Thursday, December 8, 2016

የአውሮፓ ህብረት በዶክተር መረራ መታሰር በእጅጉ እንዳሳሰበው ገለጸ።ቆንጅት ስጦታው



የአውሮፓ ህብረት በዶክተር መረራ መታሰር በእጅጉ እንዳሳሰበው ገለጸ።
በሀገር ቤት ውስ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የሆነው የኤፌኮ ሊቀመንበር የሆኑት መረራ ጉዲና ለእስር የተዳረጉት በአውሮፓ ፓርላማ ሀገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራርያ ሰጥተው በመመለሳቸው ነው። ህብረቱ እስራቱን አውግዞ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል። ዝርዝር አለው። http://mereja.com/…/chair-of-the-european-parliament-s-subc…

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ!Muluneh Yohannes



የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ!
በዛሬ ቀን ወያኔ የብሄረሰቦች ባሕል ብሎ ያመጣውን ማወናበጃ በጎንደር ዬኒብርሲቲ አልተከበረም። ምክኒያቱም ወልዲያ ላይ የታሰሩ ተማሪዎች አሉ። ከጥቂት ቀናት በፊት በግፍ የታሰሩ ከ120 በላይ የጎንደር የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብር ሸለቆ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ ስለሆነ ተማሪው አድማ ላይ ነው።
በተጨማሪም በሃገራችን ገበሬ ላይ የተከፈተው የግፍ ጦርነት በህዝባችን ላይ ወያኔ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ነው የሚል እልህና ቁጭት በተማሪው ሁሉ ላይ ፈጥሯል። ተማሪዎች እንደገለፁት ብዙወችም ወገን እያለቀ ቁጭ ብለን አናይም በማለት እየሸፈቱ በርሃ እየገቡ ነው። ሁኔታው እጅግ እየተካረረ የመጣበት የጎንደር ሁኔታ ወያኔን ጭንቅ ውስጥ ከቶታል። ሰፋ ያለ ከተማዎችን ያቀፈ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ተማሪዎች እንደገለፁት እነሱም ትምህርት አቁመው ህዝባቸውን ወደመታደግ እንደሚገቡ በቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ በጎንደሬው ገበሬ ላይ ያወጀው ጦርነት እራሱን መልሶ እየለበለበው ነው። ጦርነቱም በርትቶ ቀጥሏል። በየቀኑ ብዛት ያለው የወያኔ ሙትና ቁስለኛ ወደ ጎንደርና ሌሎች የወረዳ ከተማ ጤና ማእከላት እየተከማቸ ስለመሆኑ ዛሬም የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ሙሉነህ ዮሃንስ
Muluneh Yohannes

