Friday, January 6, 2017

እስኪ ሰከን እንበል – #የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን። ቆንጅት ስጦታው



እስኪ ሰከን እንበል ———–#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን። ————- ግን እንደኛ አገርና ህዝብ አስፈሪ የህልውና አደጋ ላይ ያለ ይኖራል? እንደኛስ መላቅጡ የጠፋበት ህዝብ ይኖራል። 100 ሚሊዮን ህዝብ፣ 100 ቁዋንቁዋ፣100 የፖለቲካ ድርጅት ፣ 100 ብሄረሰብ ፤ በኢትዮጵያ የአየር ፀባይ፣ በኢትዮጵያ መልክአ ምድር፣ በኛ ጎረቤቶች፣ በኛ መንግስት፣ በኛ ድርቅና እና ራስ ወዳድነት! እስኪ አስቡት ጎበዝ ሳት ብሎን ጦርነት ውስጥ ብንገባ ምን ሊፈጠር እንደሚችል።
ተመድ፣ አአድ ገሌ መሌ ጭው ባለ ሜዳ አንድ ቁዋንዋ አንድ ሀይማኖት ላለው አገር እንኳ ምንም እንዳልፈየደ እያየን! አንድስ የሚያክል ጠላት አስቀምጠን የጠላት ያለህ፣ ጠላት አውርድ የምንል ምን ክነቶን ይሆን። ባለፉት አስርታት የወረደብን መአት እንኳን ለኛ ለአለም ትምህርት አይሆንምን? የ25 እና 40 አመት ሰቆቃና ስቃይ ያላስተማረን ምን ሊያስተምረን ነው? ምን ስንሆን ይሆን ባንክሮ ናማሰብ ማስተዋል የምንጀምረው? ወያኔን እንላለን እንጂ እኛው እራሳችን ነን ሀገራችንን በልተን እየጨረስናት ያለው። ወያኔስ ኢትዮጲያን ማጥፋት ስራው ነው። የኛስ ምን ይሉታል።
ወያኔን በርግጥ እንጠላለን። ግን ወያኔን የምንጠላበትን ድርጊት ላለማድረጋችን ምን ማረጋገጫ አለን? በየርከኑ ስንነሰነስና ስንበጣጠስ ስንት ትንንሽ ልንሆን እንደሆነ አስተውለነዋል? ተበጣጥሰን ተሰነጣጥቀንስ አማን ውለን አማን እንደማናድርስ ነጋሪ ያስፈልገናል? እኛ እኮ እስከየሩሳሌም ግዛታችን ነው ብለው የሚያልሙ አባቶች ልጆች ነን። እኛ እኮ ለአለም ጥቁሮች ሁሉ የነፃነትን ቀንዲል የለኮሱ አርበኞች ልጆች ነን። ሌሎች ከኛ ሊማሩ እንጂ ይሳለቁ ዘንድ እንዴት እንፍቀድ! አረ ተዉ ጎበዝ! አረ በባንዲራው! እኛ ስንጎማመድ እኮ የምትጎመደው ይች ምስኪን አገር ነች። ይረከቡት የሚያጡት እኮ ልጆቻችን ናቸው።
አረ በልጆቻችን! የኛ መጠላለፍ የጠላታችንን ክንድ እያፈረጠመው ነውና ወደ ልቦናችን እንመለስ። ሰከን፣ በሰል እንበል። ቅንነት ካለ ሁሉም ይቻላል። ወደ ጎን የሰበቅነውን ሰይፍ ወደ ጠላት እንቀስረው። ለህዝባችን ስንል ትንሽ ዝቅ እንበል። ዝቅ ያለን ሁሉ አንድየ ከፍ ያደርገዋል። ይሄንን የማህበራዊ መገናኛ አሳፋሪ ጦርነት ዛሬውኑ አቁመን ትግላችን ላይ እናተኩር። አገራችን አታልቅስብን። ወገናችን አይዘንብን፣ ልጆቻችን አይፈሩብን። ጠላታችንም አይሳለቅብን። የኢትዮጵያ መፃኢ እጣ ፈንታ በእጃችን ነው። ቅን ከሆንን እግዚአብሄርም ያግዘናል።
#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።
#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።

