Tuesday, October 11, 2016

የኦሮሚያ ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏ ቆንጅት ስጦታው



የኦሮሚያ ከተሞች ህዝባዊ እምቢተኝነት በእጅጉ አይሏል፡፡ ትላንትም ሆነ ዛሬ የሚደረጉ ተቃውሞዎች የበረቱ ሲሆን፣ ህወሓትም ተቃውሞዎችን በአጋዚ ወታደሮቹ በኩል ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ከአጋዚ ወታደሮች ቁጥጥር እየወጡ መምጣታቸው እጅግ ያሳሰበው ገዥው የህወሓት መንግስት ጀምበር ያዘቀዘቀችበት እንደሚመስል ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ብርቱ ተቃውሞ መካሔዱን የሚገልጹ የዓይን ምስክሮች፣ በተቃውሞ ወቅት በተደረገ ራስን የመከላከል ድርጊት ከአጋዚ ወገን ከ30 በላይ ወታደሮች ሲያልቁ ከታጠቁ አርሶ አደሮች ወገንም የተጎዱ መኖራቸውን ምስክሮቹ ገልጸዋል፡፡ አጋዚዎቹ ተቃውሞ በሌለበት ሁኔታ አስቀድመው ተኩስ የከፈቱ ሲሆን፣ ከተገደሉት ወታደሮች በተጨማሪም የቆሰሉ መኖራቸውንም እነዚሁ የዓይን ምስክሮች አስረድተዋል፡፡
በምስራቅ ሐረርጌ ህዝባዊ ተቃውሞ መኖሩን መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን፣ በስፍራው ያለው የንግድ እንቅስቀሴ እጀግ ተዳክሞ ሱቆች ተዘግተው መዋላቸውን ከስፍራው የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡በምስራቅ አርሲ ዞንም ህዝባዊ ተቃውሞ መኖሩን እማኞች ገልጸዋል፡፡ እንደዚሁም በድሬዳዋ የተቃውሞ መንፈስ ከተማዋን የተቆጣጠራት ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም የአጋዚ ጦር በተለይ ለገሀሬ በሚባለው የከተማዋ ስፍራ መስፈሩን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
በአወዳይ ከተማ ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩን የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በርካታ ወታደሮችም በኦራል መኪኖች ተጭነው ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡ እንደዚሁ በወለጋ ያለው ሁኔታ ካለመረጋጋቱ በተጨማሪ፣ ጋምቤላን ከቄለም ወለጋ ጋር የሚያገናኘው የመኪና መንገድ በህዝቡ መዘጋቱን ተከትሎ አጋዚዎች ማለፊያ ማጣታቸውን የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአዳማ ቱሉ ህዝባዊ ቁጣ መነሳቱን ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመለከተ ሲሆን፣ በባቱ እና አካባቢው በተነሳው ተቃውሞም ቃድሮ አቦ የተባለ ወጣት በአጋዚዎች መገደሉን ተከትሎ ከተማዋ በከፍተኛ የህዝብ ቁጣ መናጋቷን እማኞች ገልጸዋል፡፡
Image may contain: text and one or more people

Monday, October 10, 2016

የአማራ ተጋድሎ መሪ አለው፣ የአማራ የጎበዝ አለቆች (አቻምየለህ ታምሩ)