Tuesday, December 6, 2016

በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተቃጥሏልMuluken Tesfaw



በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተቃጥሏል፤
o በዐማራ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቸልታ እያየው ነው፤
Muluken Tesfaw – የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በዐማራው ሕዝብ ላይ እያደረሰው ያለው በደል ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ሒዷል፤ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ የእልቂት አዋጅ ታውጇል፡፡ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል እየተጋደሉ ያሉ ዐማሮች በሕይወታቸውና በንብረታቸው ላይ ይህ ነው የማይባል ጉዳት ደርሷል፡፡ በተለይ በሰሜን ጎንደር በአርማጭሆና በወገራ ወረዳዎች የዐማራ ገበሬዎች ቤት እየተቃጠለ፣ ንብረታቸው እየተወረሰና እወደመ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችና አዛውንቶች በሜዳ ላይ ተበትነዋል፡፡
ሰሞኑን ከኅዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በወገራ ወረዳ በእንቃሽና ጃኖራ ቀበሌዎች ይኖሩ የነበሩ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ተበትነዋል፡፡ በጎተራና በአውድማ ያለ ሰብል ከከባድ መሣሪያ በሚወጣ እሳት ዶጋ አመድ ሆኗል፡፡ በ2007/8 ዓ.ም. በነበረው ድርቅ ያላገገሙ ቤተሰቦች ዘንድሮ ያመረቱት ምርት በወያኔ መንግሥት ያለምንም ምሕረት ወድሟል፡፡ ይህ የለየለት አረመኔያዊ ተግባር ሲሆን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጉዳይ ቢሆንም በቸልታ እየታየ ነው፡፡
ዛሬ ከተጎጅ ቤተሰቦች ጋር ባደረግነው ውይይት በእንቃሽ ቀበሌ ከ50 በላይ ቤቶች ወድመው ወደ 200 የሚሆኑ ቤተሰቦች ተበትነዋል፤ በጃኖራ ቀበሌም ተመሳሳይ ውድመት ደርሷል፡፡ ትናንት እና ዛሬ ተበትነው የሚገኙ ቤተሰቦች ወደ 500 እንደሚደርስ ተጎጅዎች ተናግረዋል፡፡ የሚከተሉት አባውራ ቤቶችና ቤተሰቦች ስም ዝርዝራቸውን ያገኘናቸው ነው፤
ስም የቤተሰብ ብዛት ቀበሌ
1) ምስጋነው አጠኔ 12 እንቃሽ
2) መለሠ ተሾመ 7 እንቃሽ
3) ተሾመ ደሴ 5 እንቃሽ
4) ታደለ መልሰው 4 እንቃሽ
5) ደመወዝ ነጋሽ 10 እንቃሽ
6) ለከው ይለፉ 10 እንቃሽ
7) ካሣው ታየ 5 እንቃሽ
8) ዘሪሁን ተዘራ 4 እንቃሽ
9) ንጉሥ ዘሬ 3 እንቃሽ
10) ታከለ ማረው 4 እንቃሽ
11) ቀኑ ገሠሠ 2 እንቃሽ
12) ያለው አበበ 9 እንቃሽ
13) ደጉ በዜ 5 እንቃሽ
14) መሳፍንት ተስፋ ጃኖራ
የችግሩ አሳሳቢነት ከዚህ ላይ የተገለጸውን ያክል ብቻ አይደለም፡፡ በጎዳና የተበተኑ ሕጻናትንና አቅመ ደካማ ሰዎችን ልቅሶ መስማትም የበለጠ የሚያም ነው፡፡ ማንኛውም በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እልቂት የሚያሳስበው ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ይህን አረመኒያዊ ድርጊት እያወገዘ በሚቻለው ሁሉ እንዲያግዝም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ያስመዘገቡት ዝርዝር መረጃ Muluken Tesfaw

  


በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ያስመዘገቡት ዝርዝር መረጃ – Muluken Tesfaw
በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬዎች በትግሬ ወያኔ ፋሽስታዊ ድርጅት የተቃጣባቸውን ጀምላ ዕልቂት በሚገባ ለመመከት ችለዋል፡፡ በጎበዝ አለቆች የተደራጁት የቆላ ወገራ ገበሬዎች በተደጋጋሚ ከሦስት ጊዜ በላይ የመጣውን የወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቡድን እንዳለ ሲያረግፉት በቤታቸውና ንብረታቸው ላይ በከባድ መሣሪያ ማቃጠልን መርጧል፡፡ ይህንንም በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በሦስት ጊዜ ውጊያው የሚከተሉት ድሎች ተመዝግበዋል፤
ኅዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በነበረው ውጊያ 22 የወያኔ ወታደሮች ሲገደሉ 14ቱ ደግሞ በከባድ ቆስለው የመጣው ወታደር ሙትና አስከሬን ሆኖ ተመልሷል፡፡
ኅዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በቀጣዩ ቀን ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው መጥቶ ጦርነቱ ቀጥሎ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ደግሞ 10 ወያኔዎች ተገድለው 7 ቆስለው ተመለሱ፡፡
ኅዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በባንዳዎች የሚመራ የወያኔ ጦር ድንገተኛ ጦርነት ከፍቶ ነበር፡፡ በዚህ ዕለት ደግሞ ከፍ ያለ ድል በወገራ ገበሬ ታጋዮች ተመዘገበ፡፡ 24 የነፍሰ በላ አስከሬኖችና 14 የቆሰሉ ወታደሮች ተጭነው አካባቢውን በግዴታ ለቀዋል፡፡
የተማረከ የጦር መሣሪያ፤
አንድ መትረየስ ከ260 ጥይት ጋር እንዲሁም 56 አውቶማቲክ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬ ተጋድሎ እጅ ገብቷል፡፡
ከተገደሉ የወያኔ ወታደሮችና ባለሥልጣናት ጥቂቶቹ
ኮሎኔል ይመር መሰለ አቡሃይ (የጸረ ሽምቅ ወታራዊ ግብረ ኃይል አዛዥ)፣ ምክትል ሳጅን ዋጋዬ ጫቅሉ (የፀረ ሽምቅ ግበረ ኃይል አመራር) እንዲሁም ስሙ ለጊዜው ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ይገኙበታል፡፡
በዐማራ ገበሬዎች ላይ የደረሰ ጥፋት፤
ሴት ምላስና ሰበንተራ በተባሉ አካባቢዎች በቤታቸው ውስጥ የነበሩ አንድ አቅመ ደካማ ሽማግሌ አዛውንት እንዲሁም አንድ ልጅ ተገድለዋል፡፡ በተጨማሪም ብዙ የዐማራ ገበሬዎች ቤት በጅምላ እንዲነድ ሆኗል፡፡
(ይህ ሪፖርት የተሠራው በተጋድሎው በሰነበቱ የዐማራ ገበሬዎች መረጃና ብሎም በፍላገታቸው መሠረት መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን)

