታሽን ከመግዛቱ በፊት ለአንድ ዓመት ያህል አላና ፖታሽ ስላለው ንብረትና ዕዳ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የኢትዮጵያና የውጭ ባለሙያዎች ቀጥሮ ሰፊ የምርመራ ሥራ መሥራቱን፣ ባካሄደውም ጥናት አላና ያለበትን ዕዳ አብጠርጥሮ ማወቁንና ዕዳውንም ለመክፈል መስማማቱን ተናግረዋል፡፡
‹‹እንኳን በዓለም ገበያ ላይ የተመዘገበ ኩባንያ ስትገዛ አይደለም አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አነስተኛ ቤት ስትገዛ የባንክ ዕዳ አለበት ወይ? የአገር ውስጥ ገቢ አለበት ወይ? ክርክር አለበት ወይ? መንገድ ይወጣበታል ወይ? ብለህ ትጠይቃለህ፡፡ እንዴት ነው አይሲኤልን የሚያህል ግዙፍ ኩባንያ የሚገዛውን ኩባንያ ዕዳ ሳያጣራ ገንዘብ የሚከፍለው?›› ሲሉ በሁኔታው ግራ መጋባታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ እንደሚጽፉ፣ ከተፈቀደላቸውም በአካል ቀርበው ለማስረዳት ፈቃደኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እንደምንፈታው አምናለሁ፡፡ ሁሉም ነገር በመዝገብ የተያዘ ነው፤›› ያሉት አቶ ነጂብ፣ አላና ፖታሽ ለማዕድን ፍለጋ ሥራው 90 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን፣ በወቅቱ ለ450 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል መፈጠሩን፣ አብዛኛው ባለአክሲዮን ድርሻውን ከስሮ መሸጡን ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር በስልክ ያነጋገራቸው የቀድሞ የአላና ፖታሽ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፈርሃድ አባጎቭ፣ ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር ተመካክረው ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አይሲኤል ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአላና ዕዳ የሆነ ወደ 10 ሚሊዮን ዶላር (200 ሚሊዮን ብር) የታክስ ግብር ለመክፈል ሐሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ባለሥልጣኑ 55 ሚሊዮን ዶላር የካፒታል ዕድገት ታክስ ጨምሮ እንዲከፍል በመጠየቁ ሳይስማሙ ቀርተዋል፡፡
እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 4 ቀን 2016 አይሲኤል (አላና ፖታሽ አፋር) ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንና ለማዕድን ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ የዳሎል ፖታሽ ፕሮጀክቱን ዘግቶ ለመንግሥት ማስረከብ እንደሚፈልግ፣ አላና ፖታሽ አፋር የሚጠበቅበትን (ያለበትን) በሰነድ የተደገፈ ግብር እንዲሁም ሌላ ማንኛውም ዕዳ ካለ ለመዝጋት ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል፡፡ ፕሮጀክቱን ለመዝጋት የሚልካቸውን ባለሙያዎች ምንም ዓይነት ችግር እንደማይፈጠርባቸው ዋስትና እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ሪፖርተር ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ አይሲኤል ለጻፈው ደብዳቤ እስካሁን ከመንግሥት በጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሪፖርተር ለአይሲኤል ኃላፊዎች በኢሜይል አድራሻቸው ለላካቸው ጥያቄዎች ማተሚያ ቤት እስከገባበት ሰዓት ድረስ ምላሽ አላገኘም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የማዕድኑ ዘርፍ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚችል የገለጹ ቢሆንም፣ ኢኮኖሚው በማዕድን ዘርፉ ላይ ጥገኛ እንዲሆን መንግሥታቸው እንደማይፈልግ አስረድተዋል፡፡ 

Thursday, January 12, 2017

ጨለንቆ አኖሌና “ኦሮሞው” የአጼ ሚኒሊክ ጦር ..#ግርማ_ካሳ



አኖሌን ምእራብ አርሲ ዞን፣ ጨለንቆ ደግሞ ምስራቅ ሃረርጌ ዞን ያሉ ከተሞች(መንደሮች) ናቸው። በሁለቱ ከተሞች በሚሊኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጭ ሆኖ ሁለት ሃዉልቶች ተሰርተዋል። ክሊኒክና ትምህርት ቤት ሊገነባበት ሲችል።
በነዚህ ቦታዎች ከመቶ አመታት በፊት ጦርነቶች ተደርገው ነበር። ጦርነቶቹ በአጼ ሚኒሊክ ጦር አሸናፊነት የተጠናቀቁ ናቸው። የሃዉልቶቹም አላማ ታሪክን ለማስታወስ፣ ወይንም ከታሪክ ለመማር ሳይሆን፣ በኢትዮጵያዉያን መካከል ጥላቻን ለመርጨትና ኢትዮጵያን ያቀኑ ታላቅ መሪን ስም ለማጉደፍ ነው።
እነዚህ ሃዉልቶች ምን ያህል የታሪክ መሰረት እንዳላቸው በራሱ አጠያያቂ ነው።
በጨለንቆ ጦርነቱ በጥቂት ሰዓታት የተጠናቀቀ ጦርነት ነበር። በጥቂት ሰዓታት ዉስጥ ያዉም ዘመናዊ ባልሆኑ መሳሪያዎች የተደረገ ጦርነት ብዙ እልቂትም እንዳስከተለ አድርጎ ማቅረቡ በታሪክ አንጻር አያስኬድም። አንድ በሉ።
ጦርነቱ የተደረገው ከኦሮሞ ገዢዎች ጋር አልነበረም፤ ከአዳሉ ገዢ ከሃረሩ ኤሚር አብዱላሂ ጋር ነበር። በሃረር የነበረውን ኤሚር፣ የኦሮሞ ብሄረተኞች እንደ ረቢ(መምህር) የሚቆጥሯቸው ዶር አሰፋ ጀለታ፣ የቱርክ ግብጽና አደሬዎች ጥምረት ( Turko-Egyptian and Adare alliance ) ብለው ነው የሚገልጹት። ይህ ጥምረት ለዶክተር አሰፋ ጀለታ ኦሮሞውን የጨቆነና አደሬዎችን ያፈረጠመ ጸረ-ኦሮሞ ጥምረት ነው። “ The gada system was attacked in eastern Oromia by the Turko-Egyptian and Adare alliance. The interethnic alliance and interdependence between the Adare and the eastern Oromo were shattered when the faction of the former invited the Turko-Egyptian power to colonize the Hararghe region in 1875.132 Under the Turko-Egyptian rule, between 1875 and 1885, the Adare consolidated their power and accumulated wealth and capital at the cost of the majority Oromo.” ሲሉ ነው ዶር አሰፋ የጻፉት። ዶር አሰፋ የ”ኦሮሞ ጠላት” አድርገው ያቀረቡትን አገዛዝ፣ አጼ ሚኒሊክ ማስገበራቸው በምን መልኩ በኦሮሞ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት ተደርጎ መወሰዱ በራሱ አስቂኝ ነው። ሁለት በሉ።