የአማራ ተጋድሎ መሪዎች በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የሚገኙ የጎበዝ አለቆች ናቸው። የፊታችን ጥቅምት ሶስት ወር የሚሆነው ይፋዊ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆቻችን በብቃት እየመሩት ነው።
የወያኔ ልሳኖቹ ኢቢሲ፣ ሰንደቅና ሪፖርተር ሊያንቃቸው ጋት የቀረውን ተጋድሏችንን «መሪ የሌለው ትግል» አድርገው ሊያቀርቡት ይቃጣቸዋል። እነሱ የሚያውቁት የመሪ ሞዴል ከኮምኒስት ማኒፌስቶ የሚሳብ፤ በአብዮታዊ ዲሚክራሲ የተጠመቀ፤ እንደ ሊቀ መንበር መለስ ዜናዊ አይነት ፈላጭ ቆራጭ ግለሰብ ስለሆነ ከዚያ የተለየ አገርኛ የትግል አመራር ዘዴ ውጤት እንኳ ቢያመጣ «መሪ» ያለው መስሎ ሊታያቸው አይችልም።
የኛ ተጋድሎ የመሪ ሞዴል እንደነሱ ከአውሮፓ ያመጣነው የአንድ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት የሚሰፍንበትና ሙታን እድምተኞች ጀሌ ሆነው የሚሰለፉበት ድንግዝግዝ ሳይሆን ከአባቶቻችን የወረስነው፤ ወራሪዎቻችንንም በተደጋጋሚ ያሳፈርበት አገርኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ነው።
የጎበዝ አለቃ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ጎበዞች ከመሃከላቸው አንዱን ጎበዝ አለቃ አድርገው ስራቸውን የሚሰሩበት አገርኛ የአርበኞች አደረጃጀት ነው። የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት እንደ መለስ ዜናዊ አንድ «ጎበዝ» ሺ ነፈዞችን በዙሪያው አሰልፎ የሚነግራቸውን ብቻ የሚደግሙ ደናቁርት የተሰበሰቡበት ስምሪት አይደለም። በጎበዝ አለቃ አደረጃጀች ሁሉም ጎበዞች ስለሆኑ በመካከላቸው የበላይና የበታች የለም። የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት እንደ ወያኔ አንዱ ሲሞት ያለመሪ የሚቀር ስብስብ ሳይሆን ሁሉም በማንኛውም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አለቃ የመሆን ችሎታውም ሆነ ፈቃደኝነቱ ያላቸው ጎበዞች አደረጃጀት ነው።
መለስ ዜናዊ የፈጠረው «የአብዮታዊ ዲሞክራሲ» አደረጃጀት በበሉበት የሚጮሁ፣ በሆዳቸው የሚገዙ ካድሬዎች ጥርቅም ነው። ስለሆነም ኮንትራክታቸው ሆዳቸው እስከሞላ ድረስ ስለሆነ አለመተማመን፣ አለመከባበር፣ ጥላቻ፣ አንዱ ባንዱ ላይ መረማመድ የስብስቡ መገለጫ ነው። የኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ግን የመዋቅሩ መሰረት የቆመው በእኩልነት ላይ በመሆኑ መተማመን፣ መከባበር፣ መፋቀር፣ አንዱ ላንዱ ከኔ ይብስ መባባል ጎልቶ የሚታይ የስብስቡ መገለጫ ነው። መለስ ዜናዊ የገነባው «አብዮታዊ ዲሞክራሲ» ግን የበላይና የበታች ያለበት፤ መጠራጠር፣ ፍራቻ፣ ጥላቻ፣ ቅናትንና ጊዜን ጠብቆ መጠቃቃት መርሁ የሆነ የእፉኝት ልጆች ስብስብ ነው።
መለስ ዜናዊ የፈጠረው አደረጃጀት የአንድ ግለሰብ አስተሳሰብ ያለ ገደብ የሚፈጸምበት ስርዓት ነው። ስለሆነም የሚያኮርፈው፣ የሚከፋው፣ የሚያዝነውና ቂም የሚቋጥረው ሎሌ፣ አሽከርና ጀሌ ቁጥር የትየለሌ ነው። የኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ግን የሁሉም ሃሳብ በእኩልነት የሚስተናገድበት፤ የተሻለው በውይይት ተቀባይነት የሚያገኝበት፤ ከሃሳቦች ሁሉ ምርጥ የሆነው በሁሉም የጎበዝ አለቆች ይሁንታ አግኝቶ በሙሉ ስሜት ተግባራዊ የሚሆንበትና ውጤቱም ሁሉንም የሚያረካ ስርዓት ያነበረ የአባቶቻችን አስተዳደራዊ መዋቅር በሆኑ የሚያኮርፍ፣ የሚከፋ፣ የሚያዝንና ቂም የሚቋጥር አንድም ሰው የለም።
እኩልነት ብሎ ነገር ደብዛው የሌለበት የሊቀ መንገበር መለስ ዜናዊ «የአብዮታዊ ዲሞክራሲ» አደረጃጀት ስብስቡ የሚዘወረው በአንድ ሰው ሃሳብ፣ በአንድ ሰው ፍላጎት ስለሆነ የተሻሉ ሃሳቦች ወደፊት የመምጣት እድል የላቸውም። ሊቀ መንበሩም ከራሱ የስልጣን ጥቅም አንጻር ብቻ ስለሚያስብ ውጤቱ አብዛኛውን የስብስቡን አካላት የማያረካ ይሆናል።ይህ የበለጠ ጥርጣሬ፤ የበለጠ በቀለኝነት ያሰፍናል። ሊቀ መንበሩም ይህንን ስለሚያውቅ ጥርጣሬና በቀልተኝነትን ለመቆጣጠር ሲል ነጻነትን እያፈነ ይሄዳል። «ውስጣዊ ዲሞክራሲ» የሚለው የመለስ ዜናዊ «አብዮታዊ ዲሞክራሲ» አስተሳሰብ በግለሰብ አምባገነንበት የተደመደመው ጥርጣሬና በቀልተኝነትን ለመቆጣጠር ሲል ነጻነትን በማፈኑ ነው።
የአማራን ተጋድሎ መሪ የሌለው አድርጋችሁ የምታስቡ የአማራ ተጋድሎ መሪ እንዳለው ማወቅ ይኖርባችኋል። መሪዎቹ ደግሞ በአባቶቻችን ትውፊት የተደራጁትና በዘመናዊ መልክ የተቀናጁ መሬት ላይ ያሉት የአማራ የጎበዝ አለቆች ናቸው። የአማራ የጎበዝ አለቆች የአማራን ተጋድሎ እየመሩ ያሉት እንደ ወያኔ በሞቀ ቤታቸው ቤተ ሽፍታ [ቤተ መንግስት ላለማለት ነው] ሳይሆን ህዝባችን መሃል እየዋሉ፣ እያደሩና የህዝቡ አካል ሆነው ነው። የጎበዝ አለቆቻችን ትግሉን እየመሩ ያሉት የተሰዋውን አርበኛ በክብር መዝገብ አስፍረው እንደየ ቤተ እምነቱ በክብር እንዲያርፍ በማድረግ እንጂ እንደ መለስ ዜናዊ መለስ ዜናዊ «የሟች ወታደሮችን አሃዝ ይፋ የማድረግ ግዴታ የለብኝም» በማለት የአርበኞችን ሞራል በመግደልና የጠላትን ሞራል ደግሞ ከፍ በማድረግ አይደለም።
ጀግኖች አባቶቻችን ፋሽስትን አምስት አመታት ሙሉ በዱር በገደል የተፋለሙት በመሰረቱት የጎበዝ አለቃ ስርዓት ነው። ጥሊያን የዚህን አገርኛ አደረጃጀት መሪ ቢገድልም ሁሉም የጎበዝ አለቆች መሪ ሊሆኑ የሚችሉ ጎበዞች ስለሆኑ አንድ መሪ የጎበዝ አለቃ ቢሰዋ ትግሉ ነጻነታችንን መልሰን እስክናገኝ ድረስ ሊቆም ያልቻለው ለዚያ ነበር። ይህም በመሆኑ ነጻነታችንን ልናስመልስ ችለናል። አሁንም እየሆነ ያለው ያ ነው።
ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው የሚያውቁት ግን አንድ መሪ ብቻ ስለሆነ አንዱ ሲሞት ሌላውን ደምስሶ የሚገዛ እንደ መለስ ዜናዊ አይነት አንድ ግለሰብ ያለ ስለማይመስላቸው ተጋድሏችን መሪ የሌለው ይመስላቸዋል። ወያኔዎቹ በሙሉ የባንዳ ልጆች ናቸው። ጥሊያን በወረረን ጊዜ የጥሊያን አገልጋይ የነበሩትን ባንዶቹን አባቶቻቸውን ጀግኖቹና አርበኞቹ አባቶቻችን አቧራ አስገስተው ያሸነፏቸው በዚህ አገርኛ የጎበዝ አለቆች ስርዓተ ማህበር ተደራጅተው ነበር። ዛሬም ታሪክ መደገሙ አይቀሬ ነው። የአባቶቻችን ልጆች የሆንን የዛሬ ወጣቶች አባቶቻችን በመሰረቱት የጎበዝ አለቃ ስርዓት ተደራጅተን የባንዶች አባቶቻቸው ልጆች ከሆኑት ከወያኔዎች ነጻ እንወጣለን። እኛም ከአርበኞች አያቶቻችን አናንስም፤ ወያኔዎችም ከባንዶች አባቶቻቸው አይበልጡም። በአንድ ልብ ሆነን ህልውናችንን ሊያጠፋ በመጣ ጠላት ላይ የምናደርገውን ትግል የወያኔ ኢንተርኔት ቢቋረጥ፤ የትግራይ ነፍሰ በላ ጦር ሰራዊት ቢሰማራ ወይንም ሌላ ፋሽስት ወያኔያዊ ምድራዊ ኃይል ቢመጣ የአማራን ተጋድሎ ሊያስቆመው አይችልም።
#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!



የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወደከፋ ጦርነት የሚወስደን ነው – #ግርማ_ካሳ



የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው በሶስት ምክንያቶች ብቻ ነው። አንደኛው የዉጭ ወራሪ ሃይል ሲመጣ ነው። አሁን ኢትዮጵያ በማንም አልተወረረችም። ሁለተኛ የተፈጥሮ አደጋ ወይንም ጅምላ ጨራሽ ተላላፊ በሽታ ሲመጣ። እግዚአብሄር የተመሰገ ይሁን ይሄም ብዙ በሌሎች አንዳንድ አገሮች እንደሆነ በኛ አገር ብዙም ታየ ማለት አይቻልም።
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የአስቸኳይ አዋጅ ትላንት አውጇል። (ሕወሃት አውጆ ሃይለማሪያም እንዲያነብ ተደርጓል) ከላይ በተጠቀሱት ሁለት ምክንያቶች ሊሆን አይችልም። በሶስተኛው ምክንያት እንጅ።
በሕገ መንግስቱ የተጠቀሰው ሶስተኛው ምክንያት ህግና ስርዓት ፈርሶ የሕገ መንግስታዊ ስርዓቱና አደጋ ላይ ከሆነ እና በመደበኛ የሰላም አስጠባቂ ሃይላት ነገሮች መቆጣጠር ካቃጣቸው የሚል ነው። እዚህ ላይ ልብ እንበል፣ የሕግ መንግስቱ ስርዓት አደጋ ላይ መዉደቁ ብቻ በቂ ምክንያት አይደለም። ግን የሕግ አስጠባቂ ሃይላት ሁኔታውን መቆጣጠር ካልቻሉ የሚል አለበት።
ብዙ የአገዛዙ ደጋፊዎች ነገሮች አታካብዱ ፣ ይሄን ያህል ብዙ ችግር የለም ሲሉን ነበር። ሆኖም ይኸው ድርጅታቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዉጇል። ነገሮች መቆጣጠር እንዳልችሉ፣ አገር አደጋ ላይ እንዳለች አምነዋል።
አዋጁን ተከትሎ ጠቅላይ አቅቤ ህጉ የሚከተሉትን ብለአል፡
መንግስት የተጠረጠረ “ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ ይችላል። ቤቱንም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መበርበር ይችላል”
“ሁከት እና ብጥብጥ የሚያነሳሱ ድብቅ ቅስቀሳዎች ማድረግ ክልክል ነው”
“በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ኮማንድ ፖስት “ማንኛውንም ዓይነት የመገናኛ ዘዴ የመዝጋት ስልጣን አለው” ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌታቸው አምባዬ።
ሰዎቹ አንድ የዘነጉት ነገር ቢኖር ግን ይሄ አዋጅ መታወጁ የሚለዉጠው ነገር አለመኖሩ ነው። የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው የሕዝቡን ጥያቄ በማክበርና በመስማት ነው። በዉይይት፣ በብሄራዊ መግባባት ነው። አዋጅ እያወጡ ህዝቡን ማስፈራራትና መለፈፍ፣ በሕዝቡ ላይ መዛት የሚለዉጠው ነገር አይኖርም። የበለጠ ቀዉሱን ያባብሰዋል እንጅ።
ሌላው አላሉትም እንጅ አሁን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እናደርገዋለን ያሉት ላለፉት በርካታ አመታት ሲያደረጉት ነበር። እስከ አሁን ማረጋጋት ሳይችሉ አሁን ምን ተዓምር ተገኝቶ ማነጋገር የሚችሉት ? ከሰራዊቱ መሃከል ብዙዎች ጥለው እየሄዱ ነው። ሰራዊቱ እየተከፋፈለ ነው። የትኛው ሃይል ነው ድፍን ጎጃማ፣ ድፍን ጎንደርና አብዛኛውን ኦሮሚያስ ሊያረጋጋ የሚችለው ?
ለምን ይህ አዋጅ ነገሮችን በክፉ አቅጣጫ እንደሚያባብሰው አንድ ተጨማሪ ምክንያት አልቅርብ። ከዚህ በኋላ ሰው ሰለፎችና ተቃዉሞዎች በአደባባይ አያደርግም። ሕዝቡ በአደባባይ ብሶት ቢገልጽ ይሻል ነበር። አሁን ግን ነገሮችን በአደባባይ ሳይሆን በሕቡእ ወደ ማድረግ ነው የሚኬደው። አሁን ካየነው በባሰ ሁኔታ ነው ከፍተኛ ጥፋትና ዉድመት የሚደርሰው። ህዝብን በአዋጅ አፍኖ መግዛት በችራሽ አይቻልም።
የሃይማኖት አባቶች፣ አበው፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን….ሁሉም በፊናው አገዛዙ ችግሮችን በዉይይት እንዲፈታ፣ ለብሄራዊ መግባባት እንዲዘጋጅ ሲጠይቁና ሲማጸኑ ነበር። ከነርሱ መካከል አንዱ የሆኑኢት አቶ ገዱ አንዳራግቸው ራሳቸው ህዝብን አክብሮ፣ ከሕዝብ ጋር በመወያየት እንጅ በፖሊስ፣ በደህንነት፣ በመከላከያ ሰላም ማምጣት አይቻልም ነው ያሉት። ሆኖም ግን ህወሃቶች ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። በሕዝቡ ላይ በድጋሚ ጦርነት አውጀዋል።
በሕገ መንግስቱ ላይ ያለው ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚደነግገው ሕግ ከዚህ በታች ቀርቧል፡
Article 93 Declaration of State of Emergency
(1) (a) The Council of Ministers of the Federal Government shall have the power to decree a state of emergency, should an external invasion, a break down of law and order which endangers the Constitutional order and which cannot be controlled by the regular law enforcement agencies and personnel, a natural disaster, or an epidemic occur.
(b) Sate executives can decree a State-Wide state of emergency should a natural disaster or an epidemic occur. Particulars shall be determined in State Constitutions to be promulgated in conformity with this Constitution.
(2) A state of emergency declared in accordance with sub-article 1 (a) of this article:
(a) If declared when the House of Peoples’ Representatives is in session, the decree shall be submitted to the House within forty-eight hours of its declaration. The decree, if not approved by a two-thirds majority vote of members of the House of Peoples’ Representatives, shall be repealed forthwith.
