Saturday, October 15, 2016

አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወዱ እርምጃዎች ቆንጅት ስጦታው  



አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወዱ እርምጃዎች
እርምጃ ለመውሰድ ስልጣን ስላለው ሰው በተደነገገበት የመመሪያው ክፍል፤ የህግ አስከባሪዎች የመመሪያውን ድንጋጌ ተላልፈው በተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እርምጃዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተመላክቷል።
ክልከላዎች ሲጣሱ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ፤ በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራት ተፈፅመው ሲገኙ፤
1. ህግ አስከባሪዎች ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላሉ፤
2 አዋጁ ተፈፃሚነቱ እስከሚያበቃበት ድረስ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስነው ቦታ እንዲቆዩ የማድረግ፤
3 ተገቢውን የተሃድሶ ትምህርት በመስጠት የሚለቀቀውን እንዲለቀቅ፣ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርበውን ደግሞ እንዲቀርብ ማደረግ
4 ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በማንኛውም ስአት ብርበራ የማድርግ፤ የአካባቢውን ህዘብ እና ፖሊስ በማሳተፍ ማንኛውንም ወንጀል የተፈፀመበት ወይም ሊፈፀምበት የሚችል ንብረት መያዝ፤ወይም ንበረቱ እንዲጠበቅ ማደረግ
5 በማንኛውም ሬድዮ ቴሌቭዠን ድምፅ፣ ምስል ፎቶ ግራፍ፣ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልእክቶችን መቆጣጠር እና መገደብ ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል
6 የተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ
7 በትምህርት ተቋማት ሁከት እና ረብሻ ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምት መውሰድ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለተቋማቱ ትእዛዝ መስጠት
8 ማንኛውም የህዝብን ሰላም እና ፀጥታ ሊያደፈርሱ ይችላሉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩ እና የሚታሰቡ ሰዎችን እንዲሁም ቡድኖችን ወደ ተወሰነ አካባቢ እንደይገቡ፣ እንዳይገኙ ወይም በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ ማድረግን ጨምሮ አግባብነት ያለቸውን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።
ራስን ለመከላከል በፀጥታ ሀይልች ስለሚወሰድ እርምጃም መመሪያው ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።
ህግ አስከባሪዎች እና በድርጅት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጦር መሳሪያ ወይም በስለት ህይወታቸውን እና ንብረተቻውን አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት በተሰነዘረ ጊዜ ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።
በትምህርት ተቋማት የመግባት ስልጣንም በመመሪያው ስንጋጌ ወጥቶለታል። መመሪያው እንደሚለው በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ችግሩን ለማስቆም የህግ አስከባሪ አካላት በተቋማቱ ውስውጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይችላሉ።
በሌሎች የመንግስት እና የግል ተቋማት አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አካላት እና ባልደረቦች በተቋማቱ ውስጥ ለመግባት እና አስፈላጊ ከሆነ ለማቆየት ይችላሉ።
ተሃድሶ እና ፍርድ ቤት ማቅረብን በተመለከተም መመሪያው ይህንን ይላል፤ 
በህግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረግ የተሃድሶ እርምጃዎች እንደሚኖሩ በተጠቀሰበት የአዋጁ ድንጋጌ፤ ኮማንድ ፖስቱ ለፍርድ መቅረብ ያለበትን እንዲቀርብ ያደርጋል፤
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በተፈፀሙ የሁከት እና የነውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ
የጦር መሳሪያ ሳይዝ የመንግስትም ሆነ የግለሰን ንብረት የዘረፈ እና በአቅራቢያው ለሚገኝ ፀጥታ አስከባሪ ሃይል የዘረፈውን መሳሪያ እና ንብረት፤ ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን የሰጠ ፤
ከዚህ በፊት ለህገ ወጥ ተግባራት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ፣ወረቀት በመበተን፣ አድማ በማድርግ የተሳተፈ እና ያነሰሳ፣ ሰው የገደለ፣ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ፣ማንኛውንም ወንጀል የፈፀመ ስው፤
ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን ከሰጠ እንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላል እና ከባድነት ዋና ፈፃሚ እና አባሪ ተባባሪ መሆኑ ታይቶ፣ በኮማንድ ፖስቱ የተሃድሶ ትምህርት ተሰጥቶት እንዲለቀቅ ይደረጋል።

