Tuesday, November 15, 2016

በኦጋዴን ኣዲስ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመጀመር እና ለመታገል የጋራ ንቅናቄ ተመሰረተ።tቆንጅት ስጦታው



በኦጋዴን ኣዲስ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመጀመር እና ለመታገል የጋራ ንቅናቄ ተመሰረተ።
 
በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ውስጥ በሕወሓት መንግስት የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ጭፍጨፋ በመቃውም የሚታገሉ ሃይሎች ኣዲስ እንቅስቃሴ በኦጋዴን ለማድረግ የሶማሌ ክልል የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚባል ድርጅት መመስረታቸውን በቭድዮ ባስተላለፉት ጋዜጣዊ መግለጫ ኣስታውቋል። ዝርዝሩ እነሆ ፡ http://mereja.com/network/post/369/new-movement-in-ogaden-somali-region-justice-and-democracy-move

Thursday, November 10, 2016

ሕወሓት በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው።Minilik Salsawi –



ሕወሓት በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው።

ማፊያው የሕወሓት ቡድን ከኣማራው ሕዝብ ጎን የቆሙ የመካከለኛና ዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ ሊወስድ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ። በመካከለኛና በዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ እንዲወስድ የሕወሓት ኮማንድ ፖስት ሙሉ ሃላፊነት ተሰቶታል። በክልሉ ውስጥ የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ ከጎን ቆመዋል ድርጅታችንን ከድተዋል የተባሉትን የብ አዴን ኣባላት ጨምሮ በኣጠቃላይ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ ኣባላት ልይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ሲጠቆም እርምጃው ከግድያ ጀምሮ እስከ ጅምላ እስር መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።
ምንጮቹ እንዳሉት የብአዴን ኣባላት ቀድመው እርምጃውን ማክሸፍና ሕዝቡ ኣስተባብረው በክልሉ ያለው የሕወሓት ሰራዊትና ኮማንድ ፖስት ብሎ ራሱን የሚጠራው ገዳይ ቡድን ላይ ኣስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መክረዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ ተገድለዋል፤Muluken Tesfaw



ከትናንት ጀምሮ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ ተገድለዋል፤ Muluken Tesfaw
በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ቀበሌ የዐማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለመንጠቅ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በምርኮና በሞት ተደምስሷል፡፡ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች ‹‹ሆን ብለው አዝመራችን በምንሸክፍበት በዚህ ወቅት መሣሪያ ለመግፈፍ መጡብን፤ እኛም ገጥመን ፈጀናቸው›› ብለዋል፡፡ ከትናንት ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ሌሊቱን ባደረው ጦርነት 50 የሚሆኑ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ተማርከዋል፡፡ ሁለት መትረጊስ፣ አንድ ስናይፐርና ጥቂት የሬዲዮ መገናኛዎችም አብረው ተማርከዋል፡፡
የተገደሉ ወታደሮችን በተመለከተ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹እስከ ምሽት ድረስ የተገደሉት ከ20 በላይ ነበሩ፤ ሌሊቱን ወታደሩ በየቦታው ተፈንድሷል፤ የተገደለው ወታደር ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ከመሸግንበት ወጥተን በየቦታው የወዳደቀውን አስከሬን መቁጠር ይጠበቅብናል፤ ሆኖም ግን ከማረክናቸው ወታደሮች በእጥፍ ይበልጣል›› በማለት አብራርተዋል፡፡
ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ጦርነት ከጎበዝ አለቆች መካከል የሆኑት አቶ ፈንቴ አየልኝ ዛሬ ሌሊቱን ተሰውተዋል፡፡ አቶ ፈንቴ በጠላት ቀጠና ዘለው በመግባት በርካታ ወታደሮችን ካጋደሙ በኋላ መሞታቸው በጓዶቻቸው ዘንድ ቁጭትና እልህ ፈጥሯል፡፡ የጎበዝ አለቆች በአምባ ጊወርጊስ እና በአርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ የጎበዝ አለቃዎች በአስቸኳይ እንዲደርሱላቸውና ትግላቸውንም እንዲያግዙ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹እኛ ስለሰላም ስንል ነው እንጅ እንኳን ወገራን ድፍን ዐማራን ነጻ ማድረግ አያቅተንም፤ ግን በየአካባቢው ያለው ገበሬ አሁንኑ ይቀላቀላቀለን፤ መንገድ በመዝጋት ወደእኛ የሚመጣውን ወታደር የስቁም ወይም ከእኛ ጋር ይጨመረን፡፡ ይህም በአስቸኳይ መሆን አለበት›› በማለት አብራርተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአርማጭሆ፣ በወልቃይት፣ ወገራ፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳር፣ ጢስ ዓባይና መራዊ በመሳሰሉ ቦታዎች ወያኔዎች ታካሚ በመምሰል ወደ ሆስፒታሎች ቆስለው የመጡ ገበሬዎችን ለመያዝ በየህክምና ጣቢያዎች መሰማራታቸውን ጥቆማዎች እየመጡ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ሕክምና ተቋማት የሚሔዱ ቁስለኞች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ጥቆማውን የሰጡ አካላት አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በየቦታው የሚታሠሩ ወጣቶች ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሆን እንደ ወገራና ጢሳ ዓባይ ወጣቶች ፊትለፊት በመግጠም አገዛዙን እንዲያሽመደምዱት አንዳንድ የጎበዝ አለቆች አሳስበዋል፡፡
(ማሳሰቢያ፤ በየቦታው ያሉ የጎበዝ አለቆች ለወገራ ገበሬዎች እገዛ እንዲልኩላቸው መረጃውን በማሰራጨት እንተባበር)