(b) Subject to the required vote of approval set out in (a) of this sub-article, the decree declaring a state of emergency when the House of Peoples’ Representatives is not in session shall be submitted to it within fifteen days of its adoption.
(3) A state of emergency decreed by the Council of Ministers, if approved by the House of Peoples’ Representatives, can remain in effect up to six months. The House of Peoples’ Representatives may, by a two-thirds majority vote, allow the state of emergency proclamation to be renewed every four months successively.
(4) (a) When a state of emergency is declared, the Council of Ministers shall, in accordance with regulations it issues, have all necessary power to protect the country’s peace and sovereignty, and to maintain public security, law and order.
(b) The Council of Ministers shall have the power to suspend such political and democratic rights contained in this Constitution to the extent necessary to avert the conditions that required the declaration of a state of emergency.
(c) In the exercise of its emergency powers the Council of Ministers can not, however, suspend or limit the rights provided for in Articles 1, 18, 25, and sub-articles 1 and 2 of Article 39 of this Constitution.
(5) The House of Peoples’ Representatives, while declaring a state of emergency, shall simultaneously establish a State of Emergency Inquiry Board, comprising of seven persons to be chosen and assigned by the House from among its members and from legal experts.
(6) The State of Emergency Inquiry Board shall have the following powers and responsibilities:
(a) To make public within one month the names of all individuals arrested on account of the state of emergency together with the reasons for their arrest.
(b) To inspect and follow up that no measure taken during the state of emergency is inhumane.
(c) To recommend to the Prime Minister or to the Council of Ministers corrective measures if it finds and case of inhumane treatment.
(d) To ensure the prosecution of perpetrators of inhumane acts.
(e) To submit its views to the House of Peoples’ Representatives on a request to extend the duration of the state of emergency

Sunday, October 9, 2016

ሰበር ዜና፣ሕወሃት አጣብቂኙ ስለበረታበትና ህዝባዊ ተቃውሞው እየለበለበው ስለመጣ የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ



stateofemeየመጨረሻው ሰዓት ነው። ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ አውጇል። በኦሮሞና በአማራ ክልሎች ያለው የሕዝብ ተቃውሞ በመበርታቱ አላላውስ ያለውና አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ወያኔ ትላንትና ከሰዓት በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ለተላላኪው ለኃይለማርያም ደሳለኝ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነገር አድርጓል። ይህም ወያኔ

ሰበር መረጃ !…… የሐገር መከላከያዉ ከፍተኛ አቅም ወደ ትግራይ ተዘዋዉሮ አለቀ! [ልኡል አለም]




samora-yenusበሐገር መከላከያ ሚኒስቴር ዉስጥ የብቃትና ጥራት መመዘኛ ይዘትን ተንተርሶ ኢትዮጵያን እንደ ሐገር በማቆየት ለማስቀጠል የሚያስችለዉ የማጥቃትና የመከላከል ብቃትን ባጠቃላይ ትግራይ ክልል ተረክባለች!
በተለይም የአየር ሐይል መረጃዎችን ተንተርሶ ከብርጋዴል ጄኔራል ሞላ ሐይለማሪያም ትእዛዝ ዉጪ ( Commander of the Air Force: Brigadier General Mola Hailemariam ) የበረራ ቴክኒካል እና መካኒካል ዘመናዊ መገልገያዎች ጉድለት የሌለባቸዉ ማለትም የተመረጡ የጦር ጀቶች የጦር ሄሊኮፍተሮች ዘማናዊ ሬዲዮ ቴለስኮፖች እጅግ ዉድና ዘመናዊ የራዳር ቃኚዎች አየር መቃወሚያዎች ባጠቃላይ እንከን አልባ የተባሉ ታንኮችና በተሽከርካሪ ላይ የሚጫኑ የተራቀቁ ሚሳየሎች ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘዉ መጠናቀቃቸዉን ከሐገር መከላከያ የደህንነት ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።
በመሆኑም ሐገሪቷ ካላት 180 000 ጠቅላይ ሐይል Total force strength 3/4ኛዉ 108 000 የሰሜናዊዉ ትግራይ እና አካባቢዉ ዋልታ እንዲሆን ሲደረግ ከ 3 500 የተመረጡ የአየር ሐይሎች 1 300 በላይ የሰመኑ እዝ ትግራዊያን ክልልል ዉስጥ እንዲተላለፉ ተደርገዋል።