Source  Fana Broadcast

Friday, October 14, 2016

በዘረኝነት መጠቃቀሙ ቀጥሏል፤ለምርምርና ድህረ ምረቃ በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡት የትግራይ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው ተረጋግጧል። ቆንጅት ስጦታው



በዘረኝነት መጠቃቀሙ ቀጥሏል፤ለምርምርና ድህረ ምረቃ በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡት የትግራይ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው ተረጋግጧል።
በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የምርምርና ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ማመልከቻ ያስገቡ ተማሪዎች ውድቅ ሆኖባቸው ትምህርት ቤቱ ከትግራይ ክልል ለመጡ ብቻ በመፍቀድ የሕወሓት የበላይነትን ማረጋገጡ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የሚገኙ የኣስተዳደርና የትምህርት ክፍል የሚመለከታቸው ምሁራንና ሰራተኞች በምሬት ይናገራሉ።
በተለይ ከባህራ ዳር ዩንቨርስቲ የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው ዩንቨርስቲው ለዚህ ኣመት ሊያስተናግዳቸው የፈለገውን የኦሮሚያና የኣማራ የምርምርና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በመመለስ የትግራይ ተማሪዎችን እንዲቀበል ትእዛዝ መተላለፉ ታውቋል። በዘረኝነት መጠቃቀሙ የቀጠለ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀውና ኣሁንም እንደሚሰራበት በገሃድ እንደሚታየው ኣለማቀፍ ስኮላርሺፕ ከሚሰጣቸው ተማሪዎች ውስጥ ዘጠና ስምንት ከመቶው የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በግልጽ ይታወቃል።
ጋዜጠኛና ኣክቲቪስት ሙሉቀን ተስፋው በሰጠው ኣስተያየት ፤ እነዚህ ሰዎች እኮ ምንም እፍረት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም። በውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚንስትር ለሁለተኛ ዲግሪ ወደ ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ የተላኩ ተማሪዎችን ዝርዝር ተመልከቱት፦የትግራይ የበላይነት የሌለባት ኢትዮጵያ ይህች ናት። ለማንኛውም የባሕር ዳር ወጣቶች ሰዎቹ ለመማር ይሁን ለሌላ ሥራ አመጣጣቸው ስለማይታወቅ በዝርዝር ማወቃችሁ አይከፋም። ብሏል።

የወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመውደቂያው ሰበር ዜና ነው – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት ቆንጅት ስጦታው  



የወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመውደቂያው ሰበር ዜና ነው – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት
የወያኔ መንግስት ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያደረበት ፍርሃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና እንደሰደድ የተያያዘው የህዝባዊ እምቢተኝነት ድል የነሳውና ያንበረከከው የመሆኑ ምልክት ነው። ላለፉት 25 ዓመታት በወታደር ጠመንጃና በደህንነት ታፍኖና ተወጥሮ የኖረ ህዝብ በጊዜያዊ አዋጅ ሥር ነውና ለምን ይህን አዋጅ ማወጅ እንዳስፈለገ ግልጽ አይደለም። የበለጠ ያለ ገደብ የመግደያና የማሰር፣ ሰላማዊውን ሕዝብ የማንገላታት አድማሱን አስፍቶ ለማንም ስብዕናና ሕሊና ላለው የማይዋጥ የመጨፍጨፊያ ፈቃድ አለን ለማለት ካልሆነ በስተቀር።
ከትቂት ዓመታት በፊት የወጣው የፀረ ሽብሩ አዋጅ የሃገሪቱን ሕገመንግስት ገርስሶ፣ የህዝብ መብት ነጥቆ፣ አስተዳደሩን በወታደር፣ በሰላዮችና በካድሬዎች ሥር የጣለው መሆኑን ወያኔ ዘንግቶት አይመስለንም። የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብና የእምነት ነጻነት ህዝቡ ከተነፈገ ዓመታት አስቆጥሯል። የወያኔ ገዳዮች፣ አሳሪዎችና ዘራፊዎች አይከሰሱም አይገሰሱም። ስለሆነም የፀረ ሽብር አዋጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነበር ለማለት ነው።
በአገሪቱ ሕግ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ያለበት አገር በውጭ ጠላት ሲወረር፤ የተፈጥሮ አደጋ ሲፈጠርና ደህንነትን የሚያናጋ የወረርሽኝ ደዌ ሲደርስ ነው። አዋጅ የሚሆነውም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተደንግጎና አልፎ በ2/3 ድምፅ የተወካዮች ምክር ቤት ሲያፀድቀው ነው። ወያኔዎች ሕግ አውጭም አስፈፃሚም ናቸውና በፓርላማ ሣይፀድቅ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያወጁት። ማን ቢጠይቃቸው?
በአሁኑ ሰዓት አገርን ባስመረረው የአግአዚ ጦሩና እንደ ተፈጥሮ አደጋ የደሀውን ቤት በሚያወድመው አፍራሽ ግብረ ሃይሉ አማካይነት ሰላማዊውን ሕዝብ በማሸበርና በማስጨነቅ ሕዝቡን በሽታ ላይ የጣለው ራሱ የወያኔ ሥራዓት ነው። ስለዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማወጅ የነበረበት በሕዝቡ ላይ ሳይሆን በራሱ ላይ ነበር።
ይህ የህዝብ ማጥቂያ አዋጅ የህዝቡ ቁጣና ቁርጠኝነት እንዲያይልና እንዲገነፍል ከማድረጉም በላይ እንደ ባህር ሞገድ የወያኔን የተንኮል ጀልባና ባለስልጣናቱን አረፋ እያስደፈቀ የሚያሰጥም እንደሚሆን ጥርጥር የለንም።
መታወቅ ያለበት ወያኔ የመጨረሻውን ሲቃ እስከሚተነፍስ ድረስ ከመቸውም የከፋ አደጋ ማድረሱ አይቀርምና ወገኖቻችን በአንድነት፣ በብልህነትና በጀግንነት በጋራ ለመመከት መዘጋጀት አለባቸው። ወያኔዎች ስልጣን ያሰከራቸውና በተዘረፈ ገንዘብ ያበዱና ራስ ወዳዶች ናቸውና አጥፍቶ መጥፋት የሚሳናቸው አይደሉም።
ህዝብም እርስ በእርሱ እንዲጠፋፋ ባላቸው ፕላን መሰረት የወያኔ ካድሬዎችና የደህንነት ሰዎች ባቀነባበሩት ሴራ በደቡብ ክልል በጌድዮ ዞን በዲላ ወረዳ በወያኔ በተወናበዱ ጥቂት የጌድዮ ተወላጆች በአማራና በጉራጌዎች ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ በመክፈታቸው አብያተ ክርስቲያናት፣ መስጊዶችና መኖሪያ ቤቶች የንግድ ተቋሞች እንዲቃጠሉ ተደርጓል። ይህ ዓይነቱ ወንጀል በሌላም አካባቢዎች እንዳይደገም ሕዝቡ ነቅቶ መጠበቅ አለበት።