Thursday, January 5, 2017

በአየር ኃይል አብራሪዎችና ቴክኒሺያኖች ላይ እርምጃ መወሰድ ተጀመረ By posted by ብርሃኑ አየለ




በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች እና በቴክኒክሺያኖች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ምድቦች ውስጥ በአካሄደው ግምገማ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ ግንኙነት አላቸው ተብሎ በሚጠረጠሩ አባላት ላይ ከእስር እስከ ሥራ ማገድ እርምጃ እየወሰደ ነው።
በምስራቅ አየር ምድብ በተዋጊ ሄሊኮፕተር በረዳት አብራሪነት ተመድቦ የሚገኘው የመቶ አለቃ ገመቹ ሀሰን ከግምገማ በኋላ ከአየር አብራሪነት የታገደ ሲሆን የግምገማው መሪ የነበረው የአየር ኃይል ም/አዛዥ እና የዘመቻ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ማአሾ ሀጎስ ስሙን በመጥቀስ በረራ እንድታቆም የተደረገበትን ምክንያት ታውቃለህ ብሎ ሲጠይቀው መቶ አለቃም ገመቹም በንዴት አዎ አውቀዋለሁ የታገድኩበት ገመቹ ስለሆንኩ ነው ብሎ ምላሽ ሰጥቷል። ይህን ተከትሎ አብራሪው በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ከስራው ታግዶ ይገኛል።
በሌላ በኩል በምእራብ አየር ምድብ በተደረገው ግምገማ የሚግ 23 ጄትአብራሪ የሆነው የመቶ አለቃ መስራች እንዳለ በአማራ ክልል እየተካሄደ ከአለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አለህ በማለት እርምጃ ሊወሰድበት እንደሆነ ከአየር ኃይል ምንጮቻችን ገልፀዋል። መቶ አለቃ መስራች እንዳለ ላይ ስለሚወሰድበት እርምጃ ከፍተኛ የኃይል አዛዦች እየመከሩበት የሚገኙ ሲሆን እስከ አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ውሳኔ እንዳልተሰጠበት ታውቋል።
ከዚህ በፊት ከማእከላዊ አየር ምድብ ተይዘዉ የታሰሩት 3 አብራሪዎች ከ2 አመት በላይ ተፈርዶባቸዉ ናዘሬት እስርቤት ይገኛሉ። በማዕከላዊ አየር ምድብ በተደረገ ግምገማ ላይ የአየር ሃይል አባላት ስለታሰሩት አብራሪዎች በማንሳት “እነሱ ያለጥፋታቸዉ ነዉ የታሰሩት፤ አየር ሃይሉ ያለምንም ምክንያት ሰዎችን እያሰረና እያባረረ ተቋሙን እየጎዳ ነዉ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ አመራሮቹ ማስተካከል አለባቸዉ” በማለት አባላቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በአየር ሀይል አብራሪዎችና በስርአቱ ከፍተኛ የጦር አዛዦች መካከል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት እንዳለ ከአየር ሃይል ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። የአየር ሃይል አብራሪዎች ባለው የስራ ብልሹነት ምክንያት ስራዎች እየተስተጓጎሉ ነው በማለት ቅሬታቸውን ይገልጻሉ። ለስርአቱ ታማኝ ደጋፊዎች የሚባሉት አብራሪዎች ጥፋት ቢሰሩም እንኳን ተጠያቂዎች አይደረጉም።
በምስራቅ አየር ምድብ ማዘዣ በሆነው ድሬዳዋ አየር ሃይል ሶሰት ሄሊኮፕተሮችን በመግጨት ከባድ ኪሳራ በተቋሙ ላይ ያደረሰዉ ሌ/ኮ ፀጋ ዝአብ ካሳ የተባለ የሄሊኮፍተር አብራሪ በአሁኑ ሰአት ምንም እርምጃ ሳይወሰድበት በስራው ላይ ይገኛል። ተቋሙ እንደዚህ እይነት ከባድ ኪሳራ ባደረሱት አካላት ላይ እርምጃ ሳይወስድ በሌሎች አብራሪዎች ላይ አላግባብ የሚወሰዱ እርምጃዎች በአየር ሃይል አባላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታን እያስነሳ ነው።
ለአገዛዙ ታማኝ አይደሉም ተብለው በሚጠረጠሩ የአየር ሃይል አብራሪዎች ላይም ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

የወያኔ ተልዕኮ አማራን የማጥፋት ዘመቻ = መምህር አሸናፊ ሸዋርካብን በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ውስጥ እረሽነውታል፡፡ቆንጅት ስጦታው