የጨለንቆ ጦርነት ከመደረጉ በፊት፣ አጼ ሚኒሊክ ልክ በወለጋና በጂማ እንዳደረጉት የሃረሩ ኤሚር፣ እንዲገብሩና ስልጣኑን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተማጽኖ አቅርበዉላቸው ነበር። ሆኖም የሃረሩ ኤሚር “ክርስቲያኖች ገናን ስለሚያከብሩ ይዘናጋሉ” በማለት፣ በገና ቀን በአጼ ሚኒሊክ ጦር ላይ ጦርነት ከፈቱ። ሆኖም ተሸንፈው አፈገፈጉ። በጨለንቆ የመጨረሻው ድል ሆነ። እንግዲህ የጨለንቆ ጦርነት በዚህ መልኩ፣ በወቅቱ በነበረው አስተሳሰብ ሰላማዊ የሆኑ አማራጮች ሁሉ በመሟጠጣቸው የተደረገ ጦርነት ነበር። ሶስት በሉ።
በአኖሌ፣ የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች የሴቶችን ጡት ቆርጠዋል በሚል እንደ አቶ ተስፋዬ ገብረአብ ያሉና አንዳንድ የኦሮሞ ብሄረተኞች ሲጽፉና ሲናገሩ ሰምተናል። ሆኖም ይሄን ታሪክ አፈታሪክ ነው ከማለት ዉጭ የጽሑፍ ማረጋገጫ ያቀረበ አንድም አካል የለም። በወቅቱ፣ ከዚያም በፊት የነበሩ ታሪኮችን የዘገቡ ብዙ የሙስሊም ጸሃፊዎች፣ ከአዉሮፓ የመጡ፣ እዚያው አገር ቤት የተወለዱ ነበሩ። ሆኖም አንድም ይሄ በአኖሌ ተደረገ የተባለውን በጨረፍታ እንኳን ( remotely)ያሰፈረ የለም። አፈ ታሪክ ብቻ ነው። አፈ ታሪክም በወቅቱ የነበሩ የአርሲ ተዋጊ መሪዎች ወታደሮች ለመመልመል የነዙትና እና ከመደጋገሙ የተነሳ እንደ እውነት ተደረጎ በአንዳንዶች የተወሰደ ሊሆን ይችላል።አራት በሉ።
እርግጥ ነው በአርሲ ለንጂሶ ዲጋ የተባሉ የአርሲ ኦሮሞ መሪ፣ ለአጼ ሚኒሊክ አልገብርም በማለት ከአራት አመት በላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ እንዳደረጉና በኋላ እጅ እንደሰጡ ይነገራል። በጦርነት ብዙ ሰው መሞቱ የማይቀር ነው። በአርሲ ብቻ ሳይሆን በወላይታም ተመሳሳይ የሆነ ጠንክራ ጦርነት አጼ ሚኒሊክ ገጥሟቸውም ነበር።
ሌላ የአርሲ ኦሮሞ መሪ ሮባ ቡቤ ይባሉ የነበሩና በኋላ ሮባ ቡታ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ፣ ሲጄመር ለአጼ ሚኒሊክ የመገበር ፍላጎት ያልነበራቸው፣ በኋላ ግን በሰላም የገበሩ መሪ ነበሩ። ይሄንን የሚገልጽ ብዙ የጽሁፍ መረጃዎች አሉ። እንግዲህ በአኖሌ ተፈጸመ የተባለው በተፈጸመበት ወቅት የነበሩ የነ ለንጂሶ ዳጋ እና ሮባ ቡታ ገድል በስፋት ተጽፎ፣ የአኖሌ ታሪክ በጽሁፍ አለመቅረቡ በራሱ አጠያያቂ ነው።
ለንጂሶ ዲጋ እና ሮባ ቡታ በአርሲ ኦሮምዎች ዘንድ በጣም ተወዳጅ የነበሩና የተከበሩ መሪዎች ነበሩ። ምንም ጥላቻን እና መከፋፈልን ከመንዛት ዉጭ ለኦሮሞው ማህበረሰብ የማይጠቅመውን የአኖሌና የጨለንቆ ሃዉልቶችን ከማቆም፣ እነዚህን የኦሮሞ መሪዎችን ታሪክ የሚዘክር፣ ያደረጉት አስተዋጾ የሚያስተምር ሃዉልቶች በአርሲ ቢሰሩ ባልከፋ ነበር። አስተማሪም ነበር የሚሆነው።
