Monday, October 3, 2016

በመላው ኦሮሚያ ከባድ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።



Minilik Salsawi's photo.
በመላው ኦሮሚያ ከባድ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። ለኣዲስ ኣበባ ቅርብ በሆነችው ቡራዩ የከባድ መሳሪያ ቶክስ ማምሻውን የጀመረ ሲሆን በሙገር የዳንጎቴ ንብረት የሆነ ከባድ መኪና በሕዝባዊ ንቅናቄው ኣራማጆች ሲጋይ በቡሌ ሆራ ፍርድ ቤቶች ጋይተዋል፤ ሲኤምሲ ልዩ ስሙ መሪ አካባቢ ህዝብ እና የወያኔ ወታደሮች ተናንቀዋል፡፡ ከፍተኛየተኩስ ለውውጥ እየተደረገ መሆኑንና ህዝቡ ቤንዚንና እሳት ይዞ የወያኔን ንብረት እያወደመው ነው፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በቢሾፍቱ የተገደሉ ንጹሃንን ለመቅበር በተደረገ ስነስርዓት ላይ ከባባድ ተቃውሞዎች የተሰሙ ሲሆን በምዕራብ ሀረርጌ ፪ የሰላም ባስ አውቶብሶች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። ተቃውሞው የሚቀጥል ሲሆን ኣዳዲስ የትግል ስትራቴጂዎች እየተነደፉ የሕወሓት ጉጅሌ ኣገዛዝ እስኪወድቅ ድረስ ትግሉ ተቀጣጥሎ ይቀጥላል። #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.



Sunday, October 2, 2016

አሳዛኝ ዜና ህወሀት ከሰማይ ከሂሊኮፕተርና በምድር በጨካኙ የኣግዓዚ ጦር እሬቻ በአል ላይ በተከፈተ ጥቃት በትንሽ 120 ሰው ተገድሏል።



አሳዛኝ ዜና #Irreechaa2016 #Ethiopia ህወሀት ከሰማይ ከሂሊኮፕተርና በምድር በጨካኙ የኣግዓዚ ጦር እሬቻ በአል ላይ በተከፈተ ጥቃት በትንሽ 120 ሰው ተገድሏል። እርጥብ ሳርና ኣደይ ኣበባ ይዘው ለወጡ ሕዝቦች በገዛ ኣገራቸው ከሰማይ ጥይት ማርከፍከፍ ነገ ሕወሓት ከነደጋፊዎቹ የንጹሃንን ደም ያወራርዳል ይከፍላል። በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በትግሬ ጉጅሌ ዘረኛ ኣገዛዝ በንጹሃን ላይ እየተፈጸመ ነው። ማንም ከተጠያቂኔት ኣያመልጥም።
አሳዛኝ ዜና ህወሀት ከሰማይ ከሂሊኮፕተርና በምድር በጨካኙ የኣግዓዚ ጦር እሬቻ በአል ላይ በተከፈተ ጥቃት በትንሽ 120 ሰው ተገድሏል።

በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል



አሁን ባለው ቁጥር ከ295 በላይ ሰዎች በቢሾፍቱ ተረሽነዋል፡፡ 120 አስክሬኖች ወደ ቢሾፍቱ ሆስፒታል ሲሄዱ 175 የሚሆኑት አስክሬኖች ወደ አዲስ አበባ ተጭነዋል፤ወደ ቢሾፍቱ ሀይቅ ውስጥ ከአስለቃሽ ጪስ እና ከጥይት ሸሽቶ የሰጠመ ህዝብ ቁጥር ብዛት ግን ገና አልታወቀም፡፡
በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል፤፤
#Ethiopia #Oromoprotests #Irreecha2016 #MinilikSalsawi #Shashemene
በደብረዘይት በኢሬቻ በዓል ላይ የተፈጸመውን ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል፤፤ ወጣቶች ወገኖቻችን ደም ፈሶ አይቀርም፣ የእኛም ደም ነው የፈሰሰው፡፡ ክብራችን፣ መብታችንና ነጻነታችን እስከሚመለስ ትግሉ ይቀጥላል፡፡
በተመሳሳይ የአጄ ከተማና አካባቢቀው ነዋሪዎች ለኢሬቻ በዓል በሄዱ ወገኖቻቸው ላይ በደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ለመቃወም አደባባይ ወጥቶ በከተማ መስተዳድር ግቢ የተሰቀለውን ባንዲራ አውርደው ኮከብ ጠሌለበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅና የኦነግ ዓርማ በቦታው ሰቅለዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ታጣቂ ኃይሉና ነዋሪው ከፍተኛ ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው፡፡