የባህር ዳር ማረሚያ ቤት እና የወያኔ ተልዕኮ አማራን የማጥፋት ዘመቻ
በአማራዋ ፈርጥ ከተማ ባህር ዳር ሀዘን ፣ጩኸት ፣ለቅሶ ፣ሽብር ፣ሁከት በፀረ አማራው ቡድን ወያኔ የዕለት ከዕለት ጉዳይ ከሆነ አመታትን አስቆጥራልች፡፡የአማራን ህዝብ ለማጥፋት እና ለማዳከም ጠላቴ ነው ብሎ በፕሮግራም ነድፎ በ1968 ዓ.ም የተነሳው ወያኔ አማራ የሆኑና በአማራነታቸው ፅኑ አቋም ያላቸውን የአማራ ልጆች ቤት ለቤትና በአደባባይ ካለምንም ምክንያት መረሸኑ ሳያንሰው ካለው ፍርሃትና ጭንቀት የተነሳ በቁጥጥር ስር አድርጎ በማረሚያ ቤት የፍርድ እስረኛ ያደረጋቸውን የአማራ ልጆችንም ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ እየረሸነ ጭራቃዊ ተልዕኮኑን እየፈፀመ ይገኛል፡፡
በታህሳስ 24፦2009 ዓ.ም መምህር አሸናፊ ሸዋርካብን በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ውስጥ እረሽነውታል፡፡
መምህር አሸናፊ ሸዋርካብ በታሪክ ትምህርት የሁለተኛ ድግሪ የነበረው ሲሆን ሟች ወንድማችን በጎጃም ክፍለ ሃገር በአገው ምድር አውራጃ በአዲስ ቅዳም ከተማ መሰናዶ ት/ቤት የታሪክ መምህር ሲሆን ትግሁ እና ሀገር ወዳጅ የሆነ በተማሪዎቹና የስራ ባልደረባዎቹ ዘንድ ተወዳጅ አስተማሪ ነበር፡፡አሸናፊ ሀገሩን ወዳድና በተለይ ወያኔ በአማራው ላይ የሚያደርሰውን ግድያ ፣ማፈናቀል፣ዘረፋ እና ሰብዓዊ ጥሰትን አጠንክሮ ይቃወምና በአማራነቱን በፅኑ የነበረ ጀግና ነው፡፡አሸናፊ ሀገር ውስጥ የነበረው ትግል ያስቸግረው ስለነበር ሀገር ውስጥ የነበረው አደረጃጀት ከጨረሰ በኋላ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመቀላቀል ወሰነ፤ከእዚያም በሀምሌ ወር 2007 ዓ.ም ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ(አዴሃን) ለመቀላቀል መንገዱን ወደ በረሃ አደረገ፡፡ነገር ግን ሁሉም ነገር እንደጠበቀው ሳይሆን ቀረና አብሮኝ ይሞታል የትግል አጋሬ ነው ብሎ ያስከተለው አቶ ፍቃዱ አጥናፍ ብርሃኑ የተባለ የወያኔ ሰላይ አብሮት በመከተል ሁመራ ላይ ለወያኔ ደህንነቶች ሊያሲዘው ችሏል፡፡ፍቃዱ አጥናፍም ተልዕኮውን በወገኑ አሸናፊ ላይ ከፈፀመ በኋላ በወያኔ ትልቅ ምስጋና ተችሮት በአገው ምድር አውራጃ በአንከሻ ወረዳ ግምጃ ቤት ከተማ ገንዘብና ፕላን ፅህፈት ቤት ውስጥ ሹመት ተቀብሏል፡፡
አሸናፊ ሸዋርካብ አማራነቱ ሚያንገበግበው እና ሚሳሳለት ማንነቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ያረጋግጥ ነበር፤ይህም በጠላት ምርመራ ወቅት የሰሜን ምዕራብ ቀጠና የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ወንጀል መርማሪ በሆነው ባንዳ በትውልዱ አማራ በኢንስፔክተር አብረሃም ታምራት ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊና አካላዊ ጉዳት ቢደርስበትም ጀግናው እና ኩሩው መምህር አሸናፊ ሸዋርካብ በአማራነቱ ምንም ሳያፈገፍግ እስከ ዕለተ ሞቱ ተጋፍጧል፡፡ወያኔ በአሸናፊ ላይ የአምስት(5) አመት የእስራት ቅጣት በይኖበት የነበረ ቢሆንም አማራን በማሰር ብቻ የማይረካው ወያኔ በቀን 24 ፡04፦2009 ዓ.ም አሸናፊን ከማረሚያ ቤት ውስጥ ገድሎታል፡፡
የቀብር ስነ ስርዓቱም በደቡብ ጎንደር አዲስ ዘመን በቀን 25፡04፥2009 ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡
ለሟች በቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን እየተመኘን አዴሃንም ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል፡፡ድርጅታችን አሸናፊ የሰዋለትን አላማ አማራን ከጥፋት በማዳን ዳር እናደርሳለን፡፡

የአማራ ህዝብ በቆራጥ ልጆቹ ማንነቱን ያስከብራል!!

Wednesday, January 4, 2017

የመንግስት የውጭ እዳ፣ ከ 2 ቢ.ዶላር ወደ 22 ቢ.ዶላር (በአስር ዓመት Written by  ዮሃንስ ሰ.