በቂሊንጦ እስር ቤት ወገኖቻችንን በእሳት የፈጁበት ሀዘን ከሰው ልብ ሣይጠፋ በዝዋይ እስር ቤት የሚፈልጓቸውን እስረኞች ለመግደል በማሴር የወያኔ ካድሬዎች ባስነሱት እሳት 11 እስረኞች እንደተገደሉ ይፋ ሆኗል።
ምዕራባውያን አገሮች የህዝቡ ደም ለዓመታት በግፍ ሲፈስ ጉዳዩ አሳስቦናል ከማለት ባለፈ እልቂቱን የሚያስቆም እርምጃ ካለመውሰዳቸውም በላይ ይህን የወንበዴ ሥራዓት መደጎማቸውን እንደቀጠሉ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀም በኋላ አሁንም ዓይኔን ግንባር ያድርገው ምንም አላየሁም የሚሉ ይመስላሉ። ያለፈው ልምዳችን እንደሚያሳየን ከሆነ ግን ከነሱ ብዙም መጠበቅ እንደለለብን ነው።
እነሱ በሚለግሱት ገንዘብ በተሸመተ ጥይት ሕዝባችን እንደ ቅጠል ሲረግፍ በእሳት ሲፈጁትና ገደል ሲያስገቡት ምዕራባውያን አድም እርምጃ አልወሰዱም። በዚህም ድርጊት ከእኛ ህይወት የራሳቸው ጥቅም እንደሚያመዝን እየነገሩን ነው። ስለሆነም መገንዘብና ማመን ያለብን የወያኔ ሥራዓት እየፈፀመ ካለው ድብደባ፣ ግድያ፣ እሥራትና ሽብር የፈጣሪ እርዳታ ተጨምሮበት ሕዝባችንን መታደግ የምንችለው እኛና እኛ ብቻ መሆናችንን ነው።
የወያኔን ሰው በላ ሥራዓት ከሥሩ ነቅንቆ ያንገዳገደውና ፍርሃትን በ25 ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰበረው የሙስሊሙ አይበገሬ ፊልሚያ፣ የኦሮሞው ጀግንነትና የአማራው ቆራጥነት በድምሩ የወያኔ ሥራዓት ተንኮታኩቶ ግብዓተ መሬቱ በቅርቡ የሚፈፀም መሆኑን አመላካቾች ናቸው።
መሣሪያ ታጠቃችሁ ይህን ሥርዓት በማገልገል ላይ የምትገኙ ወገኖቻችን በተለይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ ከራሳችሁ ጋር መክራችሁ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን መግደል አቁማችሁ ከወያኔ ካምፕ ውጡና ወደ ሕዝብ ጎራ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
በአገርና በውጭ ያለችሁ የትግራይ ወገኖቻችንም እናንተን የማይወክሉና ሊወክሏችሁም የማይችሉ ጥቂት ወንጀለኞች በእናንተ ስም በኦሮሞ፣ በአማራውና በኮንሶ ሕዝቦች ላይ የሚያደርሱትን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በማውገዝ እየደማ፣ እየቆሰለና እየሞተ ካለው ወገናችሁ ጎን ተሰልፋችሁ የወያኔን ስራዓት በቁርጠኝነት ታገሉ።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት የወያኔ ሥራዓት የአገሪቱን ሕገ መንግስት በመጣስና የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም በአስቸኳይ አዋጅ ከለላ ሥር ለራሱ የሰጠውን ሕዝብን የመፍጀት የምስክር ወረቀት ወይም ፈቃድ በጽኑ ያወግዛል።
የወያኔ ሥራዓት ያስተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመውደቂያው ሰበር ዜና ነውና አገዛዙ ሙሉ ለሙሉ እስኪያከትም ድረስ መራራውን ትግል በጋራ እንድንቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋላን።
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፍ ይቀጥላል!
ምንጊዜም ድል የሕዝብ ነው!
አላሁ አክበር!!!
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት
No automatic alt text available.