VIDEO – ቢሾፍቱ ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል



ቢሾፍቱ ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል
ወታደሮቹ በፒካፕና በኦራል መኪና ከተማዋን እየናጧት ይገኛሉ ይህንን ሁሉ ህዝብ ይፈራ መስሏቸው ይሁንና ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች ሲቶችና እና ወንዶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል::ለወትሮም ቢሆን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የማይታጣት ቢሾፍቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባላ በአጋዚ ጦር ውስጥ ወድቃለች በኢሬቻ በአል ምክንያት በቢሾፍቱ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሰው እየከተመባት ይገኛል ሰላም ለማስከበር ዱላም ሲበዛ ነው የዚህን ያህል መሳሪያ ይዞ መገኘት አሳዛኝም አስነዋሪም ጭምር ነው በየ 10 ሜትት እርቀት ውስጥ በርከት በርከት ብለው የቆሙ አጋዚዎች የያዙት መሳሪያ ሰላማዊ ሰውን ለመጠበቅ አይመስልም
ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከሸዋና ከወሎ የተውጣጡ ከ200 በላይ የሚሆኑ አማሮች እጅግ የበረታውን የወያኔ ፍተሻ በማለፍ በአምስት ከፍተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተሳፍረው ደብረ ዘይት በመግባት ለኦሮሞ ወንድሞቻቸው ያላቸውን አጋርነት በኢሬቻ በዓል ላይ በእንግድነት በመገኝት እየገለጡ ይገኛሉ። አማሮቹ ደብረ ዘይት ሲደርሱ በአባ ገዳዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አማሮቹም ለአባ ገዳዎች የአማራን ህዝብ ከልብ የመነጨ ወንድማዊ ሰላምታ አቅርበዋል። ይህ የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትብብር የአማራ ተጋድሎና የኦሮሞ ተቃውሞ የጋራ ትግል ምዕራፍ የሚከፈትበት የመሰረት ድንጋይ ነው።
አጋዚዎች በቀጥታ ለጦርነት ተልከው የመጡ ነው የሚመስሉት ህዝቡን ከጠዋት ጀምሮ ማሸበር ተያይዘውታል በፅሁፍ ልገልጠው በማልችለው መልኩ ወታደሮች የመጡት ሀገራቸው ውስጥ አይመስልም ወታደሩን ሳየው የኔ ወገን አልመስልህ አለኝ በቅኝ ግዛት ውስጥ ያለው ሀገሬን የተቀማው ይኽል ከበደኝ በእርግጥ ሀገሬን ከቀሙኝ ቆይቷል ማንነቴን ቀምተው ማንነት አልባ ሊያደርጉኝ ቢጣጣሩ ነው ማንነቴን መልሱ እያልኩ መጮህ የጀመርኩት ብቻ ወደ ቢሾፍቱ ቅኝቴ ልመልሳችሁ እና ወታደሮቹ በፒካፕና በኦራል መኪና ከተማዋን እየናጧት ይገኛሉ ይህንን ሁሉ ህዝብ ይፈራ መስሏቸው ይሁንና ህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ጀምሮታል በርከት ያሉ ወጣቶች ሲቶችና እና ወንዶች በሚያስገርም አንድነት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛል እስካሁኗ ባለው ሰአት ከላይ ወደታች ከታች ወደላይ እያሉ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ሲሆን ይህ ተቃውሞ በነገው እለትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምናለው እኔም እስከዛሬ በፀሁፍ ብቻ ኢህአዲግን ከምቃወም በነገው እለት ከኢትዮጵያውያ ወንድምና እህቶቼ ጋር በድምፅ እቃወመዋለሁ አዎ ህዝብ እንቢ ካለ እንቢ ነው ማንም ከህዝብ ማዕበል ሊያመልጥ አይችልም ይሄ አላስፈላጊ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱ አይቀርም Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
https://www.youtube.com/watch?v=0Q6cy0BS4pQ   video link

Saturday, October 1, 2016

በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው።Tadesse Biru Kersmo


በብዙዎች የመምህራን “ስልጠናዎች” ላይ ዝምታ ከቃላት በላይ ተቃውሞን ለማስተላለፍ ጠቅሟል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን አላስችል ያላቸው መምህራን ካድሬዎቹን አሳፍረዋል። ”ለምን እንዲህ አደረጋችሁ”፤ “ምን አቅብጧችሁ ተናገራችሁ?” ማለት አይቻልም፤ የካድሬዎቹ ድፍረት ትዕግስት ያስጨርሳል። ክፋቱ በእነዚህ አዳራሾች ውስጥ የነበሩ ጆሮጠቢዎች ሪፓርት የሚያደርጉትን አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው።
ተናገሩ ተብለው ተወትውተው ስለተናገሩ ታሰሩ !!! ያሳዝናል !!! ለዚህ ኢፍትሀዊነት ውሳኔ የምሰጠው ምላሽ ምንድነው?
ዘንድሮ ት/ቤቶች እንደተከፈቱ ወዲያውኑ የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች መጀመር አለባቸው። በሥራ መለገም፤ የታዘዙትን ሳይሆን ያልታዘዙትን መፈፀም … ወዘተ ከቀን አንድ ጀምሮ ተግባራዊ ልናደርጋቸው ይገባሉ ብዬ አምናለሁ።
“የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች” እና “የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን” የሚሉ ሁለት አጫጭር መጣጥፎችን በፌስቡኬ ለጥፌዓለሁ። እነዚህ ለመነሻ ያህል የቀረቡ ናቸው። ዜጎች እኔ ከዘረዘርኳቸው የተሻሉ ተግባራት ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህም ሆኑ ሌሎች ትምህርት እንደተጀመረ በሥራ ላይ ቢውሉ መልካም ነው እላለሁ።
ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ መምህራን የሚሆኑ ሌሎች ዝርዝሮችን ማዘጋጅት የሚያስፈልግ ከሆነም እናስብበት።
2009 የትምህት ዘመን የሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ የሕዝባዊ አሻጥር እና የአዝባዊ አመጽ – ማለትም የሁለገብ ትግል – ዘመን ይሆናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!! Tadesse Biru Kersmo