#Ethiopia የመንግስት የውጭ እዳ፣ ከ 2 ቢ.ዶላር ወደ 22 ቢ.ዶላር (በአስር ዓመት)
ብድሩ፣ ለትምህርት…የሚውል ነው።ግን፣ ጨርሶ አንድ ቃል ማንበብ የማይችሉ ተማሪዎች በዝተዋል። ………. የወለድ ክፍያው፣ በአመት 350 ሚሊዮን ዶላር ሆኗል።
Written by  ዮሃንስ ሰ.
• አምና የውጭ እዳ ለመመለስ፣ 1 ቢሊዮን ዶላር ተከፍሏል።
• የወለድ ክፍያው፣ በአመት 350 ሚሊዮን ዶላር ሆኗል።
• አዎ፣ ብድሩ፣ ለትምህርት፣ ‘ለመሰረተ ልማት’ የሚውል ነው።
• ግን፣ ጨርሶ አንድ ቃል ማንበብ የማይችሉ ተማሪዎች በዝተዋል።
ይሄ ነገር፣ እንዴት ቢገለፅ ይሻላል? የእዳውና የወለዱ ሸክምኮ፣ “በደብል ዲጂት” ሽቅብ እየመጠቀ ነው። ሸክሙ፣ ምንኛ ከባድ እንደሆነ፣ በውል ለመገንዘብና በደንብ ለመግባባት፣ ሁነኛ ዘዴ ያስፈልገናል። በምስል እያየን ለማገናዘብ እንሞክር? ወይስ በፅሁፍ… በቃላት ቢገለፅ ይሻላል?
“በምስል ወይስ በቃላት” እያልን የምናማርጠው፣ ለመቀናጣት እንዳልሆነ ይገባችኋል። እንዲያውም፣ ከጭንቀት የመነጨ ይመስላል። በእርግጥም፣ ጉዳዩ፣ የሚያሳስብ ወይም የሚያስጨንቅ ስለሆነ፣ አስተማማኝ የመግባቢያ ዘዴ ለመምረጥ ብንሞክር አይገርምም።
ይሄንን፣ እንደ ቀላል ነገር አትቁጠሩት። ስለ እዳውና ስለ ወለዱ አይደለም የማወራው። በምስል እና በቃላት አማካኝነት… መረጃዎችን የማገናዘብና የመግባባት ችሎታ፣ ቀላል ብቃት አይደለም። በየእለቱ ፅሁፍ እናነባለን – መልእክቱም ይገባናል። ‘ግራፍ’ አይተን፣ የትኛው እንደቀነሰና እንደጨመረ ወይም የትኛው እንደበለጠና ስንት እንደደረሰ እንገነዘባለን።
በአግባቡ እስከተገለፀ ድረስ፣ በፅሁፍና በመስል መግባባት፣ ብዙም አያስቸግረንም። ለሰላምታ የመነጋገር ያህል ነው። ወይም ደግሞ፣ በሁለት እግር የመራመድ ያህል፣… ገና ስንወለድ፣ አብሮን የተፈጠረ “ነባር ችሎታ” ይመስለናል። ግን አይደለም። ለነገሩማ፣ መራመድም፣ “ነባር ችሎታ” አይደለም። በፅሁፍና ‘በግራፍ’ መግባባትማ… በብዙ ቢሊዮን ዶላርም፣ ተፈልጎ የማይገኝ እየሆነብን ነው። እንዴት? ማንበብና ማባዛት የማይችሉ ተማሪዎች ተበራክተዋል። እና፣ እንዴት ነው፣ “ተማሪዎች” ብለን ልንጠራቸው የምንደፍረው? በየእለቱ፣ ክፍል ውስጥ የምንሰጣቸው ነገርስ፣ እንዴት “ትምህርት” ተብሎ ይጠራል? ማናናቄ አይደለም። ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበት፣ ብዙዎች የደከሙበት ጉዳይ እንደሆነ እየካድኩ አይደለም።
ከመንግስት በጀት ውስጥኮ፣ ሩቡ ያህል፣ ለትምህርት ነው የሚመደበው። ‘የትምህርት ጥራትን እናሻሽላለን’ ብለው፣ በብድርና በእርዳታ፣ ላይ-ታች የተሯሯጡ የውጭ መንግስታትና አለማቀፍ ተቋማትም ብዙ ናቸው (አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጃፓን… የአለም ባንክ፣ ዩኔስኮ፣ ዩኒሴፍ፣ ሴቭ ዘ ቺልድረን… በጣም ብዙ ናቸው)። ለዚያውም፣ ለብዙ ዓመታት ነው የተሯሯጡት – ለአስርና ከዚያ በላይ ዓመታት።
ግን፣… ዛሬም ድረስ፣ የትምህርት ጥራት፣… ገና ‘ጠብ’ አላለም። ይሄ፣ “በይመስለኛል” የተነገረ መርዶ አይደለም። የቆዩና ያረጁ መረጃዎችን ብቻ በመያዝ የተነገረ ድምዳሜም አይደለም።
ከአዳዲስና ሰፋፊ ጥናቶች የተገኘ መረጃ ነው።
በትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድና በዩኒሴፍ መሪነት፣ በአለማቀፍ የምርምር ተቋማት አማካኝት፣ በ297 ትምህርት ቤቶች የተካሄደውን ጥናት መጥቀስ ይቻላል። ቀለል ተደርጎ የተሰራ ‘ግራፍ’፣ ለአብዛኞቹ ተማሪዎች፣ ትልቅ ‘እንቆቅልሽ’ እንደሚሆንባቸው ሪፖርቱ ይገልፃል።