የኢትዮጵያ ጀግና የብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ተፈራ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ ቆንጅት ስጦታው  




ሶማሊያ ኢትዮጵያን በምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ ግንባሮች በወረረችበት ወቅት (1969-1970) በተዋጊ ጄት አብራሪነት ወደር የሌለው ጀግንነት በመፈጸማቸው ከቀድሞው መንግሥት ‹‹የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ›› እና የ‹‹የካቲት 1966 1ኛ ደረጃ ኒሻን›› ተሸላሚ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ተፈራ ሥርዓተ ቀብር መስከረም 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
Teddy Habesha's photo.
በሥርዓተ ቀብራቸው በተነበበው የሕይወት ታሪክ እንደተገለጸው፣ ከሶማሊያ ጋር በ1969 ዓ.ም. በነበረው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር ኃይል በምዕራፍ አንድ ዘመቻው ጄኔራል ለገሠና ጓዶቻቸውን አሰማርቶ ከሐምሌ 17 ቀን እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1969 ዓ.ም. ድረስ በተናጠልና በቡድን ሆነው ከሶማሊያ አየር ኃይል ጋር ባካሄዱት የአየር ለአየር ውጊያ የጠላትን 12 ሚግ 21 እና 13 ሚግ 17 በድምሩ 25 ተዋጊ አውሮፕላኖች ከአየር ላይ በማራገፍ አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ ጄኔራል ለገሠ በደቡብ ግንባር መስከረም 11 ቀን 1970 ዓ.ም. በነበረው ውጊያ አውሮፕላናቸው በመመታቱ በፓራሹት በመውረድ ቢተርፉም በሶማሊያ ሠራዊት እጅ በመውደቃቸው ለ11 ዓመት በጦር እስረኝነት ሶማሊያ ውስጥ ቆይተዋል፡፡ ከአባታቸው ከአቶ ተፈራ ወልደ ሥላሴና ከእናታቸው ከወይዘሮ ተናኜ ተክለ ወልድ፣ ነሐሴ 13 ቀን 1934 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ሾላ ላም በረት አካባቢ የተወለዱት ብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ፣ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በደጃዝማች ወንድይራድና በኮከበ ጽባሕ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል፡፡
Teddy Habesha's photo.
አገራቸውን በውትድርና ሙያ ለማገልገል በነበራቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ፣ ጥቅምት 1 ቀን 1956 ዓ.ም. በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሐረር ጦር አካዴሚ የ7ኛ ጊዜ ተወዳዳሪ ዕጩ መኮንን በመሆን፣ አንጋፋውን የምድር ጦር ሠራዊት ሲቀላቀሉ፣ በሐረር አካዴሚ የአዛዥነትን ትምህርት ሲያጠናቅቁም ወደ አየር ኃይል ተዛውረዋል፡፡ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበሩትና በ75 ዓመታቸው ያረፉት ጄኔራል ለገሠ ሥርዓተ ቀብር በኢትዮጵያ አየር ኃይል እግረኛ ወታደር ታላቅ አጀብና የማርሽ ባንድ የሐዘን ዜማ ታጅቦ ሲፈጸም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፣ የቀድሞዎቹ የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍሥሐ ደስታና ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስን ጨምሮ የቀድሞ መንግሥት ከፍተኛ መንግሥታዊና ወታደራዊ ባለሥልጣናት እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ተገኝተዋል፡፡