የወልቃይት አማራ የሀገር ሽማግሌዎች በወያኔ ከወጣቱ በመቀጠልተቃውማቸውን ኣሰሙ



Image may contain: crowd, one or more people and outdoor
የወልቃይት የ ኣማራ ተጋድሎ ያሳሰበው የወያኔ መንግሥት ኣገር ሽማግሌዎች እርቅ ለመፍጠር በሚል ሰበብበ 20/01/09 ዓ/ም ከክልል ትግራይ ባንዳው ፈረደ የሺወንድምእና የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽኖሮች እንዲሁም የዞኑ ኣስተዳደር
ኢሳያስ ታደሰ የከተማ ኣዲ ረመጥ ኣለቅላቂዎችን ብቻ
ለመሰብሰብ ያቀዱ ሲሆን ነገርግን ህዝቡ እሰከመቼ እነሱን
እየሰማችሁ ትሄዳላችሁ በማለት ኣደራሽ የገቡ ሲሆን በነበረው
ውይይትም ፍፁም ኣማራዊ ተጋድሎ የተነፀባረቀበትም ነበር እኛ ትላንት ዛሬም ሁሌም ኣማራ ነን ደንበራችንም ተከዜ ነው ማንነት መጠየቅ እንዴት ወንጀል መሆን ቻለ ሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን የጠየቃቸው ሲሆን የዞኑ ኣስተዳደር ተብየው ከመቀመጫው ቁጭ ብድግ በማለት ጥያቄዎችን ከመመለስ
ይልቅ ከኣሁን በፊት የነበረው ጥያቄ ትክክለኛ ኣይደለም ኣሁን እንደ ኣዲስ መጠየቅ ትችላላችሁ በማለት በቁጣ ሲያሰፈራራ
ውላል ከዚህ በፊት ከእነርሱ ጋር በመሆን ሲያስቃብጡ የነበሩ ባንዳዎች ኣፋቸውን ይዘው ውለዋል፡፡ ነገር ግን እኛምየተጠየቀው ጥያቄመልስ አንጠበቃለን እነጂ ከኣሁን በኋላ ምንም ኣይነት ጥያቄ የማንጠይቅ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
የኣማራ ተጋድሎ ያሸንፋል፡

source mereja.news.

ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ለመጄመሪያ ጊዜ በድብቅ ቀረበ ።



Image may contain: 1 person , hat
ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ለመጄመሪያ ጊዜ በድብቅ ቀረበ ።
ኮረኔል ዛሬ ወደ ፍርድቤት መምጣቱን ህዝቡ ባለመስማቱ እንደ አለፉት ጊዚያት ፍርድ ቤቱ በህዝብ አልተጥለቀለቀም። ይል ቁንም የአማራ ክልል መከላከያ በብዛት ፍርድ ቤቱን በክፍተኛ ጥበቃ ዙሪያውን ከብበውት ነበር።


ኮረኔል ደመቀ ቀደም ሲል በክልሉ የአቃቤ ህግ የተመሰረተበት ሰው የመግደል ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ የተደረገም ቢሆን ከፌደራል መንግስት የመጣው አቃቤ ህግ አንድ ዘርን በማጥቃት እና በአሸባሪነት ተጠርጣሪ ነው በማለት ክስ መስርቶበታል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለመጭው ጥቅምት ወር ቀጠሮ ሰጥቷል።


የጎንደር ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው ኮረኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረቡን ዘግይቶ የሰማው የጎንደር ከተማ ነዋሪ በተለይ እናቶች አሁን ነው የገደሉን እያሉ ሰብሰብ ብለው ሲያነቡ ታይተዋል።


በተያያዘ ዜና በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርካታ ወጣቶች ታስረው የነበረ ሲሆን በሌሊት የት እንደወሰዷቸው ማዎቅ አልተቻለም። የታሳሪ ቤተሰቦች ስንቅ ለማቀበል ሲሄዱ እዚህ የሉም የት እንደተወሰዱ አናውቅም የሚል መልስ ከጣቢያው ፖሊሶች መሰጠታቸውን ከስፍራው የአይን እማኝ አረጋግጦልኛል