ለምሳሌ፣ “የወለድ ክፍያን ለማሳየት የተዘጋጀውን ግራፍ ተመልከቱ። በ2007 ዓም፣ የኢትዮጵያ መንግስት፣ ስንት ሚሊዮን ዶላር የብድር ወለድ እንደከፈለ ግለፁ” የሚል ጥያቄ፣ በእጅጉ ይከብዳቸዋል – ለአራተኛ ክፍል ተማሪዎች።
“255 ነዋ። ማለትም 255 ሚሊዮን ዶላር” ብለው በቀላሉ መመለስ አይችሉም። ከዚህ የቀለለ ጥያቄ ቀርቦላቸው፣ በትክክል መመለስ የቻሉ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች፣ 23% ብቻ ናቸው። ከመቶ ተማሪዎች መካከል፣ 23ቱ ብቻ።
“ይሄማ መራቀቅ ነው” ልትሉ ትችላላችሁ። ፈፅሞ አይደለም። ግን ይሁን። የማንበብ ችሎታም እንደሰማይ ሩቅ እየሆነ ነው።
በእንግሊዝ መንግስት እርዳታ ተጀምሮ፣ የኔዘርላንድና የአየርላንድ መንግስታትም ድጋፍ ተጨምሮበት፣ ለአስር ዓመታት በስፋት የተካሄው ‘ያንግ ላይቭዝ’ ጥናት፣ አዳዲስ መረጃዎችን ይዞ መጥቷል። አዲሱ መረጃ፣ የ12 ዓመት ልጆች ላይ ያተኮረ ነው። ልጆቹ… ግማሽ ያህሉ፣ 6ኛ ክፍል ደርሰዋል። ሌሎቹ ደግሞ፣ በአብዛኛው ከ3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ላይ ናቸው።
ጥሩ። ግን፣ የማንበብ ችሎታቸው እንዴት ነው?
ከመቶ ልጆች መካከል 35ቱ፣ አንዲት ዓረፍተነገር እንኳ ማንበብ አይችሉም (በየትኛውም ቋንቋ)።
የሂሳብ ችሎታቸውስ? ለምሳሌ የማባዛት ችሎታቸው እንዴት ነው? ለልጆቹ የቀረበላቸው የማባዛት ጥያቄ ቀላል ነው። 2 x 4 ስንት ይሆናል?
ከመቶ ተማሪዎች መካከል፣ 30ዎቹ ጥያቄውን በትክክል መመለስ አልቻሉም። አትርሱ። የ12 ዓመት ልጆች ናቸው። አብዛኞቹም፣ ከሦስተኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል የደረሱ። ግን፣ ሲሶዎቹ፣ ገና… ማባዛት አይችሉም።
ሌላ አዲስ ጥናትም አለ – በአሜሪካ መንግስት እርዳታ አምና የተካሄደ ጥናት። የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎችን ተመልከቱ።
ከመቶ ተማሪዎች መካከል 20ዎቹ፣ ፈፅሞ አንዲትንም ቃል ማንበብ አይችሉም።
ከመቶ ተማሪዎች መካከል፣ ዓረፍተነገር አንብበው መረዳት የሚችሉት ከሃያ ያንሳሉ። 80 ከመቶ ተማሪዎች፣ አንብበው መረዳት አይችሉም።
ይሄ ትልቅ ችግር ነው – ከእዳና ከወለድ ሸክም በእጅጉ የሚበልጥ፣ የሚያሳስብና የሚያስጨንቅ ችግር!
ግን፣ ከዚህም የባሰ ችግር አለ።
የፖለቲካ ቁማር ይበልጥብናል
አብዛኞቹ የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች፣ አንዲት ዓረፍተነገር አንብበው መረዳት እንደማይችሉ አየን። 2 ሲባዛ በ4 ስንት እንደሚሆን ማስላት የማይችሉ ተማሪዎችን ተመለከትንም። እንዲህ አይነት አሳሳቢ ችግር የተጋረጠበት ሰው፣ ምን ማድረግ አለበት?
ለጤናማ አስተሳሰብ፣ ክብር ያለው ሰው፣… ከምር ጉዳዩ አሳስቦት፣ “የዚህ ችግር መንስኤ ምንድነው? ከምን ጋር የተያያዘ ነው? ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሄዎቹስ ምንድናቸው?” ብሎ ይመረምራል።
አብዛኞቻችን ግን፣ ያን ያህልም፣ ከምር አያሳስበንም። “የችግሩ መንስኤና መፍትሄ”… ምናምን… ብሎ ማሰብ፣ ሞኝነት የመስለናል። ያው፣ እንደተለመደው፣ ከሁሉም በፊት፣ “የፖለቲካ ጨዋታ” ይቀድምብናል – ጎራ ለይተን ‘ቲፎዞ’ ለመሆን። በቃ፣ ‘ጌም’ ነው።