Thursday, October 13, 2016

ሰማያዊና መኢአድ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ቤት ናቸው – #ግርማ_ካሳ  



13259998_1026870737397860_7809576735746440482_n
የሰማያዊ ፓርቲ ካለፈው ምርጫ ጀመሮ ለአንድ አመት ከአራት ወራት ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ አለማድረጉ ይታወቃል። ይሄም የሆነበት ዋና ምክንያት በሊቀመንበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እና በሌሎች አመራሮች መካከል አለመስማማቶች በመፈጠራቸው ነበር።
በፓርቲው ድርጅታዊ ደንብ መሰረት የድርጅቱ የበላይ አካል ጠቅላላ ጉብዬው ነው። የድርጅቱን ሊቀመንበር ፣ የድርጅቱን ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እና የደርጅቱን ኦዲት ኮሚሽን አባላት የሚመርጠው ይሄው ጉብዬ ነው። ሊቀመንበሩ አብረዉት የሚሰሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መርጦ በብሄራዊ ምክር ቤቱ ያጸድቃል። እንግዲህ እነዚህ ሶስቱ አካላት አንዱ ሌላውን እንዳያዝ ተደርገው ነው የተዋቀሩት። ይሄ ተጠያቂነት እንዲኖር ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ፈረንጆች check and balance የሚሉት አይነት ነው።
በፓርቲው ዉስጥ አለመስማማቱ ነገሮችን ሁሉ አስሮ ባለበት ወቅት፣ ለሁለት አመት በወህኒ ሽብርተኛ ተብሎ ከነሃብታሙ አያሌው ጋር ሲሰቃይ የነበረውና የድርጅቱ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢው የሺዋስ አሰፋ ከወህኒ ይወጣል። ሁሉም አመራሮች በማሰባሰብ የፓርቲው ችግር በዉይይት እንዲፈታ ለማድረግ ይጥራል። በዚህ ወቅት ነው ከአምስት ወራት በፊት፣ ከዚህ በታች የምታይዋት ፎቶ ለሕዝብ የተለቀቀችው። የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢውና የሕግ ባለሞያው አቶ ይድነቃቸው ከበደ፣ የምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀመነበሩ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ የኦዲት ኮሚሽን መሪ አቶ አበራ ገብሩ እና የህግ ባለሞያ የሆኑት አቶ ሳምሶን ገረመውን ነው በፎቶ የምናያቸው።እነዚህ ስድስት ወገኖች በሰማያዊ ፓርቲ ዉስጥ ያሉ ሶስት ተቋማት መሪዎች ነበሩ። ከኢንጂነር ይልቃ በስተቀር ሁሉም አሁንም መሪዎች ናቸው።
የሰማያዊ ፓርቲ መስከረም 28 ቀን ጠቅላላ ጉብዬ አድርጓል። በዚህ ፎቶ ላይ ካሉት ዉስጥ አምስቱ በጠቅላላ ጉብዬው ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በአባላት ፊት ቀርበው በድጋሚ ለመመረጥም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያላቸዉን አቋም ለመግለጽ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ጠቃላላ ጉባዬው የተጠራው ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ነው ይላሉ። ሆኖም ግን የድርጅቱ ኦዲት ኮሚሽን ጉባዬ መጠራት እንደሚችል በደንቡ ላይ በማያሻማ መልኩ በገልጽ ተቀምቷል። እርግጥ ነው እርሳቸውም ባሉበት ጉብዬው ተደርጎ ቢጠናቀቅ ኖሮ በጣም ጥሩ ይሆን ነበር። ግን በተለያዩ ምክንያቶች ለመገኘት ፍቃደኛ ካልሆኑ ፣ መቼም የሰማያዊ ፓርቲ የአንድ ሰው ፓርቲ ስላልሆነ፣ “እርሳቸው በተመቻቸው ጊዜ ሲመጡ ይመጡ” ብሎ ትግሉን ከመቀጠል ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖርም። (በዚህ አጋጣሚ ለወንድም ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በትግል ዉስጥ አለመስማማትና ግጭት እንዳለ ተረድተው፣ ከአዲሱ የሰማያዊ አመራር ጋር አብሮ በመስራት የድርሻቸዉን እንዲወጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ብዙ ሊሰሩና ሊያገለግሉ እንደሚችሉ አወቃለሁ። የሚያስፈልገው ፍቅርና ቅንነት ነው። ለመታግል፤ የግድ ሊቀመንበር መሆን የለብንም)
በመጨረሻ አንድ በጣም ትንሽ የሚመስል ግን በጣም ጠቃሚ የሆነ ነጥብ ማስቀመጥ እፈልጋለሁ። የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉብዬዉን ያደረገው በመኢአድ ጽ/ቤት ነው። ባለኝ መረጃ በዶር በዛብህ ደምሴ የሚመራው የመኢአድ አመራር “እኛና እናንተ እኮ አንድ ነን። ጽ/ቤታችን የናንተም ጽ/ቤት ነው። በፈለጋችሁበት ጊዜ ጽ/ቤቱን መጠቀም ትችላላችሁ። እኛ በፊትም መለያየት አልነበረብንም፤ አንድ ነን” በሚል ሰማያዊዎች ምን ነገር ሳይከፍሉ ጉባዬያቸውን በመኢአድ ጽ/ቤት እንዲያደረጉ በመፍቀዳቸው ነው ጉብዬው ሊደረግ የቻለው። ይህ የአንድነትና የሶሊዳሪቲ መንፈስ በአንድነት የለዉጥ ሃይሉ መካከል ፣ ያልነበረ በጣም መበረታታት ያለበት መንፈስ ነው። በዚህ አጋጣሚ ለመኢአድ አመራር አድናቆቴን እና ምስጋናዬን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።
አሁን በአገራችን ባለው ሁኔታ የአገዛዙ የግፍ ቀንበር ከመብዛቱ የተነሳ ዜጎች ወደ አመጽ እየሄዱ ነው። ፖለቲካው እጅግ በጣም ሲበዛ ከሯል። ሆኖም ግን መቼም ቢሆን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተባበረ መንገድ፣ በእውቀት ከተመራ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ጥርጥሬ የለኝም።
ሌላው ደግሞ አሁን እያየን ያለነው እንቅስቃሴ ዘር ተኮር የሆነ ብዙ ወገኖች ያላቀፈ እንቅስቃሴ ነው። ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ ያቀፈ፣ ለዘርና ለጎሳ ቦታ የማይሰጥ ድርጅት ያስፈልጋል። እንግዲህ እንደ መኢአድ ሰማያዊ ያሉ ደርጅቶች አሉ። መኢአድም ሰማያዊ አዲስ አመራር ነው ያላቸው። አብሮ የመስራት ፍላጎታቸው በጣም ጠንካራ ነው። እነዚህን ድርጅቶች በማጠናከርና በማገዝ በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ሥር እንታገል። ብሶት የምናሰማ ሳይሆን የምንታገል እንሁን። ትግል ደግሞ ከአልጋ ወደ አላጋ መዝለል አይደለም። የተሰበረዉን ጠግኖ፣ የደከመዉን አጠናክሮ መዉጣት

