Thursday, November 3, 2016

ጥልቅ ምስጢር ፥ በኢትዮጵያ የደህንነትና የስለላ መስሪያ ቤት የሕወሓት ሚና ሲጋለጥ


ጥልቅ ምስጢር ፥ በኢትዮጵያ የደህንነትና የስለላ መስሪያ ቤት የሕወሓት ሚና ሲጋለጥ
Top Secrets of TPLF Role in Ethiopia Security and Intelligence Authority       

Photo



... post your comment below                                                                                                                                                                                    




Wednesday, November 2, 2016

ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የካቢኔ ሹም ሽር ተቹ


ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የካቢኔ ሹም ሽር ተቹ
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን የካቢኔ አባላት ሹም ሽርን ተችተዋል፡፡ መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች ሹም ሽር ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ሲሉ አዲሱን የሚኒስትሮች ሹመት አልተቀበሉትም፡፡ ህዝብ እየጠየቀ ያለው የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መለዋወጥ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡
በዛሬው የካቢኔ ሹም ሽር ከ30 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ውስጥ ዘጠኝ ሚኒስትሮች ባሉበት እንዲቀጥሉ ሲደረግ ሃያ አንዱ አዲስ ሚኒስትር አግኝተዋል፡፡ ከአዲሶቹ ተሿሚዎች ውስጥ አራቱ በባለፈው ካቢኔ ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ሲመሩ የነበሩ እና ወደ አዲስ ቦታ የተዘዋወሩ ናቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ በሚኒስቴር ዴኤታነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም ሚኒስቴር የነበሩ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩ አንድ ባለስልጣን ደግሞ ወደ ሚኒስትርነት ቦታ ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሿሚዎቹን በምክር ቤት አቅርበው ከማጸደቃቸው በፊት እንደተናገሩት ለሹመት ዋና መመዘኛ ያደረጉት ውጤታማነት፣ ለህዝብ ቀልጣፋ አግልግሎት መስጠት መቻል እንደዚሁም ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የማስፈጸም ብቃትን ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራረሮች ግን ሹመቱ መሰረታዊውን የኢትዮጵያን ችግር እና የወቅቱን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ባይ ናቸው፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ህዝብ እየጠየቀ ያለው የፖሊሲ እና መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች ሹም ሽር አይደለም፡፡ ሊቀመንበሩ ሹም ሽሩን ገዢው ፓርቲ “ቀባብቶ በማለፍ” ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርገው ሲሉ ይተቹታል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ  ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ አዲስ ካቢኔ መስርቼያለሁ ባለ በአንድ ዓመት ውስጥ 21 ሚኒስትሮችን መለወጡ “መጀመሪያውኑ ችግር እንዳለበት ያመለክታል” ይላሉ፡፡
ዛሬ በድጋሚ በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በተለያየ ዘርፍ የዶክተርነት ማዕረግ ያላቸው 14 ሚኒስትሮች እንደተካተቱ የተገለጸ ሲሆን ሁለት ፕሮፌሰሮችም ቦታ አግኝተዋል፡፡ ይህም ቢሆን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ቀልብ አልገዛም፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩት ዶ/ር መረራ ግን የዶክተርነት ማዕረግ ያላቸው ተሿሚዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ገዢውን ፓርቲ ሲያገለግሉ የነበሩ እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ ሹመቱንም “ኋላ የነበሩትን ፊት ማምጣት” ሲሉ ይገልጹታል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲው አቶ ይልቃል የቀደመው ካቢኔ ሲጸድቅ “ማስተርስ ያላቸው እና የተማሩ” እየተባለ የትምህርት እና የትምህርት ልምዳቸው ሲነገር እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ የአሁን ሹመት “የተለየ ነገር የለውም” ባይ ናቸው፡፡ “የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እና ጥፍንግ ያለ የማዕከላዊነት አመለካከት እስካልተለወጠ ድረስ የግለሰብ መቀየር ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጣም” ይላሉ፡፡
ሁለቱም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ችግር የሚፈታው በሚኒስትሮች መለዋወጥ ሳይሆን “ኢህአዴግ መሰረታዊ እና የፖሊሲ ለውጥ ሲያደርግ ነው” ይላሉ፡፡ ነጻ ምርጫ፣ ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተናግድ ስርዓት እና እውነተኛ መድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲኖር ካልተፈቀደ እንደዚሁም እንደ ፍርድ ቤት እና መገናኛ ብዙሃን ያሉት ተቋማት ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ እስካልተደረገ ድረስ ለውጥ አይመጣም ባይ ናቸው፡፡
ተስፋለም ወልደየስ
አዜብ ታደሰ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጪ ዜጎች ኢንቨስተሮች ስጋታቸው ጨምሮ ኣገር እየለቀቁ ነው።


በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጪ ዜጎች ኢንቨስተሮች ስጋታቸው ጨምሮ ኣገር እየለቀቁ ነው። Minilik Salsawi
 
በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ የውጪ ዜጎች በሃገሪቱ ተቀጣጥሎ የሚገኘው የሕዝብ ተቃውሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ጭስነት ከቀየረ በኋላ ከፍተኛ ስጋት ስለገባቸው ኣገር እየለቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ የወያኔ ኣገዛዝ የሚከፍላቸውን ገንዘብ በመያዝ ሃገሪቱን ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል።የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁ ከፍተኛ ጫና በስራቸው ላይ እንደፈጠረ በመናገር ላይ ይገኛሉ።

Tuesday, November 1, 2016

የአማራ ወጣቶች በባሕር ዳር እርምጃ ወሰዱ:: የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል።Muluken Tesfaw.



የአማራ ወጣቶች በባሕር ዳር እርምጃ ወሰዱ፤  Muluken Tesfaw.
ቀበሌ 03 በሚገኘው የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት ( ከተማ አተዳደር) በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ 2 ሰዓት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል።
የህዝብን ጥያቄ ወደ ጎን በማሸሽ መልስ የማይሰጠው ወያኔና ብአዴን ትምህርት የሚወስዱበት እርምጃ በባህር ዳር ወጣቶች ተወሰደባቸው። ከቀናቶች በፊት የተለያዩ የማህበር ክፍሎችና ነጋዴዎች ከእስር እንዲለቀቁ የጠየቁት ወጣቶች ለ5 ቀን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ምላሽ ባለማግኘቱ እርምጃ መወሰዳቸውን አስታወቁ።
እርምጃውም ቀበሌ 03 በሚገኘው የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት( ከተማ አተዳደር) በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ 2 ሰዓት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል። ይሄንን ተከትሎ አካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ከመንገሱም በላይ አምቡላንሶች ሲሯሯጡ ይታያል።
አሁንም ወጣቶቹ ይናገራሉ የታሰሩ ወንድሞቻችንና ነጋዴዎች እስካልተፈቱ ድረስ ይሄ ጥቃት በሰፊው እና በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚካሄድ አስጠንቅቀዋል። ከዚህ በዃላ ሊደረግ የሚገባውን እርምጃና ማስጠንቀቂያ ከቀናቶች በዃላ ያስታውቃሉ።

በኢትዮጵያ የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ተከትሎ የውጪ ድርጅቶች የእርዳታ ስራዎች በኣብዛኛው እንቅስቃሴ ቀንሰዋል።። ሰራተኞቹንም ጭጭ ኣሰኝቷል።#MinilikSalsawi



#Ethiopia #StateofEmergency በኢትዮጵያ የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ተከትሎ የውጪ ድርጅቶች የእርዳታ ስራዎች በኣብዛኛው እንቅስቃሴ ቀንሰዋል።። ሰራተኞቹንም ጭጭ ኣሰኝቷል። #MinilikSalsawi #NGO
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ውስጥ ወራቶችን ያስቆጠረው በኣገዛዙና በሕዝብ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ያወጀው የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ በተለያዩ ተቋማት ላይ ገደብ በመጣሉ ነጻ ፕሬስ በማገዱ የሲቪሎችንና የዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ በመገደቡ የውጪ ድርጅቶች የእርዳታ ስራዎች እንቅስቃሴ ቀንሰዋል። የወያኔ ኣገዛዝ በፈጠረው ሳንካ እርዳታ ፈላጊው ሕዝብ በጣም እየተጎዳ ነው።
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ኣለም ኣቀፍ የእርዳታ ድርጅት ማህበረሰብ ኣባላት በኢትዮጵያ የተከሰተው ቀውስ በስራቸው ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ ከመናገር ይልቅ ዝምታን በመምረጥ ኣብዛኛዎቹ ስራቸውን እንቅስቃሴ ቀንሰዋል። መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በፍርሃት ተወጥረዋል። ከደርዘን በላይ የሚሆኑ በሰብዓዊ እርዳታና በልማት ስራዎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታተ የእርዳታ ኣስተባባሪ ቃለመጠይቅ ለመስጠት ፈቃደኛ ኣይደሉም።ኣብዛኛዎቹ ድርጅቶች ኣደጋ ውስጥ የሆኑ ያህል ሆኖ እንደሚሰማቸው ታውቋል።
የጸጥታ ሃይሎች በሕዝብ ላይ የሚወስዱት እርምጃ ለእርዳታ ሰራተኞች እንቅፋት ከመሆኑም በላይ የሰብዓዊ ቀውስ ኣስከትሏል። የትራንስፖርት ችግር የኢንተርኔት መቆራረጥ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ረሃብ ለማስታገስ በስራ ላይ ለተሰማሩ የውጪ ድርጅቶች የመንግስት ሃይሎች ሊያሰሩ ኣለመቻላቸው ተጠቁሟል። #ምንሊክሳልሳዊ — ዝርዝር ዘገባው እዚህ ሊንክ ላይ ቀጥለው ያንብቡ :- http://mereja.com/…/ethiopia-s-state-of-emergency-silences-…
Image may contain: 6 people , text