አንዳንዶቹ፣ የገዢው ፓርቲ ጭፍን ደጋፊ በመሆን፣ ትምህርት ምንኛ እጥፍ ድርብ እንደተስፋፋ፣ ትምህርት ቤቶች እንደተበራከቱ፣ ‘የሚሊዬኔም ግቦች’ እንደተሳኩ… እለት በእለት በመዘርዘር፣ ነገሩን ዋና የፖለቲካ መቆራቆሻ ያደርጉታል።
ገሚሶቹም፣ በጭፍን ተቃዋሚነት፣ መንግስትን ለማብጠልጠል፣ ትልቅ አዳፍኔ መሳሪያ አገኘን ብለው፣ የውግዘት ውርጅብኝ ለማዝነብ ይሽቀዳደማሉ። እንዲያውም፣ ሁሉም ተማሪ፣ ማንበብና መደመር የማይችልበት ጨለማ እንዲፈጠር እስከመመኘትም ይደርሳሉ – መንግስትን ይበልጥ ለማውገዝ።
ታዲያ ከሁሉም የከፋው ችግር፣ እንዲህ አይነት የጭፍንነት ችግር አይደለም ትላላችሁ?
እና ምን ተሻለ?
ከጭፍን የድጋፍና የተቃውሞ ስካር ተገላግለን፣ የችግሮቻችንን መንስኤዎች ለማጥናትና መፍትሄ ለመፈለግ፣ በጊዜ ብንጣጣር ይሻላል።
አለበለዚያኮ፣ ጉዟችን ወደ ጨለማ ነው የሚሆነው። አንብቦ መረዳትና የሂሳብ ስሌት የማይችሉ የሦስተኛና የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች እየተበራከቱ እያየን፣ ለፖለቲካ ጨዋታ መሽቀዳደም ሞኝነት ነው።
በበኩሌ፣ ስለመንስኤውና ስለመፍትሄው፣ ለመወያያ የሚሆኑ መረጃዎችንና የቁምነገር ሃሳቦችን ይዤ እመጣለሁ።
ለዛሬ ግን፣
በአንድ በኩል፣ በፅሁፍና በምስል፣ በቃላትና በ’ግራፍ’፣ መረጃዎችን የመግለፅና የማገናዘብ ችሎታን ቀለል አድርገን እንዳናይ ለማስታወስ በመመኘት፣…
በሌላ በኩል ደግሞ፣ የውጭ እዳና ወለድ፣ ራሱን የቻለ ትልቅ ችግር እንደሆነ እንድንገነዘብና መፍትሄ እንድናበጅለት አስቤ፣ በምስል ያዘጋጀኋቸውን መረጃዎች ተመልከቱልኝ።
መረጃዎቹ፣ ባለፈው ሳምንት በገንዘብ ሚኒስቴር ከተሰራጨው የብድር መረጃዎች ሪፖርት በመነሳት ያሰባሰብኳቸው ናቸው – የበርካታ አመታት ሪፖርቶችን በማሰስ።
መቼም፣ በምስል አጠናቅሬ ያቀረብኳቸውን መረጃዎች፣ በፅሁፍ አልደግምባችሁም። ግን… አንድ ሁለቱን ብቻ ልድገማቸው።
እዳ ለመክፈል የሚውለው የውጭ ምንዛሬ፣ በሦስት ዓመት ልዩነት በእጥፍ ጨምሮ፣ 1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱና ከዚያም ማለፉ፣ ለአገሪቱ ትልቅ ፈተና ነው። በተለይ ደግሞ፣ የኤክስፖርት ንግድ እያደገ አለመሆኑ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ያባብሳል።
በእርግጥ፣ እስካሁን፣ ከፍተኛ ቀውስ አልተፈጠረም – በሁለት ምክንያቶች።
አንደኛ፣ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቀንሷል። በዚህም ምክንያት፣ ለነዳጅ ግዢ የሚውለው የውጭ ምንዛሬ በግማሽ ቀንሷል። 1.2 ቢሊዮን ዶላር ዳነ ማለት ነው። ለዚያምኮ፣ ተገዝቶ የሚመጣው ነዳጅ አልቀነሰም። እንዲያውም ጨምሯል። ከ2005 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር፣ አምና ተገዝቶ የመጣው የነዳጅ መጠን በእጥፍ ይበልጣል። በዋጋ ግን ያንሳል። ይህም፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ፣ ክፉኛ ከመቃወስ እንድንተርፍ አግዞናል – እስካሁን።
ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ቀውስ እንዳይፈጠር የረዳን ሁለተኛ ነገር፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቤተሰብ የሚልኩት ዶላር መጨመሩ ነው። ከ2003 ወዲህ በእጥፍ ስለጨመረ፣ አምና ወደ አራት ቢሊዮን ዶላር ተጠግቷል።