Wednesday, October 12, 2016

ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገድን አድርጎ አማራውን በሶስት ዙር ትጥቁን ለማስፈታት ወስኗል። ቆንጅት ስጦታው  



ፋሽስት ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገድን አድርጎ አማራውን በሶስት ዙር ትጥቁን ለማስፈታት ወስኗል። ከውስጥ አርበኞቻችንና የጎበዝ አለቆቻችን ባገኘነው መረጃ መሰረት ፋሽስት ወያኔ በመጀመሪያ ዙር ትጥቅ የሚያስፈታው የአማራን ልዩ ኃይል ነው። የአማራን ልዩ ኃይል ትጥቁን ካስፈታች በኋላ የቀጣዩ ዙር ኢላማ ደግሞ የአማራ ገበሬ ነው። በእቅዱ መሰረት በሶስተኛ ደረጃ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ የሚደረጉት የአማራ ሚሊሻዎች ወይንም በተለምዶ «ጉጅሌ» የሚባሉት ናቸው።
በዚህ መሰረት ዛሬ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ከዛሬ ጀምሮ ትጥቅ እንዲፈቱ እየተደረገ ነው። ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት ሁሉም የልዩ ኃይል አባላት አይደሉም። በቅድሚያ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት የልዩ ኃይል አባላት የአማራ ተጋድሎ ሲካሄድ «ግደሉ» የሚል ተልኮ ተሰጥቷቸው «ወገናችንን አንገድልም!» በማለት የህዝብ ወገን መሆናቸውን ያስመሰከሩት ህዝብ አክባሪዎች ናቸው። እነዚህ የህዝብ ልጆች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ከተደረጉ በኋላ ለግዳጅ በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል፡፡
ተስፋ የቆረጠ ህዝብ ትጥቁን ስለፈታ፣ ስለተገደለ፣ ወይንም ስለታሰረ ተጋድሎውን ሊያቆም አይችልም። ይህ ያልገባው ወያኔ የማይበስል ነገር ጥዶ በከንቱ ማገዶ ይጨርሳል

Tuesday, October 11, 2016

በሳሞራ የኑስ የሚመራ ጨፍጫፊ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ። ቆንጅት ስጦታው  



በሳሞራ የኑስ የሚመራ ጨፍጫፊ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ።
ሳሞራ የኑስ —  አሰፋ አብዩ —- ሲራጅ ፉርጌሳ ——–
እነርሱ ጭፍጨፋው ከ Civilian Dictatorship ወደ Military Dictatorship ጭፍጨፋ ማደጉን ነው ይፋ ያደረጉልን ፣ ሌላ አዲስ ነገር የለም ፣ መጨፍጨፍ በቃን ማለት የኛ የተጨፍጫፊዎች ድርሻ ነው ።
Zelelie Tsegaselassie's photo.
Zelelie Tsegaselassie's photo.
Zelelie Tsegaselassie's photo.