...

በቂሊንጦ ማ/ቤት በደረሰው እሳት ቃጠሎ ወቅት 22 ሰዎች በእሳት ቃጠሎ ሲሞቱ 45 ሰዎች በጥይት ተገለዋል።– ቆንጅት ስጦታው  



በቂሊንጦ ማ/ቤት በደረሰው እሳት ቃጠሎ ወቅት 22 ሰዎች በእሳት ቃጠሎ ሲሞቱ 45 ሰዎች በጥይት ተገለዋል።
በኢትዮጵያ የፌደራሉ መንግስት ከሚያስተዳድራቸው ቃሊቲ፣ ዝዋይና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች በተጨማሪ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ እስረኞችን የያዘው ‹የቂሊንጦ ጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር› በርካታ ተጠርጣሪዎች (እስረኞች) የሚገኙበት እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ እስር ቤት 3000 ገደማ እስረኞች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በሽብር የተከሰሱና ሌሎች የፖለቲካ እስረኛ ናቸው፡፡
ቂሊንጦ እስር ቤት የኦፌኮ ም/ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ጋዜጠኞቹ ካሊድ መሃመድ፣ ጌታቸው ሺፈራውና ዳርሰማ ሶሪ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የፖለቲካ አመራሮችና አክቲቪስቶች ታስረው የሚገኙበት ነው፡፡
ይህ እስር ቤት በያዝነው አዲስ አመት ዋዜማ (ነሀሴ 2008) ላይ የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ ቃጠሎ የተነሳ በወቅቱ የተጎዱ ሰዎች ማንነትና መጠን በታሰበው ፍጥነት ቶሎ ሳይገለጽ ቢቆይም የኋላ ኋላ መንግስት በቃጠሎው ወቅት በእሳት ተቃጥለውና ‹ለማምለጥ ሲሞክሩ የተገደሉ› በሚል 23 ሰዎች መሞታቸውን ገልጾ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ባደረገው ማጣራት በወቅቱ ከተፈጠረው እሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ 67 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ሟቾች ውስጥ በቃጠሎ የሞቱት 22 ሰዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 45 ሰዎች ‹‹ሊያመልጡ ሞክረዋል›› በሚል በመንግስት ታጣቂዎች (የማ/ቤቱ ጠባቂዎች) የተገደሉ ናቸው፡፡
በወቅቱ ህይወታቸውን ካጡ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ በጭስ ታፍነው የጤና መታወክ የገጠማቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በእነ ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦበት በጊዜ ቀጠሮ ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ የመተንፈሻ አካሉ ላይ በገጠመው የጤና መታወክ ህክምና ላይ ይገኛል፡፡
ከቃጠሎው ማግስት
በቂሊንጦ የደረሰውን ቃጠሎ ተከትሎ የእስረኛ ቤተሰብ፣ ዘመድና ጓደኞች ለቀናት የጭንቅ ቀናትን አሳልፈዋል፤ እያሳለፉም ነው፡፡ በወቅቱ በደረሰው ቃጠሎ ወቅት የእስረኞችን በህይወት መኖርና አለመኖር ማረጋገጥ አዳጋች ሆኖ፣ ያለምንም መረጃ ቤተሰብ በየዕለቱ ወደቂሊንጦ ሲንከራተቱ ቆይተዋል፡፡ ይህን በማድረጋቸውም ጭንቅ ላይ የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ላይ ‹ለምን ትጠይቃላችሁ› በሚል ድብደባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡
መንግስት በወቅቱ በቂሊንጦ የነበሩ (በህይወት የተረፉትን) እስረኞችን ወደተለያዩ እስር ቤቶች ለማዘዋወር ተገድዷል፡፡ ይህንንም ዘግይቶም ቢሆን ለእስረኛ ቤተሰቦች አሳውቋል፡፡ ሆኖም የእስረኛ ቤተሰቦች ከቃጠሎው ወዲህ የሚደርስባቸው እንግልት አልቆመም፡፡ ከዚህ የከፋው እንግልትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ያለው ግን በእስረኞች ላይ ነው፡፡
ወደ ዝዋይና ሸዋሮቢት እንዲዘዋወሩ የተደረጉት እስረኞች የተለያዩ የሰብዓዊ ክብርን የሚያዋርድ ተግባር እንደተፈጸመባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዝዋይ የተዘዋወሩት እስረኞች ለአስር ቀናት ያህል ካቴና ከእጃቸው ሳይፈታ በእስር አሳልፈዋል፡፡ እነዚህ እስረኞች ሁለት፣ ሁለት ሆነው በአንድ ካቴና ታስረው መጸዳጃ ቤት ሲሄዱም፣ ሲመገቡና ሲተኙ ሳይቀር በእስር አንድ ላይ ሆነው እንደነበር ተረጋግጧል፡፡