ከመቶ አመታት በፊት ጠንካራ የኦሮሞ ግዛት በሚባለው በጂማ ይገዙ የነበሩት ኦሮሞው አባ ጂፋር፣ ከአጼ ሚኒሊክ ጋር ስምምነት ስላደረጉ ምንም አይነት ጦርነት በዚያ አልተደረገም። አባ ጅፋር አጼ ሚኒሊክ ከሞቱ በኋላ እስከ 1932 ዓ.ም በጂማ አገረ ገዢ ነበሩ። በወለጋ የለቂ ነቀምቴ ሞቲ ወይም ገዢ የነበሩት ሞሮዳ በቀሬ፣ በሰላም ለራስ ጎበና የአጼ ሚኒሊክ ጦር የጦር አዛዥ ገብረው፣ የወለጋ ገዢ ሆነው መቀጠላቸው ተጽፏል።
አጼ ሚኒሊክ ተነጥለው ይከሰሳሉ እንጅ፣ ከአጼ ሚሊኒክ ጀርባ ሆነው አገሪቷን ያሽከርክሩ የነበሩት በአብዛኛው ኦሮሞዎች ነበሩ። ያለ ኦሮሞዎች የአጼ ሚኒሊክ መንግስት የትም አትደርስም ነበር። የአጼሚኒሊክ ጦር የ”ኦሮሞ” ጦር ነበር ማለት ይቻላል። አጼ ሚኒሊክን ራሱ ከአጼ ቴዎድሮስ ካመለጡበት ጊዜ ጀምሮ ተንከባክበው ጠንክራ ሆነው እንዲወጡ ያደረጉት በዋናነት ኦሮሞዎች ነበሩ።
እንግዲህ በኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ ጦርነቶች ተደርገዋል። ለምሳሌ የተወሰኑትን ብንጠቅስ፡
– በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ግራኝ መሀመድ ድፍን ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ጦርነቶች ተደርገዋል። የግራኝ ጭፍጨፋ ለማስታወስ ስንት ሃዉልቶች መሰራት አለባቸው ?
– እነ አጼ አምደጺዮንም ሃዲያ የመሳሰሉትን ሳይቀር በጦርነት አስገብረዋል። ስንት ሃዉልቶች መሰራት አለባቸው ?
– ከዚህ በፊት የተያዘብንን መሬት ለማስለቀቅ እንደሆነ አድርገው ነው የሚናገሩት። ግን ራሳቸው የኦሮሞ ልሂቃን ( እንደ ዶር አሰፋ ጀለታ ያሉ) ከ1522 እስከ 1612 የቡታ ጦርነቶች የሚባሉ አወጀው ኦሮሞዎች እንደተስፋፉ ይገልጻሉ። ዶር አሰፋ ሲጽፉ “ The Oromo fought twelve butta wars between 1522 and 1618, recovering, expanding, and establishing Oromia to its present boundaries.19 In the course of their continued expansion into various regions, different groups established autonomous gada governments” ነበር ያሉት። “recovering” የሚለው ጦርነቱ ለመደረጉ ምክንያት ለመስጠት ተብሎ የቀረበ አጠያያቂ ቢሆንም “ expanding, and establishing “ የሚለው ግን ትክክለኛና ሊሰመርበት የሚገባው። በድፍን ኢትዮጵያ ነው የቡታ ጦርነት የተደረገው። እንግዲህ ስንት ሃዉልት ማሰራት ሊኖርብን ነው ?
– ከሃረሩ ኤሚር ጋር አጼ ሚኒሊክ ብቻ አይደለም የተዋጉት። በ16ኛው ክፍለ ዘመን የሃረሩ ኤሚር ኑር ኢብን ሙላሂድ በኦሮሞ ተዋጊዎች በጦርነት ተሸንፎ ነበር። በሃረር ሌላ ሃዉልት ሊያስፈለግ ነው ማለት ነው ?
– በዘመነ መሳፍንት ንጉሶች ስም ብቻ እንጂ ስልጣን የነበራቸው መሳፍንቱ ነበሩ። ከመሳፍንት ጠንካራ የሆነ የንጉሱ እንደራሴ ተብሎ ይጠራ ነበር። ከ1828 እስከ 1831 በደብረ ታቦር የንጉሱ እንደራሲ ሆነው የነበሩ የየጁ ኦሮሞው ማሪዬ ተከዜን ተሻግረው በትግራይ ከነበሩ ደጃዝማች ሳባጋዲስ ጋር ባደረጉት ከፍተኛ ጦርነት ብዙ ሰው ሞቷል። በትግራይ መቀሌ ካለው የሰማእታት ሃዉልት በተጨማሪ ሌላ ሃዉልት መሰራት ሊያስፈልግ ነው ማለት ነው ?