Monday, December 5, 2016

በዶ/ር መረራ እስርና በመብት ረገጣው ዙሪያ አሜሪካ አዲስ ጥረት ጀመረች ; ዋዜማ ራዲዮ



ዋዜማ ራዲዮ-የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና መታሰር በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አንድ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት አማካሪ ገለፁ።
በመጪዎቹ ቀናት የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ቅሬታና ጥያቄ ለማቅረብ እየተሰናዱ መሆኑን ያመለከቱት አማካሪው አርብ ዕለት በተደረገ ውይይት የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተከታታይ እርምጃዎች ለመውሰድ ማቀዱን አመልክተዋል።
“የዋሽንግተን አስተዳደር የኢትዮጵያን መንግስት ላለማስቆጣት በብዙ ጉዳዮች ላይ ለዘብተኛ አቋም ነበረው፣ ይህ ግን የሚቀጥል አይመስለኝም” ብለዋል ላለፉት አስራ ስድስት አመታት በአፍሪቃ ጉዳይ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን ያማከሩት ዲፕሎማት።
በአሜሪካ የስልጣን ሽግግር የሚደረግበት ወቅት ቢሆንም አዲሱ አስተዳደር ጉዳዩን በበለጠ ትኩረት ይመለከተዋል ብለው እንደሚገምቱ እኝሁ አማካሪ ለዋዜማ ተናግረዋል።
“የዶ/ር መረራ መታሰር ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የተከሰተውን ህዝባዊ አመፅ ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ ‘አስመሳይነት’ እንጂ ፈፅሞ ችግሩን የሚፈታ እንዳልሆነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈፀመው አፈና ሀገሪቱንም ሆነ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ወደተሻለ መንገድ የሚያደርሱ አይደሉም” ይላሉ ዲፕሎማቱ።
“ከመጪዎቹ ቀናት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የማሻሻያ እርምጃ እንዲወስድ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ይደረጋል። ማሻሻያ ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆነ ግን ጠንከር ያለ እርምጃ መውስድ አስፈላጊ መሆኑን ከመግባባት ተደርሷል” ይላሉ አማካሪው።
“የፀጥታ ትብብራችንን እንደመደራደሪያ ማቅረብ የሚያዋጣ አይደለም ……. ለተሻለች ኢትዮጵያ- ህዝብን ማዳመጥና ጥያቄውን የሚመጥን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል” ሲሉ ያክሉበታል።
“ከወራት በፊት ዶ/ር መረራን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ አግኝቼው ነበር፣ ለኦሮሞ ህዝብ ጥያቄና ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሂደት መወሰድ ባለበት እርምጃ ላይ ምኞቱን አጋርቶኛል። መንግስት ይህን አይነት አስተያየቶችን ለመስማት ካልፈቀደ ሀገሪቱን ወደባሰ ቀውስ ይገፋታል” ብለዋል።
ዶ/ር መረራ በአውሮፓ ህብረት በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ በአንድ አዳራሽ ተገኝተዋል ተብለው ወደሀገር ቤት ሲመለሱ መታሰራቸው ይታወሳል።
የአውሮፓ ህብረት የዶ/ር መረራን መታሰር በማውገዝ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የኢትዮጵያን መንግስት በዝግ ዲፕሎማሲ ለመጫን ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።
በርካታ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችም በኢትዮጵያ የተባባሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መላ እንዲበጅለት እየወተወቱ ነው።

ከሚኒስትሮች ጀምሮ እስከ ታችኛው ዕርከን ድረስ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት የህወሃት አገልጋዮች መሆናቸውን አንድ የኤምባሲ ባልደርባ ተናገሩ