ከዚህ በታች በሊስት ዉስጥ ከተቀመጠዉ የሐገር መከላከያ ንብረት ዉስጥ 75 በመቶዉ ወደ ትግራይ የተወሰደ ሲሆን በሊስቱ ላይ የማይሰሩና የተዳከሙት ባጠቃላይ በኣለበት የተተወ ነዉ 
reportint20130214103009703Total force strength Army: 180 000
Air Force: 3 500
Army 
Armour 75: T-62
240: T-54/55
60: T-72 (200 on order to replace T-54/55)
Reconnaissance 70: BRDM-1/2
AIFV 20: BMP-1
APC 90: BTR-40/60/152
110: M-113
Self-propelled artillery 10: 2S1 Carnation 122 mm
10: 2S5 152 mm
10: 2S19 Farm 152 mm
Towed artillery ?: M-1942 76 mm
?: M-1938 122 mm
100: D-30 122 mm
6: M-46 130 mm
18: WA-021/Type 88 155 mm
Multiple Rocket Launcher 50: BM-21 122 mm
25: Type 63 107 mm
Mortar ?: 82 mm
?: 120 mm
Anti-armour ?: AT-3/4 Sagger/Spigot
TOW
Recoilless rifle ?: D-44 85 mm
Rocket launcher RPG-7 Knout 73 mm
Air defence gun ?: ZSU-23-4 23 mm
?: ZU-23 23 mm
?: ZU-57
?: S-60 57 mm
?: M-1939 37 mm
Air defence missile ?: SA-2 Guideline
?: SA-3 Goa
?: SA-7 Strela
Air Force 
Combat aircraft 15: MiG-21 Fishbed
10: MiG-23 Flogger
12: Su-27 Flanker
8: Su-25 Frogfoot
Trainer aircraft 7: L-39 Albratros
4: SF-260
Transport aircraft 9: An-12 Cub
2: C-130 Hercules
2: DHC-6 Twin Otter
2: Y-12 
8: C-47
1: An-26
1: An-32
1: Yak-40
Combat helicopter 18: Mi-24/35 Hind
12: UH-1H (Ethiopian Army Aviation)
Transport helicopter 8: SA-316 Alouette 3
10: Mi-6 Hook
20: Mi-8/17 Hip
1: SA 330 Puma
2: Mi-14 Haze
ልኡል አለም

የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ



የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ
– ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ይወያያሉ
በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት (ቻንስለር) አንገላ መርከል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት ቻንስለሯን በፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ቢጠይቅም፣ መርከል ግን ‹‹በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ውስጥ ንግግር ማድረግ ምንም ለውጥ አያመጣም፤›› በማለት ግብዣውን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቻንስለሯ ከእሑድ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገሮች የሚጐበኙ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወደ ማሊና ኒጀር ተጉዘው ኢትዮጵያ ሲመጡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ይገናኛሉ፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረትን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡ ቻንስለሯ አዲስ አበባ ሰኞ አመሻሽ ላይ እንደሚደርሱ፣ አብሯቸውም የጀርመን ፌዴራል ጽሕፈት ቤት ባልረደቦች ብቻ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡ ከቻንስለሯ ጋር ምንም ዓይነት የቢዝነስ ልዑካን የማይመጣ ሲሆን፣ ይህም በሎጂስቲክስ ችግር መሆኑ ታውቋል፡፡ ቻንስለሯ ሰኞ አመሻሽ ላይ ከገቡ በኋላ ማክሰኞ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አቀባበል የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ረቡዕ ይገናኛሉ፡፡
ምንጮች ለሪፖርተር፣ ‹‹ቻንስለር መርከል በአገሪቱ በተፈጠረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ዜጐች ላይ እየወሰዱት ስላለው አላስፈላጊና ከመጠን ያለፈ ኃይል ከመንግሥት ጋር ይወያያሉ፤›› ከዚህም ባለፈ፣ ‹‹በቁጥጥር ሥር በተከፈተ›› የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ይወያያሉ ብለዋል፡፡ ቻንስለሯ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ስደተኞችን በተመለከተና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል፡፡
ቻንስለሯ መርከል በአዲስ አበባ ቆይታቸው ወቅት፣ ከተመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ቻንስለሯ ስድስት ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በጀርመን ኤምባሲ ይወያያሉ፡፡ ሆኖም የውይይቱ አጀንዳንና ተሳታፊዎቹ ማን እንደሆኑ ምንጮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
በቅርብ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ የአገር መሪዎች በተለየ ቻንስለሯ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችን ያነጋግራሉ ተብሏል፡፡ በቅርብ ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ፣ የደቡብ ኮሪያዋ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጉዊን ሃይና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትኒያሁ ከተቃዋሚዎች ጋር አለመገናኘታቸው ይታወሳል፡፡
ቻንስለሯ በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን አዲሱን የጁሊየስ ኔሬሬ የሰላምና ደኅንነት ሕንፃ ማክሰኞ የሚመርቁ ሲሆን፣ በኅብረቱ አዳራሽም ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ ከኅብረቱ ሊቀመንበርንና ከሌሎች የኅብረቱ አመራሮች ጋር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ አዲሱ የሰላምና ደኅንነት ሕንፃ እንዲገነባ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የጀርመን ፌዴራል የውጭ ጉዳይ ሲሆን፣ ሕንፃው የተገነባውም በጂአይዜድ ነው፡፡
ይህ የቻንስለር መርከል ጉብኝት ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እ.ኤ.አ. በ2007 ነው፡፡

በሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ኩባንያዎች ወደሙ ቆንጅት ስጦታው


በሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ኩባንያዎች ወደሙ
ካለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እንደገና ባገረሸው ተቃውሞ፣ እስካሁን ከ130 በላይ ግዙፍና መለስተኛ ኢንቨስትመንቶችን ማውደሙ ተገለጸ፡፡
በተለይ ከአዲስ አበባ ከተማ በ100 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች፣ የኤሌክትሪክና የኮሙዩኒኬሽን ኬብሎች ፋብሪካ፣ የፕላስቲክ ታንከር ፋብሪካ፣ የጠጠር ማምረቻ ፋብሪካ፣ የአበባና የተለያዩ እርሻዎች፣ ሎጆች፣ ወዘተ. ሙሉ ለሙሉና በከፊል ወድመዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የሕዝብ ማመላለሻ፣ ከባድ የጭነትና የግልና የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ወድመዋል፡፡
እንዲሁም የቀበሌ አስተዳደር ሕንፃዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ የአርሶ አደሮች ማሠልጠኛ፣ የጤና ኬላዎች ተቃጥለዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይል የሌለ እስኪመስል ድረስ በጉትጎታ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ኩባንያዎች፣ አገር በቀል ኩባንያዎች፣ የግለሰብ ቤቶችና ንብረቶች ተዘርፈዋል፤ በእሳት ጋይተዋል፡፡
ከሰኞ መስከረም 23 ጀምሮ እስከ ዓርብ መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ባሉት አምስት ቀናት ብቻ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታና ቱሉ ቦሎ አካባቢ 11 ፋብሪካዎችና አራት የአበባ እርሻዎች ወድመዋል፡፡ 62 ከባድ የሕዝብና የጭነት ተሽከርካሪዎች ወድመዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግዙፉ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሳይገን ዲማ፣ ሱፐር ፋይቨር ሮቶ ታንከር ፋብሪካ፣ ቱቱ እና ቤተሰቧ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ ቢኤምኢቲ ኬብል ፋብሪካ፣ ዳስ ትሬዲንግና ሰላም ባልትና ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ለ40 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
በምዕራብ አርሲ ጎልጀታ አካባቢ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢኮ ሎጅ የሆነው ቢሻንጋሪ ሙሉ ለሙሉ ሲወድም፣ በዚሁ አካባቢ የሚገኝ የእህል መጋዘንና የፖሊስ ጣቢያም ጋይተዋል፡፡
በምዕራብና በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ወለጋ ደምቢዶሎ፣ ቀደም ሲል አገረ ማርያም አሁን ቡሌ ሆራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ በምዕራብ አርሲ (ነገሌ፣ አሳሳ፣ ዶዶላ) ውድመቱና ደም አፋሳሽ ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግጭቱ ያስከተለውን ውድመት በትክክለኛው መረጃ ለማወቅ ከተለያዩ ቦታዎች ሪፖርቶች ቀርበዋል፡፡ ነገር ግን የክልሉ መንግሥት ሪፖርቶቹን ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ከገመገመ በኋላ በይፋ እንደሚገልጽ ጠቁመው፣ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ድርጅቶች አንዱ ቢሻንጋሪ ሎጅ ነው፡፡ የባገርሽ ቢዝነስ ግሩፕ እህት ኩባንያ ኢኮ ሎጅ እ.ኤ.አ. በ1998 የተመሠረተ ነው፡፡ ኩባንያው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ጎልጀታ አካባቢ 100 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ ግንባታ ካካሄደ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በ2002 ዓ.ም. ታዋቂውን ቢሻንጋሪ ኢኮ ሎጅ ለኢትዮጵያ በማስተዋወቅ ደንበኞችን መቀበል ጀመረ፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢኮ ሎጅ ሆኖ የተመሠረተው ቢሻንጋሪ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን፣ 60 ሠራተኞች አሉት፡፡ ኩባንያው ሙሉ ለሙሉ የሥራ ዕድል የፈጠረው ለአካባቢው ነዋሪዎች ሲሆን፣ ለአካባቢውም ነዋሪዎች 17 የቢዝነስ ሐሳቦችን በማመንጨት በዶሮ እርባታ፣ በዕደ ጥበብና በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ እገዛ በማድረግ ምርታቸውን ከመረከቡም በላይ፣ በሎጁ ውስጥም መደብር ተከፍቶ ለተጠቃሚዎች እንደሚሸጥ አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለአካባቢው ትምህርት ቤት ውኃ አውጥቶ ከመስጠት ጀምሮ፣ የተለያዩ እገዛዎች ያደርግ እንደነበር የኩባንያው መሥራችና ባለቤት አቶ ኡመር ባገርሽ ባለፈው ዓርብ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