– በ1844 የጂማ ኦሮሞ ሞቲ በሲዳማ ጃንጃሮ ግዛት ላይ ጦርነት ከፍቶ ብዙ ሲዳማዎች አልቀዋል። በ3 አመታት በኋላ የጃንጃሮ ንጉሱ መልሶ ከጂማ መንግስት ነጻ ሊወጣ ችሏል። በ1880 አባ ጂፋ የጂማው እንደገና ጦርነት ከፍተዉ የጃንጃሮችን ግዛት ወረው ከግዛታቸው ጋር ጠቅልለዋል። በጃንጃሮ ሃዉልቶች ያስፈለጋሉ ማለት ነው ?
– በ1882 የእምባቦ ጦርነት በሚባለው በሸዋ ንጉስ ሚኒሊክ ጦርና በጎጃም ንጉስ ተክለሃይማኖት ጦር መካከል ከፍተኛ ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት ተደርጓል። በጦርነቱ ንጉስ ተክለሃይማኖት ይሸነፋሉ። አጼ ዩሐነስ እና ዋግ ሹመ ጎበዜ ወይም አጼ ተክለጊዮርጊስ ከፍተኛ ዉጊያ አድርገው ። ዋግ ሹም ጎበዜ ተሽንፈዋል። በሸዋ አጼ ቴዎድሮስ ከአጼ ሚኒሊክ አባት ንጉስ ሃይለመለኮት ጋር ተዋግተው ሸዋን አስገብረዋል።
የሰገሌ ጦርነት በሚባለው በኦሮሞው የወሎ ንጉስ ሚካኤል እና በጨቦ ኦሮሞ ፊታወራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ(አባ መላ) መካከል የተደረገው ጦርነት በአባ መላ አሸናፊነት ተጠናቋል።
እንግዲህ እንዲህ እያልን እጅግ በጣም ብዙ የጦርነት ታሪኮችን መዘርዘር እንችላለን። ለዚያ ሁሉ ጦርነቶች ሃዉልት ልናቆም ነው ማለት ነው ?
የአገራችን ብቻ ሳይሆን የሌሎች አገሮች ታሪኮችም የጦርነት ታሪኮች ነው። አገሮች የተገነቡት በጦርነትና በመስፋፋት ነው። የድሮ ዘመን ሰዎችን አሁን ባለን ሊበራል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ መመዘኑ ደካማነት መሆኑን ተረድተን፣ ተበደልኩ፣ ጦርነት ተከፍቶብኝ ነበር ያለ ሕዝብ እርሱም በሌላ የታሪክ አጋጣሚ ጦርነት የከፈተና የበደለ መሆኑ አስበን፣ ስንት የከፉ ጦርነቶች እያሉ ሁለቱን ብቻ ነጥሎ በማውጣትና ሃዉልት በማቆም፣ አንድ ማህበረሰብ ብቻ ለማጥቃት የሚደረገው ደባ ቆሞ፣ በዚህም ሆነ በዚያ ሁላችንም አሁን ኢትዮጵያ በምትባል አንዲት አገር ዉስጥ ያለን መሆናችንን ተረድተን፣ ከዘረኝነት በጸዳ መልኩ ተያይዘን፣ ተከባብረን በፍቅር አገራችንን ብንገነባ ነው ይሻላል። ከታሪክ እንደምንማረው አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ከአማራው፣ ከትግሬው ባልተናነሰ የኦሮሞው አሻራ አለበት። ኦሮሞነት ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮዮጵያዊነትን የሚጠላ ኦሮሞ ኦሮሞ አይደለም። ታሪክን የማያውቅ፣ በጥላቻ የታወራ የዉሸት ኦሮሞ ነው።
http://trace.tennessee.edu/cgi/viewcontent.cgi?article=1005&context=utk_socopubs