Wednesday, November 9, 2016

የባሕርዳር ሕዝባዊ ትግል ተጋድሎ የ ኢወተን እና የ አሕን ቅስቀሳ . ቆንጅት ስጦታው  



የባሕርዳር ሕዝባዊ ትግል ተጋድሎ
የ ኢወተን እና የ አሕን ቅስቀሳ
==================
ጥቅምት 26 ለ 27 አጥቢያ በሁለት ተባባሪ ድርጅቶች ማለትም በ “አማራ ሕዝብ ንቅናቄ (አ.ሕ.ን)” እና በ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋድሎ ንቅናቄ (ኢ.ወ.ተ.ን) በጋራ በባህርዳር ቀበሌወች እና ኩታ ገጠም አጎራባች ቀጠናወች የቅስቀሳ ወረቀት ሲበተን አድሯል። በነጋታው በየአካባቢወች ነዋሪ የሆነው ሕዝብ የተበተነውን የቅስቀሳ ወረቀት ለማንበብ እና ለማስተላለፍ ተችሏል። እንደሚታወቀው ወያኔ በጥድፊያ ባወጀችው ወታደራዊ አዋጅ፤ ዜጎች ኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙ፣ የማህበራዊ ገጾችን እንዳይጠቀሙ በመፈለግ የወሰደቻቸው እርምጃወች ምንም የሕዝብን ድካም እና መከራ ቢጨምርበትም ትግሉን ግን እየገታችው እንዳለሆነ የገለጸው ይህ የቅስቀሳ ሊፍሌት፤ ትግሉ እስከ ድል የሚቀጥል መሆኑን እና በሁለቱ ድርጅቶ ማለትም በ አ.ሕ.ን እና ኢ.ወ.ተ.ን መካከል የትብብር እና በአንድነት የአማራ ተጋድሎ ቀጣይነቱን፣ ለጋራ ነጻነት በጋራ መሰዋት የሚያስፈልግ መሆኑን አብስሯል። በዚህ የተበተነ ሊፍሌት የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋድሎ ከአማራ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በመሆን በአለፉት ቀናት መጠነ ሰፊ የሆነ እስከ አፍጢሙ የታጠቀውን የጠባቧ የወያኔ አጋዚ እና መደበኛ ጦር በየቀየው ሲያራውጡት እንደሰነበቱም በተከታታይ በወጡ ዜናወች አሳውቀዋል። ወልቃይት የአማራ ነው!!! በሚል መፈክር የታጀበው ይህ የቅስቀሳ እና ትብብርን በተጨባጭ በትግሉ አውድማ ያሳየን ጽሁፍ በእውነትም እየታገሉ መሰዋትን ገሎ መሞትን ለነጻነት ሲባል የሚከፈል ከባድ ዋጋ በጸጋ የሚቀበል መሆኑን የሁለቱ ታጋይ ንቅናቄወች አስነብበውናል።
አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ከዘመን ዘመን ለአገር መሞትን፣ ለአገር ዘብ መቆምን እንጅ አገር እኔ ልግዛ ብሎ በብቸኝነትም አገር ገዝቶ የማያውቅ ሕዝብ በትምክህት ሲፈረጅ እንደኖረ የምናውቀው ሲሆን። ወያኔዋ ዛሬም ድረስ ይህን ሕዝብ በዋና ጠላትነት ፈርጃ የዘመተችበት ቢሆንም ታጋይ ልጆቹ በቃን አንገዛም። ዘራችንን ከማጥፋት እናድን በሚል በጎበዝ አለቃ ተደራጅተው መታገልን፣ ታግሎ መሞትንም እያደረጉት ነው። ምንም ቢሆን የዚህ የጀግና ሕዝብ ትግል ግቡን እንዲመታ ሳይታለም የተፈታ በመሆኑ ሕወሐት እና ባንዳ ተከታዮቿ የግዜ ጉዳይ እንጅ የመጨረሻዋን የችንፈት ጽዋ የሚጎነጩበት እሩቅ እንደማይሆን በእርግጥ እንናገራለን።
ድል ለተገፋው ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Tuesday, November 8, 2016

የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል:: Minilik Salsawi


የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል::   Minilik Salsawi
 
የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል:: ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ዲያስፖራዎችንም ቤተሰቦች በዘፍቀደ ያፍናል ሲል አንድ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ገለጸ። ሂዩማን ራይት ስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ድርጅት እንደጠቀሰው በሜልቦርን በስኔ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ በኣውስትራሊያ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው በጅምላ ታፍሰው እስር ቤት መወርወራቸውን እና እስካሁን ኣለመፈታታቸውን ያብራራል። በምስልና በቪድዮ የተደገፈውን ዝርዝር እዚህ ሊንክ ላይ ያገኙታል ፦http://mereja.com/network/post/320/australia-protests-prompt-ethiopia-reprisals-human-rights-wat

Monday, November 7, 2016

ደባርቅ ሰሜን ጎንደር የጅምላ እስር እየተካሄደ ነው! ቆንጅት ስጦታው


ደባርቅ ሰሜን ጎንደር የጅምላ እስር እየተካሄደ ነው! ለጊዜው የወጣቶች ስም ዝርዝር ደርሶኛል 
1. አግንቸ ማውሻ
2. ሐብታሙ መኮነን
3. መልስ ጌታቸው
4. ይርጋ መኩርያው
5. ለምለም አዲሱ
6. ሰለሞን ክንዴ
7. ቀናው መዝን
ይህንን እኩይ የባንዳ ሎሌነት እያስፈፀሙ የሚገኙት የከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ሐላፊዎች እነዚህ ናቸው፦
1.አዳነ ዳኘው
2. ሻምበል አምባቸው
የደባርቅ መውጫ መግቢያ በወታደር ታጥሯል
እባካችሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አርጉ የምትችሉትን መላ ፈይዱ…
ሙሉነህ ዮሃንስ

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመርቋል ፡፡ በቆንጅት ስጦታው


No automatic alt text available.
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመርቋል ፡፡
የኢትዮጲያን ህዝብ ከጭቆናና የስቃይ ህይወት ለማላቀቅ እና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ገርስሶ ለመጣል የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ለወራት ያክል በወታደራዊ ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ተጓዳኝ ትምህርቶች ዙሪያ ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ምልምል አርበኛ ታጋዮች እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል ፡፡
በዚህም የምረቃ ስነ-ስርዓት በዓል ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ግዳጅና ሃላፊነት ስለሚጠብቀን በምትመደቡበት ቦታ ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ሃገራዊና ድርጅታዊ ግዴታችሁን ለመወጣት በወታደራዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ሰራዊት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ለተቀደሰ አላማ መከፈል ያለበትን የህይወት መሰዋዕትነት ለመክፈልና የኢትዮጵያን ህዝብ ከባርነት ህይወትና ከጭቆና ለማላቀቅ በሚደረገው የትጥቅ ትግል የበኩላችሁን ድርሻ መወጣት ይጠበቅባችኋል በማለትና አጠቃላይ የስልጠናውን ሂደት የሚመለከት ሪፖርታቸውን አሰምተዋል፡፡

በዚህ የምረቃ በዓል ላይ ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእጅ በእጅ ውጊያን ጨምሮ የተለያዩ ትርኢቶችን በማሳየት ለበዓሉ ድምቀት ሰተውት የነበረ ሲሆን በተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የቀረቡ ስነ-ፅሁፎችና መነባንቦች እንዲሁም አዝናኝና ትምህርት ሰጪ ድራማዎችም ልዩ ትኩረት የሳቡ እንደነበርና በቦታው የተገኙትንም ተጋባዥ እንግዶች አስደምመውት ውለዋል ፡፡