የቢሻንጋሪ ሎጅ ኦፕሬሽን ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ ዘለዓለም ቤኩማ፣ ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት 3፡00 ሰዓት ላይ በሎጁ ጀርባ የተወሰኑ ሰዎች መግባታቸውን፣ የሎጁ የጥበቃ ሠራተኛ ሰብረው ከገቡት መሀል አንዱን በመያዝ ለአካባቢው ሽማግሌዎች በደንቡ መሠረት አሳልፈው መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ሽምግልናው ሳይሠራ የተያዘው ሰው ተለቀቀ ይላሉ፡፡ ማክሰኞ ደግሞ የተደራጁ 60 የሚሆኑ ወጣቶች እየዘፈኑ ዋናውን በር ሰብረው ገቡ፡፡ ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ወጣቶችን በመለመን እንደመለሷቸው አቶ ዘለዓለም ተናግረዋል፡፡ በተደጋጋሚ የተደረገው የማግባባት ሥራ በመጨረሻ ውጤት ማስገኘት ግን አልቻለም፡፡
ረቡዕ ምሽት 5፡00 ሰዓት ላይ ወጣቶቹ በተደራጀ መንገድ የሰው ኃይል ጨምረው ገቡ፡፡ ‹‹አሁን ከሽማግሌዎችም ሆነ ከሎጁ ሠራተኞች አቅም በላይ ስለነበር ወጣቶቹ ዘረፋ ጀመሩ፤›› ሲሉ አቶ ዘለዓለም ሁኔታውን ያስረዳሉ፡፡ ወጣቶቹ የቻሉትን ያህል ከዘረፉ በኋላ ሎጁ ላይ እሳት ለኩሰው እንደሄዱ አስረድተዋል፡፡
‹‹ለአርሲ ነገሌ ፖሊስ ሁኔታውን ብናስረዳም ፖሊስ ጣቢያው ድልድዮች በመሰበራቸው መምጣት እንደማይችሉ፣ ይልቁኑም እኛ ራሳችን ተደራድረን ችግሩን እንድንፈታ ገልጸውልናል፤›› ሲሉ አቶ ዘለዓለም ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ላለፉት 14 ዓመታት በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ቱሪስቶችን ሲያስተናግድ የቆየው ቢሻንጋሪ ሎጅ ሙሉ ለሙሉ መውደሙን፣ በአሁኑ ወቅትም ከቃጠሎ የተረፈው ንብረትም መዘረፉን ገልጸዋል፡፡
‹‹ልጄ የሞተብኝ ያህል ነው ያዘንኩት፤›› ሲሉ የቢሻንጋሪ ሎጅ መሥራችና ባለቤት አቶ ኡመር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ቱሪስት እና ሰላም አይነጣጠሉም፡፡ ቢሻንጋሪን ዳግም የመገንባት ዕቅድ የለኝም፤›› ሲሉ አቶ ኡመር ተስፋ በቆረጠ አንደበት ገልጸዋል፡፡ ከቢሻንጋሪ ሎጅ ባሻገር የሚገኘው የቀድሞ በቀለ ሞላ ሆቴሎች ሥር ይተዳደር የነበረው የአሁኑ ሲምቦ ቢች ሪዞርት ባለፈው ዓርብ በከፊል ቃጠሎ ደርሶበታል፡፡
የሲምቦ ቢች ሪዞርት ሎጅ ኩባንያ መሥራች አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ሎጃቸው በከፊል የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል፡፡ ነገር ግን የውድመቱን መጠን ለማወቅ መረጃ ተጠናቅሮ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል፡፡
ሱፐር ፋይቨር ኩባንያም ከባድ ውድመት አጋጥሞታል፡፡ ይህ ኩባንያ በሰበታ ከተማ በ13 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የፕላስቲክ ታንከር ፋብሪካ ከፍቶ ላለፉት አሥር ዓመታት ምርቱን ለገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
የሱፐር ፋይቨር ኩባንያ ባለድርሻ ወ/ሮ ትዕግሥት ጌትነት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ረቡዕ መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡30 ላይ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ በርካታ ወጣቶች መጡ፡፡ ወጣቶቹ በጀሪካን ነዳጅና ተቀጣጣይ ጎማ ይዘው በመግባት የጥሬ ዕቃ ማከማቻና ያለቀለት ምርት ማቆያ መጋዘን ላይ እሳት መልቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ትዕግሥት እንዳሉት እሳቱ ወደ ፋብሪካው ባይዘመትም፣ የተከማቸ ጥሬ ዕቃና ያለቀለት ምርት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡ ቢያንስ የወደመው ንብረት 35 ሚሊዮን ብር ግምት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹1,500 ሠራተኞች ነበሩን፡፡ አሁን ግን ሙሉ ለሙሉ ሥራ አቁመናል፡፡ ይህ ፋብሪካ የእኛ ብቻ ሳይሆን የሕዝብም ጭምር ነበር፤›› ሲሉ የገለጹት ወ/ሮ ትዕግሥት፣ ፋብሪካቸው ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከጉድጓድ ውኃ አውጥቶ ይሰጥ የነበረ ቢሆንም የውኃ ማጠራቀሚያውን ጭምር እንዳጠፉት አስረድተዋል፡፡
‹‹አጥፊዎቹ የሽምቅ ተዋጊ ዓይነት ባህሪ አላቸው፡፡ የፀጥታ ኃይሎች እንዳይገቡ መንገድ እየዘጉ ነው ይህንን እኩይ ተግባር የሚፈጽሙበት፤›› ሲሉ የተናገሩት ወ/ሮ ትዕግሥት፣ መንግሥት በተቻለው አቅም ለዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡
ሱፐር ፋይቨርን ጨምሮ በሰበታ ከተማ ከተቃጠሉት 11 ፋብሪካዎች መካከል ቢኤምኢቲ ኢነርጂ ቴሌኮም ኢንዱስትሪ ኤንድ ትሬድ የተባለው ኩባንያ ይገኝበታል፡፡ ይህ የቱርክ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ2012 በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ የሆነውን የኤሌክትሪክና የኮሙዩኒኬሽን ኬብሎች ማምረቻ ፋብሪካ ገምብቶ ወደ ምርት ገብቷል፡፡
ኩባንያው ሦስት ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ወደዚህ ሥራ ቢገባም፣ ምርት ከጀመረ ከአራት ዓመት በኋላ ያላሰበውና ያልገመተው ውድመት ገጥሞታል፡፡
የኩባንያው የሰው ኃይልና የፋይናንስ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ደረጀ ደሳለኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ብዛት ያላቸው ወጣቶች ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት ዋና መሥሪያ ቤቱን አቃጥለዋል፡፡ በቢሮው ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችና ኮምፒውተሮች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡
‹‹ከባዶ ነው የምንነሳው፤›› በማለት ፋብሪካው ያለ ሰነድ መቅረቱን አቶ ደረጀ ተናግረዋል፡፡ የኬብል ፋብሪካው ባይነካም ቢሮው ከነሰነዱና ከጂቡቲ ዕቃ ጭነው የገቡ አራት ከባድ ተሽከርካሪዎች ከያዙት ዕቃ ጋር ነደዋል፡፡
‹‹አጥፊዎቹ ብዛት ስላላቸው በወቅቱ የሚያስቆማቸው ኃይል አልነበረም፤›› በማለት የገለጹት አቶ ደረጀ፣ በአሁኑ ወቅት የፌዴራል ፖሊስ ግቢውን እንደተቆጣጠረ ገልጸዋል፡፡ የወደመው ንብረት መጠን እስካሁን አለመታወቁንም ጨምረው አስረድተዋል፡፡
ሌላኛው የጥቃቱ ሰለባ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ታዋቂ እየሆነ የመጣው አሰር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ይገኝበታል፡፡
አሰር ኮንስትራክሽን ከአዲስ አበባ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቢሾፍቱ – አዱላላ-መቂ ያለውን 55 ኪሎ ሜትር አቋራጭ መንገድ በ700 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተረክቧል፡፡
አሰር ኮንስትራክሽን ለመንገድ ግንባታ ያሰማራቸው ዘጠኝ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች በዚህ ሳምንት በተለያዩ ቀናት ውስጥ እንደወደሙበት ታውቋል፡፡
ከአሰር ኮንስትራክሽን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ በአካባቢው ንብረቶችን የሚያወድሙ አካላት ካምፑን ለማውደም በሚዘጋጁበት ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ደርሶ ከቃጠሎ አድኖታል፡፡ አሰር ኮንስትራክሽን የዚህን መንገድ ግንባታ 70 በመቶ ያህል አጠናቆ እንደነበር መረዳት ተችሏል፡፡
በኦሮሚያ ካለፈው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እንደገና ሥር እየሰደደ በነበረው ተቃውሞ ሰፊ ቦታ የሚሸፍን በመሆኑ፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና ፌዴራል ፖሊስ ሊቆጣጠሩት እንዳልቻሉ እየተነገረ ነው፡፡
ተቃውሞው እየተካሄደ ያለው የፀጥታ ኃይሎች እንዳይደርሱ መንገድ እየተዘጋ ጭምር በመሆኑ፣ አመጹም ሰፊ ቦታ የሚሸፍን ስለሆነ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ንብረት እየወደመ ነው፡፡
እየወደሙ ከሚገኙት ንብረቶች መካከል ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ፋብሪካዎች፣ የአበባ እርሻዎች፣ የቱሪስት ማረፊያ ሎጆችና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
የኦሮሚያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱና የፌዴራል ፖሊስ ምንጮች ፖሊስ አመፁን እየተቆጣጠረ መሆኑን ቢገልጹም፣ ከኦሮሚያ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን ክልሉን ቃጠሎ እየበላው መሆኑን የሚገልጹ ናቸው፡፡
አመጹ የትራንስፖርት እንቅስቃሴንም የገታ ሲሆን፣ ለአብነት በወዲያኛው ሳምንት ቅዳሜና እሑድ በምዕራብ አርሲ በሚገኙ የገበያ ሥፍራዎች ለንግድ የተጓጓዙ ነጋዴዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች እስካለፈው ዓርብ ወደ ቀዬአቸው አልተመለሱም፡፡ ከሐረር ወደ አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦና ነቀምት የሚደረጉ ጉዞዎች እንዲሁ ችግር እንደገጠማቸው መንገደኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተለይ በምዕራብ አርሲ የቀበሌ አስተዳደር አካላትን በማስወገድ በጎበዝ አለቃ ለመተዳደር እየተሞከረ መሆኑ ታውቋል፡፡
እየወደሙ ያሉ ንብረቶች የባንክ ብድር ያለባቸውና የኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸው ናቸው፡፡ ይህ ክስተት በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ተሠግቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት ዋስትና ሰጥቶ ያስገባቸው ኩባንያዎችም እንደመሆናቸው፣ ይህ ያልተጠበቀ ክስተት መንግሥትን በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ካሳ ሊያስከፍለው እንደሚችል ባለሙያዎች እየገለጹ ነው፡፡
በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መሠረት በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ ከ350 በላይ ወረዳዎች ዳግም ባገረሸው ተቃውሞ ጉዳት የደረሰው በ50 ወረዳዎች ነው፡፡ ባለፈው ዓርብ ግን በአብዛኞቹ ሥፍራዎች መረጋጋት መፈጠሩን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ በምዕራብና በምሥራቅ አርሲ ከሚገኙ ሁለት ወረዳዎችና ከነገሌ ቦረና በስተቀር ሰላማዊ ድባብ መፈጠሩን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባ አዲስ አበባ የመጡት የ31 ዓመቷ አሜሪካዊት የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ሻሮን ግሬይ ቡራዩ አካባቢ በተወረወረ ድንጋይ ተመተው ሞተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተገደሉት አሜሪካዊ አስከሬን ወደ አገራቸው ተሸኝቷል፡፡