እስረኞቹ ከምግብ ሌላ ማናቸውም ነገሮች እንዳይገቡላቸው ተከልክለው፣ ጠያቂዎቻቸውን ከ3 ደቂቃ በላይ እንዳያነጋግሩ ተደርገው ሰንብተዋል፡፡ በተለይም እየደረሰ ያለውን ግፍ በተመለከተ የተናገረ ሰው አሸዋ ላይ ራቁቱን ሆኖ ግርፋት ይፈጸምበት ነበር፡፡ አሸዋ ላይ የሚገረፈው እስረኛ ውሃ እየተደፋበት ሰውነቱ አሸዋውን እንዲይዘው ተደርጎ፣ ከዚያም ሰውነቱን እንዳይታጠብ ተገድቦ በስቃይ እንዲቆይ ይደረጋል፡፡ በጠባብ ክፍል ውስጥ በርካታ እስረኞችን በማጨቅ ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ እንዲተኛ ተገድዶ ነበር (በተለይ ዝዋይ)፡፡
ሸዋሮቢት የተዘዋወሩትም ቢሆን ተመሳሳይ በደል እንደተፈጸመባቸው ነው ማረጋገጥ የተቻለው፡፡ በዚሁ እስር ቤት የቆይ እስረኞች አንዳንዶቹ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ከመፈጸሙ ጋር በተያያዘ ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በሄደ ወቅት አንድ ክፍል ውስጥ አስቀምጠው በመስኮት ከወገብ በላይ ብቻ እየታዩ ‹አለሁ› እንዲሉ መገደዳቸውን ከቤተሰቦቻቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የእስረኞቹ ወደቂሊንጦ መመለስ
ጥቅምት 2009 ዓ.ም መግቢያ ጀምሮ ወደተለያዩ እስር ቤቶች ተበትነው የነበሩ ተጠርጣሪዎች ወደ ቂሊንጦ መመለስ ጀምረዋል፡፡ ሆኖም ግን የቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር እስረኞችን ፍ/ቤት እያቀረበ አይደለም፡፡ ይህ ሪፖርት እስከተዘጋጀበት ዕለት ድረስ እስረኞች በፍ/ቤት ቀጠሯቸው መሰረት ፍ/ቤት ሊያቀርቧቸው አልቻሉም፡፡ ለምሳሌ ጥቅምት 9/2009 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀጠሮ የነበራቸው እነ ከድር መሃመድ (20 ሰዎች) እና እነ ትንሳኤ በሪሶ (10) ሰዎች ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ተረጋግጧል፡፡
ጥቅምት 14/2009 ዓ.ም ቀጠሮ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬም በተመሳሳይ በቀጠሮው ዕለት ፍ/ቤት አልቀረበም፡፡ ለዚህም ከማ/ቤቱ አስተዳደር ተጠርጣረውን ላለማቅረቡ በቂ ምክንያት ለፍርድ ቤቱ አላቀረበም፡፡
አሁን ላይ ወደ ቂሊንጦ የተመለሱት ታሳሪዎች በአንጻራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ ናቸው ለማለት ቢቻልም አሁንም ግን የመጠየቂያ ሰዓት ገደብ አለባቸው፡፡ ቢበዛ ለ10 ደቂቃ ብቻ ነው ቤተሰቦቻቸውን እንዲያነጋግሩ የሚፈቀድላቸው፡፡ ከምግብ ሌላ ማናቸውም ነገር እንዲገባላቸው አይፈቀድም፡፡ የጥርስ ሳሙናና ቡርሽ፣ ቫዝሊን፣ በሶ እና የመሳሰሉት አስፈላጊ ነገሮች እንኳ አይገቡላቸውም፡፡
መንግስት እስረኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ ስለመሆኑ
የኢትዮጵያ መንግስት በቂሊንጦ ለደረሰው አደጋ እስረኞችን ተጠያቂ በማድረግ ክስ ሊመሰርት መሆኑ ታውቋል፡፡ መንግስት በቁጥር የበዙ እስረኞችን በተጠርጣሪነት ይዞ ምርምመራ በማድረግ ላይ እንደሆነና ምስክሮችንም እያዘጋጀ እንዳለ የታወቀ ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ በቂሊንጦ ለደረሰው አደጋና ይህንንም ተከትሎ ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ተጠያቂ ናችሁ ሊባሉ እንደሚችሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ መንግስት ይህን እያደረገ የሚገኘው የደረሰው ቃጠሎ መንስኤና ቃጠሎውን ተከትሎ የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ባልተገለጸበት ሁኔታ ነው፡፡ መንግስታዊው “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን” ማጣራት አደርጋለሁ ማለቱና በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ሪፓርት አቀርባለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
(በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ተዘጋጀ

የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ኣሻንጉሊት ሲሆን ወሳኙ ኣካል ሕወሓት/ወያኔ እንደሆነ ይቀጥላል። የዶክተሮች ጋጋታ ከዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር ፉክክር ኣድርጎታል።



#Ethiopia : New #Puppets የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ኣሻንጉሊት ሲሆን ወሳኙ ኣካል ሕወሓት/ወያኔ እንደሆነ ይቀጥላል። የዶክተሮች ጋጋታ ከዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር ፉክክር ኣድርጎታል። #MinilikSalsawi
Image may contain: one or more people and text
Minilik Salsawi – mereja.com – በኢሕአዲግ ኣገዛዝ የሕወሓት የበላይነት የሚቆመው ሕወሓት ስልጣኑን ለሕዝብ ሲያስረክብ ብቻ ብቻ ነው፤ ኣሻንጉሊቶች መሰብሰብ የለመደው ሕወሓት የፓርቲና የመንግስት ስራ ቀላቅሎ ሕዝብን ሰላምና ፍትህን ኣሳጥቶ በመግደል በማሰር ላይ ይገኛል። ሃገራችን በወታደራዊ ኣገዛዝ በኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ስር ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ ሲቪል ሚኒስትሮችን ያዉም ታማኝ ባሪያዎችን መሾም ማጭበርበር ነው።። በፖለቲካ ማጭበርበር ደሞ ወያኔ የተካነበት ስራው ነው። ሃሰትን ማራባት ኣራብቶ ማሰራጨት የወያኔ ስራው ነው።
ወያኔ የምሁራን ስብስብ እንዲባል ዶክተር ፕሮፌሰር እያለ ሚኒስቴር መሾሙ ሳቅ ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ለሕዝብ የሚፈይደው ኣንድም ነገር የለም። ዲያሶፖራ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ዶክተር ፕሮፌሰር እያሉ ከመሾም ይልቅ ለሕዝብ ጥያቄ መመለስ በጣም ቀላል ነው። ይህ ግን ወያኔ ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሕዝብን በማታለል መቀጠሉን ለማሳየት ታዛዥ የሆኑ ከብቶች በሚኒስትርነት ሾሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ያውም ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ። የሚኒስትሮን መለዋወጥ ከጉልቻ መለዋወጥ ኣይለይም ኣንዳጁ ኣካል ስልጣል ሲለቅ ነው የሚነደው ኣካል እፎይ የሚለው እሳቱ ስልጣን ሲለው የኣምባገነኖች ነበልባል ስልጣን ሲለቅ በእሳት የሚለበለበው ሕዝብ ሰላም ያገኛል። ተሿሚ ሚኒስትሮች ራሳቸውን በምቾት በማኖር ለሆዳቸው ከማደር ውጪ በሃገር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ምን ኣይነት ለውጥ ኣያመጡም።ይህ ለይስሙላ የሚደረግ ተግባር የሕዝብን ትግል ኣያቆምም። ትግሉ ይቀጥላል። #ምንሊክሳልሳዊ