አዲስ አበባ “በአዲሱ ማስተር ፕላን ወደ ጎን መለጠጧን አቁማ ወደ ላይ ከፍ ማለት ትጀምራለች” ኮሚሽኑ ቆንጅት ስጦታው



አዲስ አበባ "በአዲሱ ማስተር ፕላን ወደ ጎን መለጠጧን አቁማ ወደ ላይ ከፍ ማለት ትጀምራለች" ኮሚሽኑ
በ1994 ዓ.ም ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ዘጠነኛው ማስተር ፕላን በ2006 ዓ.ም የመጠቀሚያ ጊዜው አብቅቷል፡፡ አሥረኛው ማስተር ፕላን ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር አቀናጅቶ ለማካሄድ በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም፣ ከኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ በመቅረቡ እንዲቀር ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት ባለፉት አራት ዓመታት አዲስ አበባ ይፋ ማስተር ፕላን ሳይኖራት ቆይቷል፡፡
ይሁንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ማስተር ፕላኑ ከመፅደቁ በፊት የወረዳ፣ የክፍላተ ከተማና ማዕከል የሚገኘው ዋናው ምክር ቤት ጋር በጋራ እንዲወያዩበት ማድረጉን ገልጿል፡፡
ታኅሳስ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በተካሄደው ውይይት በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ወይም 25 ዓመታት ተግባራዊ የሚደረገው ማስተር ፕላን ይዘትና ይዟቸው የሚመጣቸው ተስፋዎች ላይ፣ የቀድሞው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ማቴዎስ አስፋው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ በ130 ዓመት ታሪኳ ዘጠኝ ማስተር ፕላን አስተናግዳለች፡፡
ከዚህ ቀደም ወደ ጎን ስትለጠጥ ቆይታ ያላትንም 54 ሺሕ ሔክታር መሬት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ግንባታ ያካሄደችበት አዲስ አበባ፣ ከኦሮሚያ ክልል በደረሰው ከፍተኛ ደም አፋሳሽ ተቃውሞ ሳቢያ “በአዲሱ ማስተር ፕላን ወደ ጎን መለጠጧን አቁማ ወደ ላይ ከፍ ማለት ትጀምራለች” ሲሉ አቶ ማቴዎስ ገልጸዋል፡፡
በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር አሁን ካለበት አራት ሚሊዮን በተጨማሪ፣ 1.3 ሚሊዮን ሕዝብ አዲስ ነዋሪ ሆኖ እንደሚመዘገብና ይህ ሁሉ ሕዝብ በመሀል ከተማ እንደሚሰፍር ይታወቃል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ወይዘሮ ፋናዬ ይርዳቸው ስለ ልጃቸው ያቀረቡት አቤቱታ ቆንጅት ስጦታው



የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ወይዘሮ ፋናዬ ይርዳቸው ስለ ልጃቸው ያቀረቡት አቤቱታ
============
24/4/2009ዓ.ም
ለኢትዮጵያሰብዓዊመብትኮሚሽን
አዲስአበባ
ጉዳዩ፡-የልጄ የተመስገን ደሳለኝን ጤንነትና የጉብኝት ሁኔታን ስለማወቅ
የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ ይዤ እናንተው ጋር መመላለስ የግድ ሆኖብኝ ዛሬም ከደጃችሁ መጥቻለሁ፡፡ ባሕሌና አስተዳደጌ ያስተማረኝ አንድቦታ ለአንድ ጉዳይ መመላለስለ ችግሩ ባለቤትም ሆነ ለመፍትሄ ሰጭው አሰልቺ መሆኑን ነው፡፤ እውነት ለመናገር ዛሬም ወደ በራፋችሁ ስመጣ እንደው እነዚህን ሰዎች ስራ እያስፈታኋቸው ይሆን ከሚል ሃፍረት ጋር ነው፡፡ ግን ምን ላድርግ? ጉዳዩ ልጅን የሚያኽል የስጋ ክፋይ ነገር ሆነብኝ፡፡ እንድትረዱልኝ የምፈልገው እኔም ተቸግሬ እያስቸገርኳችሁ መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም ጭንቀት እረፍት ስላሳጣኝና ጤናዬንም እየፈተነኝ በመሆኑ የመፍትሔ ያለህእ ያልኩ አለሁ፡፡
ከዚህ ቀደም እናንተ መ/ቤት ብቅ ያልኩት ልጄን ለመጎብኘት ፈቃድ እንዳገኝ ትተባበሩኝ ዘንድ ነበር፡፡ በወቅቱ የተሰጠኝ ምላሽ እጅግ እንዳስደሰተኝ በአደባባይ መናገሬን ማንምያውቀዋል፡፡ አንጀቴ እንደራሰም ሁሉም ተረድቶታል፡፡ ዛሬም በድጋሜ ስመጣ በባለፈው መፍትሔ ተበረታትቼ ነው፡፡ ይህን ሳልናገር ማለፍ በእኔ እድሜ ለሚገኝ ሰው መልካም አይሆንም፡፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የዛሬውም አቤቱታየ ተመሳሳይ ምላሽ እንደሚኖረው በሙሉ ልቤ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
በዝዋይ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ልጄ ተመስገን ደሳለኝ ከታሰረ ሁለት ዓመታት አለፉ፡፡ በዚህ ግዜ ውስጥ የወገብ ህመምና የጨጓራ በሽታ እየባሰበት መምጣቱን በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ፡፡ አንደኛው ጆሮውም ስቃይ እየፈጠረበት መከራውን እንዳባሰበት እሱን ባየሁበት ወቅት ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ይባስ ብሎም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አለፍ አለፍ እያለ ያለመጎብኘት እገዳ ይጥልበታል፡፡ ይኽን ታዲያ ምን ትሉታላችሁ? በእስር ላይ ሌላ እስር አይደለምን? እነዚህና መሠል ተደራራቢ ችግሮች እየከፉ መምጣታቸው በእኔና በተቀሩት ጎብኝዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ስጋትና ጭንቀትን ፈጥሮብናልን፡፡
ከሳምንንታት በፊት ህዳር 28/2009ዓ.ም የዝዋይ ማረሚያ ቤት ሰዎች ልጄ የት አንዳለ አናውቅም በማለታቸው ለአስር ቀናት እምጥ ይግባ ስምጥ ሳላውቅ በእየሰር ቤቱ ከሚንከራተቱት ልጆቼ ጋር ልጄን ፈለኩት፡፡ አለገኘሁትም፡፡ የወለደ አንጀት አልስች ልቢለኝ “እርሜን ላውጣ” እያልኩኝ ልጄን ስል ሰነበትኩኝ፡፡ መቼምአምላክ ሰሚነውና በአስረኛው ቀን ታህሳስ 7/2009ዓ.ም በዝዋይ እስር ቤት ተመሰገን ተገኘ አሉኝ፡፡
ደስም አለኝ፡፡ ግን ምን ዋጋ አለሁ ይኼን ደስታ ማቅ የሚያለብስ ሌላ ወሬ ደረሰኝ፡፡ ‹‹የልጄን ዓይን አያለሁ›› ብዬ በተነሳሁ ውዬ ሳላድር በድጋሜ የክልከላው ዕጣ እኔኑ ገጠመኝ፡፡
ከዚህም አልፎ ህመሙ እንደ ባሰበትና ከእስር ቤቱ ቅጥር ውጭ ወደሚገኘው ባቱ ሆስፒታል እንዳደረሰው ልጆቼ ቢደብቁኝም ስለጉዳዩ የሚያውቁ ሰዎች ነግረውኛል፡፡ ይህን ከሰማሁ ጀምሮ ተመስገን ስል ዛሬም አለሁ፡፡
ብቻ ተባበሩኝ፤ እርዱኝ፡፡ ይኼን መከራ ብቻዬን ለመወጣት አቅም የለኝም፡፡ የምታግዙኝ ነገር እንዳለ ስለተረዳሁ ነው የእናንተንም ደጅ የምጠናው፡፡ እገዛችሁ ልጄን የማየት ምኞቴንና እርሱም የሚያስፈልገውን የህክምና እርዳታ በአፋጣኝ እንደሚያስገኝለት ሙሉ ዕምነት አለኝ፡፡ እስኪ ለሁሉም ፈጣሪ ይርዳን፡፡
ከሰላምታጋር፡፡
ወ/ሮ ፋናዬይርዳቸው
ግልባጭ
 ለጠቅላይሚኒስቴር ጽ/ቤት
 ለተወካዮችምክርቤትአፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት
 ለተወካዮችምክርቤትየህግ፣ ፍትህናአስ/ር ጉዳዮች ቋ ኮሚቴ
 ለጠቅላይዐቃቤህግ ጽ/ቤት
 ለሰብዓዊ መብቶችጉባኤ (ሰመጉ)
 ለሕዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም
 ለኢትዮጵያቀይመስቀልማሕበር
 ለሚዲያዎች

በእነ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ አስተባባሪነት ቂሊንጦን በማቃጠልና ታራሚዎችን በመግደል የተጠረጠሩ 121 እስረኞች ተከሰሱ EthiopianReporter.com



ከጥር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ከእስር ለማምለጥ ከዶ/ር ፍቅሩ ማሩና ከተለያዩ እስረኞች ጋር ሲወያዩ የከረሙ ታራሚዎ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ቂሊንጦ ጊዜያዊ የተከሳሾች ማረፊያ ቤትን በማቃጠልና የ23 እስረኞችን ሕይወት አጥፍተዋል የተባሉ 121 እስረኞች ተከሰሱ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