Sunday, November 6, 2016

‹‹የፖሊሲ ለውጥ ከሌለ ግለሰቦችን በመቀያየር ውጤት አይመጣም›› – ተቃዋሚዎች


‹‹የፖሊሲ ለውጥ ከሌለ ግለሰቦችን በመቀያየር ውጤት አይመጣም›› – ተቃዋሚዎች
Addis Admass : ባለፈው ማክሰኞ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያዋቀሩት ምሁራን የተካተቱበት አዲሱ ካቢኔ፤ ለህዝቦች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትጋት እንደሚሰራ አዳዲሶቹ ተሿሚዎች የገለፁ ሲሆን ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ ግለሰቦችን በመቀያየር ውጤት እንደማይመጣ ጠቁመው፤ ዋና መፍትሄው የፖሊሲ ለውጥ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
30 አባላት ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩን አዲስ ካቢኔ በተመለከተ ለአዲስ አድማስ አስተያየት የሰጡት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፤ የምሁራን መሾምም ሆነ የሰዎች መለዋወጥ ብዙም ውጤት አያመጣም ብለዋል፡፡ “ወሳኙ የፖሊሲ ለውጥ ነው” በማለት፡፡
‹‹ሹመቱ በዶክተሮችና ኢንጂነሮች የተሞላ መሆኑ “የምሁራን ካቢኔ” ያሰኘዋል›› ያሉት አቶ ልደቱ አያሌው፤ ኢትዮጵያ በምሁራን የተሞላ ካቢኔ በማቋቋም በዓለም የመጀመሪያዋ ሳትሆን አትቀርም ብለዋል፡፡ “ካቢኔው በምሁራን መሞላቱ ብቻን ግን ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የሚል እምነት የለኝም” ብለዋል፡፡
አለማቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ሃይለ ማርያም በበኩላቸው፤ ውጤት ለማምጣት ወሳኙ የፖሊሲ ለውጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሠዎች መለዋወጥ ብቻውን ውጤት ያመጣል ብለው እንደማያምኑ ገልፀዋል፡፡ በአዲሱ ካቢኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤ በተሰጣቸው የኃላፊነት ቦታ አገራቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው፤ ካቢኔው ለህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችም ሆነ ሌሎች ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ምላሽ ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት አስተያየት፤ የኢትዮጵያ ሚዲያ ጥራት ያለው መረጃ በማድረስ ህዝቡን በአግባቡ እንዲያገለግል ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አስረድተዋል። “የአዲሱ ካቢኔ አባላትም፤ ለውጥ ለማምጣት መስራታቸው የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታ ነው”
አዲሱ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን  ሚኒስትር አቶ ከበደ ጫኔ በበኩላቸው፤ “ሹመቱ ፈተና ነው፡፡ ፈተናውን በአግባቡ የሰራ፣ በህዝብ ዘንድ ይመሰገናል፤ ፈተናውን በአግባቡ መስራት ያልቻለ ደግሞ ይወድቃል›› ብለዋል፡፡ መንግስትና ህዝብ የጣለብንን እምነት መነሻ አድርገን የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት እንሰራለን ያሉት ሚኒስትሩ፤ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከሚገኙ ሙያተኞች ጋር በመሆን የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍና ተገልጋዮን ለማርካት እንደሚጥሩ ተናግረዋል፡፡‹‹የፖሊሲ ለውጥ ከሌለ ግለሰቦችን በመቀያየር ውጤት አይመጣም›› – ተቃዋሚዎች

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ በአፈሳም ሆነ በሌላ መልክ የተያዙ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡


ከመስከረም 28 ቀን 2009 ጀምሮ መተግበር የጀመረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ በአፈሳም ሆነ በሌላ መልክ የተያዙ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡ መንግስትም ቢሆን የተያዙ ሰዎችን ሁኔታ እናገራለሁ ከማለት ውጪ እስካሁን ድረስ ይፋ ያደረገው መረጃ አለመኖሩ ታውቋል፡፡ አንድ ወሩን ሊደፍን የአንድ ቀን ዕድሜ የቀረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ለበርካታ ሰዎች መታሰር፣ መገደል እና አካል መጉደል ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡
አዋጁን በበላይነት እንደሚያስፈጽም የተነገረለትን ኮማንድ ፖስት በዋና ጸሐፊነት ይመሩታል የተባሉት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በተደጋጋሚ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የታሰሩ ሰዎችን ኣያያዝ በይፋ ለመናገር አልደፈሩም፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አባላት ናቸው ከተባሉ ሰዎች ጋር ስለተያዙ ሰዎች አያያዝ ተመካክረዋል ቢባልም፣ በውይይታቸው ወቅት ስለ ታሰሩ ሰዎች ወቅታዊ ሁኔታ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡
አዋጁ መተግበር ከጀመረ አንስቶ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በተለይም ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልሎች በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአፈሳ መልክ መያዛቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች ጭምር ያወገዙትን አዋጅ የሚያስፈጽሙ በተለይ አጋዚ ወታደሮች በርካታ ዜጎችን ሲገድሉ፣ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹኃን ሰዎችንም ማሰራቸው ይታወቃል፡፡ ሴቶችን መድፈርም የኮማንድ ፖስቱ አንዱ አካል ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሰዎች፣ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈጸሙባቸው የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ –  ( BBN )