ከሚኒስትሮች ጀምሮ እስከ ታችኛው ዕርከን ድረስ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት የህወሃት አገልጋዮች መሆናቸውን አንድ የኤምባሲ ባልደርባ ተናገሩ
ኢሳት
አሁን በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ውስጥ ከሚኒስትር ጀምሮ እስከታችኛው ዕርከን የሚሰሩ በሙሉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አገልጋዮች መሆናቸውን በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደርባ የነበሩ ገለጹ። ከስርዓቱ ጋር በመቆየታቸው መጸጸታቸውንም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ከህዝብ ጎን በመሰለፍ ለለውጥ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ማዕረግ የዳያስፖራ ዘርፍ ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትና በቅርቡ ከስርዓቱ የተለዩት አቶ ግርማ መንገሻ ይህንን የገለጹት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። በኦህዴድ አባልነት ስርዓቱ ተቀላቅለው ለደረሱበት ሃላፊነት መብቃታቸውንም አስረድተዋል።
በቆንስላው ውስጥ ከሚሰሩት የኢምባሲው ሰራተኞች አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን የገለጹት አቶ ግርማ መንገሻ፣ በፍራንክፈርት ከተማ ከሚገኙ የስርዓቱ ደጋፊዎች 90% የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውም አስረድተዋል። የቀሩትም 10 በመቶ የሚሆኑት ከተለያዩ ብሄረሰብ ቢሆኑም፣ እነዚህ በሃገር ቤት ንብረትና ንግድ ያላቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። ከመካከላቸው 1 በመቶ የሚሆኑት በቅንነት ሃገራቸውን እያሰቡ ከኢምባሲው ጋር ግንኙነት የሚያደርጉ መሆናቸው ገልጸዋል።
በዲያስፖራው ክፍል ሃላፊነታቸው ቁጥሮችን በማጋነንና በማዛባት ሪፖርት ሲያቀርቡ መቆየታቸውን፣ ይህም የተለመደና በሃላፊዎች የሚደገፍ አሰራር እንደነበርም አብራርተዋል። በዲያስፖራ የብሄረሰብ ልማት ድርጅቶችን ለማቋቋም የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን፣ በደቡብ በኩል የልማት ማህበር ተብሎ የተቋቋመ ቢኖርም፣ አባላቱ ራሳቸው አመራሮቹ ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል። የትግራይ ልማት ማህበር ግን ቀደም ሲልም የነበረ መሆኑን አብራርተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ዓመጽ በተቀጣጠለው ወቅት ዓመጹን ተቆጣጥረዋል የሚል መግለጫ እንዲሰጥ ተዘጋጅቶ ነበር ያሉት አቶ ግርማ መንገሻ፣ የሟቾቹን ቁጥር እንዳንናገር እንከለከል ነበር ሲሉም አስታውሰዋል። በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ይዞታ ላይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰጡት መግለጫ እንዲለዝብ ስራ ይሰጠን ነበር ያሉት አቶ ግርማ መንገሻ፣ ሰብዓዊ መብት አለመርገጥ እየተቻለ፣ ሪፖርቱ መደበቁ እንዳማይገባቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በስርዓቱ ውስጥ ከትግራይ ተወላጆች ውጭ ያሉ ከሚኒስትር እስከ ተራ ሰራተኛ ሚናቸው አገልጋይነት መሆኑንም በመዘርዘር ስልጣን በህወሃት ሰዎች እጅ መሆኑን አስረድተዋል

” ዶ/ር መረራ ጉዲናን ማሰር የአምባገነንነት ማሳያ ነው” ዶ/ር አረጋዊ በርሄ



VOA -ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
ዋሽንግተን ዲሲ — “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲጎናፀፍ በሰላማዊ መንገድ ያላሰለሰ ትግል የሚያደርጉትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን ማሰር የአምባገነንነት ማሳያ ነው” ሲሉ የቀድሞ የሕወሓት ታጋይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ሸንጎ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
የአምነስቲ የምስራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሃይቅ ሀገሮች ምክትል ስራአስኪያጅ ሚሸል ካጋሪ የዶር መረራ እስራት “ለወራት የዘለቁ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋባቸውን ሰልፎች ከመቆስቆስ ባለፈ መፍትሄ አይሆንም” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቡን የሰብዓዊ መብት ሮሮዎችና የአስተዳድር መከፋቶችን ተጨማሪ የመብት ጥሰቶችና እስራትን በማከል መፍታት እንደማይችል አምነስቲ አሳስቧል።