http://gadaa.com/oduu/22246/2013/10/06/arsi-oromo-political-and-military-resistance-against-the-shoan-colonial-conquest-1881-6/

ወልቃይት ጠገዴ ግንባር ከትግራይ የተነሳ ሃይል ተደመሰሰ | ገዱ አንዳርጋቸው በወታደሮች ታጅቦ ደባርቅ ይገኛል የሙሉነህ ዮሐንስ ዘገባ



ሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ግንባር ከትግራይ የተነሳ ሃይል ተደመሰሰ | 16 ሙቶ ብዙ ቆሰለ | ገዱ አንዳርጋቸው በወታደሮች ታጅቦ ደባርቅ ይገኛል
የሙሉነህ ዮሐንስ ዘገባ
Image may contain: outdoor
ከትግራይ በሽራሮ በኩል ተከዜን ተሻግሮ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ይጓዝ የነበረውን የወያኔ ወታደራዊ ኮንቮይ አድፍጠው የቆዩ የአካባቢው ጀግኖች ከፋኞች ድባቅ መተውታል። እጅግ የሚያስደስተው ደግሞ ወያኔ ይጠቅሙኛል ብሎ ያሰባቸው ያካባቢ ሚሊሺያ ታጣቂወች ከህዝቡ ጋር አብረው ተሰልፈው የወያኔ ሃይል መውጫ እንዳያገኝ አድርገው ቀጥተውታል።
በደረሰን መረጃ መሰረት 16 ወያኔ ተገሎ ወደ 30 ሲቆስል ብዛት ያለው ቀላልና የቡድን መሳሪያወች ተማርከዋል። ሰፊውን የሁመራ ወልቃይት ጥገዴና ጠለምት መሬቶች በገፈፋ ከጎንደር የነጠቀው ወያኔ አሁንም እንደ ግጨው የመሰሉ ሰፋፊ የጠገዴ ተጨማሪ ቦታወችን ወደትግራይ ለመውሰድ ከመሞከር አልቦዘኑም። ተከዜን ተሻግረው ካልሄዱ ጤናም የለ እረፍትም የለ! ጎንደር ወስኗል! አማራ ወስኗል! ኢትዮጵያም ወደ ቀደም ክብሯ ትመለሳለች::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ር ዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሰሜን ደባርቅ ከተማ እንደሚገኝ ታወቀ:: ዛሬውኑ ዳባት ደርሶ ወደጎንደር እንደሚመለስ መረጃ አለ::
ፎቶው ያጀቡትን ዘመናዊ መኪኖችና የወታደር ጋጋታ ያሳያል። የፈሪ ዱላ! የምንትስ ባል ከሞት አያስጥል! ለልምምጥ የሄደው ገዱ የህዝብን ጥያቄ መመለስ አይችልም።
Image may contain: one or more people and outdoor
የጎንደር ሕዝብ ላይ አለቆቹ ወያኔዎች ሙሉ ጦርነት ሲከፍቱበት ከአሽከርነት የላቀ ድርሻ የሌለው የበድኑ የብአዴን መሪ ገዱ ሰልፉን እንዲያስተካክል ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ አሟጦ እየጨረሰ ነው። ወያኔም ጉርቦውን ልትፈጠርቀው አድብታ እየጠበቀች ነው።
ወያኔን በቅጡ የተረዷትና የቀደሟት የተከፉ የጎንደር ጎበዝ አለቆች ናቸው! ሰሞኑን ቆላማውን የወገራ ህዝብ ከጎበዝ አለቆች ጋር አሸማግሉኝ ምህረት ይጠይቁ እያለች ከንቱ ልፋት ላይ ነች።
የነፃነት ጥያቄ በአፈና አይመለስም!
ህዝብ ያሸንፋል©!