Saturday, November 5, 2016

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከአዲሱ ካቢኔ ምንም አዲስ ነገር አንጠብቅም አሉ


የተቃዋሚ አመራሮች ባለፈው ሳምንት ይፋ የተደረገው አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ካቢኔ፣ የአገሪቱን አጠቃላይ ችግሮች ያልተረዳና በግለሰቦች የትምህርት ዝግጅት ላይ ብቻ ያተኮረ ነው በማለት አጣጣሉት፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ‹‹በአዲሱ ካቢኔ የተመረጡት ሚኒስትሮች

መንግስታዊ ኣሸባሪውን ቴድሮስ ኣድሃኖምን የምንቃወመው በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው።Minilik Salsawi

መንግስታዊ ኣሸባሪውን ቴድሮስ ኣድሃኖምን የምንቃወመው በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው።
Image may contain: one or more people

 – ቴድሮስ አድሃኖም የአምባገነኖች ቁንጮ የደም መጣጦች አውራ ለ አለም የጤና ድርጅት ወንበር መንበር ለመሆን እየተወዳደረ ያለው የሕወሓት ዘረኞች ቁንጮ የሆነው ቴድሮስ ኣድሃኖም በተመለከተ ተቃውሞዎች በርትተው ቀጥለዋል።ግለሰቡ በመጀመሪያ ደረጃ ለቦታው የማይመጥን ሰው ነው።ያለው የትምህርት ደረጃ ለመወዳደር ደፍሮ የሃገርን ገንዘብ ለጉቦ የሚያፈስበት መንገድ እጅግ ኣደገኛ ነው።ዋናው ነጥብ ይግ ግለሰብ የኣምባገነኖች የገዳዮች የደም መጣጮች ዋናው ኣባልና ኣስተባባሪ የነበረ ግለሰብ ሲሆን ዘርን ኔትወክ ኣድርገው ጥቅም ካካበቱ ዘራፊዎችም ኣንዱ ነው።
ቴድሮስ ኣድሃኖም በተመለከተ ሁለት የማጭበርበሪያ ምላሶች ከሁለት ወገን እየተዘረጋጉ ይገኛሉ ኣንደኛው ወገን በጦፈ የጎሳ ፖለቲካ ጣዖት ኣምላኪ የሆኑ ዘረኞች ግለሰቡ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ተቃውሞ በዛበት ሲሉ ሌሎች ለዘብተኛ መሳይ ኣስመሳዮች ደግሞ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተሸሽገው ሕዝብን ለማታለል ይሞክራሉ። እነዚህ ሁለቱም ወገኖች በፍጹም ከእውነት የራቁ መሆናቸው በገሃድ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው መንግስታዊ ኣሸባሪነት ይመሰክራል። ቴድሮስ ኣድሃኖም ላይ እየቀረበ ያለው ተቃውሞ ትግሬ ስለሆነ ኣሊያም ከመልካም ገጽታ ሃገራዊ እደምታ ጋር በተያያዘ ኣይደለም።
ግለሰቡ ለኣለም ጤና ድርጅት መወዳደር የለበትም የሚለው ተቃውሞ የሚነሳው ግለሰቡ ከሕወሓት ኣመራሮች ኣንዱ በመሆኑ ሲሆን ሕወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እጅግ ኣደገኛ ከመሆኑም በላይ የገዳይ የኣፋኝ የእስር እና የኣሳዳጆች ቡድን ነው ግለሰቡ ደግሞ የዚህ ኣደገኛ መንግስታዊ ኣሸባሪ ማፍያ ቡድን ኣባል ነው፤ ግለሰቡ የጤና ጥበቃ ሚንስትር በነበረበት ወቅት በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀ ካለሙያው ስልጣን ላይ የተቀመተ ነበር። በዚህ ሰሞን ብቻ የሚሰራቸው ስራዎች በየሚዲያውና በየስብሰባው የሚያደርጋቸው ተግባራት ሃገርን ወክሎ ለመወዳደር ኣይደለም በቦታው ላይ ለመወዳደር መቅረቡ ራሱ ኣሳፋሪ ከመሆኑም በላይ ለቦታው የማይመጥን ግለሰብ ነው።
ግለሰቡ ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን በሚያረጋግጥበት ወቅት በወንጀል የሚፈለግ በዘር ማጥፋት የሚከሰስ ግለሰብ ነው።ቴድሮስ ኣድሃኖም ለመወዳደር ብቁ ነው ተብሎ በወያኔ ኣገዛዝ የተላከው የስርዓቱ ኣመራር ስለሆነ እንጂ ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር የሚችሉ በቂ እውቀት ያላቸው የጤና ዶክተሮች ሞልተዋል፤ ይህ ግለሰብ በሃገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ እና በኣፍ መፍቻው ቋንቋ ስለሚያፍር ብቻ እንግሊዘኛን የሃገሩ ቋንቋ ኣድርጎ ቢናገርም ለተጠየቀው ጥያቋ በቂ መልስ መስጣት ካለመቻሉም በላይ ጥያቄዎች ደጋግሙልኝ ኣልገባኝም በማለት ሲደናበር ተስተውሏል። https://youtu.be/Aql-s_GjTKU የሃገሪቱን ሃብት ለሎቢ በመጠቀም ከፍተኛ ገንዘብ ድምጽ ለመግዛት በመክፈል ኢትዮጵያን ኪሳራ ላይ ጥሏታል። ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያን በማዋረድ ስራ ላይ ስለተሰማራ በጋራ ተረባርበን ለኣለም ልናጋልጠው ይገባል። መንግስታዊ ኣሸባሪውን ቴድሮስ ኣድሃኖምን የምንቃወመው በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው። #ምንሊክሳልሳዊ

ቴድሮስ ኣድሃኖም ለኣለም የጤና ድርጅት ለመወዳደር በመቶ ሺህ ዶላሮች ለሕዝብ ግንኙነት ስራ የኣሜሪካንን ድርጅት ቀጥረዋል


indexካለእውቀት ስኬትን የሚመኘው ቴድሮስ ኣድሃኖም ለኣለም የጤና ድርጅት ለመወዳደር በመቶ ሺህ ዶላሮች ለሕዝብ ግንኙነት ስራ የኣሜሪካንን ድርጅት ቀጥረዋል።
 
በራሱ የማይተማመነው ያልተሟላ የትምህርትና የስራ ማስረጃ በመያዝ የሃሰት ፕረዘንቴሽን ያቀረበው ቴድሮስ ኣድሃኖም ለኣለም የጤና ድርጅት ለመወዳደር ለዘመቻቸው በመቶ ሺዎች ገንዘብ በመመደብ መቀመጫው ኣሜሪካ ያደረገ የሕዝብ ግንኙነትና ቅስቀሳ ስራ የሚሰራ ድርጅት ቀጥረዋል ሲል ኣንድ የኣውሮፓ ሚዲያ ኣጋለጠ።

Friday, November 4, 2016

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይዘሮ ትሬዛ ሜይ ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌን እንዲያስፈቱ ተጠየቀ።Minilik Salsawi


የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይዘሮ ትሬዛ ሜይ ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌን እንዲያስፈቱ ተጠየቀ። Minilik Salsawi
የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይዘሮ ትሬዛ ሜይ በሕወሓት የማሰቃያ እስር ቤት በስቃይ ላይ የሚገኙትን ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌን ለጉዳዩ ኣትኩሮት ሰጥተው ጣልቃ በመግባት እንዲያስፈቱ ተጠየቀ። እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ቢሮ የታጋር ኣንዳርጋቸው ጉዳይ እንዳሳሰበው ከገለጸ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በታጋይ ኣንዳርጋቸው መፈታት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሯ ኣቤቱታውን እንዲያሰማ የታጋይ ኣንዲ ቤተሰቦቻቸው ጠይቀዋል። ዝርዝሩን ከዚህ ሊንክ ያንብቡት – http://mereja.com/network/post/302/calls-for-theresa-may-to-help-british-man-jailed-in-ethiopia

Thursday, November 3, 2016

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምሥረታ መግለጫ

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምሥረታ መግለጫ
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርጉት ትግል እጅግ ወሳኝ ወደሆነ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ሁላችንም የምንገነዘበዉ ነዉ፡፡ በሕወሐት ግፈኛ አገዛዝ ሥር ላለፉት ሃያ-አምስት ዓመታት በሕዝቦቻችን ላይ የወረደዉ ግፍና መከራ ከልክ በማለፉ የተቀጣጠለዉና ላለፈዉ አንድ ዓመት ካለማቋረጥ የቀጠለዉ የእምቢተኝነትና የአልገዛም ባይነት ሕዝባዊ የተቃዉሞ ትግል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረስ መገለጫ ነዉ፡፡ በዚህ ዛሬም ድረስ እየተካሄደ ባለዉ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዳግም በመስቀለኛ መንገዶች ላይ ትገኛለች፡፡ … http://mereja.com/network/post/287/-